cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Dreamers

#Dreamers ስንቃችን ተስፋ ነው፤ መድረሻችን ፍቅር። እዚህ ቻናል ላይ አነቃቂ ሀሳቦችን ፤ በፅሑፍ፣ በኦዲዮ፣ በቪድዮ ታገኛላችሁ። አንዲሁም አስተማሪ መፅሐፍትን፣ ቃለመጠይቆችን፣ ታሪኮችን እናቀርብላችኋለን። የተመቻቹን ሀሳብ ሼር ማድረግ እንዳትረሱ። እናመሰግናለን🙏 ጥያቄ ለመጠየቅ እንዲሁም ከአባላት ጋር ለመወያየት ግሩፖችንን ተቀላቀሉ 👉 @Ethiop_dreamers

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
423
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-1230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሕይወት ምንድን ናት? ስንቶቻችን ይህንን ለራሳችን ጠይቀን እናውቅ ይሆን? ምናልባት ሐብታም መሆን፣ ተምሮ ዶክተር መሆን፣ አልያም ሌላ ነገር ልትሉኝ ትችላላችሁ ። እኔ ግን ህይወት እነዚህን ሁሉ እንዳልሆነች እነግራችሗለው። እና ታዲያ ምንድነው አላችሁኝ መሰለኝ? ሕይወት እኛ እንደምናስባት የተወሳሰበች አይደለችም። ሕይወት አሁን ነች። አሁን ምን እያደረጋችሁ ነው? ምናልባት ይሄን ፅሁፍ እያነበባችሁ፣ ቤት እያስተካከላችሁ ወይም ከልጃችሁ ጋር እየተጫወታችሁ በቃ ሕይወት ማለት እሱ ነው። ሌላ ትንታኔ የለውም። እኛ ግን ብዙ ቅጥያ ፈጥረን ሕይወትን አክብደናታል። ትዝ ይላችሗል ልጅ እያለን 1ኛ ክፍል ሆነን ሁለተኛ ክፍል ስንገባ ደስተኛ ምንሆን ይመስለን ነበር። ከዛ አመቱ ያልቅና መግባታችን አይቀር እንገባለን። ግን ያሰብነው ደስታ የለም። አሁን ደግሞ ሶስተኛ ክፍል ስንገባ ደስተኛ እንደምንሆን እናስባለን። ከዛ እንዲህ እንዲህ እያልን ዩኒቨርሲቲ እንገባለን። ከዛ ከተመረቅን በሗላ ደስተኞች እንደምንሆን ማሰብ እንጀምራን። ከተመረቅን በሗላ ግን ስራ ፍለጋ መንከራተት እንጂ ደስታ የለም። ሁሌ ደስታን የሌለንን ከማሳደድ እንጂ ያለንን ከማጣጣም ለማግኘት አንሞክርም። እኛ እንዲኖረን ከምንፈልጋቸው ነገሮች በላይ መተንፈስ መቻላችን ብቻ ደስተኛ ሊያደርገን እንደሚገባ አስባችሁት ታውቃላችሁ። እባካችሁ ደስታን በቁሳቁስ ለመሸመት አትሞክሩ። በህይወታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እነደ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም በፍፁም በቁስ ልንሸምታቸው አንችልም። ምናልባት ገንዘብ ጊዜያዊ ፈንጠዝያ ውስጥ ከቶ ሊያደነዝዘን ይችል ይሆናል እንጂ የደስታችን ምንጭ ሊሆን አይችልም። ይህ ማለት ግን አትስሩ፣ ገንዘብ አታግኙ፣ አትማሩ ማለት አይደለም። እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርጉ ተማሩ ከዛ ሰርታችሁ ሀብታም ሁኑ ነገር ግን ደስታችሁን በገንዘባችሁ ለማግኘት አትሞክሩ። ደሀ ስታዩ ከሱ አንደምትሻሉ አታስቡ። ምክንያቱም ገንዘብ ለሰው ተፈጠረ እንጂ ሰው ለገንዘብ አልተፈጠረም። ያላችሁን ገንዘብም ሆነ የትምህርት ደረጃ እነደ ተራ ቁጠሩት። ለራሳችሁ ቅድሚያ ስጡ። እራሳችሁን አፍቅሩ። ለራሳችሁ ጥሩ ስሜት እንዲሰማችሁ የግድ ጥሩ ፍቅረኛ እስክቲዙ፣ ሀብታም እስክቶኑ አትጠብቁ። ምንም ነገር ባይኖራችሁም ውብ ናችሁ። ከቁሳቁስ የእናንተ ሰብአዊነት ይበልጣል። ለራሳችሁ ያላችሁን ክብር በምንም ምክንያት አትጣሉት። ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ሌላ ነገር ለራሳችሁ የምትሰጡትን ክብር እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ። በገንዘብ ሊገዛችሁ የሚፈልግ ሰው እሱ እራሱ በገንዘብ የተገዛ ሰው መሆን አለበት። አለበለዚያ እንደዚያ ማድረግ ለምን አስፈለገው? ብዙዎቻችን ሳይታወቀን ገንዘብ እየገዛን ነው። ከሰው በላይ ለገንዘብ ትልቅ ቦታ እንሰጣለን። ግን ይህ ለምን የሆነ ይመስላችሗል። ለሌሎች ሰዎች ቦታ የማንሰጠው ለራሳችን ቦታ ስለማንሰጥ ነው ወይም ሌሎችን የማናፈቅረው እራሳችንን ስለማናፈቅር ነው። እራሳችንን ምናፈቅር ከሆነ ግን ሌሎችም ልክ እንደ እኛ መፈቀር እንዳለባቸው ስለምናስብ ለማፍቀር አንቸገርም። እንደውም ብዙ ጊዜ የበታችነት የሚሰማቸው ሰዎች ሌሎችን ማፍቀር አይችሉም። ምክንያቱም የበታችነት ስሜት እራስን ብቁ አይደለሁም ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስሜት ነው። ሌላው ደግሞ የበላይነት ስሜት ነው። ይህ ስሜት ከበታችነት ስሜትም የከፋ ነው። ብዙዎቻችን የሚመስለን ይህ ስሜት እራስን አብዝቶ ከመውደድ የሚመጣ ከድርገን ነው የምናስበው። ነገር ግን ይህ ስሜት መነሻው ስጋት ነው። በሌላው የመበለጥ ስጋት የወለደው ስሜት አለበለዚያ ይህ ስሜት ለምን ይሰማዋል? አንድ በበላይነት ስሜት የተጠቃ ሰው ሁሌም ሌሎች ሰዎች ያሉበት ደረጃ ያሳስበዋል ምክንያቱም መበለጥ አይፈልግም። እንደውም የበላይነት ስሜት ትክክለኛ መነሻው የበታችነት ስሜት ነው። አንድ ለረዥም ጊዜ የበታችነት ስሜት ሲሰማው የነበረ ሰው የሚያስበው እንዴት የበላይ መሆን እንደሚችል ነው። የበላይነት ስሜት ውስጥ የታመቀ የበታችነት ስሜት አለ። እናንተ ግን በበላይነትም ሆነ በበታችነት ስሜት ውስጥ አትሁኑ። እንዲሁ እራሳችሁን አፍቅሩ። እራሳችሁን ለማፍቀር ምክንያት መደርደራችሁን አቁሙ። ለራሳችሁ ክብር ይኑራችሁ ገንዘባችሁን ከራሳችሁ አስበልጣሁ አትዩት። ገንዘብ አለማግኘታችሁ ደስታችሁን እንዲቀማችሁ አትፍቀዱ። ከዛ ሌሎችን ማፍቀረ ቀላል ይሆንላችሗል። ሌሎችን ለመውደድም ምክንያት አትደርድሩ። ዝም ብላችሁ ሰዎችን እና ይህችን አለም ውደዱ። ከዛ የህይወት ትርጉም ይገለጥላችሗል። © ዘፊሎሶፊ Group 👉🏽@vipbooksEth ምን ይመስላችኋል ሀሳባችሁን ወዲ በሉ @BHEREMETSHAFTOCH @BHEREMETSHAFTOCH #share join 👆🏾
إظهار الكل...
👍 1
የመደብ ትግል - ማርከስ ምንጭ ፦ ፍልስፍና (ከዘርዐያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ) ዝግጅት ፦ ፍሉይ አለም ከበርቴዎች ስለ ሃብታቸው መጨመር እንጂ ስለ ድሃው ለምን ያዝናሉ? እነዚያ ቦርጫም ደም መጣጮች ሁሉም ነገር ላይ ዋጋ ሲጨምሩ፣ የሰውነትን ዋጋ ዘንግተዋል፡፡ በእነርሱ ምክንያት ነው በዓለም ላይ ኢፍትሃዊነት የሰፈነው፤ በእነርሱ ምክንያት ነው እርስ በእርስ ከመተሳሰብ ይልቅ ስግብግብነት እና ገንዘብ አሳዳጅነት የነገሰው፡፡ መርዝ ናቸው፤ በሆድ ያለ ጥገኛ ትል ሰውነትን እንደሚያቀጭጭ ሁሉ እነርሱም ጥገኞች ናቸው... ደማችንንም ይመጡታል፡፡ እኛ ስለምናፈሰው ላብ ግድ የላቸውም፤ ከትርፋቸውም በቀር የሚያስቡት የለም፡፡ የናጠጡ ሃብታሞች “ቡርዥዋ” ይባላሉ። በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ፈላስፋ እና የኮሚኒዝም መስራች የሆነው ካርል ማርክስ እነዚህን ነው ደም መጣጭ ትሎች የሚላቸው፡፡ ብዙዎች የማርክስን ሃሳቦች ጠቅልለው እንዲሁ በደፈና ደሃ ሳይሰራ ይብላ' እያለ ነው ይሉናል፡፡ ሆኖም መመርመሩ አይከፋምና ማርክስ ምን አለ የሚለውን እንመርምረው፡፡ ማርክስ የፋብሪካ ባለቤቶች እና ገንዘብ እያምታቱ የሚኖሩ ባንከኞች ወይም ቡርዥዋ የወለዳቸው ካፒታሊዝም ነው ይሉናል። የፋብሪካቸውን የምርት ሂደት ትርፋማ በሚያደርጋቸው መንገድ ይቆጣጠሩታል፡፡ የመጀመሪያ የቁጥጥራቸው መንገድ ስራተኞችን በርካሽ ዋጋ ማሰራት ነው፡፡ ጥቂት ገንዘብን ብቻ ወደ ላብ-አደሩ ይበትናሉ... እነርሱ ግን ሚልዮኖችን ያፍሳሉ፡፡ ይህም የምስኪኑን ሰራተኛ ደም ከመምጠጥ አይተናነስም፡፡ በተቃራኒው የሰራተኛው ክፍል የተሻለ የስራ ሁኔታ፣ ደሞዝ እና እርካታን ማግኘት ይፈልጋል። በተጨማሪም ልክ እንደ ቡርዥዋዎቹ የቅንጦት ኑሮን መምራት ባይችሉ እንኳ የተመቻቸ ሕይወትን መምራት ይፈልጋሉ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ሃሳባቸው ይቃረናልና ወደ ግጭት ማምራታቸው አይቀርም። እናም ማርክስ “class struggle ወይም የመደብ ትግል ይከሰታል ይለናል፡፡ በቀጥታ ሜዳ ወርደው፣ ጦር ተማዘው የሚዋጉበት ሳይሆን የሃሳብ ጦርነት ይከሰታል። ማርክስ ካፒታሊዝም የባሪያ እና የጌታ ስርዓት የነበረውን ፊውዳሊዝምን አስወግዶልናል ይለናል፡፡ ሆኖም ግን ራስ ወዳድ እና ስግብግብ ባለሃብቶች አሁንም ቢሆን ደሃውን እንደ ባሪያ እየገዙት ነው ይለናል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ስርዓቱ በእነርሱ እጅ ላይ ነው፡፡ ቡርዣዎች ምርቱን ተቆጣጥረውታልና የኢኮኖሚው ሽጉጥ በእነርሱ እጅ ነው፡፡ እንደፈለጉም ወደ ፈለጉት አቅጣጫ ሊተኩሱት ይችላሉ፡፡ የጫወታው ህግም በእነርሱ ይመራል፤ ልክ እንደ ፊውዳል ባላባትም ሆነዋል። ማርክስ ለዚህ የሚያቀርበው መፍትሄ ይህ ነው - ሰዎች ሸቀጥ አይደሉም፣ ጉልበታቸውን ባሰኘን ዋጋ እየገዛን መበዝበዝ የለብንም። አማራጭ አጥተው ለእኛ ስለሚሰሩልን ብቻ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም መንፈግ የለብንም፡፡ የሰው ክብር ከሁሉ ይበልጣል፡፡ እናም ማርክስ Community ከሚለው ቃል ኮሚኒዝም ወይም ማህበረሰባዊነት የተሰኘ ስርዓትን ፈጠረ፡፡ በዚህ ስርዓት ሁሉም የማሕበረሰብ አካል የአቅሙን ያህል ይሰራል፤ የሚገባውንም ያገኛል። ጥቅምም መገኘት ያለበት እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ መሆን አለበትም ብሎ ያምናል። መምህሩ ያስተምራል፤ ግንበኛው ይገነባል... ሆኖም በሁለቱም መሃል ያለው የመስራት ፍላጎት እና አቅም መለያየት እንጂ የኑሮ ደረጃ ልዩነት ወይም የደሞዝ ልዩነት መሆን የለበትም፡፡ የኮሚኒዝም የመጨረሻ ግቡ ገንዘብ እና መደብ አልባ የሆነ ማህበረሰብን መገንባት ነው፡፡ ሰው በወደደው መንገድ እና የፈቀደውን ያህል ይሰራል፤ በምላሹም የሚያስፈልገውን ምግብ፣ መጠለያ፣ ልብስ እና የኑሮ ሁኔታ ያገኛል። ገንዘብ ከፋይም ሆነ ተቀባይ የለም። ስራን የምትሰራውም ለራስህ ጥቅም ወይም ገንዘብ ማግኘት አስበህ ሳይሆን፣ ለማህበረሰቡ የጋራ እድገት አስተዋጽኦን ለማበርከት ነው። Group 👉🏽@vipbooksEth ምን ይመስላችኋል ሀሳባችሁን ወዲ በሉ @BHEREMETSHAFTOCH @BHEREMETSHAFTOCH #share join 👆🏾
إظهار الكل...
ደስተኛ መሆን "ደስተኛ ነኝ ባላችሁ ቅፅበት ደስታችሁ ይጠፋል፤ ደስታ የሚመጣው ሳይፈልጉት ስትቀሩ ነው" ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ (ክሪሽናሙርቲ) ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ ታውቃላችሁ፤ መማር ምን እንደሆነ ማወቁ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ስለሂሳብ፣ ስለጂኦግራፊ፣ ስለታሪክ ከመፃሀፍት፣ ከመምህራን እንማራለን፣ ለንደን ወይም ሞስኮ ወይም ኒውዮርክ የት እንደሚገኙ እንማራለን፤ አንድ ማሽን እንዴት እንደሚሰራ ወይም ኣዕዋፋት ጐጆዋቸውን እንዴት እንደሚሰሩና ልጆቻቸውን እንዴት እንደሚንከባከቡ ወዘተ እንማራለን፡፡ በማስተዋልና በማጥናት እንማራለን፡፡ ይህ አንደኛው አይነት ትምህርት ነው፡፡ ግን ሌላም አይነት ትምህርት ይኖር ይሆን - በልምድ የሚገኝ ትምህርት? አንዲት ጀልባ ስራዋ በፀጥታማው ባህር ላይ እየተንፀባረቀ ስትጓዝ ማየቱ እጅግ የተለየ ልምድ አይደለምን? ያን ጊዜ ምን ይሆናል? አዕምሮ እውቀት እንደሚያከማቸው ያንንም ልምድ ይይዝና በሚቀጥለው ቀን ምሽት ያን የደስታና የሰላም ስሜት ሽተን ጀልባዋን ለማየት እንወጣለን፡፡ እናም አዕምሮ ይህን አይነቱን ልምድ ያስቀምጣል፡፡ ያን ልምድ በትውስታ መልክ ያስቀምጥና አንድናስብ ያደርገናል፡፡ አስተሳሰብ የምንለው የትውስታ ምላሽ ነው፡፡ ያቺን ጀልባ በባህሩ ላይ ካየንና የደስታ ስሜት ከተሰማን በኋላ ልምዱን እንደ ትውስታ በአእምሯችን አስቀምጠን ልንደግመው እንፈልጋለን፡፡ እናም የማሰቡ ሂደት ይቀጥላል፣ አይደለም እንዴ? እንደ እውነቱ ከሆነ እንዴት ማሰብ እንዳለብን የምናውቅ ጥቂቶች ነን፡፡ አብዛኞቻችን ከመፃህፍት ያነበብነውን ወይም ከሰው የሰማነውን ነው የምናስተጋባው፡፡ ወይም ደግሞ አስተሳሰባችን የውስኑ ልምዳችን ውጤት ይሆናል፡፡ በመላው ዓለም ዞረን አጅግ ብዙ ልምድ ብንሰበስብም፣ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ብንገናኝም፣ የሚሉትን ብንሰማም፣ ባህላቸውን ብንመለከትም፣ ሃይማኖትና ልማዳቸውን ብንጎበኝም  አስተሳሰባችን የሚመነጨው ከዚህ ሁሉ ትውስታ ነው። እናነፃፅራለን፣ እንመዝናለን፣ እንመርጣለን፡፡ እናም በዚህ ሂደት ለህይወት የሚኖረንን አስተሳሰብ እንቀርፃለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አይነቱ አስተሳሰብ፣ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ነው። በውሀ ላይ የምትንሳፈፍ ጀልባ፣ በሰዎች ትከሻ ወደማረፊያው የሚጓዝ አስከሬን ወይም ሸክሟ የከበዳት ሴት በማየት ልምድ ሊኖረን ይችላል- እነዚህ ሁሉ ስሜቶች አሉ፤ ነገር ግን ወደ ውስጣችን ገብተው አያብቡም፤ በዙሪያችን ለሚገኙ ነገሮች በሙሉ ስሜት ሲኖረን ብቻ በልማድ ያልተወሰነ የተለያየ አይነት አስተሳሰብ ይኖረናል። አንድን እምነት አጥብቃችሁ ስትይዙ ሁሉንም ነገር በዚያ የእምነት መነፅር ትመለከታላችሁ ፤ ከእውነታው ጋር ምንም ግንኙነት አይኖራችሁም፡፡ አንዲት የገጠር ነዋሪ ሴት የከበደ ሸክም ተሸክማ ወደ ከተማ ስትወጣ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ይህን አይነቱን ትዕይንት ስትመለከቱ ምን አይነት ስሜት ይሰማችኋል? ወይስ ሴትዮዋን ሁልጊዜ ስለምታዩዋት ሁኔታውን ለምዳችሁት ምንም አታስተውሏትም? አንድን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመለከቱት ምን ይከሰታል? ያያችሁትን ነገር ወዲያውኑ በሚዛናችሁ ላይ አስቀምጣችሁ ትተረጉሙታላችሁ፣ አይደለም? ትዕይንቱን የምትገነዘቡት እንደ ኮሚኒስት፣ እንደ ሶሻሊስት፣ እንደ ካፒታሊስት ወይም ሌላ <<ስት» ሆናችሁ ነው፡፡ ከእነዚህ ነገሮች ከወጣችሁ፣ በየትኛውም አስተሳሰብ ወይም እምነት መነፅር መመልከት ካቆማችሁና ከእውነታው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላችሁ በእናንተና በምታዩት ነገር መካከል እጅግ ልዩ የሆነ ግንኙነት እንዳለ ታስተውላላችሁ:: ምንም አይነት ሚዛን ከሌላችሁ፣ ምንም አይነት ዝንባሌ ከሌላችሁ፣ ለሁሉም ነገር ክፍት ከሆናችሁ በዙሪያችሁ የሚገኘው ነገር በሙሉ እጅግ የሚስብ ህያው ይሆንባችኋል፡፡ ለዛም ነው ወጣቶች ሳላችሁ ይህን ሁሉ ነገር መገንዘብ የሚኖርባችሁ፡፡ በውሃ ላይ የምትጓዘውን ጀልባ አስተውሏት፣ በአጠገባችሁ የሚያልፈውን ባቡር ተመልከቱት፤ ሸክም የከበዳትን ሰራተኛ እይዋት፣ የሀብታሞችን ብልግና፣ የሚኒስትሮችን ኩራት፣ እራሳቸውን እንደ አዋቂ የሚቆጥሩ ሰዎችን ጉራ አስተውሉ- ሳትተቹ ዝም ብላችሁ አስተውሏቸው:: ትችት በጀመራችሁ ቅፅበት ግንኙነታችሁ ይቋረጣል፤ በመካከላቹ ወሰን ይኖራል። ዝም ብላችሁ ብታስተውሉ ግን ከሰዎችና ከነገሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖራችኋል፡፡ ሳትፈርዱ፣ ሳትደመድሙ ከልባችሁ በንቃት ማስተዋል ከቻላችሁ አስተሳሰባችሁ በሚያስደንቅ ሁኔታ የሰላ ሲሆን ትመለከታላችሁ፡፡ ያን ጊዜ የሁልጊዜ ተማሪዎች ትሆናላችሁ በዙሪያችሁ ውልደትና ሞት፣ ገንዘብ፣ ስልጣን፣ ሃይል ለማግኘት የሚደረጉ ትግሎች፣ ማብቂያ የሌለው የህይወት ዑደት አሉ፡፡ ልጆች ሳላችሁ ይህ ሁሉ ምንድነው ብላችሁ ተገርማችሁ አታውቁም? አብዛኞቻችን አንድ ምላሽ እንፈልጋለን፤ እንዲነገረን እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህም አንድ የፖለቲካ ወይም የሃይማኖት መፅሃፍ እናነሳለን፣ ወይም ሌላ ሰው እንጠይቃለን፡፡ ነገር ግን ምላሽ የሚሰጠን ሰው አናገኝም ምክንያቱም ህይወትን በአንድ መፅሃፍ መገንዘብ አይቻልም፣ ቁም ነገሩም አንድን ሰው በመከተል አይገኝም:: እኔና እናንተ ህይወትን ራሳችን መገንዘብ አለብን፤ ይህን ማድረግ የምንችለው ግን ሙሉ በሙሉ ህያው ስንሆን፣ በጣም ንቁ፣ ተመልካች፣ አስተዋይ ስንሆን፣ በዙሪያችን በሚገኙ ነገሮች በሙሉ ስንማረክ ነው፡፡ ያን ጊዜ እውነተኛ ደስታ ምን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች ደስተኞች አይደሉም፡፡ ደስታ ያጡት በልባቸው ፍቅር ስላጡ ነው፡፡ በልባችሁ ፍቅር የሚኖራችሁ በእናንተና በሌሎች መካከል ወሰን ሳይኖር ሲቀር፣ ያለምንም ሚዛን ከሰዎች ጋር ስትገናኙና ስታስተውሏቸው፣ በውሃ ላይ የምትንሳፈፍ ጀልባን ውበት ማድነቅ ስትጀምሩ ነው፡፡ ቅድመ ሚዛናችሁ አስተወሎታችሁን እንዳይሸፍነው አድርጉ፤ ዝም ብላችሁ ብቻ አስተወሉ፡፡ በዚህ ቀላል አስተውሎታችሁ፣ እፅዋቱን፣ የሚራመደውን፣ የሚስቀውን፣ የሚሰራውን ሰው በምታዩበት ንቀታችሁ ሳቢያ በውስጣችሁ አንድ ነገር ሲከስት ትገነዘባላችሁ፡፡ ይህ ልዩ ነገር በውስጣችሁ ካልተፈጠረ፣ ፍቅር በልባችሁ ካልነገሰ፣ ህይወት ትርጉም አይኖራትም፡፡ ለዛም ነው መምህራችሁ የእነዚህም ሁሉ ነገሮች ፍሬ ነገር እንድትገነዘቡ ለማድረግ ራሱ መማር ያለበት፡፡ #share @BHEREMETSHAFTOCH -vip @BHEREMETSHAFTOCH -vip
إظهار الكل...
እውነተኛ ፍቅር -ኘሌቶ ምንጭ ፦ ፍልስፍና ( ከዘርዐ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ) ትርጉም ፦ ፍሉይ አለም ግሩም ከሆኑ የፍልስፍና እሳቤዎች አንዱን ፕሌቶ ከክርስቶስ ልደት 385 ዓመታት በፊት በጻፈው The symposium መጽሐፍ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ይህ መጽሐፍ በታላቁ የቲያትር ደራሲ አጋቶን ቤት ስለተዘጋጀ የራት ግብዣ ያትታል። ብዙ ጠቢባን ጣፋጭ ምግብን ሊመገቡ፣ ወይን ሊጠጡ እና ቁምነገር ሊያወጉ ታደሙ። በወንበሮቻቸውም ላይ እንዳሉ የተጠበሱ ምግቦችን እና ጣፋጭ አትክልቶችን መመገብ ጀመሩ፤ ግማሾቹ የወይኑ ስካር በአናታቸው ላይ ይወጣ ጀምሯል፡፡ እናም የድግሱ አዘጋጅ የነበረው አጋቶን ሁሉም እየተነሱ ስለ ኤሮስ ወይም ስለ ፍቅር የሚሰማቸውን እንዲናገሩ ጋበዛቸው፡፡ እናም ፕሌቶ ንግግር ማድረግ ጀመረ፤ ፍቅርን በሁለት ከፈለው - የመጀመሪያው ምድራዊ ፍቅር ሲሆን፣ ሁለተኛው ፍጹም ንጹህ የሆነ መለኮታዊ ፍቅር ነው፡፡ ምድራዊ ፍቅር የፍቅር መነሾ ነው፡፡ ልክ መሰላል ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደምንወጣው ሁሉ፣ ይህም ወደ ፍጹማዊ ፍቅር የሚያደርስ ጅማሮ ነው፡፡ በውስጡም ወሲባዊ ፍላጎት እና ምኞትን ይይዛል። ይህ ፍቅር የሚገናኘው ከሰውነት አቋም እና ከፊት ማማር ጋር ስለሆነ፤ ቆዳ ሲሸበሸብ፣ ጸጉር ሲሸብት የሚጠፋ ፍቅር ነው፡፡ ንጹህ ፍቅር በአንጻሩ ከነፍስያ ጋር ይቆራኛል። በዚህ ፍቅር ውስጥ ስንሆን ከፊት ገጽታም በላይ ጠልቀን የምንገባበት እና ስለ ስውነት መቀየር ግድ የማይሰጠን እንሆናለን፡፡ ይህ ሁለት ነፍሶች በፍቅር የሚወድቁበት ቦታ ነው፡፡ ዛሬ ላይ እንደዚህ አይነቱን ፍቅር ለመግለጽ platonic love የሚል ቃልን እንጠቀማለን፡፡ ፕሌቶ የፍትወት ፍላጎትንም ይቅር አስፈላጊ አይደለም አላለም፡፡ ይልቁኑ አንድን ሴት በመልኳ ተማርከን ልንቀርባት እንችላለን፤ ሆኖም ይህን ምድራዊ ፍቅር ንጹህ ወደሆነው መለኮታዊ ፍቅር ማሻገር ይጠበቅብናል፡፡ ፍቅራችን ከሰውነቷ ጋር ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ከዚህም በላይ ነፍሶቻችን ሊቆራኙ ይገባል፡፡ በእርጅና ዘመናችን አብሮን የሚሆን እና ከውበታችን መክሰም ጋር የማይጠፋ ፍቅር ውስጥ መሆን አለብን፡፡ እውነተኛ ፍቅር እውር አይደለም፤ ሆኖም በማስተዋል እና በጥበብ ይመራል። ከመልክ፣ ቁንጅናም በላይ ይሄዳል፡፡ ላይለያዩ የተጣመሩ ነፍሳት ፍቅራቸው ከምድራዊው ዓለም አይደለም። #share @BHEREMETSHAFTOCH -vip @BHEREMETSHAFTOCH -vip Group 👉🏽@vipbooksEth
إظهار الكل...
ይህ መፅሀፍ በተለያየ ወቅት፥ በአዲስ አድማስ'ና በኔሽን ጋዜጣ ይፃፉ ለነበሩት የኢ አማኝ ሀሳቦች፣ ግብረ መልስ ይሆን ዘንድ ከአንድ አማኝ ጎራ (ጤርጥዮስ ከቫቲካን በሚል የብእር ስም) የተፃፉ ሀሳቦች በመፅሀፍ መልክ ተጠርዘው ነው። ስለሆነም እንደርሱ “የአማኝ አላማኝ” ሰጣ ገባ ሳይሆን የአንድ #አማኝ ሀሳብ መሆኑን አስቀድመን እንናገራለን።   #share @BHEREMETSHAFTOCH -vip @BHEREMETSHAFTOCH -vip Group 👉🏽@vipbooksEth
إظهار الكل...
አማኝ አላማኝ .pdf5.22 MB
🍄የጅብ ጥላ🍄      ብርሀን ርቆ                   ሲመጣ ጨለማ       የፀሀይ ነፀብራቅ                      ድምቀቷ ሲቀማ        ምሽቱ ሲነግስ                        በድፍን ሀገሩ         ከመሬት በመጥፋት                      ዛፍ ቁጥቋጦ ሳሩ          አየው በጅብ ጥላ                          ተሸፍኖ ምድሩ።
إظهار الكل...
"የጠገበች ነፍስ የማር ወለላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ዅሉ ይጣፍጣታል።" (ምሳ 27:7)
إظهار الكل...
ከመርፌ ቀዳዳ በጠበበ እምነት እንዴት ይነገራል ፍቅርና እውነት? መጠርጠር ባህሩ ስንቱን አሰጠመ? ማመን ያልቻለውን ባለማመን ቆመ:: አማኝም ሞኝ ነው እምነቱን ያብራራል ከመስበኩ ብዛት አምላኩን ይሽራል:: ሰባኪም ይጮሀል በእምቢልታ መለከት የሚያምነውን ሚኖር አንዱ ቢገኝማ ምን ያደርጋል ስብከት? ኤልያስ ሽታኹን
إظهار الكل...
Repost from Art of Daniel
Photo unavailableShow in Telegram
title ፦ ሰማያዊ ሹመት ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ፣ ምኒሊክ ስዩመ እግዚአብሔር ፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.