2 057
المشتركون
+324 ساعات
+217 أيام
+6130 أيام
أرشيف المشاركات
በፋብሪካ ተቀነባብረው የታሸጉና በውስጣቸው ከፍተኛ ጨው፣ ስኳርና የስብ ይዘት ያላቸው ምግቦችና መጠጦችን አዘውትሮ መመገብ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ከማሳጣቱም በላይ ለውፍረት፣ ለልብ በሽታ፣ ለስኳር፣ ለካንሰርና ሌሎች ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነታችንን ይጨምራል፡፡
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
#HealthForAll
መስከረም 25/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXx
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 20/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXx
Repost from Ministry of Health ET
+1
የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም በሆነዉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ ስለተሰየሙ የተሰማንን ልባዊ ደስታ እየገለጽን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸዉ እንመኛለን!
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V
ሁሉም ሰው ኦክስጅን ያስፈልገዋል፤ አንዳንድ ሰዎች ግን ትንሽ ተጨማሪ ያስፈልጋቸዋል!
የዓለም ኦክስጅን ቀን፣ በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ ይከበራል
መስከረም 22፣ 2019 ዓ.ም
October 2, 2026
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
እናቶችና የጨቅላ ህፃናት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶች በጤና ልማት አጋር ድርጅቶች ድጋፍ ተደረገ::
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ መስከረም 20/2019ዓ.ም
ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ እና ሂሊንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ (Healing Hands Of Joy) በተባሉ ሁለት ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶች የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ፣ ምክትል ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ድጋፉን በተረከቡበት ጊዜ እንደተናገሩት ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ እና ሂሊንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስና ጤናቸውን ለማሻሻል እየተደረገ ባለው ርብርብ ላይ ያላቸው አበርክቶቱ እጅግ የላቀ መሆኑን ተናግረው፤
ቢሮው የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቢሯችን በክልሉ ከሚገኙት ቢሮዎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ በመሆነበት የድል ማግስት ድጋፍ ማድረጋቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት የተደረገው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ያለውን ክፍተት ታሳቢ ያደረገ እና በአንዳንድ የጤና ተቋማት ያጋጥም የነበረውን የማዋለጃ ቁሳቁስ እጥረት የሚቀርፍ በመሆኑ በተጠቃሚው ማህበረሰብ እና በራሳቸው ስም የቢሮ ሀላፊዋ ድርጅቶቹን አመስግነዋል::
በኢንጀንደር ሄልዝ የሲዳማ ክልል አስተባበሪ አቶ ተስፋዬ አርዶሎ ግብአቱን ባስረከቡበት ጊዜ እንደተናገሩት የተደረገው ድጋፍ በሰለጠነ የጤና ባለሙያ የሚሰጠውን የወሊድ አገልግሎት በማጠናከር የእናቶችና ሕፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚያግዙ፣ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የተገዙ የህክምና ቁሳቁሶች መሆናቸውን ገልፀው፣ ድጋፉ ቀጣይነት ያለው እንደሆነም ተናግረዋል።
በሂሊንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ(HEALING HANDS OF JOY) የክልሉ አስተባባሪ አቶ ሽመልስ ምትኩ በበኩላቸው ድርጅታቸው በሲዳማ ክልል 6 ወረዳዎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ፣ ለፊስቱላ ችግር የተጋለጡ እናቶች ላይ እንደመስራቱ ያለውን አሳሳቢ ችግር አስቀድሞ ለመቅረፍ ደህንነቱና ንፅህናው የተጠበቀ የወሊድ አገልግሎት እንዲሰጥ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአልትራ ሳውንድ እና ሌሎች የማዋለጃ መሳሪያዎች በሁለት ዙር ለ8 ጤና ጣቢያዎች በድርጅታቸው በኩል ድጋፍ በመደረጉ የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ ገልፀው ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሴክተሩ እያስመዘገበ ያለውን አመርቂ ውጤት እንደ ሁልጊዜው በመደጋገፍ እንደሚያስቀጥሉ አክለው ተናግረዋል።
በሁለቱም ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተደረገው ድጋፍ በጤና ተቋማት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን የወሊድ አገልግሎት ጥራቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል የሚያግዙ መሆናቸው ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የጤና አገልግሎቱን ለሚሰጡ ባለሙያዎች አስቀድሞ ስልጠና መሰጠቱ፣ የእናቶች ማቆያና የነፍሰጡር እናቶች ፎረም እንዲጠናከር እየተሰራ መሆኑ ሊጠናከር የሚገባ ተግባር በመሆኑ ይበልጥ ተቀናጅቶና ተናብቦ በማስቀጠል የላቀ ውጤት ማምጣት ተጠባቂ መሆኑ በአፅንኦት ተነስቷል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 20/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/
እንኳን ደስ አላችሁ /እንኳን ደስ አለን !
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በክልሉ ውስጥ ካሉት ቢሮዎች አንደኛ በመውጣት ተሸለመ !
የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም በገመገመበት በዚህ ጉባኤ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ በክልሉ ከሚገኙት ቢሮዎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ ፣ በጉባኤው ፊት ከክብርት አፌጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እጅ የዋንጫ እና ሴርተፍኬት ተሸላሚ በመሆኑ ቢሮው የተሰማውን ደስታ ይገልጻል።
ባለፉት ዓመታት ቢሮው ህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሠራሮችን በመንደፍ ፣ በጤና ሚኒስቴር የተቀረጸ የጤና ፖሊስ እና ከፖሊስው የተቀዱ ስትራቴጅዎችን በአግባቡ በመምራት ፣ እንዲሁም የአለም ጤና ድርጅት የቀረጸውን ስድስቱን ምሰሶዎች (WHO 6 bulding blocks) ገቢራዊ ለማድረግ እንደ ክልል ''ለውጤት እንስራ ፣ ለላቀ ውጤት እንስራ ፣ ለላቀ ውጤት እና ለጥራት እንስራ '' በመጨረሻው ምዕራፍም "ሞዴል የሆነ የጤና ስርዓት እንፍጠር!" በሚል የራሱን ክልላዊ ኢኒሼቲቭ በመቅረጽ ''የማይዋዥቅ የጤና ስርአት/ Resilient Health System '' ለመዘርጋት በተሠራው ስራ የላቀ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል።
የክልሉ ጤና ቢሮ የሀገሪቱን የጤና ፓሊሲ መሠረት ያደረጉ በሽታን አስቀድሞ መከላከል እና አክሞ የማዳን እንዲሁም ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት የሚያረጋግጡ አሠራሮችን በመንደፍ ፣ ግብአት በማሟላት ፣ የማህበረሰቡን ንቃተ ጤና የሚያጎለብቱ አሰራሮች መተግበር እና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለህብረተሰቡ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ፣ ከሁሉም በላይ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቅድሚያ በመስጠት በተሰራው ስራ ከፍተኛ መሻሻል እንደመጣ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በተለያዩ ጊዜያት የመስክ ምልከታ እና በዴስክ ግምገማ በማድረግ በሴክተሩ የተሻለ አሠራር መፈጠሩን በማረጋገጡ የተሰጠ እውቅና እንደሆነም ታውቋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ለተመዘገበው ውጤት ዕውቀታቸውንና ጊዜያቸውን ሳይሰስቱ የጤና አገልግሎቱን ለመሩ ፣ ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ቢሮ በሙያቸው ላገለገሉ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ለሰጡ አመራሮች ፣ ሙያተኞች ፣ ለጤናው ዘርፍ አጋሮች እና ለመላው ባለድርሻ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናውን እያቀረበ የተገኘው እውቅና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ እና የሚያተጋ በመሆኑ ለቀጣይ በጀት አመት መልካም የስራ ዘመን ይመኛል ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ /እንኳን ደስ አለን !
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/
በተገልጋዩን ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ መስከረም 19/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ለቢሮ፣ ለሆስፒታሎች፣ለተጠሪ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ዙሪያ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል።
ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታሪኩ ዱካሞ በመልዕክታቸው የጤናው ሴክተር ከ19,000 በላይ ሰራተኞች እና ከ7 ሚሊዮን በላይ ተገልጋይ ያለው ግዙፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ ከዚህ ቀደም ከመድሀኒት አቅርቦት ጋር፣ ከአገልግሎት ተደራሽነትና ፍትሀዊነት ፣ከዲውቲ ክፍያ እና ከደረጃ እድገት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ይነሱ እንደ ነበር አስታውሰው በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን በማድመጥና ደረጃ በደረጃ በመፍታት ሴክተሩ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።
በሴክተሩ የላቀ የማህበረሰብ እርካታን ለማረጋገጥና በክልሉ የተሻለ የጤና ቱሪዝም ለማስፈን
በቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ዙሪያ በየተቋማት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ በመሆኑ ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም የተሻለ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የቢሮው የስነምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ቦኩ በበኩላቸው አቤቱታ ተገልጋይ በተሰጠው አገልግሎት፣ በአሰራር ወይም በሠራተኛ አያያዝ ላይ ቅሬታ ሲኖረው ለተቋሙ/ቅሬታ ሰሚው የሚያነሳው ጥያቄ በመሆኑ ይህንን በየጊዜው መፍታታ ለተቋም አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ፋይዳው የጎላ መሆኑን በመግለፅ፣ ስልጠናው ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴር ለመጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ አለማየሁ አክለውም የስልጠናው አላማ የቅሬታ ባለሙያዎች ያለባቸውን ክፍተቶች በመሙላት በተቋማቸው የተሻለ አገልግሎት እንዲትሰጡ ማስቻል በመሆኑም ስለ ቅሬታ አቀራረብና አፈታት፣ የቅሬታና አቤቱታ የማጣራት ስርዓት እንዲሁም ሌሎች ርዕሶችን በጥልቀት በመረዳት የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።
በአሰልጣኞች በቀረበ ሰነድም የተገልጋዩን ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት በተገቢው መፈፀም የተገልጋይ እርካታ የሚያሻሽል፣የአገልግሎት ጥራትን የሚያሳድግ፣ችግሮች እንዳይደገሙ የሚያግዝ
ተጠያቂነትና ግልጽነት በመፍጠር በተቋሙና በተገልጋይ መካከል እምነትን ይገነባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ በርካታ ሀሳብ አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው መግባባት ላይ ተደርሷል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/
በዛሬው ምሽት የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን የ2018 አፈጻጸም እና በ2019 ዕቅድ ላይ በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሐም ማርሻሎ መሪነት በበይነ መረብ ከታችኛው መዋቅር ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ሁሉም ዞኖች ፣ የሀዋሳ ከተማ እና ሁሉም ወረዳዎች የተሳተፉ ሲሆን ባሳለፍነው በጀት ዓመት 2018 በጀት 85 በመቶ
የነበረውን በዚህ በጀት ዓመት ወደ 95% ለማሳደግ መታቀዱን ለማወቅ ተችሏል።
Repost from Ministry of Health ET
ከክትባት በኋላ በህጻናት ላይ የሚከሰቱ እንደ ትኩሳት፣ መቅላት ወይም እብጠት ያሉ ቀላል ምልክቶች ክትባቱ እየሰራ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።
#ChildImmunization
#VaccinesSavesLives
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V
Repost from South Radio And Television agency
ኢትዮጵያ የወረርሽኝ ቀድሞ ማስጠንቀቅና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሟን እያጠናከረች ነው
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተከስተው ከነበሩ ወረርሽኞች ትምህርት በመውሰድ የወረርሽኝ ዝግጁነት፣ ቀድሞ ማስጠንቀቅና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሟን እያጠናከረች መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መልካሙ አብቴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢንስቲትዩቱ የወረርሽኝ ስጋትን ቀድሞ በመለየትና በመከላከል ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በቴክኖሎጂ ራሱን እያበቃ መሆኑን ጠቁመው፤ የሀገር ውስጥ የምርመራ አቅምን ማሳደጉንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 እና በማርበርግ ወረርሽኞች ወቅት ካጋጠሟት ፈተናዎች በመማር የወረርሽኝ ዝግጁነት፣ ቀድሞ ማስጠንቀቅና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሟን እያጠናከረች መሆኑን ተናግረዋል።
በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ወረርሽኞች ከችግር በኋላ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ቀድሞ ዝግጁ የሆነ ሥርዓት መገንባት ያለውን ጠቀሜታ ያሳዩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በዚህም መሠረት በሰው ኃይል ሥልጠና፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በላቦራቶሪ አቅም፣ በአሰራር ሥርዓትና በወረርሽኝ ማስተባበሪያ መዋቅሮች ላይ መዋዕለ-ንዋይ መፍሰሱን ገልጸዋል።
በዚህም በክልልና በዞን ደረጃ 24 የሚደርሱ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን ማዕከላት ተስፋፍተው ከብሔራዊ ማዕከል ጋር ተሳስረው እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።
የአቅም ግንባታ ስራው ውጤታማነት በማርበርግ ወረርሽኝ ወቅት ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን ጠቅሰው፣ በዚህም በአጭር ጊዜ ወረርሽኙን መቆጣጠር ማስቻሉን ገልጸዋል።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/photo/?fbid=1561399832693073&set=pcb.156140003602
Repost from Ministry of Health ET
+3
በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን የደም መፍሰስ እንዳይከስት መከላከል የሚያስችል እና የእናቶችና ህጻናት ጤናን የሚያሻሽሉ መመሪያዎች የማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ
___________
በማስተዋወቂያው መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ በመልዕክታቸው መመሪያዎቹ በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን የደም መፍሰስ እንዳይከሰት መከላከል የሚያስችል እና የእናቶችና ህጻናት ጤናን የሚያሻሽሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2030 ለማሳካት ለያዘችው የእናቶችና ህጻናት ሞት ቅነሳ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ለተፈጻሚነታቸው የሁሉም ባለድርሻ አካላት እና አጋር አካላት ርብርብና ትብብር ይጠይቃል ብለዋል...More
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V
በጤናው ሴክተር ሁሉም ሠራተኛ በተሰማራበት የሥራ መስክ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ አለበት — አቶ ታሪኩ ዱካሞ
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ መስከረም 11/2019 ዓ.ም
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ዱካሞ፣ ሁሉም ሠራተኛ በተሰማራበት የሥራ መስክ ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጣ ጠንካራ የሥራ ተጠያቂነትና ቁርጠኝነት እንዲኖር አሳስበዋል።
አቶ ታሪኩ ከጤና ቢሮው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ማንኛውም ሠራተኛ ለጤና ዘርፉ የተቀጠረ በመሆኑ የተሰጠውን ኃላፊነት በትጋት፣ በተጠያቂነትና በተገቢው የሥራ ሥነ-ምግባር መወጣት እንደሚገባው ገልጸዋል።
የሥራ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም፣ የሥራ ቦታን ጽዱና ማራኪ ማድረግ፣ የቢሮና የግቢውን ንጽህናና ውበት መጠበቅ፣ የተሰጡ ተግባራትንም በጥራትና በወቅቱ ማጠናቀቅ የእያንዳንዱ ሠራተኛ የዕለት ተዕለት ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በጤናው ሴክተር ውጤት የአንድ አካል ሳይሆን የሁሉም ሠራተኞች የጋራ ጥረት ውጤት በመሆኑ፣ በመናበብ፣ በመተባበርና በጋራ ኃላፊነት መሥራት እንደሚገባ አቶ ታሪኩ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ለተገልጋይ ማኅበረሰብ የሚሰጠው አገልግሎት በተገቢው መስፈርትና በጥራት እንዲሰጥ፣ ባለጉዳዮችን በአክብሮት፣ በትህትናና በቅልጥፍና ማስተናገድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ ታሪኩ እንዳሉት፣ የሠራተኞች የሥራ መደብ ምዘናም የሠራተኛውን ኃላፊነት፣ የሥራ አፈጻጸምና ያመጣውን ውጤት በመመዘን ተጠያቂነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ በመሆኑ፣ ሁሉም ሠራተኛ የተሰጠውን ሚና በብቃት በመወጣት ለጤና ዘርፉ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በበኩላቸው፣ የተነሱት ሀሳቦች የሥራ ኃላፊነትን፣ ተጠያቂነትንና ውጤታማነትን በተግባር ለማሳደግ ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የተሰጠንን ኃላፊነት በተገቢው መወጣት፣ ተገልጋዮችንም በአክብሮትና በቅልጥፍና ማስተናገድ የሁሉም ሠራተኛ ድርሻ መሆኑን ከውይይቱ መረዳታቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም የተሰጣቸውን ሚና በተጠያቂነት በመወጣት ለተቋሙና ለጤና ዘርፉ ውጤታማነት የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
