ar
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

الذهاب إلى القناة على Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

إظهار المزيد
1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
፫ኛ ወረብ ከመ እንግር ኃይለ ዚአከ @EOTCW

፪ኛ ወረብ ጊዮርጊስ ግሩም @EOTCW

አመ ፯ለሕ ጊዮርጊስ ፩ኛ ወረብ ይቤሎ መድኃኒነ @EOTCW

ከእስመ ለዓለም-ሰላም @EOTCW

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 ሥርዓተ ማኅሌት ዘህዳር ጊዮርጊስ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCW ✨መልክዐ ሥላሴ ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ። ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ። ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ። ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ። ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ። @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብሕ ምሥጢረ ሥላሴ በዓይኑ ነጸረ ሃሌ ሉያ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ እምሰማዕታት ዘአልቦ ወምስለ ጊዮርጊስ በፍቅረ አምላኩ ተጋደለ ገድለ ኀየለ ወተቀደሰ አክሊለ። @EOTCW 🔸ነግሥ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ጻድቃን ይበውዑ ውስቴታ የዋሃን የዓዉዱ መሠረታ ሰማዕት ይቀውሙ ዓውደ በዕለተ ጊዮርጊስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። @EOTCW 🔸ነግስ፦ ሰላም እብል ለጊዮርጊስ ቅዱሱ፣ኅሩይ አንተ እምንስሱ ፣አስማተ ፅሁፍ በከተማ ርዕሱ፣ሰማእት ሀይለ በመንፈሱ፣ሰርጎ ሜላት ወርቀ ልብሱ፣ ዐየራተ ሠረረ ፈረሱ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ሶበ ይበዉዑ ሰማዕት በውስተ ስምዕ፤ ይፀውሩ ሠለስተ አስማተ፤ ወየአትቡ ገጾሙ በሥላሴ፤ ከመ ይማዕዎ ለእኩይ ሕሊና፤ በገድሎሙ ሰማዕት ወበትዕግሥቶሙ፤ አድምፁ ተስፋ። @EOTCW ✨መልክዐ ጊዮርጊስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ። ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ። ጥዑመ ዜና ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ። ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ። አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝሉፉ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ይቤሎ መድኃኒነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኩሉ ዘሐነፀ ቤተ ክርስቲያን በስምከ፤ አነ አሐንፅ ሎቱ፤ ማኅደረ ዘበሰማያት። @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ይቤሎ መድኃኒነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለጊዮርጊስ ፤ ኩሉ ዘሐነፀ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን በስምከ ✨መልክዐ ጊዮርጊስ ሰላም ለመዛርኢከ ከመ ቀስተ ብርት እለ ጸንዐ፣ ለረጊዘ በረምዐ እንበለ ምምዐ፣ጊዮርጊስ በለኒ ለጸውዖ ስምየ በዕለተ መርዐ፣ ነዐ ነዐ ውስተ ውሣጤ ጽርእ ነዐ፣ ፍቅረ ዚአየ ኢትቁም በአፍዐ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ጊዮርጊስ ግሩም በመንፈስ ቅዱስ ኅቱም፤ መዓዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም፤ ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም፤ በበዓልከ ባርከነ ዮም። @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ጊዮርጊስ ግሩም በመንፈስ ቅዱስ ኅቱም፤ መዓዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም ጊዮርጊስ ግሩም @EOTCW ✨መልክዐ ጊዮርጊስ ሰላም ለአዕጋሪከ ዘተሞቅዐ ከመ አብድ፣በርኀወተ ዓቢይ ጒንደ፣ ገባሬ መንክራት ጊዮርጊስ በአቊጽሎ ይቡስ አምድ፣ ከመ እንግር ሐይለ ዚአከ ለዘይመጽህ ነገድ፣ ተራድዐኒ በገአድ አብ ለወልድ። @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ከመ እንግር ሐይለ ዚአከ ለዘይመጽህ ነገድ፣ ተራድዐኒ ተራድዐኒ በገአድ አብ ለወልድ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ ሙታነ አንሳእከ በሥልጣነ አቡከ ሰናይ ገድለ ተጋድልከ @EOTCW ✨መልክዐ ጊዮርጊስ ተወከፍ ሰላምየ ዘንተ ስብሐት ወይባቤ፣ከመ ጼና ስኂን ወመአዛ ከርቤ ፣ጊዮርጊስ ኩነኒ በኪዳንከ ዐቃቤ፣አንተ ምስካይየ በጊዜ ምንዳቤ፣ ተሰጥው ቃልየ ወሰልጥ ዘይቤ። @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ተወከፍ ጸሎቶሙ ለአግብርቲከ ወለአዕማቲከ፤ እለ ፃመዉ ወመጽኡ ጽርሐ መቅደስከ ኀበ የኃድር ኃይለ ስብሐቲከ። @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ተወከፍ ጸሎቶሙ ለአግብርቲከ ወለአዕማቲከ፤ እለ ፃመዉ ወመጽኡ ጽርሐ መቅደስከ ጊዮርጊስ ሰማእት @EOTCW @EOTCW ❄️ምልጣን ትቤሎ ብእሲት መበለት ፤ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አምላኮሙ ለክርስቲያን ተመሲሎ ሰብዐ መጽአ ሀቤየ፤ ወይቤላ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አንሰ ኢኮንኩ አምላክ ፤ አላ ገብረ አምላክ አነ @EOTCW ❣❣ወረብ፦ አምላኮሙ ለክርስቲያን ተመሲሎ ሰብዐ መጽአ ሀቤየ ወይቤላ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አንሰ ኢኮንኩ አምላክ አላ ገብረ አምላክ አነ @EOTCW 🔹እስመ ለዓለም ውእተ አሚረ ይውዕዝ ማየ ህይወት እምእየሩሳሌም፤ ውእተ አሚረ ይነግስ ሎሙ ለሰማእት፤ ፩ደ እግዚአብሔር ወአሀዱ ስሙ፤ ውእተ አሚረ ይሁቦሙ አዕቦሙ ዘአሰፍዖሙ ፤ማ፦ እለ በእንቲአሁ፤መጠዉ ነፍሶሙ መንግስተ ክብር ይደልዎሙ @EOTCW 🧩🔹አመላለስ፦ እለ በእንቲአሁ መጠዉ ነፍሶሙ፤ መጠዉ ነፍሶሙ መንግስተ ክብር ይደልዎሙ @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ውእተ አሚረ ይነግስ ሎሙ ለሰማእት እግዚአብሔር ዐሀዱ እግዚአብሔር፤ እለ በእንቲአሁመጠዉ ነፍሶሙ መንግስተ ክብር ይደልዎሙ @EOTCW 🔹❣ወረብ አዲ፦ ውእተ አሚረ ይውዕዝ ማየ ህይወት ማየ ህይወት እምእየሩሳሌም፤ ይነግስ ሎሙ ለሰማእት ዐሀዱ እግዚአብሔር ወዐሀዱ ስሙ https://t.me/Eotcw # Join & share 🧩

አመ ፯ለሕ ቅ/ጊዮርጊስ ዚቅ በዜማ @EOTCW

አመ ፯ለሕ ቅ/ጊዮርጊስ ከዋዜማ-ሰላም @EOTCW

🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵 አመ ፯ ለህዳር ቅ.ጊዮርጊስ ዋዜማ 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 በከመ ይቤ ነቢይ እንባቆብም፤ እግዚአ ሰማዕኩ ድምፅከ ወፈራዕኩ ፤ርኢኩ ግብርከ ወለንከሩከ፤ትቤሎ ብእሲት መበለት ፤ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ተሊወ እግዚአብሔር ይኄይሰኒ ፤ ኢአይኩ ቤትየ ኃደጉ ትርሲትየ፤ ማ፦ ኢትዕፅወኒ በመንግሥተ ሰማያት @EOTCW 🔹አመላለስ፦ኢትዕፅወኒ በመንግሥተ ሰማያት @EOTCW 💎ለእ/ር ምድር፦ ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር ሰአል ለነ ጊዮርጊስ @EOTCW 💎እ/ር ነግሠ፦ ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ ሙታነ አንሳእከ በሥልጣነ አቡከ ሰናይ ገድለ ተጋድልከ @EOTCW 🔸ይት፦ ጊዮርጊስ ሀያል መስተጋድል እስመ ክርስቶስ ዐበሣ ዘይሠሪ፣ ለቡ ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ አንተ ጊዮርጊስ @EOTCW ✴️ሰላም፦ ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ሰናይ ገድለ ተጋድልከ አምደ ቤትየ ዘአቋፀልከ ፤ሰላም ለከ ጊዮርጊስ @EOTCW 🔹አመላለስ፦ አምደ ቤትየ ዘአቋፀልከ ፤ሰላም ለከ ጊዮርጊስ ሰላም ለከ https://t.me/Eotcw # Join & share #

አብሬሽ ልመለስ ድንግል አዛኝቱ እንኳን ለእመቤታችን ለጉስቋም ማርያም ለዓመት ክብሯ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን 💚💛❤ ህዳር 6 በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤ 💚💛❤ ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ 💚💛❤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው"ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤ 💚💛❤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል። 💚💛❤ በቃል ኪዳን እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል። 💚💛❤ እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤ 💚💛❤ በ400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው ፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤ 💚💛❤ በዚያን ጊዜ በተለይ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ፀሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤

photo content

በዓለ ደብረ ቁስቋም እንኳን አደረሳችሁ ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳ የህጻኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነስ እናቱን እና ህጻኑን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ ማቴ 2፤20 እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ጋር ከስደት ወደ ሀገሯ የተመለሰችበት ቀን ነው ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭) የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡ እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡›› ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም) ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡ ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም በመምህር ተስፋ ሚካኤል፤ ፳፻፫ ዓ.ም. @..,

photo content

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ 6፥ 5-16 - "ወሶበሂ ትጼልዩ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን" - ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.38 KB

6/3/2015 ዓ.ም (፮/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት። ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ። እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ። መዝ 78 ፥ 8 🕯 ትርጉም የቀደመው በደላችንን አታስብብን። ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን። እጅግ ተቸግረናልና። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ 22፥14-24 - "ወሶበ ኮነ ጊዜሁ ረፈቀ ኢየሱስ" -ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ። እርሱም ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤ እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው። ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም። ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት፤እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም አለ። እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ። ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ እጅ እነሆ በማዕድ ከእኔ ጋር ናት። የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል፥ ነገር ግን አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት። ከእነርሱም ይህን ሊያደርግ ያለው ማን እንደ ሆነ እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ጀመር።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.53 KB

6/3/2015 ዓ.ም (፮/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ። ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር እጉሊሃ። ምሥዋዒከ እግዚኦ እግዚአ ኃያላን፡፡ መዝ. 83፥3 🕯 ትርጉም ወፍ ለእርሷ ቤትን አገኘች። ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ቤት አገኘች። የሰራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ እርሱ መሠዊያህ ነው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content