cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ETH Coffee Network News

አስተማማኝ እና ጊዜውን የጠበቀ ትኩስ የቡና መረጃዎችን እዚህ ያገኛሉ። Join Group @EthCoffeeCommunity

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 449
المشتركون
+224 ساعات
+67 أيام
+4630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ 2024 የመጨረሻ ዙር 40 አሸናፊዎች ዝርዝር ለዓለም አቀፍ የዘርፉ ውድድር ያለፉት እነዚህ ምርጥ 40 ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ነሐሴ መጨረሻ በበይነ መረብ በሚወጣ የቡና ጨረታ ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ እንደሚሸጡ ይጠበቃል። የሁሉም ስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
2
በወጪ ንግድ የዋጋ ጥናት ቦርድ የሳምንታዊ የዋጋ ማነፃፀሪያ ማሳወቂያ ቅፅ ከሀምሌ 06 እስከ ሀምሌ 19 2016 ዓ.ም @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
12 07 24_ Weekly Reference Price.pdf9.56 KB
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የባለልዩ ቡና ጣዕም ቅምሻ ውድድር 40ዎቹ አሸናፊዎች ተለዩ በ4ኛው የባለልዩ ቡና ጣዕም ቅምሻ ውድድር 40 ዎቹ የመጨርሻዎቹ አሸናፊዎች ሲለዩ ባሻ በቀለ፣ ማቲዎስ ለሜሳና ቡኩቶ ዱሬ ከሲዳማ ክልል ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘው አጠናቀዋል። ከ20 ሄክታር በታች ያላቸው ከ800 በላይ የቡና አርሶ አደሮች ላለፉት 6 ወራት መወዳደራቸውና ከእነዚህም ውስጥ 150ዎቹ ለሀገር አቀፍ ውድድር ማለፋቸው በመርሀግብሩ ወቅት የተገለጸ ሲሆን የተወዳዳሪዎች ናሙና ከጅማ፣ ሃዋሳ፣ ድሬዳዋና አዲስ አበባ መሰብሰቡም ተጠቁሟል። ትናንት በተካሄደው 4ኛው የባለልዩ ቡና ጣዕም ቅምሻ ውድድር 40 አርሶ አደሮች የተቀመጠላቸውን መስፈርት በመሟላት ለዓለም አቀፍ የዘርፉ ውድድር ያለፉ ሲሆን ምርጥ 40 ተወዳዳሪዎቹ 12 ዓለም አቀፍ ገዢዎች በተገኙበት የተለዩ ናቸው። የውድድሩ አሸናፊዎች ነሐሴ መጨረሻ በበይነ መረብ በሚወጣ የቡና ጨረታ ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ እንደሚሸጡና ላመጡትም ውጤት ሽልማት እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 3
NYCE Market Closing Date: 11/07/2024 Arabica = + 0.03US cents lb.                                             (0.01%)               245.30 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
አርሶ አደሮች የሚበላሹ ምርቶችን በቀጥታ የሚሸጡበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ አርሶ አደሮች ለረዥም ጊዜ መቆየት የማይችሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርቶችን የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የገበያ ማዕከላት በቀጥታ የሚሸጡበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ አርሶ አደሮች በቶሎ የሚበላሹ ምርቶችን ከማሳቸው ሰብስበው እጃቸው ላይ ስለሚያቆዩ በርካታ ምርቶች ያላግባብ ባክነው እንደሚቀሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ግብይትና የገበያ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ ተናግረዋል፡፡ ለረዥም ጊዜ መቆየት የማይችሉ ምርቶችን አርሶ አደሮች ለአንድ ወር ያህል የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጃቸው የገበያ ማዕከላት በማስገባት ሸጠው እንዲሄዱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አክለው ገልጸዋል፡፡ በተለይ ቲማቲም፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ማንጎና ሌሎች የፍራፍሬና የአትክልት ምርቶች ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደማይችሉ የገለጹት ኃላፊው፣ ምርቶቹን ለማቆየት የከተማ አስተዳደሩ ባስገነባቸው የገበያ ማዕከላት ውስጥ ማቀዝቀዣዎች በቅርቡ ለማስገጠም በሒደት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ መከልከሉ ሕግን መሠረት ያላደረገ ነው ሲል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተቃወመ ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር፣ ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት፣ በነዳጅ ኃይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉ፣ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችንና የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ማስተጓጎል መሆኑን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሐና አርዓያ ሥላሴ ተፈርሞ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በቀጥታ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡ በተለይ ለማንኛውም አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡ በግብርና፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር፣ በሆልቲካልቸር፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግንባታና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑንም ኮሚሽነሯ በደብዳቤያቸው አብራርተዋል፡፡ በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ ምንጭ፡ሪፖርተር @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 4👏 1
NYCE Market Closing Date: 10/07/2024 Arabica = -2.70 US cents lb.                                             (-1.09%)               245.27 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የነዳጅ  ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ ቤንዚን በሊትር 82 ብር ከ60 ሳንቲም ሲገባ ነጭ ናፍጣ 83 ብር ከ74 ሳንቲም ሆኗል። ከዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአይሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል። በዚህ መሰረት ፦ ➡ ቤንዚን - ብር 82.60 በሊትር ➡ ነጭ ናፍጣ - ብር 83.74 በሊትር ➡ ኬሮሲን - ብር 83.74 በሊትር ➡ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 65.48 በሊትር ➡ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 64.22 በሊትር  ሆኗል። የአውሮፕላን ነዳጅ በሊት 70 ብር ከ83 ሳንቲም ሆኖ ባለበት ይቀጥላል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለም አቀፍ የቡና ገበያ በአንድ ቀን ልዩነት ከፍተኛ ዋጋ መጨመር አስመዘገብ የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በአንድ ቀን 13.79 ዶላር ጭማሪ በማድረግ 247.97 በመድረስ ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ አስመስግቧል። ለዋጋ መጨመር እንደ ዋነኛ ምክንያት የተጠቀሰው የአቅርቦት እጥረት ሲሆን መነሻውም የቬትናም መጥፎ የአየር ጠባይ እና የተጓተተ የኤክስፖርት ሂደት፣ የብራዚል ከሚጠበቀው በታች ዝናብ እንደሆን ተጥቀሷል። ባለሞያውች እንደሚሉት ከሆን እንዚህ ምክንያቶች እስከ ተያዘው የፈርንጆች ዓመት መጨረሻ ድረስ ተጽኖ መፈጠራችው ሊቀጥል እንደሚችል እና ከዛም ጋር ተያይዞ የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል መላምት ሰተዋል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 2 2
NYCE Market Closing Date: 9/07/2024 Arabica = +13.79 US cents lb.                                             (5.899%)               247.97 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
إظهار الكل...
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.