cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

🔰ንቃት ለትውልድ🔰 ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 203
المشتركون
+124 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-2130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እራሳችሁን አስቀድሙ! ፡ መጀመሪያ እራሳችሁን አድኑ፣ አስቀድማችሁ በደህንነታችሁ እርግጠኛ ሁኑ፣ ባላችሁበት  ሁኔታ ሰላም ይሰማችሁ። ትናንታችሁ ጠባሳ የጣለባችሁ ሳያንስ ዛሬም እናንተው በፍቃዳችሁ ተጨማሪ ጠባሳ እራሳችሁ ላይ አትጣሉ። ከህመማችሁ ለመንፃት መተው ያለባችሁን ነገር ተዉ፤ ስለወደፊት ህይወታችሁ የሚገዳችሁ ከሆነ እስራታችሁን ፍቱ፣ በእርግጥም ህይወትን በሙላት መኖር ካሻችሁ የይቅርታ ልብ ይኑራችሁ። ሸክማችሁን አራግፉ፣ ለደህንነታችሁ ዋስተና አስቀምጡ፣ በምርጫችሁ ወደፊትን ተመልከቱ፣ ኋላ ከቀረውና ከተበላሸው ይልቅ የሚመጣውና ማስተካከል የምትችሉት ጉዳይ ላይ አተኩሩ። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
🥰 4🔥 2
ሳትጀምር አትሸነፍ! : እግርህን ሳታነሳ አትሰበር፤ ባልሆነው አትሸበር፤ ባልተከሰተው አትታሰር፤ ገና ለገና ሊመጣ ይችላል በተባለ የወረደ መላምት ትልቁን ሃሳብህን አትቅበረው። ውድቀትም ይግጠምህ ስኬት ሞክሮ ማየትን የመሰለ ነገር የለም። ምንም ነገር ልታልም ትችላለህ መሳካቱን ልታውቅ የምትችለው ግን ስታደርገውና ስታደርገው ብቻ ነው። ምንም ነገር ሊሆንም ላይሆንም የሚችልበት መንገድ እኩል ነው። የህይወትህ ሚዛን እምነትና አመለካከትህ ነው። እንዲሳካ የምትፈልገው ነገር ቢኖር በፍረሃት ውስጥም ሆነህ ማድረጉ ካለማድረግ የተሻለ ነው። ድፍረት፣ እድገት፣ መነቃቃት፣ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድርጊት ውስጥ ሆነህ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው። የበይ ተመልካች የምግቡን ጠዓም ሊያውቅ አይችልም፤ በፍረሃት ታስሮ፣ በስጋት ውስጥ ወድቆ ሳይሞክር የቀረም ሊገጥመው የሚችለውን መልካም ነገር ሊያውቅ አይችልም። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
6🥰 1👏 1
የተፃፈ ነገር የለም! : አንዳች አስቀድሞ የተወሰነልህና አንተ ምድር ላይ መጥተህ በተግባር የምትገልፀው ነገር ከቶ የለም። ድርሰት ሲኖር ተዋንያን ይኖራሉ። በዚህም ሁኔታ የሰው ልጅ የተፃፈ ወይም የተደረሰ ህይወት ካለው እኛ እየኖርን ሳይሆን እየተወንን ነው ማለት ነው። የህይወት አመክንዮ ግን ፈፅሞ ከዚህ የተለየ ነው። ብዙ ጊዜ "የተፃፈልኝን ነው የምኖረው፣ ይሔ የአርባ ቀን እድሌ ነው ምንም ማድረግ አልችልም፣ ተፈርዶብኛል።" እያሉ የሆነባቸውን ነገር ሁሉ ፈጣሪያቸው እንዳመጣባቸው የሚጠቅሱ ሰዎች ከእያንዳንዱ ምርጫቸው በስተጀርባ ለሚመጣው ውጤት ሃላፊነት ለመውሰድ ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ፈጣሪ የትኛውንም የሰውን ልጅ ሰነፍ አድርጎ አልፈጠረውም፣ ሰነፍ እንዲሆንም አልፈረደበትም፣ አምላክ ማንም ወድቆ እንዲቀር አይፈልግም። ሁላችንም ነፃ ፍቃድ (Free will) አለን። ያሰኘንን ህይወት ከመኖር በላይ የምንፈልገውን ነገር የማምለኩ ነፃነትም ጭምር በፈጣሪያችን ተሰጥቶናል። ጣዖት አቁመው የሚሰግዱለት ሰዎችም እየኖሩ ነው፣ ፈጣሪዬ አምላኬ ብለው የሚያመልኩት ሰዎችም እኩል እየበሉና እየጠጡ እየኖሩ ነው። ፈጣሪ ፈራጅ ቢሆንና ነፃነትን ባይሰጥ መጀመሪያ እንዲጠፉ የሚፈርድባቸው እነዛ አምላክነቱን ክደው ለጣዖት የሚሰግዱትን ነበር። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
5🔥 2
የተፃፈ ነገር የለም! ፨፨፨//////////፨፨፨ የተፃፈልንን ነው የምንኖረው ወይስ ህይወታችንን የምንፅፈው እኛ ነን? ብዙ አከራካሪ ጥያቄ ቢሆንም ምላሹ ግን አንድና ግልፅ ነው። የተፃፈልን የሚባል ነገር የለም። እርግጥ ነው ፈጣሪ የሚሆነውን ያውቃል ነገር ምንም የወሰነልን ነገር የለም፣ እውነት ነው እግዚአብሔር ታሪካችንን ያውቃል ነገር ግን ያን ታሪክ እንድነኖረው ወስኖና መርጦ አልሰጠንም። የሰው ልጅ የሚኖረው ህይወት ገና ከጅምሩ የተፃፈ ቢሆን ምንም መውጣትና መውረድ፣ መልፋትና መታከት ባላስፈለገው ነበር። የሰው ልጅ ተፈጥሮ ለፅድቅ እንጂ ለኩነኔ አይደለም፣ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩ ለትርፍ እንጂ ለኪሳራ አይደለም። ፈጣሪ የማንንም ውድቀት አይፈልግም፣ አምላክ ለማንም ስቃይን አይሰጥም። ወደድንም ጠላንም የሁሉም ነገር ጦስ የገዛ ምርጫችን ነው። ሁለት ሰዎች ከአንድ ቤት ወጥተው አንዱ ገዳይ አንዱ ደግሞ ነፍስ አድን የሚሆኑት ስለተፃፈላቸው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? አንድ አካባቢ በጓደኝነት ካደጉ ሰዎች አንደኛው ሱሰኛ ሌላኛ ስኬታማ የቢዝነስ ሰው የሚሆኑት ስለተፃፈላቸው ይመስላችኋል? ሁለት ከነመፈጠራቸውም የማይተዋወቁ ሰዎች ሌላ የማያውቁት ሰው በለኮሰው እሳት ህይወታቸውን የሚያጡት ስለተፃፈላቸው ነውን? በፍፁም አይደለም። ፈጣሪ የነፃነት አምላክ ነውና የማንንም ህይወት ፅፎና ወስኖ አላስቀመጠም። አዎ! ጀግናዬ..! የተፃፈ ነገር የለም! አንዳች አስቀድሞ የተወሰነልህና አንተ ምድር ላይ መጥተህ በተግባር የምትገልፀው ነገር ከቶ የለም። ድርሰት ሲኖር ተዋንያን ይኖራሉ። በዚህም ሁኔታ የሰው ልጅ የተፃፈ ወይም የተደረሰ ከሆነ እኛ እየኖርን ሳይ እየተወንን ነው ማለት ነው። የህይወት አመክንዮ ግን ፈፅሞ ከዚህ የተለየ ነው። ብዙ ጊዜ "የተፃፈልኝን ነው የምኖረው፣ ይሔ የአርባ ቀን እድሌ ነው ምንም ማድረግ አልችልም፣ ተፈርዶብኛል።" እያሉ የሆነባቸውን ነገር ሁሉ ፈጣሪያቸው እንዳመጣባቸው የሚጠቅሱ ሰዎች ከእያንዳንዱ ምርጫቸው በስተጀርባ ሚመጣው ውጤት ሃላፊነት ለመውሰድ ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ፈጣሪ የትኛውንም የሰውን ልጅ ሰነፍ አድርጎ አልፈጠረውም፣ ሰነፍ እንዲሆንም አልፈረደበትም፣ አምላክ ማንም ወድቆ እንዲቀር አይፈልግም። ሁላችንም ነፃ ፍቃድ (Free will) አለን። ያሰኘንን ህይወት ከመኖር በላይ የምንፈልገውን ነገር የማምለኩ ነፃነት በፈጣሪያችን ተሰጥቶናል። ጣዖት አቁም የሚሰግዱለት ሰዎችም እየኖሩ ነው፣ ፈጣሪዬ አምላኬ ብለው የሚያመልኩት ሰዎች እኩል እየበሉና እየጠጡ እየኖሩ ነው። ፈጣሪ ፈራጅ ቢሆንና ነፃነትን ባይሰጥ መጀመሪያ እንዲጠፉ የሚፈርድባቸው እነዛ አምላክነቱን ክደው ለጣዖት የሚሰግዱትን ነበር። አዎ! ተፈጥሮ ረቂቅ ነች፣ የሰው ልጅ ደግሞ ከዛም በላይ ረቂቅና ምጡቅ ነው። በርቀቱና በሃይሉ የሚያምን ሰው ተዓምራዊ ህይወትን መኖርን ምርጫው ያደርጋል፣ በተቃራኒው ርቀቱንና ሃይሉን ያልተረዳ ወይም ያላመነበት ሰው ግን እድሜውን በሙሉ እድሉን እያማረረና ሰበብ እየደረደረ ህይወቱን ይገፋል። የሚያምነውን ነገርም ይኖረዋልና ምንም ቢያደርግ ማሻሻል የሚችለው ነገር ያለ አይመስለውም። እሳትና ውሃ ከፊት ተቀምጦ እጅህን ወደፈለከው የመስደድ ምርጫው እያለህ እጅህን ወደ እሳቱ አስገብተህ ከተቃጠልክ ቦሃላ የተፃፈልኝ መቀጣል ሰለሆነ ነው የተቃጠልኩት የሚባል እውቀት የለም። አንድ የተፃፈ ፅሁፍ ወይም ድርሰት ካለ ደራሲ ወይም ፀሃፊ ይኖራል። ደራሲው ሲፅፍ ወስኖና ፈርዶ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ የማንንም ልክቶና ወስኖ አላስቀምጠው። ነፃ ፍቃድህን በአግባቡ ተጠቀም፣ እድልህን በማማረር፣ በፈጣሪህ በማዘንና፣ አንዳንድ አካላት ላይ በማላዘን ህይወትህን ትርጉም አልባ ጉዞ አታድርገው። ህይወትህን በሚገባ ቃኝ፣ በተጠኑ ውሳኔዎችህ መለወጥ ያለብህን ነገር ለውጥ፣ በህይወትህ ለሚከሰተው እያንዱ ነገር ሃላፊነት ውሰድ፣ ትናንትህን ማስተካከል ባትችል መጪው ጊዜህ ላይ ስልጣን እንዳለህ እወቅ። በተሰጠህ ነፃ ፍቃድ እራስህን ከሰበበኛው ማንነት ነፃ አውጣ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
إظهار الكل...
ኑሮህን ኑር! ፡ መስታወት ፊት ቆመህ የእራስህን ገፅ መመልከት ሲኖርብህ ካንተ እንደሚሻሉ የምታስባቸውን ሰዎች ህይወት እየተመለከትክ እራስህን የማይረባ ቅዠት ውስጥ አትክተት። ምንም እንኳን ማህበራዊ ህይወት አስፈላጊ ቢሆንም ማህበራዊ ቅናትና ፉክክር ግን አላስፈላጊ ነገር ነው። ብዙ ሰው ጠልፎ የሚጥለውን እንቅፋት ከፊቱ አስቀምጦ በፍጥነት ይሮጣል፣ የውድቀቱ ምክንያትም እራሱ ይሆናል። የውድቀቱ ጠባሳ ይኖራል ሲሽቀዳደማቸው የነበሩ ሰዎች ግን የሆነ ጊዜ አይኖሩም። አንድ ሰሞን የእርሱ ከእንተና በልጦ መገኘት ከምንም በላይ ያሳስበው ነበር፣ የሆነ ጊዜ የእርሱ አለማደግና የጓደኛው ማደግ ያብከነክነው ነበር፣ የሆነ ሰሞን ከሚያገኛቸው ሰዎች ሁሉ አንሶ መገኘቱ እንቅልፍ ይነሳው ነበር። በስተመጨረሻ ግን እነዚህ ሁሉ ሰዎች አጠገቡ አይኖሩም። ብቻውን የሚቀረው እርሱና እርሱ ብቻ ነው። ጅማሬህ ከማንም ጋር ቢሆንም ፍፃሜህ ግን ከእራስህ ጋር ብቻ ነው፣ ማንንም አይተህ አዲስ ነገር ብተጀምር የመጨረሻው ግብህ ብቻህን ውጤታማ መሆን ነው፣ ማንንም እንዲያግዝህ ብትጠይቅ ዋናውን ስራ የምትሰራው እራስህ ነህ። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
ለትውልድ | LETIWULID 🦋

🔰ንቃት ለትውልድ🔰 ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏

5👍 3🥰 2
የሰው ልጅ የሚኖረው? ምክንያታችሁን #Comment አድርጉ!Anonymous voting
  • የተፃፈለትን ነው።
  • እራሱ የመረጠውን ነው።
0 votes
🔥 4
ፍቅርን ያዘው! : ፈታኝ አጣብቂኝ ውስጥ ብትገባም፣ አለመግባባት፣ አለመረዳዳት ላሰብከው ግንኙነት መሰናክል ቢሆንብህም፣ ቅድሚያ መስጠት የሚገባህ ነገር ግን ያላስቀደምከው፣ ትኩረትህን የሚፈልግ ነገጰር ግን ያልሰጠሀው ነገር ቢኖርም የፍቅርን ጉዳይ በፍቅር መንገድ ለመፍታት ቅድሚያ ስጥ። የቃላት ጋጋታ፣ ጣፋጭ ንግግር፣ ጊዜያዊ ማሽቃበጥ ለፍቅር ጥላው ቢሆን እንጂ መገለጫው ሊሆን አይችልም። ፍቅርን መኖር ካለብህ በትክክለኛው፣ በአስደሳቹ፣ ስሜት በሚሰጠውና በአምላክ በተባረከው ፍቅር ውስጥ እራስህን አስገባ። ፍቅር ብረሃን ነው። የለም ወይስ አለ የሚል ሰጣገባ ውስጥ ከምትገባ ቢኖር ምን ይጠቅመኛል? ምን አተርፋለሁ? በህይወቴ ብተገብረው፣ ብኖረው ምን አገኛለሁ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ለእራስህ የምትሰጠው ክብርና ፍቅር ከሌሎች ከሚሰጥህ ጋር የተቆራኘ መሆን አይጠበቅበትም። ፍቅር የመሆንህ ዋነኛው ምክንያት እራስህን መቀበል መቻልህና ማንነትህን መውደድህ ነው። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
5🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ድል አለን! : ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከትሽ እስከ ትልቅ ሁላችን እንደክብራችን ሁላችን እንደ ኢትዮጲያዊነታችን ድል አለን። ድል ሲባል አንድ ሰሞን የሚነሳ በሌላ ጊዜ የሚወድቅ አይደለም፣ ድል ሲባል በቁስ ወይም በገንዘብ የሚገለፅ ድል አይደለም ድላችን የማንነት ነው፣ ድላችን የእኛነት ነው፣ ድላችን የኢትዮጲያዊነት ብሎም የጥቁር ህዝቦች ጌጥ ነው። ማንም ብቻውን ተዋግቶ ያላሸነፈው፣ ማንም ልብቻው ተጋፍጦ ያላለፈው፣ ማንም ከኢትዮጵያዊነት በላይ ዘሩን ያላስቀደመበት፣ ሁሉም በኢትዮጵያውያዊነቱ እራሱን የሰጠበት፣ በህብረት የተፋለመበት፣ በሃሳብ በአላማ አንድ ሆኖ ተባብሮ ድል ያደረገበት፣ ወራሪውን ሃይል ያሳፈረበት ዘመን የማይሽረው፣ ታሪክ የማይረሳው ታላቅ ድል አለን። እኛ ዛሬ እኛን ስለመሆናችን፣ እያንዳንዳችን የሚያኮራንን ማንነት ስለመያዛችን፣ በየራሳችን ቋንቋ፣ በየራሳችን ባህል ስለመታወቃችን፣ ውስጣችን በጀብድ ልባችንም በንቃት ስለመሞላቱ ዋናው ምክንያት የአያት ቅድመ አያቶቻችን አርበኝነት ነው።
إظهار الكل...
የምትሰጠው አትጣ! ፡ የሚሰስት ትርፍ የለውም፣ መስጠት የማይወድ በረከት የለውም፤ እርካታ የለውም። መኖር በመስጠት ውስጥ ነው። ስትሰጥ የምታገኘውን ስጦታ፣ የሚሰማህን ስሜት ምንም ብታደርግ አታገኘውም፣ ምንም ብትፈፅም ሊሰማህ አይችልም። የህይወት ትርጉም የአምላክን ፀጋ በእኛ በኩል ለሰዎች ማሻገር ነው። ሁሉን የሚሰጥ ደግ አምላክ፣ ቸር ፈጣሪ ነው። ባህሪው መስጠት ነው፤ ንፉግነት የለበትም። የእርሱን ባህሪ ለሚከተለው ሌላ ይጨምርለታል፤ ለማይሰጠው ለንፉጉም የሚገባውን ባይከለክለውም እንኳን በመስጠት የሚያገኘውን የተትረፈረፈ በረከት ግን ያሳጣዋል። ለጋስ ለመሆን ከሰፊ አዛኝ ልብ ውጪ የሚያስፈልግ ነገር የለም። ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! @MentalCounsel ❤️ LIKE & SHARE ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid
إظهار الكل...
🥰 6 1
❇️ VACANCY ANNOUNCEMENT❇️ Position: Sales Person Job type: Full Time with Shift Quantity: 2 Gender: Female Company: Dagnu Wood Work and Furniture Salary: 4500 - 5000 + 1% Commission Location: Gurd Shola Requirements: Excellent communication and negotiation skills Excellent Customers handling Note: First applicants will get a priority Don't forget to Consider the proximity of your residence with work place Contact: @epha_aschalew Deadline: Wed, 31/01/2024
إظهار الكل...
2👍 1👏 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.