ሰዋስው ☘☘☘☘
الذهاب إلى القناة على Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
إظهار المزيد1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 161
❤ ከዚህም በኋላ አንጾኪያ ከተማ አደረሱበት ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አቀረቡት እርሱም በእሳት በአፈሉት በወይን በሙጫ ድፍድፍ በማቃጠል አሠቃየው ከዚያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አዳነው። ዳግመኛም በአንገቱ ከባድ ደንጊያ በሰንሰለት አሥረው ወደ ባሕርም አንከባለው ግማሽ ሥጋውን እንዲአሠጥሙ ግማሹን ግን እንዳያሠጥሙ አዘዘ እነርሱም በባሕሩ ዳር ታላቅ ምሰሶ ተከሉ በዚያም እንዳዘዛቸው አድርገው አሥረው ተዉት በዚህ ሥቃይም ከቀኑ እስከ ሰባት ሰዓት ዋለ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ፈትቶ አወጣው እንደ ቀድሞውም ጤነኛ አደረገው ንጉሡም አይቶ አደነቀ ሰያፊውንም ፈጥኖ አንገቱን ሰኔ 5 ቀን ቆርጦ በባሕር ዳር ከምድር ላይ ጣለው ሥጋውንም አንሥቶ ከቊርበት በተሠራ ጋን ውስጥ ጨምረው ሥጋውም ከራሱ ጋራ ተገናኘና እንዳልተቆረጠ ሆነ ጋኑም በሃያ ቀን እስክንድርያ እስከሚደርስ ድረስ ሰው ሳይሸከመው ብቻውን የሚጓዝ ሆነ።
❤ የቦሀ አገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ መጡ ተሸክመውም በቦሀ አገር ከአለው ቤቱ ውስጥ አስገብተው ከወንድሙ አባ ጴጥሮስ ጋራ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባ ብሶይና በአባ ጴጥሮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ቢፋሞን፦ ይህ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ የእናቱ ወንድም ልጅ ነበር ዮሐንስም ታሥሮ ሳለ ያገለግለው ነበር። ዮሐንስም ገድሉን በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ገነዘ በበድኑ ላይም እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእግዚአብሔር የተለየሁ ሁኜ ብቻዬን እንዴት ትተወኛለህ" ከቅዱስ ዮሐንስ ሥጋም እንዲህ የሚል ቃል ወጣ ወዳጄ ቢፋሞን ከእኔ ጋራ መኖርን ከፈለግህ ፈጥነህ ወደ መኰንኑ ሔደህ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመን ነገም ወደ እኔ ትመጣለህ"። ይህንንም ሰምቶ የዮሐንስን ሥጋውን ቀበረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሔደ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ የረከሱ ጣዖታቱን ሰደበ። መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚህም በኋላ ራሱን ሰኔ 5 ቀን በሰይፍ ቆረጠ የምስክርነቱንም አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ መነኰሳዪት ቅድስት ማርታ፦ ይቺም ቅድስት ሃይማኖቷ የጸና ምግባርዋም የቀና ክርስቶስ ያደረባት ናት። በስደትም ዐረፈችና በተራራ ውስጥ ተቀበረች የመነኰሳዪት የቅድስት ማርታ በረከቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 5 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለብሶይ ዘምድረ ቦሀ ሀገሩ። እለ አውጽኡ በመጥባሕት አሥራወ እዴሁ ወእግሩ። ላዕሌሁ ዳግመ እንዘ ይትዔየሩ። መንፈቀ ሥጋሁ ውስተ ባሕር ወገሩ። ወመንፈቆሰ ኢይረድ ዲበ ዐምድ አሠሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የሰኔ 5።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን ለታማኛና ተጋዳይ ለሆነ ለምሥራቃዊው አባት ለቅዱስ ያዕቆብ ፣ ለተመረጠ ኃያል ተጋዳይ ለአባ ብሶይ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅል ለአጎት ልጅ ለቅዱስ ቢፋሞን ምስክር ለሆነበትና ሃይማኖቷ ለጸና ምግባርዋም ለቀና ክርስቶስ ላደረባት ለመነኰሳዪት ለቅድስት ማርታ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን ከመርቆሬዎስና ከመቃርስ፣ ከይስሐቅና ከዕብሎን ከዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ ከአብላርዮስም ከምስክርነቱ መታሰቢያና በጌታችን ስም በባሕር ውስጥ በመስጠም ከዐረፈ ከቅዱስ መቃርስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ምሥራቃዊው አባት ቅዱስ ያዕቆብ፦ ይህም ቅዱስ ከምዕመን ዋልንጦስ ዘመን በኋላ የታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ በሆነ በታናሹ ቈስጠንጢኖስ ዘመንና በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን በምሥራቅ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም በገድል ተጠምዶ ኖረ። ዋልንጦስ ከተገደለ በኋላም በእርሱ ፈንታ ወንድሙ ነገሠ እርሱም አርዮሳዊ ነበር የጣዖት ቤቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሃይማኖታቸው የቀናውን የምዕመናንን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲዘጉ አርዮሳውያንን አዘዛቸው ምዕመናን በግዳጅ እስቲገቡ ድረስ እንዲሁ አደረጉ። ይህም የንጉሡ ትእዛዝ በሚገዛው አገር ሁሉ ደረሰ።
❤ ይህም አባ ያዕቆብም ይሁን በሰማ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ ያንጊዜም ተነሥቶ ወደ ቊስጥንጥንያ ሔደ በምዕራብ በኩል የተነሡበትን ጠላቶቹን ሒዶ ለመውጋት ሲወጣ ንጉሡን አገኘው። ይህ አባት ያዕቆብም በፊቱ ቆሞ "ንጉሥ ሆይ በጠላቶችህ ላይ እግዚአብሔር ይረዳህ ዘንድ ምዕመናን እንዲጸልዩልህ አብያተ ክርስቲያናቸውን ክፈትላቸው ብዬ እለምንሃለሁ ይህን ካላደረግህ ግን እግዚአብሔር ይጥልሃል ከጠላቶችህም ሸሽተህ በእሳት ቃጠሎ ትሞታለህ" አለው። ንጉሡም ይዞ ለሚጠብቀው ወታደር "በሰላምና
በደኅንነት እስከምመለስ ጠብቀው" ብሎ ሰጠው። ቅዱስ ያዕቆብም "አንተ በደኅና ከተመለስክ በእኔ አንደበት እግዚአብሔር አልተናገረም ማለት ነዋ" አለው።
❤ ያንጊዜም ቅዱሱን ይዘው ደብድበው አሠሩት ንጉሡም ከሠራዊቱ ጋራ ወደ ጦርነቱ ሔደ በረከሰች ጸሎታቸው አርዮሳውያን ምንም ቢራዱት ክብር ይግባውና ጌታችን በጠላቶቹ አንጻር ጣለው እነርሱም ጠላቶቹ እየተከተሉት ሸሽቶ ከአንዲት ዐፀድ ውስጥ ገባ በዚያም በረከሰች ሃይማኖቱ ከሚያምን ወገኖቹ ጋር በእሳት አቃጠሉት። የቀሩትም ሠራዊት ሁሉ ሸሽተው ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ ይህንንም መልካም ዜና ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን ተናገሩ የዚህም ጻድቅ አባት ያዕቆብም ትንቢቱ ተፈጸመ ከእሥር ቤትም በክብር አወጡት። ምዕመናንም ከሀድያንም በላዩ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ተረዱ ከአርዮሳውያንም ብዙዎቹ የአባቶቻችን ሐዋርያት ወደሆነች ቅን ሃይማኖት ተመለሱ በዚህ አባት እግር በታች ሰግደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ ታመነ።
❤ ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ቦታው ተመለሰ አርፎ የሕይወትና የሰማዕትነት አክሊልን እስከ ተቀበለ ድረስ እንደ ቀድሞው በገድል ተጠምዶ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ በቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ብሶይ፦ የዚህ ቅዱስ አባቶቹ ክብር ይግባውና ጌታ ክርስቶስን የሚያመልኩና ትዕዛዙን የሚጠብቁ ክርስቲያን ነበሩ የአባቱም ስም ታግኅስጦስ ነው እርሱም ከአንጾኪያ የቃው ገዥ ነበር የእናቱም ስም ክሪስ ይባላል። እነርሱም ልጅ ሳይኖራቸው ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖሩ ስለዚህም እጅግ እያዘኑ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ይለምኑ ነበር። ከሌሊቶችም በአንዲቱ ለታግኅስጦስ ብርሃን የለበሰ ሰው ተገልጦለት እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቷል ሚስትህም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች ስሙንም ብሶይ ትለዋለህ እርሱም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ዕቃ ይሆናል እርሱም ደግሞ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ ምስክ ይሆናልና ሥቃይና መከራም ተቀብሎ የሰማዕትነት አክሊልን ይቀዳጃል"። ከእንቅልፉ ነቅቶ ራእይ እንዳየ ለሚስቱ ነገራት። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ፀንሳ ይህን ቅዱስ ሚያዝያ አንድ ቀን ወለደችው ዕውቀትን ጥበብንና ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት።
❤ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ አክሚም ዮሴፍ ወደሚባል አንድ አረጋዊ መምህር ላኩት በዚያም እየተማረ ከወንድሙ ጴጥሮስ ጋር በጸሎትና በጾም ተጠምዶ ድንቆች ተአምራትን እያደረገ ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃያ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ የስዒድ መኰንን ወዳለበት ወደ ቃው ከተማ መጣ እርሱም ክርስቲያኖችን እያሳደደ ከእርሳቸው ይገድል ነበር። ያን ጊዜም ክፉዎች ሰዎች ወደ መኰንኑ መጥተው "ለቃልህ የማይታዘዙና ለአማልክት መስገድንም እምቢ የሚሉ ሁለት ዲያቆናት አሉ" ብለው እኒህ የከበሩ አባ ብሶይንና አባ ጼጥሮስን ከሰሱአቸው። በዚያም ጊዜም እንዲአቀርቧቸው አዘዘና አቅርበው በፊቱ አቆሙአቸው ስለ ሥራቸውም መረመራቸው ክርስቲያን እንደ ሆኑም ከቃላቸው ሰምቶ እንዲአሥሩአቸው አዘዘ።
❤ ከሦስት ወር በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦላቸው "እኔ የምሥራች የምናገር ገብርኤል ረዳችሁና እነግራችሁ ዘንድ ወደእናንተ እግዚአብሔር ላከኝ ስም አጠራራችሁና መታሰቢያችሁ ለዘላለሙ ይኖር ዘንድ አለውና" አላቸው። "አንተም ወዳጄ ብሶይ ታላቅ ተጋድሎ አንተን ይጠብቅሃል ወደ እስክንድርያ ከተማ ሊሰዱህ አላቸው። ከዚያም ወደ አንጾኪያ ወስደውህ በዚያ የምስክርነትህ ገድል ይፈጸማል"።
❤ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ከወህኒ ቤት አውጥቶ ለጣዖት እንዲሰግድ አስገደደው እምቢ ባለውም ጊዜ ከባላ ላይ አውጥተው በግንድ ውስጥ እጅግ እንዲጨምቁት ወታደሮቹን አዘዘ። በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወሪዶ ግንዱን ሰብሮ ቅዱስ ብሶይን በመዳሠሥ አዳነው። ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ጨምሩት በዚያም ብዙ በሽቶኞችን ፈወሳቸው። ዳግመኛም እንዲህ አዘዘ ከወህኒ ቤት አውጥተው በመርከብ ሆድ ውስጥ አስገብተው አንገቱን በብረት ማሠሪያ እንዲአሥሩት እንጀራና ውኃ እንዳይሰጡት አዘዘ እንደዚህም ኖረ ዐሥር ቀን ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ አውጥተው በፊቱ አቁሞ "ለአማልክቶቼ ስገድ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከባላ ግንድ ላይ አውጥተው አጥብቀው እንዲጨምቁት ሁለተኛ አዘዘ። እንዲሁም በእርሱ ላይ አድርገው በወህኒ ቤት አሠሩት። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ ተገለጠለትና "አይዞህ መልካም ገድልህን እስከምትፈጽም እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አትፍራ" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወደ ቁልቁልያኖስ መኰንን ሰደዱት እርሱም ስለ ሥራው ሁሉ መረመረውና ሕዋሳቱ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ። ሁለተኛም ዘይትን አፍልተው በጆሮው፣ በአፉና በደረቱ ላይ እንዲአፈስሱ ጐኖቹንም በእሳት ሠብራት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ደግሞም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በዐይኖቹ ውስጥ አደረጓቸው። ሁለተኛም የእጆቹንና የእግሮቹን ሥሮች ሕዋሳቱንም ሁሉ እንዲነቅሉ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሕዋሳቱን ሁሉ ፈወሰው።
1 161
በዓለ ጰራቅሊጦስ
በዲያቆን የአብስራ ጌታሁን
ክፍል ሦስት
ከዚሁ ኹሉ ጋር ለማሳሰብ የምንፈልገው ቁም ነገር በዓለ ጰራቅሊጦስን ተከትለው ሁለት ዐበይት አጽዋማት ይጀመራሉ፡፡
እነዚህም፦
ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት (ረቡዕና ዓርብ) ሲኾኑ፣ ቍጥራቸውም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ነው፡፡
ስለኾነም ኹላችንም ልንጾማቸው እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ታዝዟል፡፡
ይህም ከቀደሙ አባቶቻችን ጀምሮ የመጣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት እንጂ እንግዳ ሕግ አይደለም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚናገሩት በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበለውን ሕገ ኦሪት ለሕዝቡ ከማስተማሩ በፊት ጾሟል። ዘፀ.፴፬፥፳፰
ቅዱሳን ነቢያትም የተስፋውን ቃል መፈጸም እየተጠባበቁ እግዚአብሔርን ውረድ፤ ተወለድ እያሉ ይጾሙ፣ ይጸልዩ ነበር፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጾም የምግባር መሠረት መኾኑን ሊያስተምረን ወንጌልን ከመስበኩ አስቀድሞ ጾሟል። ማቴ.፬፥፩-፲፩፤
ሐዋርያትም በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ሕገ ወንጌልን ለሕዝቡ ከማስተማራቸው አስቀድሞ ጾመዋል፡፡
እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትንና ሌሎችንም አጽዋማት መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል /ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፹፮/፡፡
ጾመ ድኅነት ስሙ እንደሚያመለክተው የመዳን ጾም ማለት ሲኾን፣ ይህም በብሉይ ኪዳኑ አጽዋማት በጾመ አስቴር እና በጾመ ዮዲት የተተካ የሐዲስ ኪዳን ጾም ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን በሐማ ምክንያት በእስራኤል ላይ ታውጆ የነበረው ሞት በጾመ አስቴር እንደ ተሻረ ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም በዕለተ ረቡዕ በጌታችን ላይ በተፈጸመው ምክር የሰይጣን ሴራ ፈርሷልና በጾመ አስቴር ምትክ ረቡዕን እንጾማለን፡፡
እንደዚሁም በብሉይ ኪዳን በጾመ ዮዲት ምክንያት ሆሎሆርኒስ ድል እንደ ተደረገበት ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት ዲያብሎስ ድል ተደርጓልና በጾመ ዮዲት ምትክ ዓርብን እንጾማለን፡፡
የእነዚህ የሁለቱ ቀናት (የረቡዕና ዓርብ) ጾም ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡
በአጠቃላይ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ድኅነት እንደ ጾመ ነነዌና ዐቢይ ጾም የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ቀመርን ተከትለው የሚመጡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሚመደቡ ጾሞች ናቸው፡፡
የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ (መፈጸሚያ) የቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት (ሐምሌ ፭ ቀን) ሲኾን፣ ጾመ ድኅነት ግን ከበዓለ ኀምሳ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ የሚጾም ጾም ነው፡፡
ዕለተ ረቡዕ የጌታ ሞት የተመከረበት፤ ዓርብም አምላካችን የተሰቀለበት ዕለት ነውና በመስቀሉ መሥዋዕትነት ያገኘውን ድኅነት ዘወትር ማሰብ ስለሚገባን ሁልጊዜ እንድንጾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ በዚህ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፮፤ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፰ ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመኾኑም እንደ ክርስቲያን የምንጠቀመው በራሳችን መልካም ተግባር፤ የምንወቀሰውም በራሳችን መጥፎ ድርጊት መኾኑን ተረድተን ይኼ የቄሶች፤ ይኼ የመነኰሳት ነው የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ኹላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘው ጸጋና ሀብት ይበዛልናልና ራሳችንን ለጾም እናዘጋጅ፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በደስታ እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ እንዳቆየን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ኾነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይኹን፡፡አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ቃለሕይወት ያሰማልን
~ተፈጸመ~
ምንጭ፡-
መጽሐፈ ስንክሳር፣ ግንቦት ፲፰ ቀን፡፡
መጽሐፈ ግጻዌ ዘደብር ዓባይ፣ ሊቀ ሥልጣናት አባ ጥዑመ ልሳን፤ አዲስ አበባ፣ ፳፻፩ ዓ.ም፡፡
መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፣ ገጽ ፹፬-፹፭፣ መ/ር ኅሩይ ኤርምያስ፣ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፡፡
ማኅቶተ ዘመን ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፣ መ/ር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፲፬ዓ.ም፡፡
https://t.me/Eotcw
1 161
በዓለ ጰራቅሊጦስ
በዲያቆን የአብስራ ጌታሁን
ክፍል ሦስት
ከዚሁ ኹሉ ጋር ለማሳሰብ የምንፈልገው ቁም ነገር በዓለ ጰራቅሊጦስን ተከትለው ሁለት ዐበይት አጽዋማት ይጀመራሉ፡፡
እነዚህም፦
ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት (ረቡዕና ዓርብ) ሲኾኑ፣ ቍጥራቸውም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ነው፡፡
ስለኾነም ኹላችንም ልንጾማቸው እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ታዝዟል፡፡
ይህም ከቀደሙ አባቶቻችን ጀምሮ የመጣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት እንጂ እንግዳ ሕግ አይደለም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚናገሩት በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበለውን ሕገ ኦሪት ለሕዝቡ ከማስተማሩ በፊት ጾሟል። ዘፀ.፴፬፥፳፰
ቅዱሳን ነቢያትም የተስፋውን ቃል መፈጸም እየተጠባበቁ እግዚአብሔርን ውረድ፤ ተወለድ እያሉ ይጾሙ፣ ይጸልዩ ነበር፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጾም የምግባር መሠረት መኾኑን ሊያስተምረን ወንጌልን ከመስበኩ አስቀድሞ ጾሟል። ማቴ.፬፥፩-፲፩፤
ሐዋርያትም በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ሕገ ወንጌልን ለሕዝቡ ከማስተማራቸው አስቀድሞ ጾመዋል፡፡
እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትንና ሌሎችንም አጽዋማት መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል /ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፹፮/፡፡
ጾመ ድኅነት ስሙ እንደሚያመለክተው የመዳን ጾም ማለት ሲኾን፣ ይህም በብሉይ ኪዳኑ አጽዋማት በጾመ አስቴር እና በጾመ ዮዲት የተተካ የሐዲስ ኪዳን ጾም ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን በሐማ ምክንያት በእስራኤል ላይ ታውጆ የነበረው ሞት በጾመ አስቴር እንደ ተሻረ ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም በዕለተ ረቡዕ በጌታችን ላይ በተፈጸመው ምክር የሰይጣን ሴራ ፈርሷልና በጾመ አስቴር ምትክ ረቡዕን እንጾማለን፡፡
እንደዚሁም በብሉይ ኪዳን በጾመ ዮዲት ምክንያት ሆሎሆርኒስ ድል እንደ ተደረገበት ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት ዲያብሎስ ድል ተደርጓልና በጾመ ዮዲት ምትክ ዓርብን እንጾማለን፡፡
የእነዚህ የሁለቱ ቀናት (የረቡዕና ዓርብ) ጾም ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡
በአጠቃላይ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ድኅነት እንደ ጾመ ነነዌና ዐቢይ ጾም የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ቀመርን ተከትለው የሚመጡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሚመደቡ ጾሞች ናቸው፡፡
የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ (መፈጸሚያ) የቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት (ሐምሌ ፭ ቀን) ሲኾን፣ ጾመ ድኅነት ግን ከበዓለ ኀምሳ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ የሚጾም ጾም ነው፡፡
ዕለተ ረቡዕ የጌታ ሞት የተመከረበት፤ ዓርብም አምላካችን የተሰቀለበት ዕለት ነውና በመስቀሉ መሥዋዕትነት ያገኘውን ድኅነት ዘወትር ማሰብ ስለሚገባን ሁልጊዜ እንድንጾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ በዚህ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፮፤ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፰ ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመኾኑም እንደ ክርስቲያን የምንጠቀመው በራሳችን መልካም ተግባር፤ የምንወቀሰውም በራሳችን መጥፎ ድርጊት መኾኑን ተረድተን ይኼ የቄሶች፤ ይኼ የመነኰሳት ነው የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ኹላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘው ጸጋና ሀብት ይበዛልናልና ራሳችንን ለጾም እናዘጋጅ፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በደስታ እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ እንዳቆየን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ኾነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይኹን፡፡አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ቃለሕይወት ያሰማልን
~ተፈጸመ~
ምንጭ፡-
መጽሐፈ ስንክሳር፣ ግንቦት ፲፰ ቀን፡፡
መጽሐፈ ግጻዌ ዘደብር ዓባይ፣ ሊቀ ሥልጣናት አባ ጥዑመ ልሳን፤ አዲስ አበባ፣ ፳፻፩ ዓ.ም፡፡
መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፣ ገጽ ፹፬-፹፭፣ መ/ር ኅሩይ ኤርምያስ፣ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፡፡
ማኅቶተ ዘመን ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፣ መ/ር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፲፬ዓ.ም፡፡
https://t.me/Eotcw
1 161
በዓለ ጰራቅሊጦስ
በዲያቆን የአብስራ ጌታሁን
ክፍል ሁለት
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ
ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡
ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ከዕብራይስጥ ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጸውላቸው ምሥጢራትን መተርጐም ጀምረዋል፡፡
ሐዋርያት በየአገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ ከአይሁድ ወገን አንዳንዶቹም ሐዋርያትን ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የኾነ ያልኾነውን ይቀባጥራሉ ይሏቸው ነበር፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሃሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡
ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ዳሩ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ።
ኢዩ ፪፥፳፰
ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ በማለት ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ መኾኑን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መኾኑን እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡
በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ምን እናድርግ ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገራቸው፡፡
በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል ሐዋ ፪፥፩-፵፬፡፡
ይህም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ያደረባቸው የማሳመን ጸጋና ተአምራትን የማድረግ ኃይላቸው እንደ በዛላቸው ያመላክታል፡፡
ይህ ዕለት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠበት፤ ብዙ ሺሕ ምእመናን የተገኙበት ዕለት በመኾኑ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሩታል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤ በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም ስለ በዓሉ ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤
በአንጻሩ በዚህ ወቅት (በበዓለ ኀምሳ) መጾምና ማዘን ተገቢ አለመኾኑን ተናግረዋል ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸
የጰራቅሊጦስ መዝሙርና ምንባባት
በዓለ ጰራቅሊጦስ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲኾን በዕለቱ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው የቅዱስ ያሬድ መዝሙርም ይትፌሣሕ የሚለው የትንሣኤ መዝሙር ነው፡፡
እንደ መዝሙሩ ኹሉ በጰራቅሊጦስ በዓል በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም በትንሣኤ ዕለት የተነበቡት ምንባባት ናቸው፡፡
እነዚህም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ፣ በማረጉና መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት በመላኩ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ቈርሶ፣ ደሙን አፍስሶ የሰውን ልጅ ከዘለዓለም ሞት በማዳኑ የሰው ዘር ብቻ ሳይኾን የሰማይ መላእክት፣ የምድር ፍጥረታት ሳይቀሩ ሐሤት እንደሚያደርጉ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም በመንጻቷ የጌታችንን ትንሣኤ በደስታ እንደምታከብር ያስረዳሉ፡፡
ከበዓለ ጰራቅሊጦስ በኋላ ባሉት ሰንበታት (እሑዶች) የሚዘመሩ መዝሙራት ትንሣኤን፣ ዕርገትን፣ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ የሚያስረዱ ሲኾኑ፣ ዓላማቸውም ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው፣ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ባርነትና ከሲኦል ላወጣቸው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ ነው፡፡
ከዚሁ ኹሉ ጋር ለማሳሰብ የምንፈልገው ቁም ነገር በዓለ ጰራቅሊጦስን ተከትለው ሁለት ዐበይት አጽዋማት ይጀመራሉ፡፡
እነዚህም....
ክፍል ሦስት ይቀጥላል………
https://t.me/Eotcw
1 161
በዓለ ጰራቅሊጦስ
ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም
በዲያቆን የአብስራ ጌታሁን
ክፍል አንድ
ጰራቅሊጦስየሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡
በዓለ ጰራቅሊጦስ በሌላ ቃል በዓለ ጰንጠቆስጤ በመባልም ይታወቃል፡፡ ይኸውም በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው። ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮ እና ፱፻፯/፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡
በሚያርግበት ጊዜም እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤
ሉቃ ፳፬፥፵፱ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡
በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ኹሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ
ሐዋ ፪፥፩-፬
ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡
ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ ከ፶ኛው፤ ከዐረገ ከ፲ኛው ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለው እሑድ ድረስ ያለው ወቅትም ዘመነ ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ሲኾን፣ ይህ በዓል ካህናተ ኦሪት ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ይቀበሉበት ነበርና በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ይባል ነበር፡፡
በበዓለ ጰራቅሊጦስም ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለውበታልና በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡
የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብፅ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ኹሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡
የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በ፶ኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት ያከብሩ ነበር፡፡
ከግብፅ እስከ ከነዓን ምድር የደረሰው የእንስሳት መሥዋዕት ሲጠናቀቅ በ፶ኛው ቀን ይሰባሰብ የነበረው የአይሁድ ጉባኤም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለት ጀምሮ ተበትኗል፡፡
መሥዋዕተ ኦሪቱ በአማናዊው መሥዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንደ ተለወጠ ኹሉ ጉባኤ አይሁድም በኢየሩሳሌም ከተማ በተሰበሰቡ በቅዱሳን ሐዋርያት ጉባኤ ተለውጧል (ተቀይሯል)፡፡ይህችውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
ከኹሉ በላይ በምትኾን፣ ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፤እንዳሉ ሠለስቱ ምእት ጸሎተ ሃይማኖት
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
https://t.me/Eotcw
1 161
➦📆የ2014 ፆመ ሐዋርያት (የሰኔ ፆም) መቼይገባል ?
➦ ለምንስ ይፆማል ??
✍ ፆመ ሐዋርያት ወይም ሰኔ ፆም ሰኔ 6 ይገባል(ይጀምራል) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።
➦ ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።
✍ የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።
➦ የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል
የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን
የተቀበሉበት እለት ነው ።
➦ ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን
በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡
✍ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡
➦ ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡
‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው ?አሉት
✍ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16
➦ አሜን አሜን አሜን እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!
https://t.me/Eotcw
1 161
ይግባውና ክርስቶስ የምታመልክ ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች።
❤ ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስ ስም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተሞላ ወደ እርሱም እንዲያቀርቧት አዘዘ በቀረበችም ጊዜ "ለአጵሎን ስገጂ አላት "የሰው እጅ ለሰራው ለረከሱ አጋንትም ማደርያ ለሆነው እንዴት እሰግዳለሁ" አለችው ይህንንም ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከብረት በተሰራ ጅራፍም እንዲገርፏት አዘዘ ሁለተኛም አንገቷን ከባድ ደንጊያ አስረው ሥጋዋ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ በከተማው ጥጋጥግ እዲጎትቷት አዘዘ ይህን አድርገው ወደ ወሂኒ ቤት አስገቧት። በማግስቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ በመጣችም ጊዜ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጰሎን ሰዊ" አላት እርሷም "ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ይሕወት ነው" አለችው። እርሱም "ከገደልኩሽ በኋላ ትነሽ ትነሻለሽን?" አላት "አንተ ሰነፍ የእኔን ተዋውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ" አለችው። ይህንንም በሰማ ጊዜ አጥንቶቷ ሁሉም እስኪሰበሩ በብረት በትሮች እዲደበድቧት አዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉባት።
❤ ዳግመኛም በብረት አልጋ አስተኝተው ከበታቿ እሳት እንዲያነዱ አዘዘ ቀኑ በመሸም ጊዜ ወደ ወህኒ ቤት እንዲያስገቧት አዘዘ። በዚያችም ሌሊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሰስ አጽናናት። በማግሥቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ምን ሕማም እንዳላገኛት ሁና በእግራ መጣች ከመታጠቢያ ቤት ታጥባና ተቀብታ የመጣች ትመስል ነበር ንጉሡም ደኅንነቷን አይቶ አደነቀ፣ "የዚችን ክርሰቲያን ሴት የሥራይዋን ጽናት እዩ ትናንት በእሳት አሰቃይተናት ነበር ዛሬ ድናለች" አለ "ሥራይንስ አላውቀውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይ የሚሽር ነው" አለችው።
❤ ከዚያም በኋላ እሺ ያሰኛት ዘንድ ሊሸነግላት ጀመረ እንቢ ባለችውም ጊዜ እራሷን በሰይፍ ሊቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ሊቆርጧት ይዘዋት ሲሆዱ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለፀላት ብዙ ቃል ኪዳኖችንም ሰጣት በማይታበል ቃሉም "መታሰቢያሽን የሚያደርገውን፣ ሁሉ በስምሽ የሚመጸውተውን፣ የገድልሽንም መጻሕፍ የሚጽፈው ሁሉ እቀበለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ" አለ። ከዚያም በኋላ አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ በጌታችንም ዘንድ የድል አክሊልን ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅድስት ሶፍያ በጸሎቷ ይማረን በረከታም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ሳኑሲ፦ ይኽም ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለጦም አዳሪዎች እየሰጠ እርሱ ግን እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር፡፡ በአንዲት ሌሊት የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት "የክብርን አክሊል ትቀበል ዘንድ ወደ መኰንኑ ሄደህ ስለ ፈጣሪህ ስለ ክርስቶስ መስክር" አለው፡፡ ቅዱስ ሳኑሲም ትእዛዙን በመቀበል እናቱን ተሰናብቶ ማርያ ከምትባል ደገኛ ሴት ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ወደ ከሃዲው ገዥ ወደ አርሳኖስ ዘንድ ሄዱ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ በከሃዲው ገዥ ፊት ቀርበው ክርስቲያን መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ገዥውም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰባቸው፡፡ ቅድስት ማርያ በስቃይ ውስጥ ሳለች ዐርፋ ሰማዕትነቷን ስትፈጽም ቅዱስ ሳኑሲ ግን በጌታችን ኃይል ታደሰ፡፡ መኰንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው ገዥ በግዞት ላከው፡፡ በዚያም እጅግ አድርገው አሠቃዩት፡፡ ተረከዙን ሰንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ ሲጎትቱት ዋሉ፡፡ ሥራየኛ ሰው አምጥተው ሥራየኛው ሰው በጽዋ የተመላ መርዝ እንዲጠጣ ቢሰጠው ቅዱስ ሳኑሲ በመስቀል ምልክት አማትቦ ቢጠጣው ምንም አልሆነም፡፡ እንዲያውም ምግብ ሆነው፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያየው ሥራየኛም "በቅዱስ ሳኑሲ አምላክ አምኛለሁ" ብሎ በመመስከር እርሱም ሰማዕት ሆነ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ሳኑሲን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘና ሰኔ 4 ቀን የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በክብር ፈጽሞ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 4 ስንክሳር።
+ + +
❤ " አቄርብ ለከ አሞኒ ሰለም። ወሶፍያ ምስሌከ ዘተሳተፈት ሕማመ። በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥመሩ ፍጹመ። ከዊነክሙ ትሕፅኑ ኪያየ ደክታመ። ለሊከ አበ ወይእቲ እመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 4።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ቀስቶኒ ወተረ ወአስተዳለወ። ወአስተዳለወ ቦቱ ሕምዘ ዘይቀትል። ወአሕፃሁኒ እለ ይነዱ ገብረ"። መዝ 7፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥9-18፣ 1ኛ ዮሐ 2፥12-20 እና የሐዋ ሥራ 12፥18-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-29። የሚቀደሰው የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የበዓለ ዕርገት ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፬ (4) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ለዕረፍቱ በዓል፣ በኪም ከሚባል አገር ለሆነ ለቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን አንገቷን በመቆረጥ ሰማዕትነት ለተቀበለች ተጋድይ ለሆነች ለቅድስት ሶፍያ ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ከቅዱሳን ከአርቃድዮስ፣ ከእህቱ የዲሙናስና ከግብጻውያን ከአሞኒና ከሚናስ ከንጉሥ ከዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም ከገድላቸው ፍጻሜ፣ ከአባ አሞንና ከሚናስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱስ የሐንስ ዘሐራቅሊ፦ የዚህም ቅዱስ አባት ስሙ ዘካርያስ ነው እርሱም የጳንጦስና የአብልያ አገሮች ገዢ ነበር የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም ይህን የተባረኩ ልጅ በተሰጡ ጊዜ ስሙን ዮሐንስ ብለው ጠሩት እርሱ ከአባቱና ከእናቱ ጀምሮ ከመጥምቀ አምላክ ዮሐንስ ጋር በስም አንድ ሁኗልና በተግሣጽና በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ሂሣቦችንና ጥበቦችን ሁሉ አስተማሩት እናቱም በዘመኗ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይወጣ ታማጽነው ነበር። አባቱም እንዲሁ ይመክረውና ያስተምረው ነበር።
❤ ከዚህም አባቱ ከሞተ በኋላ የሃያ ዓመት ልጅ ሲሆን መስፍን ሆነ የጳንጦስና የሐራቅሊ ሌሎችም አገሮች ሁሉ ተገዙለት። እንዲሁም እያለ በመልአክ አምሳል ሰይጣን ታየው እንዲህም አለው "አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሒደህ የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ አግባ ብሎ ጌታ አዝዞሃል" አለው ቅዱሱም "በውኑ ይህ መልአክ ነውን ግን አፉ የእግዚአብሔርን ስም ከሰማሁ አንጾኪያ እሔዳለሁ" አለ።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ተገናኘው ንጉሡም በአየው ጊዜ አከበረው እጅግም ወደደው። በማግሥቱም በምሳ ላይ ከእርሱ ጋራ እያለ ከሃዲ ዲዮቅልጥያኖስ አጰሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ ያንንም ጣዖት ባመጡት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ አቃለለው ስለዚህም ሥራ ንጉሡን ረገመው ሰደበውም። ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገውን በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በእሥር ቤት አሠረው። በእሥር ቤትም ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ታየው ከእርሱ ጋራም መላእክት አሉ። ይዞም ሳመው ብዙዎች ቃል ኪዳኖችንም ሰጠው።
❤ በማግሥቱም ንጉሡ ልኮ ከእር ቤት አወጣው ወደ ርሱም አቀረበውና "ለአጰሎንና ለአርዳሚስ ስገድ" አለው ቅዱሱም "የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ" አለ ንጉሡ ግን ከእርሱ ጋራ መታረቅ ሽቶ ብዙ የሽንገላ ነገርን ተናገረው። ከዚህም በኋላ ግብርን ያስገብር ዘንድ ከሹመት ጋራ ወደ ግብጽ አገር ላከው ወደ ግብጽ ገዢ ወደ ስርያቆስም ስለ ርሱ እንዲህ ሲል ጽፎ ላከ "እንሆ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤቶች አፍርሶ አዲስ እንዲአሠራ ከግብጽና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሥልጣን ሰጥቼለሁ። ቅዱሱም ይህን ምክንያት ይዞ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሶ ተዋቸው።
❤ በዚያም ወራት መኰንኑ ስርያቆስ የሰማዕታት ራስ መቆረጥን ሊያዝዝ በፍርድ አደባባይ ተቀምጦ በዚያን ጊዜ ከስዒድ፣ ዲዮስቆሮስ፣ ቢፋሞን፣ አሕራጋኖስ፣ ኪሮስ፣ ዮልዮስ እለእስክድሮስ፣ ዮሴፍ፣ ይስሐቅና እስጢፋኖስ የሚሉአቸው ሰዎች መጥተው እሊህ ሁሉም እኛ ክርስቲያኖች ነን እያሉ በግልጥ ጮኹ ያን ጊዜ መኰንኑ ይዞ ያለርኅራኄ ያሠቃያቸው ጀመር። ቅዱስ ዮሐንስ ይህን በአየ ጊዜ የሹመቱን ሥራ ትቶ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በግልጥ ጮኸ መኰንኑም ተቆጥቶ በእግር ብረት እንዲአሥሩትና ወደ እንዴና አገር ወደ መኰንኑ አርያኖስ እንዲወስዱት አዘዘ እርሱም ስለሆነው ሁሉ መረመረው ከቃሉ መልስም የተነሣ ተቆጣ በባላ እንጨት ላይ ሰቅለው በመንኰራኵር አጣበቀው እንዲጨምቁት ከዚያም ከባላው አውርደው ሥጋው እስኪቀልጥ ሆዱ ላይና ራሱ ላይ በቀጭኔ እንዲደበድቡት አዘዘ ምድሪቱም በደሙ ተመላች ከዚያም ወደ እሥር ቤት አስገቡት።
❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ ያሹት ዘንድ ዳግመኛም አመድ ጐዝጊዘው በላዩ የእሳት ፍም ከጐኑ በታች አድርገው በላዩ እንዲአስተኙት አዘወ እንዲሁም አደረጉበት። ሁለተኛም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በፊቱ ላይ በጀሮዎቹም ላይ እንዲያኖሩዋቸው አዘዘ። እንዲህም አድርገው ከወህኒ ቤት ጨመሩት። በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ሰላምታ ሰጥቶ አጸናው። በማግሥቱም ከወህኒ ቤት አውጥተው በጋሉ ብረት ዘንጎች ደበደቡት። ከዚህም በኋላ በግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጭራ ላይ በገመድ አሠሩ።
❤ ከዚህም በኋላም ባለ ሰይፍ መጥቶ እግርቹንና እጆቹን ራሱንም ቆረጠ እንዲህም የምስክርነቱን ተጋድሎ ሰኔ 3 ቀን ፈጽሞ የድል አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅድስት ሶፍያ፦ የዚች ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያን ነበሩ በወለዱዋት ጊዜም በመልካም አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የአባቶቻችን ሐዋርያትንም ሥርዓት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጓት።
❤ ከዚህም በኋላ በአደገች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ መስፍን ልጅ ሊአጋቧት ፈለጉ ቅድስቲቱም ይህን በመንፈስ ቅዱስ ዐውቃ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ መቶ ስግደትን ሰገደች ቆማም ረጂም ጸሎትን ጸለየች በጸሎቷም ውስጥ እንዲህ አለች "የክብር ባለቤት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህ ለእኔ ለባርያህ ለሶፍያ ምራኝ ወደ ጥፍት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ የሚጠፍውንም ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው ወላጆቼ በሚመክሩብኝም በረከሰ በሥጋ ፍትወት ውስጥ የኃጢአት ባርያ እንድሆን አቤቱ አትተወኝ የከበደ የዓለማዊ ፍላጐት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትከሻዬ ዘንበል አድርገው እጂ"። ጸሎቷንም ከፈጸመች በኋላ በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ጥቂትም ቆይታ እንዲህ የሚል ሃሳብ መጣባት "ተነስቼ በስውር ልውጣ ወደ ሩቅም ሔጄ ከበረሀ ውስጥ ገብቼ ለልዑል አምላክ ላገልግል"።
❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቿ የሰጣትን የምታገለግላት ብላቷናዋን ጠራች ወይን አምጥታ እንድታጠጣትም አዘዘቻት በአመጣችላትም ጊዜ እርሷ ጥቂት ቀምሳ ያመጣችው ወይን እስኪያልቅ ትጠጣ ዘንድ ብላቷናዋን አዘዘቻት ከስካርም የተነሣ ልባ በተሰለበ ጊዜ "ልብስሽ አንጪ የእኔንም ልብስ ውሰጂ" አላቻትና ሰጠቻት ወይኑ ስካር አእምሮዋን ነስቷታልና ተኚ አለቻት በላይዋም እንቅልፍ በከበዳት ጊዜ ማን ሳያያት ቅድስት ሶፍያ በስውር ወጣች ከወላጆቿም ማደርያ ነበርና። እርቃ በሄደችበት ጊዜ በተራራና በዋሻዎች ውስጥ ሊሰወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሚሸሹ ሰዎችን አገኘች "እናንተ ከወዴት ናችሁ?" ብላ ጠየቀቻቸው የእያንዳንዳቸውን አገራቸው ነገሯት ደግማ "ወዴት ትሔዳላችሁ?" አለቻቸው እነርሱም ስለ ሃይማኖት ከዲዮቅልጥያኖስ የሆነውን ሉሁ ነገሯት። "ይቺ መንገድ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ታደርሰኛለችን" አለቻቸው "አዋ ታደርስሻለች" አሏት ከዚያም ጥቂ ተጉዛ ቁማ እረጅም ጸሎትን ጸለየች ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ደርሳ ክብር
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፫ (3) ቀን።
❤ እንኳን መጀመርያ ዘማዊ ሆና በንስሓ ከተመረሰች በኋላ በትኅርምትና በተጋድሎ ለሃያ አምስት ዓመታት ለጸናች ለቅድስት ማርታ ለዕረፍቷ በዓል፣ ለኤጲስቆጶስ ለአባ ኤላርዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ኮርዮን ዕረፍትና በሰማዕትነት ከዐረፈው ከኤጲስቆጶስ ኤላርዮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅድስት ማርታ፦ ይቺም ቅድስት ከምስር ተወላጆች ውስጥ ነበረች ወላጆቿም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ከታናሽነቷም ጀምራ የረከሰ ዝሙትን የምትወድ ነበረች የከተማ ጐልማሶችና ታላላቆችም በሥውር ወደርሷ እየመጡ ያመነዝሩ ነበር። ከዚህ በኋላም ሥራዋ ተገለጠ የርኵሰት ሥራንም በግልጥ አብዝታ የምትሠራ ሆነች።
❤ ክብር ምስጋና ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ ልደቱ በዓል በሆነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ልትገባም በፈለገች ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ከለከላት እንዲህም አላት "አንቺ በምግባር የረከስሽ ስለሆነ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት አይገባሽም" ይተዋትም ዘንድ አባበለችው እርሱ ግን ከለከላት በመካከላቸውም ታላቅ ጸብ ሆነ። ኤጲስቆጶሱም ጨኹት ሰምቶ ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ደረሰ ማርታንም በአያት ጊዜ "የእግዚአብሔር ቤቱ የከበረና የነጻ እንደ ሆነ አታውቂምን አንቺም የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገቢ ዘንድ አይገባሽም" አላት። በዚያን ጊዜም አለቀሰች "ንስሐ እገባለሁ እንጂ ወደዚህ ሥራ እንግዲህ አልመለሰም ብትቀበለኝም እመነኵሳለሁ" አለችው። ኤጲስቆጶሱም "ገንዘብሽንና ጥሪትሽን ሁሉ ወደዚህ አምጥተሽ በፊትሽ ካላቃጠልነው አላምንሽም" አላት። ያን ጊዜም ሒዳ ጥሪቷንና ወጋው ብዙ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶስ ፊት ጣለችው እርሱም በፊቷ አቃጠለው።
❤ ከዚህም በኋላ የራስዋን ጠጉር ተላጨች ኤጲስቆሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት በዚያም ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች ነፈሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር "በጭቃና በደንጊያ ወደ ታነፀው ቤት ለመግባት ካልተዉሽ በብርሃን ወደ ተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ" ሁለተኛም "በጸሎቷ አቤቱ ቤተ ክርስቲያንህን ከሚጠብቀው የደረሰብኝን ኅፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ" አለች።
❤ ይችም ቅድስት ሰይጣን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሃያ አምስት ዓመት ስትጋደል ኖረች በዚህ ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም ከዚህም በኋላ በሰላም ሰኔ 3 ቀን ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ማርታ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ኤጲስቆጶስ አባ ኤላርዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከሀዲውን ንጉሥ ዮላኪዮስ ጣዖታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር። ንጉሥ ዮላኪዮስም "አይሁድ የተሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሀዲ ትለኛለኛለህ እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ" አለው።
❤ ከዚህ በኋላም ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኰንን ሰጥቶ ባለመራራት ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እንዲአሠቃየው አዘዘው መኰንኑም ወስዶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አንዲት ቀን እንኳን ከቶ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ እያሠቃየው አንድ ዓመት ሙሉ ኖረ። በዓመቱም ፍጻሜ በእሳት ውስጥ ጣሉት እርሱም ከእሳት መካከል ቁሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ስለዚህችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
❤ ከዚህም በኋላ ከአታክልት መካከል እንደ ሚወጣ ሁኖ ከእሳት አወጡት። መኰንኑም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ በእርሱ ላይም የሚያደርገውን በአጣ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕታት አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኤላርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ3 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለማርታ ጥዕምተ ዝክር ወዜና። ዘተዐጽፈት ሠቀ አልባሰ ወርቅ መኒና። አመ ገሠጸ ኢትባእ ውስተ ቤተ መቅደስ እንበለ ንጽሕና። እስከነ ሞዓቶ ለእኩይ ሕሊና። ዓቃቤ ኆኅት ምክንያተ ኮና"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 3።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አርኅው ሊተ አናቅጸ ጽድቅ። ዕባእ ውስቴቶን ወእግነይ ለእግዚአብሔር። ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር"። መዝ 117፥19-20። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 2፥1-4፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 20፥16-25። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 7፥37-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠልስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የበዓሉ ዕርገቱ ሶሞን ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፫ (3) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት የሥርዓተ ቅዳሴ ሕግ በአዋጅ ላስደነገጉልን ለአቡነ ቄርሎስ ዘትግራይ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ቄርሎስ ዘትግራይ፦ አባታቸው ግሪካዊው እስክንድር እናታቸው ሶፊያ ሲባሉ ትውልዳቸው አክሱም ነው። አቡነ ቄርሎስ ዘትግራይ የሥርዓተ ቅዳሴ ሕግ በአዋጅ ያስደነገጉልን ትልቅ አባት ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት "ቅዳሴ በ 5 ቀሳውስት እንዲቀደስ ከ 5 እንዳይጎድል፣ እሁድ እሁድ ከንጋቱ 12ሰዓት እንዲገባ ቅዳሜ በ 1 ሰዓት እንደመገባ ከጠዋቱ በ 3 ሰዓት እንዲወጣ፣ ረቡዕና አርብ ደግሞ በ 7 ሰዓት ተገብቶ በ9 ሰዓት እንዲወጣ መነኵሴም የሴት ፊት እንደሠያይ..." በማለት አበው የወሰኑትን በአዋጅ ሊቃውንቱን ሰብስበው ያስወሰኑና የደነገጉ እኚህ ደገኛ አባት ናቸው። ከአባታች ከአቡነ ቄርሎስ ዘትግራይ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ የተባረከ የሰኔ ወር ቀኑ ዐሥራ አምስት ሰዓት ነው። ከዚህም በኋላ ይጐድላል።
❤ ሰኔ ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን እስራኤል ለተባለው ለያዕቆብ ልጅ ለጻድቁ ለቅዱስ ዮሴፍና ለሚስቱ ለቅድስት አሰኔት ለዕረፍት ቀን መታሰቢያ በዓል፣ ከእርሱ ተአምራት ለተገለጡ ለሶርያ ሰው ለሆነ ለቅዱስ ለውንትዮስ ለቤተ ክርስቲያኑ ለቅዳሴ ቤቱ በዓልና ለመስተጋድል ለሰማዕት ለቅዱስ ቢፋሞን ለዕረፍቱ መታሰቢያና በስሙ ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የመጀመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከላይኛው ግብፅ ከጣሀ አውራጃ ከሆኑ ከባልጀራሞች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕት ቆዝሞስ ከዕረፍቱ መታሰቢያና፣ ከእስክድርያ ከተማ ሰማዕታትና ከሊቀ ጳጳሳት ቶማስም ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የቅዱስ ለውንትዮስ የቤተ ክርስቲያ ቅዳሴ ቤት፦ ይኸውም ቅዱስ ለውንትዮስ በሐምሌ ወር በሃያ ሁለተኛው ቀን በሰማዕትነት በዐረፈ ጊዜ ከታላላቅ መኳንንቶች የአንዱ መኰንን ሚስት መጣች ለወታደሮቹም ብዙ ገንዘብ ሰጠች የቅዱሱንም ሥጋ ወሰደች በባሏም ልብስ ገነዘችው በሣጥንም አድርጋ በቤቷ ውስጥ አስቀመጠችው በቀንና በሌሊትም የሚያበራ መብራት በፊቱ አኖረች። እንሆም ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኰንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቈጣ። በአንጾኪያም ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው።
❤ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራች ለመስፍኑ ሚስት መልካም ወጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ለባልዋ ተገለጠለት በወህኒ ቤቱም ብርሃን ወጣ ለመኰንኑም የራሱ የሆነውን በቤቱ ያለውን የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጐልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ተገለጠለት።
❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ አለው "አትዘን አታልቅስም ዛሬ ከዚህ ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደ ቤትህ በሰላም ትሔዳለህ"። የታሠረው መስፍንም ይህን ጐልማሳ ፈረሰኛ ስለ አየው በላዩም ስለ ወጣው ብርሃን የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደ ተዘጋና እንደ ተቆለፈ ወደ ርሱ ስለ መግባቱ ደግሞም የራሱ የሆነውን በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለ ማየቱ በዚህ ሁሉ ሥራ ያደንቅ ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለውንትዮስ በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሔደ በመኝታውም ተኝቶ ሳለ ረገጠው እጅግም ደነገጠ ለንጉሡም እንዲህ አለው "ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን ዕገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም በክፉ አሟሟትም ሙተህ እንዳትጠፉ ወደ ቤቱ ይሔድ ዘንድ ተወው"። ንጉሡም ከግርማው የተነሣ እየተንቀጠቀጠ "እሺ ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብሎ መለሰለት። በነጋ ጊዜም ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ልኮ መስፍኑን አወጣው ታላቅ ክብርንም አከበረው መልካም ልብሶችንም አልብሶ ከእርሱ ጋራ በማዕዱ አስቀመጠው። ፈረሰኛም እንደ ተገለጠለትና ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ነገረው መስፍኑም አደነቀ። ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ አድርጎ አሰበ መስፍኑም "እኔ መጠበብንና ሥራይን አላውቅም ከእሊህ ከምትለኝም ነገሮች ማን እንደተገለጠልህ ምንም አላውቅም"። ንጉሥም ከተገለጠለት ራእይ ፍርሀት የተነሣ ክፉ ነገርን ሊናገው አልደፈረም ነገር ግን ወደ አገሩ በታላቅ ክብር ሰደደው።
❤ መስፍኑም በጎዳና ሲጓዝ ሁለተኛ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ጠራብሎስም እስኪደርስ እያነጋገረው ያጽናናው ነበር ከዚህም በኋላ ተሠወረው። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ቤተሰቦቹን ሰላም አላቸው የእርሱን የወርቅ ልብስ የሚመስል ልብስ ለብሶ ፈረሰኛ ጐልማሳ እንደ ተገለጠለትም ነገራቸው ከወህኒ ቤትም እሥራት ያድነው ዘንድ ቃል እንደገባለት ነገራቸው። ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ እንደሆነ አውቃ "ብታየው ታውቀዋለህን" አለችው "አዎን" አላት ከዚያም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወደ አለበት ቦታ አስገባችው አይቶም "የተገለጠልኝ በእውነት ይህ ነው" አለ።
❤ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን ሣጥን ከፈተች ያንንም የርሱን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው። የፊቱንም መሸፈኛ ገለጠ የተገለጠለትና ከእሥራት ያዳነውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ። መስፍኑም ማን እንደሆነ ስለ እርሱ ሚስቱን ጠየቃት እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል ነገረችው መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ ስለ ሠራች ሚስቱን አመሰገናት መረቃትም የተመሰገነ እግዚአብሔርንም በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ሥራ ስለሚሠራ አመሰገነው። መብራትና ማዕጠንትም እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስከ አጠፋው ድረስ እንዲሁ የምትሠራ ሆነች።
❤ ከዚህም በኋላ መልካም ቤተ ክርስቲያን አንፀው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ በዚች ዕለትም ሰኔ 1 አከበሩዋት ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንትዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 1 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ ናሁ ዘእንተ ሠራዕከ እሙንቱ ነሠቱ። ወጻድቅሰ ምንተ ገብረ። እግዚአብሔር ውስተ ጽርሐ መቅደሱ። መዝ 10፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥42-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወሤሞ መልአከ አሕዛብ። ወረሰዮ እግዚአ ለቤቱ። ወአኰነኖ ላዕለ ኵሉ ጥሪቱ"። መዝ 104፥21-22። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥21-32፣ 1ኛ ጴጥ 4፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥9-23። የሚነበበው ወንጌል 24፥45-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የቅዱስ ዮሴፍና የሚስቱ የቅድስት አሰኔት የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው ለሐዋርያው ለቅዱስ ቆሮስ ለዕረፍት፣ ተጋዳ ለሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ላደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ላሰነች ለቅድስት አርዋ ለዕረፍት በዓልና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስሳ ስምንተኛ ለሆነ ለእስክድርያ ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ አባት ለአባ ሚካኤል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። ተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት ዲማዲስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ፦ ይህም ቅዱስ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል ከዕረገቱ በኋላም ሐዋርያትን አገልግሏቸዋል ከእርሳቸውም ጋራ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ጋራ በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ አገለገለው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትና አጠመቃቸው።
❤ ከዚህም በኋላም በምሥራቅ ወዳሉ አገሮች ሔደ ከምኵራቦችም ብዙ መከራ ደርሶበት ግንቦት 30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቆሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ሚካኤል፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ለእስክንድርያ ጳጳሳት ስሳ ስምንተኛ ነው። የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸዌ በቃሉም አጠናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ንጸሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ።
❤ ከዚህም በኋላ በግጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። የትሩፋቱ የጽድቁምና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማሙ ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
❤ በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚአመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅዱሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል። ሕዝቡንም ያስተማራቸዋና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። አንድ ጊዜ ከመጻሕፍት አንድ ጊዜም ከቃሉ።
❤ መልካም አገልግሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕማም በላዩ አመጣ። ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ግንቦት30 ቀን ሰጠ መላ ዕድሜውም ዘጠና ዓመት ከስምንት ወር ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ሚካኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። የግንቦት ወር ንባብ ተፈጸመ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ለመንግሥተ ሰማያት የተዘጋጀን ያደርገን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የንግቦት30 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለቆሮስ ለወልደ ማርያም ዘተልእኮ። መጠነ ፫ቱ ዓመት በኢያውክኮ። ወእምድ ኅረዝ ዐርገ ካዕበ ምስለ ጳውሎስ ተወሲኮ። እምነ ሥቃይ ዘረከቦ ወእምንዳቤ ዘሆኮ። አመ ፍጻሜ ወርኅ አዕረፈ በሠናይ አምልኮ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 30።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ኃጢአትየ ዘበንእስየ ወዕበድየ ኢትዝክር ሊተ። ወበከመ ሣህልከ ተዘከረኒ። በእንተ ምሕረትከ እግዚኦ"። መዝ 24፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 7፥44-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እስመ ጽድቅ ወምጽዋት ያበድር እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ይሁብ ክብረ ወሞገስ። እግዚአብሔር ኢያስተፄንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየዋሃት"። መዝ 83፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 18፥23-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቆሮስ የዕረፍት በዓል፣ የቅድስት ዜና ማርያም የዕረፍት በዓልና የበዓለ ዕርገት ሰሞን ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት በማሰብ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) ትመመገብ ለነበረች ለታላቋ እናት ለቅድስት ዜና ማርያም ለልደት በዓል፣ ለቅድስት ወለተ ማርያም ዘጎንደር የዕረፍት በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም፦ ከአባቷ ከቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ከእናቷ ከቅድስት አመተ ማርያም በ11 መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30 ቀን የተወለደች ሲሆን ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንፅህ ድንግልና በምድረ ሂንፍራንስ ጣራ ገዳም አካባቢ በሚገኘው በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25 ዓመት በጾም በፀሎት ምንም አይነት የላመ የጣፈጠ እህል ሳትቀምስ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) በመዘፍዘፍ ከ3 ቀን በኃላ በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ላይ የቀመሰውን መራራ ሐሞትን በማሰብ ሙሉ ሕይወቶን እየተመገበች ታላቅ ተጋድሎዋን ፈፅማለች፡፡ ከዚህ የተነሳ ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜ ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ ተብሎ እስከ አሁን ድረስ በስሞ እየተጠራ ይገኛል፡፡
❤ ከአቡነ እድርያስ ዋሻ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ተነስተን ስንጓዝ አዲስ ዘመን ከተማ በስተቀኝ በኩል ተገንጥለን 15 ኪሜ ያክል የጥርጊያ መንገድ እንደተጓዝን በስሟ የተሰየመውን ደሪጣ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ገዳም ላይ ቀሪ ሕይወቶን ምንም አይነት ዋሻ ባልነበረበት በከፍተኛ ተራራ ላይ እጅግ አስቸጋሪ ቀዝቃዛ አየር ባለበት ብርዱን፣ ፀሐዩን፣ ቁሩን፣ ረኃቡንና ጥሙን በመቋቋም ራቁቶን በመሆን መራራ ምግቦችን አዋህዳ በመመገብ በጾም በፀሎት በመትጋት አስቸጋሪ የሆነውን ተጋድሎዋን በመፈፀም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን በታላቅ ክብር አርፋለች፡፡
❤ በዚህም ወቅት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አላፋት ቅዱሳ መላዕክት ጋር እንዲሁም ከሐዋርያት ፣ ከሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከደናግል ጋር በመሆን ከሰማይ በመውረድ በታላቅ ክብር ዕረፍቷን አክብሮላታል ታላቅ ኪዳንም ገብቶላታል፡፡
❤ በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ወይንም በአሁኑ ሰዓት መቃብሯ በሚገኝበት ዋሻ ቤተመቅደስ አካባቢ በተጋድሎዋ ጊዜ ራቁቷን በሆነች ሰዓት መላ ገላዋን የሸፈነላት ፀጉር በእየ ዛፎቹ ላይ እስከ አሁን ድረስ አለ፡፡ ይህም የጸጉር አምሳያ ከገዳሙ በመውሰድ ብዙ ሰዎች በቤታቸው በመታጠን ከአስም እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች እየተፈወሱና እየዳኑ ሲሆን ታላላቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡
❤ በዚህ ገዳም ከሌሎች ገዳማት ለየት የሚያደርገው ታሪክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ በመውረድ ራሱ የባረከው ልዩ ታሪክ ያለው ጠበል የሚገኝ ሲሆን ይህም ጠበል በቦታው ላይ ሆኖ የተጠመቀ ፣ የጠጣ ፣ አልያም በአለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀመ እስከ አሁን ድረስ መካን የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ልጅ የሚያገኙ ከመሆናቸው ባሻገር ከማንኛውም ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ታላላቅ ታምራትን እየሰራ ይገኛል፡፡
❤ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ላሊበላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሰረት ወደዚሁ ታላቅ ስፍራ በመምጣት የጻድቋ ማረፈያ መታሰቢያ ዋሻ ቤተ መቅደስ በመፈልፈል የሰራላት ሲሆን በመቀጠል አፄ ይስሐቅ በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህን ገዳም በስሟ በመገደም በዚሁ ዋሻ ውስጥም የጻድቋ የቅድስት ዜና ማርያም መቃብሯ እንዲሁም የመታሰቢያዋ ፅላት የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢው ያሉት ሕዝበ ክርስትያን ከካህናት ጋር በመሆን ሥርዓተ አምልኮ በመፈፀም እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
❤ ይህ ዋሻም አስቀድሞ ሦስቱ ቅዱሳን ማለትም አቡነ እንድርያስ ዘጣራ ገዳም ፣አቡነ ተክለኃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፣ ጻድቋ ቅድስት ዜናማርያም ዘደሪጣ ውስጥ ለውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በፀጋ እግዚአብሔር ይገናኙበት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓትም እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ይመላለሱበታል፡፡
❤ ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ስፍራ ተነስቶ የጻድቋ ደጃን የረገጠ ለ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ የሚል ቃል ኪዳን ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ተሰቶታል። ከእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ማኅበረ ዜማ ማርያም ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት የተወረደ።
+ + +
❤ ቅድስት ወለተ ማርያም ዘጎንደር፦ ትውልዷ ጎንደር ሲሆን በዐፄ ወናአግ ሰገድ ዘመን የነበረች ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነች ጻድቅ እናት ናት፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ከመነኰሰች በኋላ ወደ ጣና ገዳም ገብታ በጣና ባሕር ውስጥ ለ11 ዓመት ቆማ የጸለየች ድንቅ እናት ናት፡፡ ከእናታችን ከቅድስት ወለተ ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን እኛንም በጸሎቷ ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
