cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦ https://m.facebook.com/104755325677864/ Website:- www.hakimethio.com

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 913
المشتركون
+424 ساعات
+277 أيام
+3030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
Urgent Battle: Dr. Bethel's Fight Against Leukemia, organized by Amu Bazenu

"This is Dr. Bethel Germamo. I hope this message finds you well. I am a … Amu Bazenu needs your support for Urgent Battle: Dr. Bethel's Fight Against Leukemia

👍 2
የስጋ ለባሽ ሰውን እጣ ፈንታ ከእግዜሩ በቀር ማንም ሊያውቀው አይችልም። በየትኛው ቅጽበት የተፈጥሮ ኡደት እንደሚዛባ ማናችንም የማናስተውለው የተፈጥሮአችን ምስጢር ነው።    ከታች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች። ከጥቂት አመታት በፊት ከጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ዶክትሬት ድግሪ ተመርቃ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርቲ በህክምና እና በማስተማር ሲታገለግል ቆይታ በመጨረሻም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመቀላቀል የራዲዮሎጂ ስፔሻሊት ስልጠና ከጨረሰች ገና 3ኛ ወሯ ትዳር ከመሰረተች ደግሞ ገና 2ኛ ወሯ ነው።    ዶ/ር ቤቴል  የመመረቋን እና የማግባቷን ደስታ ገና ሳታጣጥም እንደቀልድ ለቶንሲል ህመም ምርመራ ለመደረግ በሄደችበት  ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረዳች።   ቤቲ  የደም ካንሰር በአይነቱም acute lymphoblastic leukemia የሚባል በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት። የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድ አፋጣኝ የሆነ የመቅኔ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplant) ከሀገር ውጭ እንዲደረግላት ወስኗል።    የደም   ካንሰር ምንም እንኳን አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኔ ንቅለ ተከላ ከተደረገ የመዳን ዕድል ያለው በሽታ በመሆኑ፣,እናንተ ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን ሀኪም ህይወት በደጋግ እጆቻችሁ ተባብራችሁ እንድትታደጉ ስንል በፈጣሪ ስም እንለምናችኋለን።    ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ የምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት። እንደአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰቧም ሆነ ባለቤቷ  አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም።  ቤቲ የምታገለግላችሁ እናንተ ኢትዮጲያዊያን፣ እናንተ ቤተሰቦቿ ናችሁ እና በፈጣሪ ስም የመልካምነት እጃችሁን ዘርግታችህ የቤቲን ሀዘን የቤተሰቦቿን ድንጋጤ እንድትመለከቱ እንላችኋለን። CBE-1000105102384 Bethel Germamo Ganebo 1000156496317-Mengistu Tumea Madalcho Dashen-2939236369311- mengistu Tumea madalcho የፈጣሪ ሰላም እና ጤና ቤታችሁን ይጎብኝ።
إظهار الكل...
😭 3👍 2
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ __ የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት 2016 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩ ይታወሳል፡፡  ነገር ግን ከሲስተም ችግር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለማስተናገድ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ምዝገባውም እስከ ግንቦት 2/2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በምዝገባ ላይ ያላችሁን ማንኛውም ቅሬታ በስልክ ቁጥር 011(8)-27-59-36 እንዲሁም 011(8)-27-59-45 መደወል የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- በምዝገባ ወቅት ለመመዝገብ ያስቸገራችሁ ወይም የአያት ስም አልገባ ያላችሁ ተመዛኞች Do you have MoH IDNO or Ministry of Education (MoE) User Name ?  በሚለዉ ጥያቄ ላይ Yes የሚለውን በመጫን ከዚህ በፊት በጤና ሚኒስቴር የተሰጣችሁን MoH IDNO ወይም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጣችሁን User Name በማስገባት እና የቀረውን ዘርዝር መጠይቅ ጨርሶ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ Telegram: t.me/HakimEthio1
إظهار الكل...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

*ነጩ እና ጥቁሩ ዓይነ-ስውርነቶች* ======== በዓለም ላይ በከፍተኛ መጠን ዓይነ-ስውርነትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች ሁለቱ (ቀዳሚዎቹ) ነጩ እና ጥቁሩ ዓይነ-ስውርነቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ነጩ - ሞራ ግርዶሽ ሌንስ፡- የዓይን ፊተኛዉ ክፍል ውስጥ ያለ ንዑስ-ዓይን አካል ሲሆን - በተፈጥሮዉ ጥርት ያለ ነዉ፡፡ ስራዉ ብርሃንን ወደ ኋለኛዉ የዓይን ክፍል - የብርሃን ግድግዳ (ረቲና) - መርቶ ማስተላለፍ አንዱ ነዉ፡፡ ሞራ ግርዶሽ፡- ሌንስ ጥራቱን በተለያዩ ምክንያት ሲያጣ - በተለያየ መጠን ወደ ነጭነት ሲቀየር እና ዋናዉ አገልግሎቱ ሲታወክ - ሞራ ግርዶሽ ተከሰተ ይባላል፡፡ ይህ ዓይነ-ስውርነትን ከሚያመጡ ምክንያቶች በዓለም ላይ በአንደኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ ሞራ ግርዶሽ አብዛኛዉ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን ሌላው ደግሞ ከእድሜ መግፋት ጋር ያልተያያዘ ነዉ፤ በብዙ ምክንያት ሊመጣ ይችላል፣ ለምሳሌ ... ከግርዶሹ ጋር አብሮ በመወለድ (ብዙ ምክንያቶች አሉት)፣  በምት፣ እስቴሮይድ መድሃኒት ከመጠቀም ጋር የተያያዘ፣ በዉስጣዊ የዓይን ቁጣ፣… ወዘተ ናቸው፡፡ ሆኖም ይህ የሞራ ግርዶሽ በቀዶ-ጥገና የሚገላገሉት አይነት ነዉ፡፡  በዚህም ምክንያት ከጥቁሩ - ግላኮማ ይልቅ ነጩ-ሞራ ግርዶሽ  ለታማሚዉም  ለሀኪሙም  ቀዶ-ጥገና ከተከናወነ በኋላ ትልቅ የእርካታ እና የደስታ ምንጭ ነዉ፡፡ የሀዘን እና የብስጭት ምንጭ የሚሆነዉ ሞራ-ግርዶሹ ተጓዳኝ የዓይነ-ስዉርነት የሚያመጣ ምክንያት ካለዉ/ካሉት ነዉ፤ አንዱም ያ..ጥቁር-ግላኮማ ሊሆን  ይችላል፡፡ ጥቁሩ - ግላኮማ የዓይን ነርቭ፡- የዓይን ህዋሳት ከብርሀን ግድግዳ (ረቲና) ተሰባስበዉ ህብረ-ህዋስ ፈጥረዉ በኋለኛዉ የዓይን ክፍል ወደ አንጎል የሚጓዙበት ገመድ ነዉ፡፡ ስራዉም ብርሃንን እና ያየነዉን ምስል/እንቅስቃሴ በነርቭኛ ተርጉሞ ወደ እይታ-አንጎል ክፍል ማስተላለፍ ነዉ፡፡ ግላኮማ፡- የአይን ነርቭ መጎዳት ሲሆን ፤ የዓይናችን ነርቭ ጉዳት ለመገንዘብ ያህል በግላኮማ ምክንያት እና በሌላ ምክንያት ብለን መክፈል እንችላለን፡፡ ግላኮማ - በጊዜ ሂደት ጉዳቱ የሚጨምር፣ የማይድን ግን የሚታከም የራሱ አይነተኛ አጎዳድ ያለዉ፤ የራሱ አይነተኛ የዓይን -አድማስ እክል የሚያመጣ ነዉ፡፡ ለግላኮማ አጋላጭ ከሆኑት ዉስጥ ዋናው ከፍተኛ የዓይን ግፊት (ከ 21 ሚሊ ሜትር በላይ) ሲሆን ፤ ነገር ግን የግድ ከፍተኛ ግፊት ላይኖር ይችላል፡፡ ብዙ አይነት ግላኮማ አለ፡፡ በመንስኤዉ - የሚታወቅ እና የማይታወቅ፣ በእድሜ - የህጻናት፣ የወጣቶች እና የአዋቂዎች፡፡ በማዕዘኑ (የዓይን ፈሳሽ የሚፈስበት ቦይ)- ማዕዘነ ክፍት እና ማዕዘነ-ዝግ ተብሎ በዋናነት ይከፈላል፡፡ የህጻናት ገላኮማ፡- ከ4 ዓመት በታች ያለዉን የእድሜ ክልል የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ከሌላዉ ዕድሜ የሚለየው አልፎ አልፎ የሚከሰት መሆኑ፤ ሁሌም ከፍተኛ የዓይን ግፊት መኖሩ፣ ጉዳቱ የዓይን ነርቭ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉም እድገታቸዉን ያልጨረሱ የዓይን ክፍሎች ላይ መሆኑ፤ ጠቁሮ ያልጠቆረ…የሚታይ ምልክቶች ማለትም ሶስትዮሽ መገለጫ ያለዉ ሲሆን፤ ማንባት፣ ብርሃን መፍራት እና የዓይን ቆብን መጭመቅ ናቸው፡፡ ህክምናዉም የዓይኑን ግፊት በቀዶ-ጥገና መቀነስ ነዉ፡፡ የወጣቶች እና አዋቂዎች ግላኮማ፡- እነዚህ በጥቁር የሚመሰሉት ሲጀምሩ ምንም ምልክት የማያሳዩ፤ በጭለማ እንደሚዘርፍ ሌባ ከፍተኛ ጉዳት ካመጡ በኋላ ነዉ የሚታወቁት፡፡ ምክንያቱም የዓይን እይታን መጀመርያ አካባቢ ምንም አይቀንሱም፡፡ የአይን አድማስ በከፍተኛ ሁኔታ ጠቦ ከነገሮች ጋር ስንጋጭ ወይም ዓይነ-ስውርነት ሲከሰተ ነዉ የሚታወቀው፡፡ ይህ እንግዲህ በዓለም ከነጩ-ሞራ ግርዶሽ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ዓይነ-ስዉርነትን ከሚያመጣዉ የማዕዘነ-ክፍት ግላኮማ መገለጫ ነዉ፡፡ በዚህ በሽታ ዕድሜያቸዉ ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ተጋላጭ ሲሆኑ፣ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነትም ይጭምራል፡፡ ለዚህም ሲባል በዚህ ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያለ ሰዉ ቢያንስ በአመት አንዴ የዓይን ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል፡፡ ተጨማሪ ተጋላጭነት ያላቸዉ ሰዎች ለምሳሌ የቅርብ ቤተሰብ አባል በግላኮማ የተጠቃ ካለ የቅርብ ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወደ ህክምናዉ ስንመጣ ብቸኛ ማከሚያዉ መንገድ የዓይን ግፊቱን ካለበት መነሻ መቀነስ ነዉ፡፡ ይህም ጉዳቱን ባለበት ማቆም ወይም ዓይነ-ስውርነት እንዳይከሰት ማቆየት ነው፡፡ ግፊቱን ካለበት ለማውረድ ሶስት ዓይነት የህክምና አማራጮች አሉት፤ እነሱም የአይን ጠብታ፣ ጨረር እና ቀዶ-ህክምና ናቸዉ፡፡ ብርሃንዎን ይጠብቁ! ሙሉቀን ጎ.ኃ (የዓይን ህክምና ሪዝደንት- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ©️CHSAAU Telegram: t.me/HakimEthio1
إظهار الكل...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

👍 5
የወንድማማች ፉክክርን በብልሀት የያዙ እናት =========================== ስብሀት ለአብ ገብረእግዚአብሄር በአስር አመቱ ከወላጆቹ ተለይቶ ከርባ-ገረድ ወደ አዲስአበባ ቢመጣም በልጅነቱ ጥሩ ፍቅር ስለተሰጠው ለመልመድ እንዳልተቸገረ ይናገራል። በተለይ ለእናቱ ወ/ሮ መአዛ ተወልደ መድህንን ያለው ፍቅር ከፍተኛ ነው። እናቱን በስማቸው ሳይሆን "ወለላይ" እያለ ነው የሚጠራቸው። ከዚህ በፊት የእትማማቾች (የወንድማማቾች) ፉክክር የልጆች ስነልቦና ላይ የሚያሳድረውን ዘላቂ አሉታዊ ተፅእኖ አይተናል። የነ ስብሀት እናት ወለላይ ግን በብልሀት ነበር ልጆቻቸውን ያሳደጉት። "ስብሀት ገ/ሄር ህይወትና ክህሎት" የሚለው የአለማየሁ ገላጋይ መፅሀፍ ገፅ 37 ላይ ስብሀት የሚከተለውን ይላል፦ "ለተቃና ስነ ልቦና ደግሞ የእናቴ ድርሻ ከፍተኛ ነው። በጣም ነበር የምትወደኝ። እኔ የራሴን ሳስታውስ እናታችን እኔን ከሁሉ አስበልጣ የምትወደኝ ነበር የሚመስለኝ፣ ትንሽ ካደግን በኋላ ተወልደ (ታናሽ ወንድም) ስጠይቀው "እኔን ከሁሉ አስበልጣ የምትወደኝ ይመስለኝ ነበር" አለኝ።ዮሴፍም (የታናሽ ታናሽ ወንድም) እንደዚሁ። ስለዚህ ጥበብ ነው ያ። እናቴ የጥሩ ተፅዕኖ ገድ ሆነችኝ። በመልካም ተፅእኖ በሩን ከፈተችልኝ።" የወንድማማች (የእህትማማች) ፉክክርን ወላጆች በብልሀት ሲይዙት ይህንን ይመስላል። በዩቲዩብ ተቀላቀሉን https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386 ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም! ዶ/ር ዮናስ ላቀው Telegram: t.me/HakimEthio1
إظهار الكل...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

👍 4
Tazma's Heart team performed Ventricular Septal Defect Closure and Patent Ductus Arteriosus ligation for a 7months old female infant.  Intraoperatively there was large posterior muscular Ventricular Septal Defect with bidirectional shunt and Patent Ductus Arteriosus. Ventricular Septal Defect (VSD) was closed with autologous pericardial patch and PDA was ligated. The infant was told to have this congenital heart disease by the age of 5 months after experiencing excessive sweating and interruption during breast feeding, fast breathing and lack of adequate weight gain since birth. Our patient is now doing well after procedure. Telegram: t.me/HakimEthio1
إظهار الكل...