ሰዋስው ☘☘☘☘
الذهاب إلى القناة على Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
إظهار المزيد1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 161
14/3/2015 ዓ.ም (፲፬/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
እማዕምቅ ጸዋዕኩከ እግዚኦ።
እግዚኦ ስምዓኒ ቃልየ።
ወይኩን ዕዝንከ ዘያፀምዕ ቃለ ስእለትየ። መዝ. 9፥1
🕯 ትርጉም
የጽድቄ አምላክ በጠራሁት ጊዜ መለሰልኝ።
በጭንቀቴም አሰፋህልኝ።
ማረኝ ጸሎቴንም ስማ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ለአገረ ጠራክያ ኤጲስ ቆጶስ ለቅዱስ አባት ለአባ መርትያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ላደረገና ክቡር ይግባንና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላሳመነ ለአባ ዳንኤል ዕረፍት ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ሱራስጦስ፣ ከእንድራዎስ፣ ከመብራኖስ፣ ከራጢስና ከይስጥ ከጋርሴስ ከበጥላንና ከመታሰቢያቸው በደብረ ቀልሞን ከተሠራች ቤተ ክስትያን ከከበረችበት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የአገረ ጠራክያ ኤጲስ ቆጶስ አባ መርትያኖስ፦ ይህ ቅዱስ ሶርያ ከምትባል አገር ነው ወላጆቹም ክርስቲያን ናቸው እርሱም በገድል የተጠመደ ተጋዳይ ነው። አርዮሳውያንንም የሚቃወማቸው ከሀድያን የሚላቸው አውግዞም የሚያሳድዳቸው ሆነ። ስለዚህም በእርሱ ላይ ታላቅ መከራ ደረሰበት። በሚያልፍባትም ጎዳና ጠብቀው ይይዙታል አብዝተውም ገርፈው እግሩን ይዘው በሜዳ ውስጥ ይጎትቱታል እንዲህም ብዙ ጊዜ አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ሸሽቶ ወደ ሩቅ አገር ተጒዞ ከኤርትራ ባሕር ዳር ደረሰ ከምድር የሚበቅሉ ቅጠሎችን እየተመገበ በዚያ ዋሻ ውስጥ ብዙ ዓመታትን ኖረ። ኤጲስቆጶስም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው እነሆ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜና በተሰማ ጊዜ ከዚያ ወስደው ጠራክያ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በሹመቱ በጎ አካሔድን ተጓዘ በዘመኑም በብዙዎች ላይ ሰላም ፍቅር ቸርነት ሆነ።
❤ እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ተአምራትን አደረገ በጐዳናም አልፎ ሲሔድ የሞተ ሰው አየ ሌላም ዓመፀኛ ልቡ የደነደነ በሐሰት "ከእርሱ ላይ አራት መቶ የወርቅ ዲናር አለኝ ያንን ካልሰጠኝ አላስቀብርም" ብሎ ዘመዶቹን ሲከለክል ነበር። ይህም ቅዱስ "የሞተውን ይቅበሩት ተዋቸው" ብሎ ብዙ ለመነው እርሱ ግን አልሰማውም። በዚያንም ጊዜ ይህ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ማለደ ያን ጊዜ የሞተው ሰው ተነሥቶ ምንም ምን ዕዳ እንደሌለበት ተናገረ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርትያኖስ ያንን ዓመፀኛ በሰፊት እንዲህ አለው "ለምን በሐሰት ተናገርክ የተሠወረውን የሚያውቅ እግዚአብሔርን አትፈራውምን" በዚያንም ጊዜ ያ ዓመፀኛ ሞተ ከሞት የተነሣው ግን በሰላም ወደ ቤቱ ገባ።
❤ ከዚም በኋላ ይህ ቅዱስ መርትያኖስ ብዙ ዘመናትን ኖረ መልካም አገልግሎትንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ ኅዳር 14 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መርትያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ዳንኤል፦ ይህም አባት ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ያደረገና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳመነው ነው። የእምነቱም ምክንያት እንዲህ ነው ይህ ንጉሥ ጽኑዕ የሆነ የሆድ በሽታ ታሞ ነበር ባለ መድኃኒቶችም ሊአድኑት አልቻሉም ንጉሡም ከማዕዱ የሚመግበው አብሮት የሚኖር ሥራየኛ ሰው ነበርው ንጉሡም እንዲህ አለው "ያንተ ከእኔ ጋር መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው ከዚህ በሽታ ካልፈወስከኝ እገድልሃለሁ"። ሥራየኛውም ንጉሡን በተንኰል እንዲህ ብሎ ተናገረው "ንጉሥ ሆይ የምነግርህን ካደረግህ ከደዌህ ትድናለህ። አሁንም ለአባትና እናቱ አንድ ብቻ የሆነ ልጅ ይፈልጉልህ እናቱ አሥራ ትያዘው አባቱም ይረደው በእርሱም ደም ትድናለህ" መሠርዩ ይህን ማለቱ ግን እንዲህ ያለ ሥራ መሥራትን ንጉሥ ይፈራል ወይም ልጁን የሚሰጥ አይገኝ ብሎ አስቦ ነው።
❤ ንጉሥም በሚገዛው አገር ውስጥ ፈልገው በአንድ ሺህ የወርቅ ዲናር ሕፃን ልጅ ይገዙለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። በዚያችም አገር አንድ ልጅ ያላቸው ድኆች የሆኑ ባልና ሚስት ነበሩ እነርሱ ይህን ነገር ሲሰሙ ልጃቸውን ወደ ንጉሥ ወሰዱ ልጁም በማልቀስ "እኔ በፈጠረኝ እግዚአብሔር ላይ ተማምኛለሁና እርሱም ያድነኛል" ይል ነበረ። እናቱም አጥብቃ አሠረችው አባቱም ሊያርደው በንጉሡ ፊት ሾተሉን መዘዘ በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ አይኖቹን ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ ወደ እግዚአብሔር በልቡ ሲጸልይ ከንፈሮቹን አንቀሳቀሰ እግዚአብሔርም በንጉሡ ልብ ርኅራኄን አሳደረ ፈትታችሁ ልቀቁት ብሎ አዘዘ ወደርሱም አቅርቦ "ዐይኖችህን ወደ ሰማይ በአቀናህ ጊዜ ምን አልክ" አለው "ጌታዬ ሆይ ልጅን የሚገፋው ቢኖር አባቱና እናቱ ያድኑታል ከዚያም የጸና ሥራ ቢኖር ንጉሥ ዳኛ ያድነዋል እኔ ግን ከሁላችሁም ርዳታ በአጣሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመንኩ" አለው። ንጉሡም ሰምቶ ራራለት አንድ ሽህ የወርቅ ዲናርንም ሰጠው።
❤ ስለዚህም እግዚአብሔር ይቅር ልለው ወዶ መነኰስ አባ ዳንኤልን ላከለት እርሱም ወደ ንጉሡ በደረሰ ጊዜ በፊቱ ተአምራትን አደርጎ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳመነው ከበሽታውም ፈወሰው ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋርም አጠመቀው ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሶ እየተጋደለ ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ኅዳር 14 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባ ዳንኤል በረከቱም ትድረስን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 14 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለመርትያኖስ ምሉአ ጸጋ ወሀብት። ከመ ይስብክ ሃይማኖተ በመጣርያ አንተ ተውህበቶ ሢመት። እምአርሳውያን ሕዝብ ሶበ ረኮቦ ስደት። ኀበ ሖረ ወፈለሰ ውስተ ምድር ርኅቅት። በኃይለ ጸሎቱ ተንሥአ ምውት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 14።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉኒ። ወእግዚአብሔር ተወክፈኒ። ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ"። መዝ26፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥12-24፣ 1ኛ ጴጥ 5፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 23፥6-10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥46-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ዮሐንስና የአቡነ ቄርሎስ ዘሽሬ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ኤርትራ ውስጥ በሚገኘው ታላቁ ገዳም ደብረ ቢዘን ከአቡነ ፊሊጶስ በኋላ አበምኔት ለነበሩት ልክ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብ እንዳዘንብ ሦስት ዓመት ሰማይን ለለጎሙት ለታላቁ አባት ለሃይማኖት መምህር ለአቡነ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና ለአቡነ ቀሌምንጦንስ ዘሽሬ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ዮሐንስ ዘአስገዶ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው ትግራይ አድዋ ነው። የመነኰሱት በአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን እጅ ነው። ደቀ መዝሙራቸውም ሆነው በጸሎት አብረው ኖረዋል። ወደ ደብርነት የተለወጠው ገዳማቸውም ከደብረ ቢዘን አጠገብ ይገኛል።
+ + +
❤ አቡነ ቀሌምንጦንስ፦ የትውልድ አገራቸው ትግራይ ሽሬ ሲሆን ጻድቁ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ገድል አላቸው። ድፍን ኢትዮጵያን በአራቱም አቅጣጫ ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ በባዶ እግራቸው ዞረው ገዳማትን እየተሳለሙ ሥርዓትን እያጸኑ የኖሩ ታላቅ አባት ናቸው። በስማቸው የተጠራው ቤተ ክርስቲያን ትግራይ አሎጌን ውስጥ ይገኛል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ ገሣጼ ሕዝብ አብዳን። በከሊአ ዝናም ወጠል መጠነ ሠለስቱ አዝማን። እንበይነ ዝንቱ ኃይልከ ኃይለ አንጥናን። ትትሜሰል በኤልያስ ወበዮሐንስ ካህን። ወበቴስባን ትትሜሰል ቢዘን"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 14።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለ፻፻ አዕላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መላእክት"። ትርጉም፦ ለአእልፍ አእላፋትና ትእልፊተ አእላፋት መላክት ሰላምታ ይገባል።
+ + +
❤ "ሰአሉ ለነ ማኅበረ መላእክት ፍሡሓን እለ ኢትነውሙ ትጉሃን እንበለ አፅርዖ ሰባሕያን ሰአሉ ለነ አስተምህሩ ለነ"። ትርጉም፦ ያለ ዕረፍት አመስጋኖች የማታንቀላፉ ትጉሃን የምትኾኑ ደስ ያላችኍ የመላእክት አንድነት ለምኑን አማልዱን። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በአንዲት ዕለትም በሥጋው ለምጽ ያለበት ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ወደርሱ መጣ አባ ዘካርያስም በትሕትና በቅን ልቡና እንዲህ አለው። "ወንድሜ አባ መርቆሬዎስ ሆይ በአንተ ላይ ስለደረሰ ስለዚህ ደዌ እኔም በጸሎቴ ረዳሃለሁ እግዚአብሔር ሙሴን በፍርድ ውስጥ ለማንም አታድላ ያለውን አንተ ታውቃለህ ስለዚህ ይህ የለምጽ ደዌ በላይህ እያለ ክህነት አይገባህም መጽሐፍ ርኲስ ነው ብሎታልና" አለው ኤጲስቆጶሱ አባ መርቆሬዎስም አለቀሰና "አባቴ በጸሎትህ ርዳኝ" አለው ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወጥቶ ሔደ በሀገረ ስብከቱ ወዳለች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ ከዚህም ደዌ ታነጻው ዘንድ ወደርሷ በመጸለይና በመማለድ እያለቀሰ በእመቤታችን ማርያም ሥዕል ፊት ቆመ ከሰኞ ጥዋት ጀምሮ እንዲህ እያደረገ ቀንና ሌሊት እየጸለየና አየጾመ ኖረ። በረቡዕ ዕለትም በዘጠኝ ሰዓት ደክሞት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከበላዩ ካለችበት ግድግዳ ላይ ራሱን አስጠግቶ አንቀላፋ ። በእንቅልፉም ውስጥ ሳለ የሥዕሊቱ እጅ ሥጋውን ሲዳሥሥ አየ በዚያንም ጊዜ ነቅቶ ሥጋው ከለምጹ ነጽቶ አገኘው ታላቅ ደስታም አደረገ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም አመሰገነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም አመሰገናት ረድኡም ሲመጣ "ና ልጄ ሆይ ሥጋዬን እይ እመቤቴ ማርያም ከደዌ አንጽታኛለችና" አለው በዚያችም ቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ድረስ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዘካርያስ ሔደ በዕለተ እሑድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያለ በእርሱ ላይ የሆነውን አስረዳው እንዲህም አለው ይህ ሁሉ የተደረገልኝ በከበረች ጸሎትህ ነው። የከበረ አባ ዘካርያስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እግዚአብሔር ንጹሕና ቅን የሆነ ልቡናህን ተመልክቶ ልመናህንና ዕንባህንም ተቀብሎ ከደዌህ አነጻህ አሁንም ከተቀበልከው ጸጋ እንባረክ ዘንድ ቀድሰህ ሥጋውንና ደሙን ልታቀብለን ይገባሃል"። ያን ጊዜም መሥዋዕትን ሠርቶ ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው በቤተ ክርስቲያን ያሉትም ሁሉ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበሉ ስለዚች ምልክትም አደነቁ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርግ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።
❤ ሁለተኛም አንድ ዲያቆን ወደ አባ ዘካርያስ መጥቶ ሰገደለት በፊቱም አለቀሰ እግሮቹንም እየሳመ እንዲህ አለው "አባቴ ሆይ ራራልኝ እኔ ተሳስቼ በኃጢአት ወድቄአለሁና ወዲያውኑ ሥጋዬ ሁሉ ለምጽ ሆነ"። አባ ዘካርያስም "ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በድካም ላይ መጽናት ይቻልሃልን" አለው "አዎን አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ ።
❤ በዚያንም ጊዜ በእርሱ ዘንድ በጨለማ ቤት ዘጋበትና እንዲህ ብሎ አዘዘው ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ በመቆም በቀንም በሌሊትም ስለ ኃጢአቱ እየተጸጸተ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት እንዲማልድ አባ ዘካርያስም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጥቂት እንጀራ በሚዛን መዝኖ ጥቂት ውኃም ሰጠው ሦስት ሱባዔዎችም እንዲህ አድርጎ ሥጋውን ጐበኘ ለምጹንም አገኘው በወር መጨረሻም ጐበኘው ለምጹን በሥጋው ላይ አገኘ። "ልጄ ሆይ በርታ አትፍራ" አለው አርባ ቀኖችም ከተፈጸሙ በኋላ ጐበኘው ሥጋው ከለምጹ ነጽቶ አገኘው ዘይትንም ቀባው "ልጄ ሆይ እነሆ ድነሃል ነፍስህን ጠብቅ ከእንግዲህም ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ሥራ እንዳትመለስ ተጠበቅ አሁንም በሰላም ወደ ቤትህ ግባ" አለው እርሱም የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ገባ።
❤ እግዚአብሔርም በዚህ አባት እጆች ድንቆች ተአምራትን አደረገ በሹመቱም ወንበር ሃያ ስምንት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ ይኸውም ከንጹሐን ሰማዕታት ዘመን በሰባት መቶ ስልሳ ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዘጋርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 13 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዘይሬስዮሙ ለመላእክቲሁ መንፈስ። ወለእለ ይትለአክዎ ነደ እሳት። ሣረራ ለምድር ወአጽንዓ" መዝ 103፥40-41። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥1-14።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ መላእክቲሁ። ፅኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ"። መዝ 102፥20። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-25፣ ይሁ 1፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 12፥6-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-46 ወይም ማቴ 6፥5-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የያዕቆብ ዘሥሩግ ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ እግዚአብሔር አብ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲውን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን እግዚአብሔር በአጠፋው ጊዜ እግዚአብሔርን የሚወድ ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ በዚያንም ጊዜ ክርስቶስን በመታመን የታሠሩትን ሁሉ ይፈቱአቸው ዘንድ መልእክቱ በሀገሮች ሁሉ ደረሰች። ይህ ቅዱስ አባት ጢሞቴዎስም ከእሥር ቤት በወጣ ጊዜ በሀገረ ስብከቱ ያሉትን መነኰሳቱንና ካህናቱን ሁሉ ሰበሰባቸው ስለዚያ ስለአሠቃየው መኰንን ነፍስ ድኅነትም እግዚአብሔርን እየለመነ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ ፍጹም የሆነ ጸሎትን በማድረግ አደረ።
❤ እንዲህም ብሎ ጸለየለት "አቤቱ ይህን መኰንን ማረው እርሱ ለእኔ ታላላቆች የሆኑ በጎ ነገሮችን አድርጎልኛልና ወደ አንተም ለመድረሴ ምክንያት ሁኖኛልና አቤቱ እንዲሁ በአንተ አምኖ ወዳንተ ይደርስ ዘንድ ምክንያት አድርግለት"። የዚህ አባትም ልብ ከቂም ከበቀል የነጻ በመሆኑ ሰዎች አደነቁ።
❤ ይምረው ዘንድ ነፍሱንም ያድንለት ዘንድ አባ ጢሞቴዎስ ስለርሱ ወደ እግዚአብሔር እንደሚለምን ለመኰንኑ ነገሩት መኰንኑም ሰምቶ እጅግ አደነቀ እንዲህም አለ "እኔ ግን ጽኑ ሥቃይን ስለአሠቃየሁት እንደሚረግመኝ አስብ ነበር አሁን እርሱ ግን ስለ እኔ ምሕረትን ይለምናል የእሊህ ክርስቲያን ሃይማኖታቸው በውስጡ የተሠወረ ሰማያዊ የሆነ ምሥጢር" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ልኮ ይህን አባት ጢሞቴዎስን አስመጣውና ስለ ክርስትና ሕግ ያስረዳው ዘንድ ለመነው እርሱም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ያለውን ገለጠለት ዳግመኛም የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የሆነበትን ምክንያት ከብዙ ዓመታትም አስቀድሞ ነቢያት ስለርሱ ትንቢት እንደተናገሩ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው በመሆኑ ትንቢታቸው እንደተፈጸመ ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ስለመሞቱ ስለትንሣኤውና ስለ ዕርገቱ ዳግመኛም ለፍርድ ስለመምጣቱ አስረዳው።
❤ መኰንኑም በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በዚህ አባት እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ሹመቱንም ትቶ መነኰሰ በገድልም ተጠመደ ከዚህም አባት ጢሞቴዎስ መንጋዎች ውስጥ የተቈጠረ ሆነ። ይህም አባት ጢሞቴዎስ የቀረ ዘመኑን መንጋዎቹን ሁልጊዜ እያስተማረ በቀናች ሃይማኖትም ላይ እያጸናቸው ኑሮ በሰላም በፍቅር አንድነት ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የእስክንድርያ ስልሳ አራተኛ ሊቀ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዘካርያስ፦ ይህም አባት ከእስክንድርያ ሰዎች ወገን ነው በቤተ ክርስቲያንም ንብረት ሁሉ ላይ መጋቢነትና ቅስና ተሾመ እርሱም በተጋድሎ የጸና ንጹሕ ድንግል ነው በጠባዩም የዋህ ቅን የሆነ በዕድሜውም የሸመገለ ነው ።
❤ ሊቀ ጳጰሳት አባ ፊላታዎስም በዐረፈ ጊዜ ለዚች ሹመት የሚገባ ሰው ይመርጡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር ኤጲስቆጶሳት ተሰበሰቡ እነርሱም ለዚች ሹመት ስለሚሻል ሰው በወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው እየተነጋገሩ ሳሉ እነሆ አንድ ሰው መማለጃ በመስጠት ያለ ኤጲስቆጶሳት ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ከንጉሥ የመልእክት ደብዳቤ ይዞ እንደሚመጣ ከእርሱም ጋር ከንጉሥ የተቀበላቸው ጭፍሮች እንዳሉ ሰሙ። ኤጲስቆጶሳቱም የአባቶቻችንን የሐዋርያትን ሥርዓት በመተላለፍ መማለጃ በመስጠት ስለሚደረገው የሊቀ ጵጵስና ሹመት አዘኑ። ስለዚህም እርሱ ራሱ የመረጠውን ይሾምላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ተግተው በማዘውተር የሚጸልዩና የሚማልዱ ሆኑ ።
❤ እነርሱም እግዚአብሔርን እየለመኑ ሳሉ እነሆ ይህ አባት ዘካርያስ ከቤተ ክርስቲያን ጫፍ በመሰላል ሲወርድ ሆምጣጤ የተመላ እንስራ በእጁ ይዞ ነበር እግሩንም አድጦት ከመሰላሉ ጫፍ እስከታች ወደቀ እንስራውንም እንደያዘ ፈጥኖ ተነሣ እንስራውም አልተሰበረም ሆምጣጤውም አልፈሰሰም። ኤጲስቆጶሳቱም ይህን ምልክት በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ የአገሩንም ሰዎች ትንሹንም ትልቁንም ስለርሱ ጠየቋቸው እነርሱም ጽድቁንና ትሩፋቱን ተናገሩ ስለርሱም መሾም ሁሉም ተስማምተው ይህን አባ ዘካርያስን በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
❤ ከዚህም በኋላ ብዙ መከራና ኀዘን በላዩ ከግብጽ ንጉሥ እልሐክም ዘንድ ደረሰበት ይህም ገዢ ማለት ነው። በዚያም ወራት ከአባ መቃርስ ገዳም አንድ መነኲሴ ወደርሱ መጥቶ "ኤጲስቆጶስነት ሹመኝ" አለው አባ ዘካርያስም "ልጄ ሆይ ታገሥ አባቶቻችን ሐዋርያትም ያዘዙትን ሥርዓት አትተላለፍ ግን ወደ ገዳምህ ተመልሰህ ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል እግዚአብሔርም የፈቀደው ይሁን" አለው። ይህንንም በጎ ምክር በሰማ ጊዜ ያ መነኵሴ ተቆጣ በልቡም ሰይጣን አደረበትና ወደ ግብጽ ንጉሥ ሒዶ በሐሰት ነገር አባ ዘካርያስን ወነጀለው ንጉሡም የከበረ አባት ዘካርያስን ይዞ አሠረው።
❤ ከዚህም በኋላ ተነጣጥቀው ይበሉት ዘንድ ለአንበሶች ጣለው አንበሶችም ከቶ አልቀረቡትም ንጉሡም የአንበሶቹን ጠባቂ ተቆጣ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጉቦ የተቀበለ መስሎት ነበርና። ከዚህም በኋላ አንበሶቹን አስራባቸውና ሊቀ ጳጳሳቱን የላም ደም ቀብቶ በድጋሜ ለአንበሶች ጣለው እነርሱም ከቶ አልቀረቡትም ንጉሡም አደነቀ ከአንበሶች መካከልም እንዲአወጡት አዘዘ።
❤ ከዚህም በኋላ ሦስት ወር አሠረው ሁል ጊዜም እንዲህ የሚለው ሆነ "የክርስቲያንን ሃይማኖት ትተህ ወደእኛ ሃይማኖት ካልገባህ አለበለዚያ እኔ አሠቃይቼ በሰይፍ እገድልሃለሁ። ዳግመኛ ለአንበሶች እጥልሃለሁ ወይም ከእሳት ውስጥ እጨምርሃለሁ" የከበረ አባ ዘካርያስ ግን በሃይማኖቱ በመጽናት ምንም ምን አልፈራም።
❤ ሁለተኛም ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባለት እንዲህም አለው "ትእዛዜን ተቀብለህ ወደ ሃይማኖቴ ብትገባ እኔ ብዙ ሀብት እስጥሃለሁ በሁሉ መሳፍንትም ላይ መስፍን አድርጌ እሾምሃለሁ ቅዱስ አባት ዘካርያስም "በዓለም ያለ መንግሥትን ሁሉ ብትሰጠኝም የቀናች ሃይማኖቴን አልተውም" ብሎ መለሰለት ።
❤ ከዚህም በኋላ ጥቂት ቀን አሥሮ ለቀቀው ከእሥር ቤትም ወጥቶ አባ ዘካርያስ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። ንጉሡንም ስለ መፍራት ከእርሱ ጋር የሔዱ ብዙ ኤጲስቆጶሳት ነበሩ በሚገዛቸው አገሮች ሁሉ ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉንም እንዲአፈርሱአቸው ንጉሥ አዞ ነበርና። ታላቅ ሥቃይንም እያሠቃየ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ከሃይማኖታቸው አወጣቸው የክርስቲያንም ወገኖች በዚህ መከራ ውስጥ ዘጠኝ ዓመት ኖሩ ።
❤ ከዘጠኝ ዓመትም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡን ይቅር አለ ቊጣውንም መለሰ መከራውንም ሁሉ ከላያቸው አስወገደ ንጉሡ በሚገዛቸው አገሮች በሁሉ ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ ከእነርሱም የወሰዱትን ገንዘባቸውን ሁሉ የምድራቸውን ጒልት እንዲመልሱላቸው ንጉሡ አዘዘ ።
❤ ከዚህም በኋላ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩ ከፊተኛውም እጅግ የተሻሻሉ ሁነው ዳግመኛ ታደሱ ይህም አባት ዘካርያስ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ ክርስቲያኖችም በአብያተ ክርስቲያኖቻቸው በሚጸልዩና በሚቀድሱ ጊዜ ያለ ሥጋት ደወሎቻቸውን እንዲደውሉ ንጉሥ አዘዘ። ክርስቲያኖችም በታላቅ ደስታ የሚኖሩ ሆኑ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ሁሉ የቀና ሁኗልና ይህም አባት አብያተ ክርስቲያናትን እያሠራ የሚያሻቸውንም እያሰበ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ ።
1 161
❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ እግዚአብሔር አብና ለአእላፍ መላእክት ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ዐሥራ ሦስት ወንበዴዎች ስርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ ከከበረ ባለጸጋ ከአስከናፍር ዕረፍትና ከአገረ እንጽና ኤጲስቆጶስ ከከበረ ከአባት ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ስልሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት ከዘካርያስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "እሎንቱ ሊቃናት መላእክተ ምሕረት እለ ኪሩባን በነደ እሳት ሱራፌል ወኪሩቤል ይትፌነው ለሳእል እምኀበ ልዑል ሩጾቶሙ ይቀልል እም ሩጸተ ነፋሳት"። ትርጉም፦ እነዚህ የይቅርታ መላእክት በሚነድ እሳት የሚጫኑ ሱራፌልና ኪሩቤል ከነፋስ ፍጥነት በሚፈጥን ከልዑል ዘንድ ለምሕረት ይላካሉ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን የአእላፍ መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን፦ እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው። ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ "በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም አእላፋት መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው" አለ።
❤ ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር። ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻም በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ" አለ።
❤ ሙሴም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቊጥር አሕዛብን አውራራጃዎች እንደ ወሰናቸው። ሁለተኛም እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ" አለ።
❤ ዳዊትም እንዲህ አለ "መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው"። ሁለተኛም "የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው" አለ። ኤልያስም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ።
❤ ዳንኤልም እንዲህ አለ "ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ ከየሁ ብሉ፣የ መዋዕል እግዚአብሔር በላቸው ተቀምጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉር እንደ ብዝት ነጭ ነው ዙፉኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው። ነእሳት ጎርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ" አለ።
❤ ሉቃስም እንዲህ አለ "ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ" እያሉ" አለ።
❤ ማቴዎስም እንሆ መላእክትም ሊአገለለግሉት መጡ" አለ። ሁለተኛም "የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል" አለ።
❤ ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ" አላቸው የሚል ነው።
❤ ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል" አለ።
❤ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓርጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ "መላእክት፣ አጋዕዝት፣ ሥልጣናት፣ ኃይላት፣ መናብርት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፣ አርባብ፣ ኪሩቤልና ሱራፌል" ብለው ተናገሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በበቅዱን አእላፍ መላእቶቹ አማላጅነት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ተስፋ ኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ዐሥራ ሦስት ወንዴዎች ስለርሱ በእርሱ ሃይማኖቶ ከዓለም የተለዩ የሆነ የከበረ ባለጸጋ ቅዱስ አስከናፍር፦ ይህም አስከናፍር ከሮሜ መኳንንት አንዱ ነው እርሱም ለድኆችና ለምስኪኖች ምጽዋትን የሚሰጥ እንግዶችንና መጻተኞችን የሚቀበል ነው።
❤ በዚያም ወራት ያገኙትን ሰው ሁሉ የሚነጥቁና የሚያጠፉ ዐሥራ ሦስት ሽፍቶች ነበሩ እንግዳ እንደሚቀበል ይልቁንም መነኰሳትን እንደሚወድ የአስከናፍርን ዜና በሰሙ ጊዜ ወደርሱ ሒደው በተንኰል ይገድሉት ዘንድ ገንዘቡንም ሁሉ ሊወስዱ ተማከሩ። ከዚህም በኋላ የምንኲስና ልብስ ለብሰው ከደጁ ቆሙ በአያቸውም ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደሆኑ አንዱ ጌታ ክርስቶስ እንደሆነ አሰበ ሰገደላቸውም ወደ ቤቱም አስገብቶ ማዕድ አቀረበላቸው እግራቸውንም አጠበ ሠላሳ አምስት ዓመት ሽባ ሆኖ በኖረ ልጁ ላይ ያንን እግራቸውን ያጠቡበትን ውኃ ረጨ ወዲያውኑ ልጁ ዳነ።
❤ እነዚያ ሽፍቶችም የሆነውን በአዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ እርሱ አስከናፍር ግን "አባቶቼ ሆይ ጌታ ክርስቶስ ከእናንተ መካከል የቱ እንደሆነ ንገሩኝ እሰግድለት ዘንድ" አላቸው የአገር ሰዎችም የመኰንኑ ልጅ እንደዳነ በሰሙ ጊዜ ወደርሳቸው መጥተው ሰገዱላቸው እንዲህም አሏቸው "የእግዚአብሔር ቅዱሳንኖች ሆይ ባርኩን በሽተኞችንን አድኑልን"።
❤ ከዚህም በኋላ እሊህ ወንበዴዎች ሾተሎቻቸውን አውጥተው "በእርሳቸው ልንገድልህ በወደድንበት እኛን ይገድሉን ዘንድ እሊህን ሾተሎች ውሰድ" አሉት "እግዚአብሔር በአንተ ጽድቅ የራራልን ባይሆን በአጠፋን ነበር"። ይህንንም ከአሉት በኋላ ተሰናበቱት ከእርሱም አንዳድ መስፈሪያ ምስር ለየአንዳቸው ተቀብለው ሃያ አምስት ቀን ያህል የሚያስጒዝ ጎዳና ወደ ምድረ በዳ ተጓዙ ያንንም ምስር ከአሸዋ ውስጥ በተኑት ፀሐይ በሚገባም ጊዜ ከአሸዋው ውስጥ ሦስት ሦስት ፍሬ ምስር ፈልገው ይቀምሳሉ እንደዚህም ሠላሳ ዓመት ኖሩ። ከዚህም በኋላ በከሀዲ መኰንን በመጣ ጊዜ እርሱ ወዳለበት ሒደው በጌታችን ታመኑ እርሱም ገደላቸው የሰማዕትነት እክሊል ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አስከናፍርና በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የሀገረ እንጽና ኤጲስቆጶስ የከበረ አባ ጢሞቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ልቡ ንጹሕ የሆነ ጻድቅ ሰው ነው ታላቅ ተጋድሎንም የተጋደለ ነው። የእንጽና አገር መኰንንም ለሰዎች የቀናች ሃይማኖትን በማስተማሩና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አመነ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን ብዙ ዘመናት አሠቃየው። ከእሥር ቤትም አውጥቶ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ ወደ እሥር ቤት ይመልሰው ነበር ከእርሱም ጋር ስለ ሃይማኖት የታሠሩ ብዙዎች ቅዱሳን ሰማዕታት ነበሩ ከእሳቸውም በወህኒ ቤት ጥቂቶች እስከቀሩ ድረስ ያ ከሀዲ መኰንን ብዙዎቹን አውጥቶ አሠቃይቶ ንጹሕ ደማቸውን በማፍሰስ ፈጃቸው።
1 161
#ቅዱስ ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል (3) ነብሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
#አዝ
አንተ ስለሆንክ ሚካኤል
የአምላክ ባለሟል ሚካኤል
ልመናቅ ፈጥኖ ሚካኤል
ካምላክ ይቀርባል ሚካኤል
የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (2)
#አዝ
ደዌ የጸናበት ሚካኤል
ባንተ ይድናል ሚካኤል
በአደባባይህ ሚካኤል
ምስክር ሆኗል ሚካኤል
ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ
በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ (2)
#አዝ
ካምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል
ክብርህ ያበራል ሚካኤል
ለጎስቋላው ሰው ሚካኤል
መጠጊያ ሆኗል ሚካኤል
ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ
ለምኖ አግኝቷል ካምላክ በስሙ (2)
#አዝ
በብሉይ ኪዳን ሚካኤል
ከአምላክ ተልከህ ሚካኤል
ሕዝበ እስራኤልን ሚካኤል
ነጻ ያወጣህ ሚካኤል
በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ
በተአምራትህ ትፈውሳለህ (2)
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
1 161
#ይበራል በክንፋ
ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2)
#አዝ
ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ
እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ
ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ
ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ
#አዝ
በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ
ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ
#አዝ
በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን
ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን
የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ
እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ
#አዝ
ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር
ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር
ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ
ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ
#አዝ
ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ
መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ
የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ
በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ብዙ ልጆች አሉት
ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለፍፁም ምልጃው ለኔግን ይለያል
መላኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል
#አዝ......
ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
#አዝ.......
ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
#አዝ.........
በባህራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
#አዝ........
በጉዞ የረዳቹ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላቹ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
#አዝ.......
ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰልኝ
ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰልኝ
ኦ ከሳሼን ረግጦ አዋረደልኝ
ክንፉን ቀጥ አድርጐ ዙሪያየን ሰፈረ
የጠላቴን መንገድ ወጥመድ ሰባበረ (2 )
#አዝ........
ሌጌዎን መከረኝ በሐሰት እንድቆም
ሊያሳየኝ ፈልጐ የሙሴን መቃብር
አይጠቅመኝምና ሰወረዉ ሚካኤል
ፈርቶ ተመልሷል ተዋርዶ ሳጥናኤል (2 )
#አዝ.......
ጽድቅን አስተማረኝ ሀጢአትን ሳበዛ
ነፍሴ እንዳትኮነን በበረት ተይዛ
ወደ ህይወት መንገድ ይዞ እየመራኝ
የመዳኔን እራስ ጌታን አሳየኝ ( 2 )
#አዝ.......
ከታናሽነቴ ተግቶ የጠበቀኝ
ከአጋንንት እስራት ምልጃ የታደገኝ
ዛሬም አለ ጐኔ በጐልማሳነቴ
የልቤ ብርሀን ነው ሚካኤል አባቴ ( 2 )
#አዝ.......
ፀጋዬ እንዳይጐድል ጠላት እንዳይረግመኝ
ተራዳኢው መልአክ ከፊቴ ቆመልኝ
በአህያ አንደበት ነቢዩን ገሰፀው
እብደቱን አግቶ ከመንገድ መለሰው ( 2 )
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ይትለዓል መንበሩ
ይትለዓል መንበሩ /3*/
ሚካኤል ይትለዓል መንበሩ /2*/
#ትርጉም
የሚካኤል ስልጣኑ ከፍ ከፍ ይላል
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#አርአዮ ለሙሴ
አርአዮ ለሙሴ አርአዮ ለሙሴ
ግብራ ለደብተራ ለደብተራ ለደብተራ ግብራ ለደብተራ
#ትርጉም
ለሙሴ ታየው ድንኳኑንም ሠራ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ሚካኤል እም መላእክት(ግእዝ ቸብቸቦ)
ሚካኤል እም መላእክት መኑ ከማከ ልዑል
አስተምህር ለነ ሰአልናከ በአሥርቱ ወአርባእቱ ትንብልናከ
አዝ
ዓይኖ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ
አዝ
ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመፅእ ሥርየት ለኃጥአን
አዝ
መኑ ከማከ ልዑል መኑ ከማከ ክቡር
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
