ar
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

الذهاب إلى القناة على Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

إظهار المزيد
1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
❣❣❣እንዘ ተሐቅፊዮ @EOTCW

❣❣ኢየሐፍር ቀዊመ@EOTCW

ዘሳድስ ሰንበት @EOTCW

🌹🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🌷🌷 ሥርዐተ ማሕሌት ዘሣድስ  ሳምንት በዓለ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ 💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ   ሉያእመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡ @EOTCW @EOTCW ✨መልክዐ  ሥላሴ ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም። @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም በዝ መካን መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘቔላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት ለዘቀደሳ ለሰንበት /ለዘአክበሮ ለቂርቆስ/ ኪያሁ ፍርህዎ ወሰብሕዎ ወተማኅፀኑ ኀቤሁ። @EOTCW 🔸🌱ዓዲ ዚቅ፦ ኀበ ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት፤ ዬዬዬ ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት ብሂል ውስተ ርስቶሙ ለኩሎሙ ሐዋርያት ብሂል @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡ @EOTCW ❣❣❣ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/2/ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/2/ ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/2/ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። @EOTCW ❣❣❣ወረብ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/2/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክት ይትለአኩኪ፣ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ሶበ ዴገነኪ አረዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጎይየ፤አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤ተአምርኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ አመ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ/2/ ተአምርኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምርኪ/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ፤ምስለ ዮሴፍ አረጋ፤ነገደት ቁስቋመ ናዛዚት ኃዘን ወብካይ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ @EOTCW ❣❣❣ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ  ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/2/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል። @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ @EOTCW @EOTCW ❣❣❣ወረብ ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/2/ አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡ @EOTCW @EOTCW ✨ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡ @EOTCW ❣❣ወረብ ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/2/ ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። @EOTCW @EOTCW ❄️መዝሙር ፦ በ6 ሃሌታ- ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ @EOTCW 🔹አመላለስ፦ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/2/ ከመ አሐዱ እምእሉ/4/ https://t.me/Eotcw     # Join & share

1.13 KB

2/3/2015 ዓ.ም (፪/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ። ወኢይፈርህ እምነገር እኩይ። ጥቡዕ ልቡ ለተወክሎ በእግዚአብሔር። መዝ 111፥6 🕯 ትርጉም የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል። ከክፉ ነገር አይፈራም። በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን ከአባ ጢሞቴዎስ በኋላ ለተሾመ አረማውያን ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራ ላደረሱበት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛው ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ጴጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ ለሆነ ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ሱንትዩ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ ነቢዪት ከሆነች ከሴቴንዋ፣ ከቅድስት አንስጣስያና ከአባ ሊባኖስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድር ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አባት አባ ጴጥሮስ ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልክትን ጻፈለት "እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን"። ዳግመኛም በዚች መልክት ውስጥ እንዲህ ብሎ ገለጠ "የተዋሕዶ ጥቅም እንዳይሻር ከተዋሕዶ በኋላ የአካላዊ ቃልን መለኮትን ከትስብእቱ ሊለዩት አይገባም"። ❤ ይህ አባ ጴጥሮስ እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት። ❤ ከዚህም በኋላ ሌላ መልክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳን መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ። ❤ ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀዲያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሢመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት። ❤ ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን ዳግመኛ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሱንትዩ ዐረፈ። ይህም አባት መንጋዎቹን እያስተማረ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ አምስት ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 2 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለብፁዕ ሱንትዩ። ወለጴጥሮስ ዓዲ ሱታፌ ዕበዩ። ኪያሆሙ ሕዝብ በከመ ሠምሩ ወኀርዩ። ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ ቤተ ክርስቲያኑ ይርዐዩ። እንተ አጥረያ በደሙ ወማዩ"። ሊቂ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር2። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ። ወኢይፈርህ እምነገር እኩይ። ጥቡዕ ልቡ ለተወክሎ በእግዚአብሔር"። መዝ111፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 4፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 20፥18-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ.16፥24-ፍ፡ም፡ "ወእምዝ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ" - "በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡አለ፦እኔን፡መከተል፡የሚወድ፡ቢኖር፥ራሱን፡ይካድ፡መስቀሉንም፡ተሸክሞ፡ይከተለኝ። ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚወድ፡ሁሉ፡ያጠፋታል፤ስለ፡እኔ፡ግን፡ነፍሱን፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡ያገኛታል። ሰው፡ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢያተርፍ፡ነፍሱንም፡ቢያጐድል፡ምን፡ይጠቅመዋል፧ወይስ፡ሰው፡ስለ፡ነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? የሰው፡ልጅ፡ከመላእክቱ፡ጋራ፡በአባቱ፡ክብር፡ይመጣ፡ዘንድ፡አለውና፤ያን፡ጊዜም፡ለዅሉ፡እንደ፡ሥራው፡ያስረክበዋል። እውነት፡እላችኋለሁ፥የሰው፡ልጅ፡በመንግሥቱ፡ሲመጣ፡እስኪያዩ፡ድረስ፡እዚህ፡ከሚቆሙት፡ሞትን፡የማይቀምሱ፡አንዳንድ፡አሉ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.56 KB

1/3/2015 ዓ.ም (፩/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኃፈር። ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ። ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ። መዝ 118፥46 🕯 ትርጉም በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፤ አላፍርምም። እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል። እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 14:28-ፍ፡ም፡ "ወእመቦ አሐዱ እምኔክሙ" - "ከእናንተ፡ግንብ፡ሊሠራ፡የሚወድ፡ለመደምደሚያ፡የሚበቃ፡ያለው፡እንደ፡ሆነ፡አስቀድሞ፡ተቀምጦ፡ከሳራውን፡የማይቈጥር፡ማን፡ነው? ያለዚያ፡መሠረቱን፡ቢመሠርት፥ሊደመድመውም፡ቢያቅተው፥ያዩት፡ሁሉ፦ ይህ፡ሰው፡ሊሠራ፡ዠምሮ፡ሊደመድመው፡አቃተው፡ብለው፡ሊዘብቱበት፡ይጀምራሉ። ወይም፡ሌላውን፡ንጉሥ፡በጦርነት፡ሊጋጠም፡የሚሄድ፥ከሁለት፡እልፍ፡ጋራ፡የሚመጣበትን፡ባንድ፡ እልፍ፡ሊገናኝ፡የሚችል፡እንደ፡ሆነ፡አስቀድሞ፡ተቀምጦ፡የማያስብ፡ንጉሥ፡ማን፡ነው? ባይሆንስ፡ሌላው፡ገና፡ሩቅ፡ሳለ፡መልክተኛዎች፡ልኮ፡ዕርቅ፡ይለምናል። እንግዲህ፡እንደዚሁ፡ማንም፡ከእናንተ፡ያለውን፡ሁሉ፡የማይተው፡ደቀ፡መዝሙሬ፡ሊሆን፡አይችልም። ጨው፡መልካም፡ነው፤ጨው፡ዐልጫ፡ቢኾን፡ግን፡በምን፡ይጣፈጣል? ለምድር፡ቢሆን፡ለፍግ፡መቈለያም፡ቢሆን፡አይረባም፤ወደ፡ውጭ፡ይጥሉታል። የሚሰማ፡ጆሮ፡ያለው፡ይስማ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.83 KB

1/3/2015 ዓ.ም (፩/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ሐነጹ አህጉረ ኀበ ይነብሩ። ተከሉ ወይነ ወዘርዑ ገራውሀ። ወገብሩ ማእረረ እክል፡፡ መዝ. 106፥ 36 🕯 ትርጉም የሚኖርባትንም ከተማ ሠሩ። ዕርሻዎችንም ዘሩ ወይኖችንም ተከሉ። የእህልንም ሰብል አደረጉ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content
+2

❤ "በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የተባረከ የኅዳር ወር ቀኑ ዐሥር ሰዓት ሲሆን ከዚህም ይጎድላል። ❤ ኅዳር ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን አፍራቅያ አገር ለሆኑ ለቅዱሳን ሰማዕታት ለመክሲሞስ፣ ለማንፍዮስ፣ ለፊቅጦርና ለፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኪዎስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያው በዓልና ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለጻድቁ ለቅዱስ ነአኵቶ ለመታሰቢያው በዓሉ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ቅዱሳን ሰማዕታት ከመክሲሞስ፣ ከማንፍዮስ፣ ከፊቅጦርና ከፊልጶስ፦ እነዚህ ቅዱስ በገሀዲ ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት ያረፉ ናቸው። በዚህም ከሀዲ ንጉሥ ዘመን ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው የነቁ ከእርሱ በሸሹ ጊዜ ነው። እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲአሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ "እኛ በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጦ የምናምን ክርስቲያኖች ነን ለእርሱም እንሰግዳለን እናመልከዋለንም" ብለው ጮኹ። ❤ ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፋአቸው አዘዘ አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም ታላቅ ግርፋትን ገረፏቸው በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች ደበደቧቸው። ❤ ከዚህም በኋላ በበርኖስ እላቂ ጨርቅ ከመጸጸና ከጨው ነክረው ቊስላቸውን አሹአቸው የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰሙ ጊዜ ሥቃዩንም ፈርተው ከበጎ ምክራቸው ባልተመለሱ ጊዜ ቁጣን በማብዛት ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ከዚያ የነበሩ ብዙ ሕዝብም ትዕግሥታቸውን በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አጠቃቅነውም እንዲቈርጧቸው አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ኅዳር 1 ቀን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 1 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለመክሲሞስ ወለአኃዊሁ በጽድቅ። እለ አበዩ ሰጊደ ለስብኮ ወርቅ። ሐራ ዳኬዎስ ዓላዊ ኰናኔ ሰብዓቱ ደቂቅ። በዘአርሐስዎ በብሂእ ወበፄው ድቁቅ። ቊስላቲሆሙ መዝመዙ በሠቅ"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 1። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር። ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ። ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ"። መዝ 118፥46-47። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 10፥32-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥4-12 እና የሐዋ ሥራ 4፥10-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ.16፥24-ፍ፡ም፡ "ወእምዝ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ" - "በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡አለ፦እኔን፡መከተል፡የሚወድ፡ቢኖር፥ራሱን፡ይካድ፡መስቀሉንም፡ተሸክሞ፡ይከተለኝ። ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚወድ፡ሁሉ፡ያጠፋታል፤ስለ፡እኔ፡ግን፡ነፍሱን፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡ያገኛታል። ሰው፡ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢያተርፍ፡ነፍሱንም፡ቢያጐድል፡ምን፡ይጠቅመዋል፧ወይስ፡ሰው፡ስለ፡ነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? የሰው፡ልጅ፡ከመላእክቱ፡ጋራ፡በአባቱ፡ክብር፡ይመጣ፡ዘንድ፡አለውና፤ያን፡ጊዜም፡ለዅሉ፡እንደ፡ሥራው፡ያስረክበዋል። እውነት፡እላችኋለሁ፥የሰው፡ልጅ፡በመንግሥቱ፡ሲመጣ፡እስኪያዩ፡ድረስ፡እዚህ፡ከሚቆሙት፡ሞትን፡የማይቀምሱ፡አንዳንድ፡አሉ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.47 KB

30/2/2015 ዓ.ም (፴/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ናሁ ይእዜ አልዐለ እግዚአብሔር። ርእስየ ዲበ ጸላእትየ። ፆድኩ ወሦጽከ ውስተ ደብተራሁ መስዋዕተ ወየበብኩ ሎቱ። መዝ. 26፥6 🕯 ትርጉም እንሆ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ። በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን፡ሠዋሁ። ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፣እዘምርለትማለሁ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 11:1-6፡ "ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ" - "ኢየሱስም፡ዐሥራ፡ሁለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ማዘዝ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡በከተማዎቻቸው፡ሊያስተምርና፡ ሊሰብክ፡ከዚያ፡ዐለፈ። ዮሐንስም፡በወህኒ፡ሳለ፡የክርስቶስን፡ሥራ፡ሰምቶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ሁለት፡ላከና።የሚመጣው፡አንተ፡ነህን? ወይስ፡ሌላ፡እንጠብቅ፧አለው። ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ኼዳችሁ፡ያያችሁትን፡የሰማችሁትንም፡ለዮሐንስ፡አውሩለት፤ ዕውሮች፡ያያሉ፡ዐንካሳዎችም፡ይሄዳሉ፥ለምጻሞችም፡ይነጻሉ፡ደንቈሮዎችም፡ይሰማሉ፥ሙታንም፡ይነሣሉ፡ ለድሃዎችም፡ወንጌል፡ይሰበካል፤በእኔም፡የማይሰናከለው፡ሁሉ፡ብፁዕ፡ነው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨