ሰዋስው ☘☘☘☘
الذهاب إلى القناة على Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
إظهار المزيد1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 161
በፍልሰታ ጾም #ነሐሴ_፩ ቀን
በቅዳሴ ግዜ
#ምንባባት
፩ቆሮ ም፰ቊ፩-ፍጻሜ
፩ጴጥ ም፬ቊ፩-፯
ግብ ሐዋ ም ፳፮ ቊ፩-፳፰
#ምስባክ
እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ።
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።
ወውእቱ ልዑል ሣረራ።
#ትርጉም
ሰው ጽዮንን እናታችን ይላታል
በውስጧም ሰው ተወልደ
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት
#ወንጌል
የማቴዎስ ወንጌል ም ፲፪ ቊ፴፰ -ፍጻሜ
#ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
1 161
ሱባዔ ለምን?
#ክፍል_ሁለት
የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡
በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡
ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡
እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡
ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡
ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡
አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡
ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡
ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡
ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡
#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት?
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
https://t.me/Eotcw
1 161
ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ
ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡
ሱባዔ ምንድን ነው?
ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡
ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ሱባዔ መቼ ተጀመረ?
ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡
#ይቀጥላል ....
በቀጣይ ሱባዔ ምንድን ነው ጥቅሙ?
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
https://t.me/Eotcw
1 161
+++''ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር''+++
ፍልሰታ የሚለው ቃል “ፈለሰ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፣ ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ጾመ ፍልሰታ ወይም ጾመ ማርያም ከ7ቱ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነ እና የዓመቱ የመጨረሻ ጾም ነው፡፡
ጾም የሚለው ቃል ጾመ ከሚለው የመጣ ሲሆን መከልከል መታቀብ ማለት ነው፡፡ ጾም የተጀመረው ትርጉሙ መከልከል እስከሆነ ድረስ አዳም ከዕፀ በለስ እንዳይበላ በተከለከለ ጊዜ እየጾመ ነበር ማለት ነው፡፡ ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይኾን ከክፉ ተግባር ዅሉ መቆጠብ ጭምር ነው፡፡ ሠለስቱ ምዕትም “ጾምሰ ተከልኦተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ ዕውቅ በውስተ ሕግ - ጾምስ በታወቀው ሰዓት፣ በታወቀው ዕለት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው” በማለት የጾምን ትርጕም ያስረዳሉ ፍትሐ ነገሥት፣ አንቀጽ 15
ጾም የጸሎት መፍለቂያ ምንጭ ነው ለዚህም ቅዱስ ያሬድ “በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት፣ ወይደመሰስ ኩሉ ጌጋይ - በጾም እና በጸሎት ኃጢአት ይሠረያል፣ በደልም ሁሉ ይደመሰሳል” እንዳለ፡፡
እውንተኛ ጾም የውስጣዊ ንጽህናና የመንፈሳዊ እድገት ምልክት ነው፡፡ ጾምህ በእርግጠኝነት ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስህ መንገድ መሆኑን የምታምንበት ይሁን፡፡ ክርስቶስ እንኳን ስራውን የጀመረው በጾም ነው ስለምን ቢሉ ጾም የትሩፋት መሠረት ነውና “እማ ለጸሎት ወእኅታ ለአርምሞ ወነቅዓ ለአንብዕ ወጥንተ ኩሉ ገድል ሠናይት - ጾም የጸሎት እናት የአርምሞ እኅት የእንባ ምንጭ የመልካም ተጋድሎ ሁሉ መሠረት ናት” እንዳለ ማር ይስሐቅ
ዳግመኛም ጾም ማለት እየከፈሉ ለነዳያን እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ እያደለቡ መብላት ነው፡፡ አይረባም ፤ “በምትጾምበት ጊዜ ምሳህን አውጥተህ ስጥ፡፡ አንተም ሲመሽ ተመገብ ይህች ዓይነቱ ጾም ትጠቅምሀለች” ሄሮማ
ጾምን፣ ጸሎትን ምጽዋትን ሰውሮ ያደርጓል እንጂ ለውዳሴ ከንቱ እንዳይሆን ልብን ዋዛ ፈዛዛ አያደርጉትም፡፡
“ጾም የምግባራት ሁሉ እናት ናት ምጽዋት እና ጸሎትም ልጆቿ ናት ሦስቱም ሐገራቸው አንድ ነው” ርቱዓ ሃይማኖት
“በጾም ትትፌወስ ቁስለ ነፍስ - ጾም የነፍስን ቁስል ትፈውሳለች” ቅዱስ ያሬድ እንዲሁም ጾም በደልን ይቅር ለማስባል ትጠቅማለች “ወሀበነ ጾመ ለንስሓ በዘይሰረይ ኃጢአት፤ ኃጢአት የሚሠረይበትን ይቅር የሚባልበትን ጾምን ሰጠን” እንዲል
እስኪ ወደ ርዕሳችን እንመለስ ''ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር'' ማይሆን ነገር ነው፤ ነገር ግን በእመቤታችን ተከናውኗል ከሁሉ በላይ የእመቤታችን ሞት ያስገርመኛል ልጇስ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል ሞት ግድ ሆነ እመብርሃንስ መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን - ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ እንዴት ትሞታለች ይህስ ድንቅ አይደለምን ቅዱስ ያሬድም “ሞትስ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኩሉ - ሞት ለሟች ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል” በማለት ተደንቋል
ይልቁንም አበው “ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ - የማርያምስ ሞት ሠርግ ይስላል” ብለዋል እንጂ እንባ የሚለቀስለት ሙሾ የሚወረድለት አይደለም፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን አስቀድሞ አባቷ ቅዱስ ዳዊት “ተንስእ እግዚኦ ውስተ እረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ - አቤቱ ወደዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት” እንዳለ
በጥር 21 ዕለት ዕረፍቷም ብዙ ተአምራት አደረገች የታውፋንያም አንዱ ነው እመብርሃን ስታርግ ቶማስ በደመና ላይ እንዲያያትም አድርጋ ነበር ስትሞት አልነበረምና እንዳያዝን መግነዟን ሰተዋለች፡፡ ከሐዋርያትም ደርሶ መሞቷን ቢነግሩት ካላየሁ አላምንም አላቸው አንተስ መጠራጠር ልማድህ ነው ብለው ቢከፍቱ ስጋዋን አጡት እርሱም ያየውን ነገራቸው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ቶማስም የእርሷን ስጋ ከሐገረ እስያ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ተመለከተ፡፡ ሐዋርያትም አዘኑ ነሐሴ በባተ በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ፤ ነሐሴ 14 ቀን ሁለት ሱባዔ ሲጨርሱ ሥጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው በጥር ሞታ በነሐሴ በጌቴሴማኔ ቀበሯት፡፡
ይህ የሱባዔ ወቅትም በክረምት በመሆኑ ሱባዔ ይዘን እመቤታችንን እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ ብለን አመስግነን፤ እንደ ቅዱሳን አባቶች ሰአሊ ለነ ቅድስት በማለት ለምነን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስን የምናገኝበት ልዩ ወቅት ነው፡፡ ይህ ጾም ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገውም ምስጋና ቀንም ሆነ ሌሊት ሳይቋረጥ የአባ ጊዎርጊስ ሰዓታት፣ የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ፣ የአባ ህርያቆስ ቅዳሴ ማርያም በጥልቀት የምንሰማበት የሚተረጎምበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡
“ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የመሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም' በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማኅፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
“በእርሱ ምክንያት ሰማይ ተብላ የተጠራችበት የሚመስለው የሌለ የማኅፀንዋ ፍሬ ለመሞትና ለመቀበር ፈቃደኛ ከሆነ ያለ ዘር የወለደችው እናቱ እንዴት ሞትን ትፈራለች” ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ The life of Virgin mary
ይህንንም ጾም ስንጾም እንደድሮው ስብሐት እና አቡነን በአንድ ሚያስብል አጎራሳችንን ትተን ምግብ ዋዛ ፌዝ ወሬ ቀንሰን ለነዳያን መጽውተን እንድንጾም አሳስባለሁ
ጾሙን ከህጻን እስከ ሽማግሌ የሚጾመው ነውና በሱባዔያችን መልስ እንዲሠጠን እንዲሁም በዚህ ጾም ራሳችንን ለውጠን ከኃጢአት አጥር ወጥተን ለሀገራችን ለኢትዮጵያም ትንሳኤዋን የሚገልጥበት ጾም ያድርግልን፡፡ እንኳን አደረሳችሁ መልካም ጾም
“በፍጹም ልባችሁ፣ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ” ኢዮ 2፡12
ዲያቆን የአ+++
2014 ዓም
ኢትዮጵያ
መልካም ጾም
1 161
ነሐሴ ፩
#ምንባባት
፩ጢሞ ም፭ቊ፩-፴፬
፩ዮሐም ፭ቊ፩-፯
ግብ ሐዋ ም፭ቊ፳፮-፴፬
#ምስባክ
መዝ፻፲፰÷፵፮-፵፯
ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት፤ ወኢይትኅፈር።
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ።
ወአንሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝ ዘአፍቀርኩ።
#ትርጉም፦
በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለው፥ አላፍርምም፤
እጅግም በወደድካቸው በትእዛዝህ ደስ ይለኛል።
እጄንም ወደ ወደድኳቸው ወደ ትእዛዝህ አነሣለሁ፤
#ወንጌል
የዮሐንስ ወንጌል ም፲፱ቊ፴፰-ፍጻሜ
#ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
1 161
ሰገደለት።
❤ ስሙ አብስኪሮን የሚባል አንድ ባለ ጸጋ ነበር የቤቱንም ግድግዳ አፍርሰው አዲስ ይሠሩለት ዘንድ ሠራተኞችን አመጣ ሥራቸውንም እስኪጨርሱ ከዚያ ይቆሙ ዘንድ ሁለቱን ልጆቹን አዘዛቸው። ከግርግዳውም ላይ በወጡ ጊዜ ግርግዳው ተደርምሶ ዐሥራ ስድስት ሰዎችና ሁለቱ ልጆቹ ሞቱ። ባለጸጋውም የሆነውን በአየ ጊዜ ልብሱን ቀደደ ጩኾም አለቀሰ ወደ ቅዱስ አቦሊም ሒዶ ከእግሩ በታች ሰገደለት እንዲህም አለው "ራራልኝ ሁለቱ ልጆቼ ሙተዋልና ከእነርሱም ጋራ ዐሥራ ስድስት ሰዎች ሞቱ። ከሞትም ብታሥነሣቸው እኔ በአምላክህ አምናለሁ"።
❤ ያን ጊዜም ቅዱስ አቦሊ ተነሣ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ስለ ቅዱስ ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ የመረጥከኝ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኒህ በሞቱ ሰዎች ላይ ኃይልህን ግለጥ። እኒህ ሰዎች ሁሉ እንዲአምኑ ያለ አንተም ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ከሞት አንሣቸው። ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን"።
❤ ከዚህም በኋላ የተገፈፈ ቆዳውን ወስዶ በሞቱት ሰዎች ላይም ዘረጋውና "በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሞት ተነሡ" አለ። ወዲያውም ሁሉም ድነው ተነሡ በዚያ ያሉ ሕዝብም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ "የክርስቲያን አምላክ የቅዱስ አቦሊም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው እኛም እናምንበታለን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለምና" እያሉ ጮኹ።
❤ ባለ ጸጋው አብስኪሮንም መጥቶ ለቅዱስ አቦሊ እንዲህ እያለ ሰገደ "ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ዛሬ አወቅሁ እኔም አምንበታለሁ። ከቤተሰቦቹም ሁሉ ጋር አመኑ መኰንኑም" ዐፈረ።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ አቦሊ ተገለጠለት እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው። "በመከራ ውስጥ ያለ ሰው በስምህ ርዳታ ቢለምን እኔ እሰማዋለሁ ልመናውን ፍላጎቱንም እፈጽምለታለሁ። በስምህ ቤተ ክርስቲያን ለሠራም እኔ በሰማያት ብርሃናዊ ማደሪያ ቤት እሠራለታለሁ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን ወይም የሚሰማውን እኔ በኪሩቤል ክንፎች ላይ ስሙን እጽፉለሁ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍም አሳርፈዋለሁ ተድላ ደስታ ካለባት ከገነት ፍሬዎችም እመግበዋለሁ። ብዙ ኃጢአትን ሠርቶ የበደለውንም በስምህ ወደኔ እየለመነ ንስሐ ቢገባ በደሉን ሁሉ ይቅር እለዋለሁ። ከጻድቃንም ጋርም እቈጥረዋለሁ ሰላሜም ካንተ ጋራ ይሁን" ይህንንም ብሎ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።
❤ መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ሥጋውም ከምስር ከተማ ውጭ ሕንቅ በሚባል ገዳም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አቦሊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 1 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኒቆዲሞስ ለወልደ ማርያም ዘአምኖ። ከመ እመኀበ አብ መጽአ ለምሕረት ወለአድኅኖ። በዕለተ ተሰቅለሂ እንዘ ይከድን ዕርቃኖ ለዮሴፍ ቢጾ ወሱታፌሁ ከዊኖ። ምስለ አፈዋት ገነዘ ወቀብረ በድኖ"። ትርጉም፦ ከአብ ዘንድ ለይቅርታና ለማዳን እንደመጣ ዐውቆ የማርያም ልጅን ያመነው ለኾነ ለኒቆዲሞስ ሰላምታ ይገባል፤ በተሰቀለ ዕለትም ዕርቃኑን እየሸፈነ ዮሴፍ ተባባሪውና ባልጀራውን ኾኖ ከሽቱ ጋር በመገነዝ በድኑን ቀበረ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ1።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለእየብቻቸው ለያያቸው ቅዱስ ዮስጦስን ወደ እንዴናው ከተማ ሚስቱን ታውክሊያን ፃ ወደ ሚባል አገር ልጃቸው አቦሊንም ብስጣ ወደ ሚባል አገር ሰደዳቸው ለእያንዳንዳቸውም የሚአገለግላቸው አንዳንድ አገልጋይ ሰጣቸው። ቅዱስ አቦሊም ወደ ሀገር ብስጣ በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፉት ታመነ። መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን በእሳት ቃጠሎና በመንኰራኵር አሰቃየው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ለአንበሶች ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ከሥቃዩ ሁሉ አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አነሣው።
❤ ብዙዎች ሰዎችም ስቃዩንና ዳግመኛ መዳኑን በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው ሰማዕታት ሆኑ። መኰንኑ ግን እጅግ ተቆጥቶ የቅዱስ አቦሊን ቆዳውን እንዲገፍፉትና ጨውና መጻጻን በማቅ አምጥጠው ቍስሉን እንዲያሹ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ ቆዳውን አሸክመው በከተማ ውስጥ ሁሉ አዞሩት ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ጸለየ "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ"። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጣ ሁለመናውንም ዳስሶ አዳነው። መኰንኑም በእርሱ ላይ የሚያደርገውን እስኪያስብ ከእሥር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ። ቅዱስ አቦሊም ቁሞ ጸለየ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና "የመረጥኩህ አቦሊ ሰላም ለአንተ ይሁን እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ" አለው ጌታችንንም በአየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው ክብር ይግባውና ለጌታችንም ሰገደለት።
❤ ስሙ አብስኪሮን የሚባል አንድ ባለ ጸጋ ነበር የቤቱንም ግድግዳ አፍርሰው አዲስ ይሠሩለት ዘንድ ሠራተኞችን አመጣ ሥራቸውንም እስኪጨርሱ ከዚያ ይቆሙ ዘንድ ሁለቱን ልጆቹን አዘዛቸው። ከግርግዳውም ላይ በወጡ ጊዜ ግርግዳው ተደርምሶ ዐሥራ ስድስት ሰዎችና ሁለቱ ልጆቹ ሞቱ። ባለጸጋውም የሆነውን በአየ ጊዜ ልብሱን ቀደደ ጩኾም አለቀሰ ወደ ቅዱስ አቦሊም ሒዶ ከእግሩ በታች ሰገደለት እንዲህም አለው "ራራልኝ ሁለቱ ልጆቼ ሙተዋልና ከእነርሱም ጋራ ዐሥራ ስድስት ሰዎች ሞቱ። ከሞትም ብታሥነሣቸው እኔ በአምላክህ አምናለሁ"።
❤ ያን ጊዜም ቅዱስ አቦሊ ተነሣ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ስለ ቅዱስ ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ የመረጥከኝ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኒህ በሞቱ ሰዎች ላይ ኃይልህን ግለጥ። እኒህ ሰዎች ሁሉ እንዲአምኑ ያለ አንተም ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ከሞት አንሣቸው። ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን"።
❤ ከዚህም በኋላ የተገፈፈ ቆዳውን ወስዶ በሞቱት ሰዎች ላይም ዘረጋውና "በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሞት ተነሡ" አለ። ወዲያውም ሁሉም ድነው ተነሡ በዚያ ያሉ ሕዝብም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ "የክርስቲያን አምላክ የቅዱስ አቦሊም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው እኛም እናምንበታለን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለምና" እያሉ ጮኹ።
❤ ባለ ጸጋው አብስኪሮንም መጥቶ ለቅዱስ አቦሊ እንዲህ እያለ ሰገደ "ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ዛሬ አወቅሁ እኔም አምንበታለሁ። ከቤተሰቦቹም ሁሉ ጋር አመኑ መኰንኑም" ዐፈረ።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ አቦሊ ተገለጠለት እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው። "በመከራ ውስጥ ያለ ሰው በስምህ ርዳታ ቢለምን እኔ እሰማዋለሁ ልመናውን ፍላጎቱንም እፈጽምለታለሁ። በስምህ ቤተ ክርስቲያን ለሠራም እኔ በሰማያት ብርሃናዊ ማደሪያ ቤት እሠራለታለሁ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን ወይም የሚሰማውን እኔ በኪሩቤል ክንፎች ላይ ስሙን እጽፉለሁ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍም አሳርፈዋለሁ ተድላ ደስታ ካለባት ከገነት ፍሬዎችም እመግበዋለሁ። ብዙ ኃጢአትን ሠርቶ የበደለውንም በስምህ ወደኔ እየለመነ ንስሐ ቢገባ በደሉን ሁሉ ይቅር እለዋለሁ። ከጻድቃንም ጋርም እቈጥረዋለሁ ሰላሜም ካንተ ጋራ ይሁን" ይህንንም ብሎ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።
❤ መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ሥጋውም ከምስር ከተማ ውጭ ሕንቅ በሚባል ገዳም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
❤ የዮስጦስ ልጅ ሰማዕቱ ቅዱስ አቦሊ፦ ይህም ቅዱስ አቦሊ ከመንግሥት ልጆች ውስጥ ነበር ዐላውያንን ወግቶ በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ አገኘው። ያም አቦሊና አባቱ ዮስጦስ ሌሎችም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን ሊያጠፉትና መንግሥትን ከእርሱ ሊወስዱ ችሎታ ሲኖራቸው የማታልፍ ሰማያዊት መንግሥትን አሰቡ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አቦሊ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አብዝቶ አባበለው። እንዲሁም አባቱ ዮስጦስንና የከበረች እናቱ ታውክልያን አባበላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም ልባቸው በመድኅን ክርስቶስ ፍቅር ተነድፏልና። ንጉሡም እነርሱን በዚያ ማሠቃየትን ፈራ ስለዚህም ከመልእክት ደብዳቤ ጋር ወደግብጽ ስሙ ኄርሜኔዎስ ወደሚባል የእስክንድርያ ገዥ ላካቸው በመልእክቱም እንዲህ አለው "ዮስጦስና ሚስቱ ታውክልያ ልጃቸው አቦሊም ወደአንተ በሚደርሱ ጊዜ አባብላቸው አለዚያም እየአንዳንዳቸውን ለያያቸው"።
❤ በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዮስጦስና ለሚስቱ ታውክልያ ለልጃቸው አቦሊም ተገልጦላቸው አጽናናቸው ከእነርሱም የሚሆነውን ነገራቸው የጸና ቃል ኪዳንም ሰጣቸው። ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስም በደረሱ ጊዜ ስለእነርሱ እጅግ አደነቀ እነርሱ መንግሥታቸውን ትተዋልና ክፋ ነገርንም ሊናገራቸው አልደፈረም ከምክራቸው ይመለሱ ዘንድ በለሰለሰ ቃል ሸነገላቸው እንጂ ነገር ግን አልሰሙትም።
❤ ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለእየብቻቸው ለያያቸው ቅዱስ ዮስጦስን ወደ እንዴናው ከተማ ሚስቱን ታውክሊያን ፃ ወደ ሚባል አገር ልጃቸው አቦሊንም ብስጣ ወደ ሚባል አገር ሰደዳቸው ለእያንዳንዳቸውም የሚአገለግላቸው አንዳንድ አገልጋይ ሰጣቸው። ቅዱስ አቦሊም ወደ ሀገር ብስጣ በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፉት ታመነ። መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን በእሳት ቃጠሎና በመንኰራኵር አሰቃየው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ለአንበሶች ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ከሥቃዩ ሁሉ አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አነሣው።
❤ ብዙዎች ሰዎችም ስቃዩንና ዳግመኛ መዳኑን በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው ሰማዕታት ሆኑ። መኰንኑ ግን እጅግ ተቆጥቶ የቅዱስ አቦሊን ቆዳውን እንዲገፍፉትና ጨውና መጻጻን በማቅ አምጥጠው ቍስሉን እንዲያሹ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ ቆዳውን አሸክመው በከተማ ውስጥ ሁሉ አዞሩት ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ጸለየ "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ"። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጣ ሁለመናውንም ዳስሶ አዳነው። መኰንኑም በእርሱ ላይ የሚያደርገውን እስኪያስብ ከእሥር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ። ቅዱስ አቦሊም ቁሞ ጸለየ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና "የመረጥኩህ አቦሊ ሰላም ለአንተ ይሁን እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ" አለው ጌታችንንም በአየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው ክብር ይግባውና ለጌታችንም
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የተባረከው የነሐሴ ወር የቀኑ ሰዓት ዐሥራ ሦስት ነው ከዚህም በኋላ ይጎድላል።
❤ ነሐሴ ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም፣ ጌታችንን ለገነዙ ለአምላካዊ ምሥጢር አገልጋዮች ለሆኑ ለተገባቸው ለከበሩ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ ለመታሰቢያ በዓላቸውና ለታላቁ ሰማዕት ለዮስጦስ ልጅ ለቅዱስ አቦሊ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ አምላክን ከወለደች ከእመቤታች ከድንግል ማርያም እናት ከቅድስት ሐና ከመታሰቢያዋ፣ ከፋኑኤል ልጅ ከነቢይት ሐና ከመታሰቢያዋና ከንግሥት ሶፍያ ልጆች ከቅዱሳን ደናግል ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "በጾም ወበጸሎት ወበምጽዋት ወበተፋቅሮ ይሰረይ ኃጢአት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም"።
ትርጉም፡- በጾምና በጸሎት በምጽዋት በመፋቀርም ኃጢአት ይወገዳል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሴፍ ወኒቆዲሞስ እለ አምጽኡ አፈወ ከርቤ ወዐልወ ወበልብሰ ገርዜን ሐዲስ፤ እለ ገነዝዎ ለክርስቶስ፤ እለ ገሰሱ ሥጋሁ ወእለ ሰዓሙ አፉሁ"። ትርጉም፦ ከርቤ፣ ሽቱ፣ የሽቱ ወገን የሚኾን ዋግራ አምጥተው አዲስ ለኾነ በፍታ ክርስቶስን የገነዙት፤ ሥጋውን ዳስሰው አፉን የሳሙት ለኾኑ ዮሴፍና ለኒቆዲሞስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ፦ በፈቃዱ መከራ ተቀብሎ ስለ ደኅንነታችን በሞተ ጊዜ የደኅንነታችንንም ምሥጢር በፈጸመ ጊዜ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ እነርሱ ከመስቀል ላይ አውርደዋልና። የአይሁድም መገርመም ከጲላጦስ ዘንድ የመድኃኒታችንን ሥጋ እስከ ለመኑ ድረስ አላስፈራቸውም።
❤ ጲላጦስም በፈቀደላቸው ጊዜ የእጆቹንና የእግሮቹን ችንካሮች ነቅለው ከመስቀል አውርደው በትክሻቸው ተሸከሙት ሲገንዙትም እንዲህ የሚል ቃል ከበድኑ ሰሙ። "ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በዮርዳኖስ የተጠመቀ በእንጨት መስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ በክብር ወደ ሰማያት ያረገ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ የሚመጣ አቤቱ ይቅር በለን። ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን አሜን ይሁን ይሁን። ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ይቅር በለን"።
❤ ይህንንም በሰሙ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖታቸው ጸናች። ዮሴፍም በፍታ ኒቆዲሞስም ሽቶዎችን አምጥተው ጌታችንን ገነዙት በአዲስ መቃብር ውስጥም ቀበሩት።
❤ ይህ ዮሴፍም ለሰማዕታት መጀመሪያ ለእስጢፋኖስ ዘመድ ለሆነው ለቀለዮጳ ወንድሙ ለኒቆዲሞስ ዘመዱ ነው ኒቆዲሞስም የአይሁድ አለቃ ፈሪሳዊ ነበር እርሱም ወደ ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ በሌሊት የሔደና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣ ያመነ ነበር። ጌታችንም ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንደማይችል የነገረው ነው።
❤ ይህ ኒቆዲሞስም የጌታችንን ቃል በሚአቃልሉ ጊዜ አይሁድን ይገሥጻቸው ነበር። ከተነሣ በኋላም በኢማሁስ መንገድ ሲሔድ ጌታችን ኢየሱስ የተገናኛቸው እሊህ ኒቆዲሞስና ቀለዮጳ ናቸው። እነርሱም ሳያውቁት በእርሱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገሩት። እርሱም ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ አስተማራቸው።
❤ ከዘህም በኋላ እርሱ መሆኑን ባወቁት ጊዜ ተሠወራቸው እነርሱም ተመልሰው ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩ። ክብር ይግባውና የጌታችንን ሥጋ ስለ ቀበረ ሊገድሉት ፈልገው አይሁድ ዮሴፍን በወህኒ ቤት አሠሩት። የወህኒ ቤቱም በር በሊቃነ ካህናቱና በጲላጦስ ማኅተም ተቆልፎ ሳለ ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ዮሴፍ ወደ አለበት ገባ ከእርሱ ጋርም እልፍ አእላፋት መላእክት ነበሩ። ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው በፊቱ ያጥናሉ በቀኝ በኩል ተሰቅሎ የነበረ ወንበዴውም ብሩህ ልብስ ለብሶ በቀኝ ቁሞአል ባለሟልነትን በልዑል ፊት አግኝቶአልና ስለ ኃጢአተኞች ይማልድ ነበር።
❤ የወህኒ ቤት ጠባቂዎችም በአዩ ጊዜ ደነገጡ ፈርተውም መንቀጥቀጥ ያዛቸው ጌታችንም ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው "ከአይሁድ ግርማ የተነሣ አትፍራ ከማሠሪያህ ልፈታሕ እኔ መጣሁ አንተ መከራዬን የተሳተፍከኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ አኔ ጌታህና የዓለሙ ሁሉ ጌታ እንደሆንሁ ፈጽመህ ታውቅ ዘንድ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን የተወጋ ጐኔንም እይ"።
❤ ከዚያም ዮሴፍን ነጥቆ ወደ አገሩ አርማትያስ ወሰደው። የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎችም ሔደው ጌታችን ያደረገውን ሁሉ ዮሴፍንም ይዞ ከእርሱ ጋር እንደወሰደው ለካህናት አለቆች ነገሩ። የካህናት አለቆችም በሔዱ ጊዜ የወህኒ ቤቱ በር ተቆልፎ አገኙ እሽጉም አልተለወጠም ነበር። እሊህ ቅዱሳንም ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን እየሰበኩ ኖሩ ብዙ መከራም አገኛቸው። ከዚህም በኋላ በሰላም ዐረፉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ የዮስጦስ ልጅ ሰማዕቱ ቅዱስ አቦሊ፦ ይህም ቅዱስ አቦሊ ከመንግሥት ልጆች ውስጥ ነበር ዐላውያንን ወግቶ በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ አገኘው። ያም አቦሊና አባቱ ዮስጦስ ሌሎችም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን ሊያጠፉትና መንግሥትን ከእርሱ ሊወስዱ ችሎታ ሲኖራቸው የማታልፍ ሰማያዊት መንግሥትን አሰቡ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አቦሊ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አብዝቶ አባበለው። እንዲሁም አባቱ ዮስጦስንና የከበረች እናቱ ታውክልያን አባበላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም ልባቸው በመድኅን ክርስቶስ ፍቅር ተነድፏልና። ንጉሡም እነርሱን በዚያ ማሠቃየትን ፈራ ስለዚህም ከመልእክት ደብዳቤ ጋር ወደግብጽ ስሙ ኄርሜኔዎስ ወደሚባል የእስክንድርያ ገዥ ላካቸው በመልእክቱም እንዲህ አለው "ዮስጦስና ሚስቱ ታውክልያ ልጃቸው አቦሊም ወደአንተ በሚደርሱ ጊዜ አባብላቸው አለዚያም እየአንዳንዳቸውን ለያያቸው"።
❤ በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዮስጦስና ለሚስቱ ታውክልያ ለልጃቸው አቦሊም ተገልጦላቸው አጽናናቸው ከእነርሱም የሚሆነውን ነገራቸው የጸና ቃል ኪዳንም ሰጣቸው።
ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስም በደረሱ ጊዜ ስለእነርሱ እጅግ አደነቀ እነርሱ መንግሥታቸውን ትተዋልና ክፋ ነገርንም ሊናገራቸው አልደፈረም ከምክራቸው ይመለሱ ዘንድ በለሰለሰ ቃል ሸነገላቸው እንጂ ነገር ግን አልሰሙትም።
1 161
❤ ከዚህም በኃላ የአራዊትን ጠባይ ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት ክብር ይግባውና ጌታችንም ይህን የአራዊት ጠባይ አራቀላቸው። ሰዎች የሚመገቡትንም የሚመገቡ የዋሆች ሆኑ። አባቶቻችን ሐዋርያትም ብዙ ተአምራትን አደረጉ በሽተኞችን ሁሉ ፈወሱ ከዚህም በኃላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ግሪክ አገር ተመለሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁንእኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ቅዱስ እንድርያስና በቅዱስ ማትያስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእርሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ኤጲስ ቆጶሳት ከክርስቲያን ወገኖችም ሁሉ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ብልጽግናን ንቆ የተወ አባ ጳውሎስ፡- ይህም ቅዱስ ባለ ጸጋ ነበር። ደግ የሆነች ሚስትና የተባረኩ ልጆችንም ነበሩት፡፡ መነኰስ ሊሆን ወደደ ሚስቱንና ልጆቹንም ጠርቶ "እነሆ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር እሸጣችሁ ዘንድ ወደድኩ" አላቸው እነርሱም "አሳዳሪያቸን ነህና የወደድከውን አድርግ" አሉት።
❤ ከዚያም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ሚስቱንም ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት አመ ምኔቱንም ጠራትና እንዲህ አላት "ለገዳምሽ አገልጋይ ትሆን ዘንድ ሚስቴን ልሸጥልሽ አወዳለሁ" እርሷም "እሺ" አለችው የመሸጫዋንም ደብዳቤ ጻፈ የሺያጭዋን ዋጋ ተቀብሎ ለድኆች ሰጠ ልጆቹንም ወደ አበ ምኔቱ ወስዶ እንደ እናታቸው ሸጣቸው ለአበ ምኔቱም አሳልፎ ሰጣቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ ራሱንም ለገዳሙ አለቃ ሸጠ አለቃውንም "ወደ ቤተ ክርስቲያን ልገባ እሻለሁ" አለው፡፡ በገባም ጊዜ በሩን በላዩ ዘጋ። እጆቹን ዘርግቶ ቆመ በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብሎ ጮኸ "አቤቱ በፍጹም ልቡናዬ ወዳንተ እንደ መጣሁ፣ አንተ ታውቃለህ" ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ሀሳብህን ሁሉ አወቅሁ በፍጹም ልቤም ተቀበልሁህ"
❤ ከዚህም በኋላ ከመነኵሶ አስጨናቂ የሆኑ የገዳሙን ሥራዎች ሁሉ እንደ ባሪያ እየሠራ ኖረ ራሱንም ከሁሉ እጅግ አዋረደ ነገር ግን ስለ መዋረዱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው። ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ 30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውሎስ ጸሎት ይማሰን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕታት ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም፡- እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንድማማቾች በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ፡፡ በጾም በጸሎትና በስግደት በታላቅ እየተጋደሉ በገዳሙ ውስት ሃያ ዓመት ዓመት ያህል ኖሩ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕት ሊሠው ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ሊሠዉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ፡፡ እኒህ ቅዱሳንም አምላካዊ ቅንአትን ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተነኑት። እንዲህም አሏቸው "በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም"።
❤ ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንም ገረፏቸው ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖርዋቸው ከእነርሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መርቆሬዎስ ኤፍሬም ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
❤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ በሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት እንዲሁም በሁላችን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን። በሐምሌ ወር የሚነገበብ ንባብ ደረሰ ተፈጸ። እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 30 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ዕብል ለቤትከ ቅዳሴሃ። ድኅረ ፈጸመ በቊስጥንጥንያ ሕንፄሃ። ሱርያል ገሀደ ተአምሪከ አሜሃ። እምዘይት ማኅቶት ዘሥዕልከ ተቀቢዖ ሶቤሃ። ዐይነ ዕውረሰ በቅጽበት በርህ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 30።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይቤ ወመጽአ መንፈስ አውሎ። ወተለዓለ ማዕበል። የዐርጉ እስከ ሰማይ"። መዝ 106፥25-26። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥47-53።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እምውኂዝ እምሰጠት ነፍስነ። እምሰጠት ነፍስነ እማየ ሀከክ። ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክነ ዘኢያግብአነ ውስተ መሥገርተ ማዕገቶሙ"። መዝ 123፥4-5። 1ኛ ቆሮ 2፥1-9፣ 2ኛ ጴጥ 1፥12-17 እና የሐዋ ሥራ 3፥1-10። የሚነበበው ወንጌል ማር 4፥35-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሱርያል (እስራልዩ) ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት (ለቅዳሴ ቤቱ)፣ ለሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ አስገራሚ ተአምር በማድረግ ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስን ከእስር አስፈትቶ ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ላዳነበት፣ ክብርንና ብልጽግናን ንቆ ለተወ ራሱን ስለ ጽድቅ ለሸጠ ለቅዱስ ጳውሎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን ለገሊላ ሰዎች ለመርቆሬዎስና ለኤፍሬም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ጢሞቴዎስ ከምስር በአስቄጥስ ወደ አለወደ አባ መቃረስ ገዳም ከሥጋው ፍልሰት፣ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከት ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን የእስራልዩ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ይኸውም ቅዱስ ሱርያል መልአክ ነው። የቅዱስ ሱርያል አማላጅነቱና ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስ ተአምራትን አደረገ። እንድርያስ በጽርዕ አገር እያለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ እንዲህ አለው "ማትያስን ከእሥር ቤት ታወጣው ዘንድ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሒድ የዚያች አገር ሰዎች ከሦስት ቀን በኃላ ሊበሉት ያወጡታልና"። እንድርያስም ጌታችንን እንዲህ አለው "የቀረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ ነገር ግን ፈጥኖ የሚያወጣውን ከመላእክት አንድ ላክ እንጂ"።
❤ ጌታችንም ለእንድርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት "ስማ ሀገሪቱን ወደዚህ ነዪ ከልዃት በውስጧ ከሚኖሩ ሁሉ ጋር ትመጣለች አንተና ደቀ መዘሙሮችህ ግን ጠዋት በሆነ ጊዜ ተነሥታችሁ ወደ ባሕር ሒዱ የተዘጋጀ መርከብንም ታገኛላችሁ እርሱም ያደርስሃል" ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ በክብር ዐረገ። በነጋ ጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተነሥቶ ወደ ወደብ ደረሰ ጥሩ መርከብንም አየ ጌታችንንም በሊቀ ሐመር አምሳል አየው ጌታችን እንደሆነ አላወቀም "ሊቀ ሐመር ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን" አለው ጌታም "የእግዚእብሔር ሰላም ይደርብህ" አለው እንድርያስም ደግሞ "በዚህ መርከብ ወዴት ትሔዳለህ" አለው "ሰውን ወደ ሚበሉ ሰዎች አገር እሔዳለሁ" አለው እንድርያስም ሊቀ ሐመሩን "ወንድሜ ሆይ ከአንተ ጋር ትጭነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ" አለው ሊቀ ሐመሩም "እሺ" ብሎ ወደ መርከቡ አወጣቸው። በባሕሩ ላይም ሲጎዙ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ ብሎ ጠየቀው "ጌታህ ምን ኃይል አደረገ" እንድርያስም ጌታችን ከአደረጋቸው ተአምራቶች ይነግረው ጀመረ ጌታችን እንደሆነ አላወቀም ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ሐመሩ እነደሚአንቀላፋ ሰው ሆነ ያንጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተኛ በዚያን ጊዜም ጌታችን እንድርያስንና ሁለቱን አርድእቱን ይሸክሙአቸው ዘንድ መላእክትን አዘዛቸውና ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አኖሩዋቸው። እንድርያስም ከእነቅልፍ በነቃ ጊዜ መረከብን አላገኘም እጅግም አደገቀ ለደቀ መዛሙርቱም እንድህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ በመርከብ ውስጥ ከጌታችን ጋር ነበርን ግን አላወቅንም"።
❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ተነስቶ ጸለየ ክብር ይግባውና ጌታችንም በመልካም ጎልማሳ አምሳል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ወዳጄ እንድርያስ አትፍራ እኔ ይህን አድርጌአለሁና አንተ በሦስት ቀን አልደርስም ብለህ ነበር ስለዚህ በፍጥረት ሁሉ ላይ ኃይል እንዳለኝ የሚሳነኝምእንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንግዲህም ወደ ከተማው ገብተህ ማትያስን ከእሥር ቤት አውጣው ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሁሉ"።
❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተነሥቶ ወደ ከተማ ገባ ማትያስ ወዳለበትም እስር ቤት ሔደ። በደረሰም ጊዜ የወሀኒ ቤቱ ደጀ ራስዋ ተከፈተች በገባ ጊዜም ማትያስን ተቀምጦ ሲዘምር አገኘው እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሳጣጡ እንድርያስም ማትያስን "ከሁለት ቀን በኋላ አውጥተው እንደ እንስሳ አርደው ይበሉኛል አልክ አንተ በጌታችን ዘንድ ያየናትን ያቺን ምሥጢር ረሰሃትን በምንናገርበት ጊዜ ሰማይና ምድርን ይናወጣሉ" አለው። ማትያስም "ወንድሜ ሆይ እንሆ ይህን አወቅሁ ነገር ግን በዚች ከተማ ውስጥ ሥራዬን እንድፈጽም የጌታችን ፍቃድ እንደ ሆነ እኔ እናገራለሁ እርሱ ራሱ "እንሆ እኔ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እንኳችኋለሁ" ብሏልና ወደ ዚህም እሥር ቤት በጨመሩኝ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ጠራሁት እርሱም ሃያ ሰባት ቀን ሲፈጸም ወንድምህ እንድርያስን ወዳንተ እልከዋለሁ እርሱም ከእሥር ቤት ያወጣሃል ከአንተ ጋራ ያሉትን ሁሉ ያወጣችዋል ብሎ ገለጠልኝ እንሆም ደርሰሃል የምትሠራውን አስተውል" አለው።
❤ እንድርያስም ወደ እስረኞች በተመለከተ ጊዜ እንደ እንስሳ ሣር ሲበሉ አይቶ አዘነ አለቀሰም ሰይጣንንም ከሠራዊቱ ጋር አሠረው ከዚህ በኃላ አንድርያስና ማትያስ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ማለዱ እጆቻቸውንም በእሥረኞች ሁሉ ላይ ጫኑ አእምሮአቸውም ተመለሰ ከከተማው ውጭ ወጥተው በዚያ በአንድነት እንድቀመጡ አዘዙአቸው።
❤ እኒያ ሐዋርያትም የሚሆነውን ያዩ ዘንድ ወጥተው በሀገሩ ጎዳና ዳር ተቀመጡ የከተማው ሰዎችም እነደ ልማዳቸው የሚበሉትን ከእሥረኞቹ ውስጥ ሊአመጡ መጡ የእሥር ቤቱን ደጅ ክፍት ሆኖ አገኙ እሥረኞችም አልነበሩም ደነግጠውም "በእኛ የደረሰብን ምንድነው ወዮልን" አሉ ያን ጊዜም ሰይጣን በሰው መስሎ ሐዋርያት ይህን እንዳደረጉ ነገራቸው የአሉበትንም አመለከታቸው የከተማው ሰዎችም በመቀዳደም ሮጡ እንድርያስንና ማትያስንም ይዘው በከተማው ጥጋጥግ አስጎተቱአቸው በሌሊትም በእሥር ቤት ያሳድሩአቸው ነበር ሦስት ቀናትም እንዲህ አደረጉባቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ሰለ ከተማዋ ሰዎች ድኀነት ወደ እግዚአብሔር ጸለዪ ጸሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ በላዩ ምስል ወደአለበት የዕብነ በረድ ምሶሶ ቀርበው በመስቀልመ ምልክት አመተቡት እንዲህም አሉት "አንተ ምሶሶ ፍራ ከበታችህም እንደ ጥፋት ውኃ ያለ ብዙ ውኃን በዚች ከተማ ላይና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ላይ አውጣ" ያን ጊዜም ከምሶሶው ሥር ብዙ ውኃ መነጨ የከተማው ሰዎችንም ያሠጥማቸው ዘንድ ገነፈለ ሰዎችም ከከተማው ወጥተው ሊሸሹ ወድደው ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ያዙ ውኃውም በዝቶ ከበባቸው ማምለጥም አልቻላቸውም ውኃውም እስከ እስከ አንገታቸው ደረሰ ያን ጊዜም አለቀሱ እንዲህም አሉ "ወዮልን ይህ ሁሉ በእኛ ላይ የመጣው በእነዚህ በተመረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር አገልጋዮች ምክንያት ነው እኛም በአምላካቸው እናምናለን"።
❤ ቅዱስ እንድርያስም "የዕብነ በረደ ምሰሶ እንግዲህስ በቃህ እነሆ የጥፋት ጊዜ አለፈ" ያን ጊዜም ውኃው ተገታ ውኃውም እንደተገታ የከተማው ሰው አይተው ወደ ሐዋርያት ሔዱ ስለዚያች ከተማ ሰዎች ድኅነትም ቁመው እጆቻቸውን ዘርግተው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ አገኙአቸው ሐዋርያትን "ይቅር በሉን" ብለው ለመኑአቸው። ሐዋርያትም "በሕያው እግዚአብሔር እመኑ እንጂ አትፍሩ" አሏቸው ሐዋርያትም ሁለተኛ ጸለዩ በውኃ ስጥመት የሞቱትንም ሙታን አስነሡአቸው በዚያም ውኃ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበሏቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው። ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተምረው በቀናች ሃይማኖት አጸኑአቸው እንዲህም አሏቸው ያዘዝናችሁን ጠብቁ ከእናንተ በኃላ ለሚነሡ ልጆቻችሁም አስተምሯቸው።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፱ (29) ቀን።
❤ እንኳን ለሐዋርያው ለቅዱስ ታዴዎስ ከሶርያ አገር ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ሥጋው ለፍልሰት በዓልና ለሰማዕቱ ለቅዱስ ወረስኖፋ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት ከልደቱ (ከበዓለ ወልድ) ከወራዊ መታሰቢያ በዓል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን ከሶርያ አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስ የሥጋ ፍልሰት ሆነ። ይህ የሆነው ክርስቶስን የሚወድ ጻድቁ ንጉሥ ቊስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ነበር። በሱ ትእዛዝም የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስን ሥጋ አፈለሱ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሥጋውን በውስጡ አኖሩ።
❤ በዚችም ቀን አከበሩዋት ከእርሱም ብዙ የሆኑ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። እግዚአብሔር ምስስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ታዴዎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ዋርስኖፋ፦ ይህም ቅድስ አዋቂ ሃይማኖቱ የቀና የዋህና በገድል የተጠመደ ሰው ነበረ። ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በፈለጉት ጊዜ ከእርሳቸው ሸሸ ወደ አንዲት አገርም ደርሶ እግዚአብሔርን በሚወዱ ሁለት መነኰሳት ዘንድ አደረ። በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲ ታመን የሰማዕትነትንም አክሊል እንዲቀበል አዘዘው። በነቃም ጊዜ ለእኒህ ለሁለቱ ወንድሞች ያየውን ነገራቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ተስማሙ።
❤ ከዚህም በኃላ መኰንኑ ወደ አለበት ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃያቸው ከዚያም ሰንዑር ወደሚባል አገር እስከሚሔድ ድረስ በወህኒ ቤት ጨመራቸው።
የሚሔድበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወሰዳቸው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው በሚያሠቃያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ያጸናቸውና ቁስላቸውን ይፈውስ ነበር።
❤ ከዚህም በኃላ ፃ ወደሚባል አገር ወሰዳቸው። በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙዎች አማንያንንም ሰብስቦ ስለ አምልኮ ጣዖት የሚያዝዝ የከሃዲውን ንጉሥ ደብዳቤ አነበበላቸው። ይህም ቅዱስ ወርስኖፋ ተነሥቶ ያቺን ደብዳቤ ከአንባቢው እጅ ነጥቆ ቀደዳት መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እሳትንም እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ። ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን በእሳቱ እቶን ውስጥ ፈጸመ።
❤ እነዚህንም ሁለት ወንድሞች ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዝዞ ቆረጧቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ዋርስኖፋ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 29 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለልደትከ በአፈ ነቢያት ዘተዜነወ። እንበ ያርኁ ፍጹመ ድንግልና እሙ ዕጸወ። እንዘ ይሰድድ ጽልመተ ወእንዘ ያቈርር ሐወ። ናሁ ተረክበ መድኃኒነ ህልወ።ወከመ ዝናም ከዊኖ ፍንወ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የሐምሌ 29።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር የዐቅዐብ ኵሎ አዕፅምቲሆሙ። ወኢይትቀጠቀጥ አሐዱ እምውስቴቶሙ"። መዝ 33፥19-20። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
