ሰዋስው ☘☘☘☘
الذهاب إلى القناة على Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
إظهار المزيد1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 161
ኪዳነ ምህረት
🖊 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡
🖊እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡
🖊እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡
🖊ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡
🖊ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9 : 16
🖊በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለ
እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!
https://t.me/Eotcw
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢ ˢʰᵃʳᵉ
1 161
የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ በቃል ኪዳንሽ ክንፍ ሰውረሽ ከኩነኔ አድኚኝ ቃል ኪዳንሽ የማዳን ስልጣን ባይኖረውስ የበላዔ ሰብዕ ነፍስ መዳን ባልተቻለው ነበርና
መልክዐ ኪዳነ ምህረት
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ ላአዘዘበት ዕለትና መልካም ሽምግልና ላለለው ስም አጠራሩ ለከበረ በገዳም ለሚኖርና በገድል ለተጠመደ ለስልሳ ዓመት ብቻው ሰው ሳያይ ለኖረ አባት ለላይኛው ግብጽ ሰው ለአባ አቡናፍር ዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ የአባ አቡናፍርን ገድል ከተናገረ ከአባ በፍኑትዮስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ። ወኢትጎንድዪ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ። በላዕሌኪ አልቦ ዘያመጽእ ሁከተ። ለወልድኪ ዘየኀሥሥ ይእዜሰ ሞተ። በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ"። ትርጉም፦ እመቤቴ በአንቺ ላይ ሁከትን የሚያመጣ የለም ቤት እንደሌለሽ በግብፅ አገር አትዘግዪ መልአክ ለዮሴፍ የምሥራችን እንደ ነገረው አሁንስ ልጅሽን ሊገድለው የሚፈልገው ኄሮድስ ሞቷልና ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሺ። ሰቆቃወ ድንግል።
+ + +
❤ አባ አቡናፍር፦ የዚህም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቊጥሩ ከገዳማውያን ነውና። አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ።
❤ በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጒሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያት ጸለየ ከዚህም በኋላ "አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" አለው ይህንንም በማለት ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት።
❤ ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ። ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ በዚያ በረሀ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው። አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኰሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ "እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን?" አልኳቸው እነርሱም "አወን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው" አሉኝ። ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ። ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳምውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚች ምንጭ እጠጣለሁ በዚች በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም" አለኝ። ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው። ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገብን። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ። ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው።
❤ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ። ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ የከበሩ ገዳማውያን በአባ አቡናፍርና በአባ በፍኑትዮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 16 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለአቡናፍር ጊዜ ተዳደቆ መዊት። እንተ ተለወጠ ገጹ አምሳለ ውዑይ እሳት። ድኅረ ቀበሮ በፍኑትዮስ በውሳጤ በዓት። ኢትትዋስ ለካልአን ዘተውህበቶ ሲሲት። ነቅዐ ማይ የብስት ወወድቀት በቀልት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የሰኔ16።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ138፥16-17። የሚነበበው ወንጌል ማቴ2፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለሚናስ ኅሩይ ዘክርስቶስ ሐራይ ጽድቀ ዘአብደረ እምነ ንዋይ፤ አምሳለ ወርኅ ወከመ ፀሓይ ብሩህ"። ትርጉም፦ የክርስቶስ ምርጥ ጭፍራ ከገንዘብ ይልቅ ጽድቅን የመረጠ እንደ ምሳሌው እንደጨረቃ ለደመቀና እንደ ፀሓይም ብሩህ ለኾነ ለሚናስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ለሰማይ ጭፍራ ለተባለ ለቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን መርዩጥ በተባለ አገር ለከበረችበት ለቅዳሴ ቤቱ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት፦ ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበሸ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጒድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ።
❤ ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋራ አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ለንሡም የቊስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ ከዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አላት። ከእንቅልፍም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ስሟም መርዩጥ ተባለች።
❤ እግዚአብሔር ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቊጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ሰኔ 15 ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ15 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ እንተ ተሐንፀት በመርዩጥ። በትእዛዝ ንጉሥ ሥሉጥ። ሚናስ ዘአንቃሕከ በድነ ሐራውያ እምጸጥ። አስተዋጺኦሙ ዕደው ዘበበ፪ቱ ቂራጥ። መባአ ለከ ዘነሥኡ በሤጥ"። አርከ ሥሉስ(አርኬ) የሰኔ 15።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ"። መዝ 88፥19። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 7፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥44-51። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ የቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ለሰማዕቷ ለቅድስት ለባሲተ ክርስቶስ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
+ + +
❤ ቅድስት ለባሲተ ክርስቶስ ሰማዕት፦ ስለዚች ቅድስት እናት ብዙ የተጻፈ ባይገኝም በተጋድሎዋ እጅግ የተመሰገነች ታላቅ እናት እንደሆነች ትግራይ እንደርታ ውስጥ የሚገኝ አስደናቂው ገዳሟ ምስክር ነው። ትውልዷ ትግራይ ሲሆን በታህታይ ተንቤን እንደርታ ውስጥ በሚገኘው ገዳሟ ውስጥ አስደናቂ ጸበል አላት። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱስና ቅዱሳን በዓላት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ ሰኔ ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱሳን አባ አክራና ለዮሐንስ፣ ለአብጥልማና ለፊልጶስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱሳን አባ አክራ፣ ዮሐንስ፣ አብጥለሰማና ፊልጶስ፦ ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ። መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አደረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ሰኔ 14 ቀን ቆረጡአቸው።
❤ ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጠ።
❤ እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዱሳን የፊልጶስን፣ የአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገንዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቊጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት በአባ አክራና ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ14 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለአብጥልማ ወፊልጶስ አብያጽ። ዮሐንስ ወአክራ ዘደቡብ ግብጽ። አመ ቆሙ ለስምዕ በዐውደ መኰንን ስሑጽ። እግዚአብሔር ባልሖሙ እምዘ ይሰርር ሐፅ። ወአድኃኖሙ ካዕበ እምእሳት ብቊፅ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የሰኔ 14።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥7-15፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 27፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ መልካም በዓልና ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለቃይናን ወለመላልኤል ወለያሬድ እለ ዓቀቡ ሕጎ ለልዑል ወፈትሑ ለሕዝቡ በጽድቅ ወበርትዕ"። ትርጉም፦ የልዑልን ሕጉን ጠብቀው ለሕዝቡ በእውነትና በቀና ፍርድን ላደረጉ ለቃይናን፣ለመላልኤልና ለያሬድም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ ሰኔ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ መልአክ ለሐዲስ የምሥራች ነጋሪ ለሆነ ለመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል (በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ሠሩላቸው)፣ ለኄኖስ ልጅ ለቅዱስ ቃይናን ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ለአባ ዮሐንስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከሰማዕቱ ከቅዱስ አቡላግ፣ ከሁለት መቶ ሰማዕታትና ስለ እውነት ከሰደደ ከአባታችን ከማትያንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚችም ዕለት ለከበረ መልአክ አዲስ የምሥራች ነጋሪ ለሆነ የመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ሠሩላቸው።
❤ ይህ የከበረ መልአክ የእራኤል ልጆች ከሰይጣን እጅ ስለመዳናቸውና ከምርኮም ስለ መመለሳቸው ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር በሚጸልይና በሚማልድ ጊዜ አስቀድሞ የተገለጠለትና ስለ ድኅነታቸውና ስለ ቤተ መቅደስም መታነፅ የነገረው ነውና። ዳግመኛም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መምጣትና መገደል ስለ ቤተ መቅደስም መፍረስ ከዚያም በኋላ ስለ ሐሳዊ መሲሕ መምጣት ነገረው።
❤ ለመድኅን መምጣትም በሱባዔ የወሰናቸው ዘመናት በተፈጸሙ ጊዜ ይህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ቅድስት ድንግል ወደ እመቤታችን ማርያም መጣ ዓለምን ስለ ማዳን የእግዚአብሔር ልጅ ከርሷ ሰው ስለመሆኑ ነገራት።
❤ ስለዚህም የበዓላቶቹን መታሰቢያ እንድናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን። እኛም ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ያድነን ዘንድ ለመንግሥቱም የተዘጋጀን ያደርገን ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ እኛ እንለምነው። ልዕልና ችሎታም ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የዚህም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ቃይናን፦ ቃይናንም መቶ ሰብዓ ዓመት ኖረ መላልዔልንም ወለደው መላልዔልንም ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ ሴቶች ልጆችና ወንዶችም ወለደ። ቅዱስ ቃይናን መላ ዘመኑ ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ነው ከዚያም በኋላ ዐረፈ። የቅዱስ ቃይናን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ አባ ኢላርዮንና በታላቁ አባ ኤስድሮስ ገዳም በታናሽነቱ መነኰሰ ከአባ ኤጲፋንዮስ ጋራም በገድል በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የደግነቱ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜናም በቦታው ሁሉ ተሰማ። ከዚህም በኋላ ኤጲፋንዮስ በቆጵሮስ አገር ኤጲቆጶስነት ከተሾመ በኋላ እርሱን መርጠው በኢየሩሳሌም ኤጲስቆስነት ሾሙት።
❤ ይህ አባት በሹመት በነበረ ጊዜ ሰይጣን በገንዘብ ፍቅርና በዚህ ዓለም ክብር አሳተው ብዙ ገንዘብ ሰብስቦ ለማዕዱ የሚመገብበት የወርቅና የብር ሣህን አሠርቶ ነበርና ለድኆችና ለምስኪኖችም መራራትን ተወ፤ ምንም የእንጀራ ቁራሽ አይሰጣቸውም ነበር። ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በሰማ ጊዜ የቀድሞውን ተጋድሎውንና የዓለም መናኒነቱን ፍቅሩንም አስታውሶ እጅግ አዘነ ከቀድሞ ጀምሮ በመንፈስ ወንድሙና ወዳጁ ነበርና።
❤ ስለዚህም ብፁዕ ኤጲፋንዮስ ከቆጵሮሰሰ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አባ ዮሐንስ መጣ አባ ዮሐንስን በጥበብ ከስሕተት ያድነው ዘንድም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ባለበት ቤተ መቅደስ ለመስገድ እንደመጣ አገኘው። በተገናኙም ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን ወደ ቤቱ አስገብቶ ማዕድ አዘጋጀለት በማዕድም ላይ ከብርና ከወርቅ የተሠራ ሣህኖችን አኖረ አባ ኤጲፋንዮስም በልቡ አዘነ ለድኆችና ለምስኪኖች ርኄራኄ እንደሌለውም አየ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወጥቶ በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት በአንዱ አደረ። ምክንያትም አዘጋጀ ይህም እንዲህ ነው ወደ አባ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከ "ወንድሜ ሆይ ከቆጵሮስ አገር ሽማግሎችና የሕዝቡ መምህራን ወደ እኔ መጥተዋልና በእነርሱ ፊት ታከብረኝ ዘንድ ከወርቅና ከብር የተሠሩ የማዕድ ዕቃዎችን ይመገቡባቸው ዘንድ እንድትልክልኝ እሻለሁ" እርሱም ላከለት። ያን ጊዜም አባ ኤጲፋንዮስ ዕቃዎቹን ወስዶ ሸጣቸው ዋጋቸውንም ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወታቸው።
❤ ከዚህም በኋላ በተገናኙ ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን "የላክሁልህን የማዕድ ዕቃዎቼን መልስ" አለው እርሱም "እሺ" አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ነገረው አባ አረጲፋንዮስም "እሺ" አለው። በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ካለበት ቤተ መቅደስ ሲወጣ አገኘው ያን ጊዜም ያዘውና "ገንዘቤን እስምትሰጠኝ አልለቅህም" አለው አባ ኤጲፋንዮስም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያን ጊዜም የአባ ዮሐንስ ዐይኖቹ ታወሩ። ያን ጊዜም ይቅር ብሎት ዐይኖቹን ይገልጥለት ዘንድ እያለቀሰ ወደ አባ ኤጲፋንዮስ ማለደ እርሱም መጸጸቱን አይቶ አንዲቱን ዐይኑን ገለጠለት እንዲህም አለው "ነፍስህን ታስብ ዘንድ አንዲቷ ዐይንህ ዕውርት እንደሆነች ትቶልሃል"። ገሠጸውም እንሆ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀድሞ ድካምህን ብርታትህንና ተጋድሎህን አስቦ ራራልህ ከስሕተትም አዳነህ" አለው።
❤ "የማዕድ ዕቃዎችንም እኔ እንደሸጥኳቸውና ስለ አንተ ለድኆችና ለምክኪኖች እንደ መጸወትኳቸው ዕወቅ አንተ በገንዘብ ፍቅር መጠመድህንና የቀድሞውን መልካም ሥራህን መተውህን ብሰማ ነው እንጂ ከቆጵሮስ ወደ ኢየሩሳሌም አልመጣም ነበር"። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ቅዱስ ዮሐንስ ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆነ በርኅራኀረም መንገድ ሔደ ያለውንም ጥሪቱን ሁሉ ሰጠ ምንም አላስቀረም ልብሶቹንም ለተራቆቱ ሰጠ በሞተ ጊዜ አንድ አላድ ከዚያም በታች ከእርሱ ዘንድ እስከ አልተገኘ ድረስ ሰጠ።
❤ ጌታችንም የመፈውስ ሀብትን ሰጠው ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከተቀደሰ ዘይት እየቀባ ፊታቸውንም አዳኝ በሆነ መስቀል ምልክት እያማተበ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ አዳናቸው። መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ ክብር ይግባውና ጌታችንን አገልግሎ ሰኔ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 13 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለገብርኤል በእደዊሁ ዘተአሥሩ። መላእክተ ሰማይ ጌጋየ በትውልደ ሰብእ ዘገብሩ። ለዝንቱ መልአክ በእንተ ዕበዩ ወክብሩ። በብሔረ ግብጽ መምህራን ሥርዓት አንበሩ። በዛቲ ዕለት ይትገበር ተዝካሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 13።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ይትሌቃሕ ኃጥእ ወኢይፈዲ። ወጻድቅሰ ይምሕር ወይሁብ። እስመ እለ ይበርክዎ ይወርስዋ ለምድር"። መዝ 36፥21-22። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 6፥7-20፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 8፥20-26። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
