ar
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

الذهاب إلى القناة على Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

إظهار المزيد
1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን አምላክ ለወለደች ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለወራዊ መታሰቢያ በዓሏ፣ ለትንሣኤዋና ዕረገቷና የጨረሻ ቀን መታሰቢያ በዓልና የስሟ ትርጓሜ ሰላም ፍቅር ለሆነ ለንጉሥ ሉክያኖስ ልጅ ለሐዋርያዊቷ ሰማዕት ለቅድስት ኄራኒ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል። + + + ❤ "መዓዛ ረድኤትሽን ለሚሻ አፍንጫ ደስ የምታሰኚ የተአምር አበባ (የገነት ዛፍ አበባ) ማርያም ሆይ ልጅሽ በክንዱ አቅፎ በአፉ እየሳመ ከአንቺ የነሳውን ስጋ በቀኙ ለማስቀመጥ በአሳረገሽ ጊዜ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መላእክት ክንፍ ለክንፍ እየተማቱ አንቺን ለመቀበል ወረዱ"። ሊቁቹ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማኅሌተ ጽጌ ላይ። + + + ❤ በዚች ቀን አምላክ በሥጋ የወለደች የእመቤታችን የድንግል የማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው። እርሷ ስለእኛ ሁልጊዜ ትማልድልናለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የሕይወትና የደኅነት ወደብ ትሆነን ዘንድ እርሷን እናቱን ስለሰጠን በረከቷም በሁላችን በክርስቲያን ወገኖች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሐዋርያዊቷ ሰማዕት ቅድስት ኄራኒ፦ የስሟ ትርጓሜ ሰላም ፍቅር ማለት ነው። ለንጉሥ ሉክያኖስ ልጁ ነች እርሱም አባቷ ያማረ አዳራሽን ሠራላት መስኮቶቹንም ስምንት አደረገ ቅጽሩንም በዙሪያው ዐሥራ ሁለት አደረገ ማዕድንም ሠራላት። የወርቅና የብር የሆኑ ሣህኖችና ጽዋዎችንም አዘጋጀላት የሚያስተምራትም አንድ ሽማግሌ ሰው አደረገላት። ❤ ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አኖራት የሚያገለግሏትም ሦስት አገልጋዮችን በእርሷ ዘንድ አድርጎ ደጃፎችን በላይዋ ዘጋ መምህርዋም በውጭ ሆኖ ያስተምራታል። ❤ ዕድሜዋም ሰባት ዓመት ሆናትና ያን ጊዜ ራእይን አየች በማዕዷ ላይ ርግብ ስትቀመጥ በአፍዋም የወይራ ቅጠል አለ ። በማዕዱም ላይ አኖረችው ሁለተኛም ንስር መጣ ከእርሱ ጋር አክሊል አለ በማዕዷ ላይም አኖረው። ደግሞ ቊራ መጣ ከእርሱ ጋራ ከይሲ አለ በማዕዷ ላይም አኖረው። ደነገጠችም ለመምህርዋም ነገረችው እርሱም እንዲህ ብሎ ተረጐመላት "ርግብ የሕግ ምልክት ናት የዘይቱም ቅጠል የክርስትና ጥምቀት ናት፣ ንስርም ድል አድራጊነት ነው አክሊልም ለሰማዕታት የሚሰጥ ክብራቸው ነው። ቊራ የንጉሥ ምሳሌ ነው ከይሲውም መከራ ነው አንቺም የክብር ባለቤት በሆነ ክርስቶስ ስለ ስሙ ትጋደዪ ዘንድ አለሽ" አላት። ❤ ከዚህም በኋላ ይጐበኛት ዘንድ አባቷ ወደርሷ መጣና "ልጄ ሆይ ከመንግሥት ታላላቆች ለአንዱ ላጋባሽ እኔ እሻለሁ" አላት እርሷ ግን ከልቡናዬ እስተምመክር ሦስት ቀኖችን አባቴ ሆይ ታገሠኝ" ብላ መለሰችለት። አባቷም በሔደ ጊዜ በጣዖታቱ መሠዊያ ፊት ተነሥታ ቆመችና ስለጋብቻ የሚሆነውን ይገልጡላት ዘንድ ለመነቻቸው እነርሱም ምንም ምን ከቶ አልመለሱላትም። ❤ ከዚህም በኋላ ዐይኖቿን ወደ ሰማይ አቅንታ "የክርስቲያን አምላክ ሆይ ወደምትፈቅደው ምራኝ" ብላ ጸለየች ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንዲህ አላት። "እነሆ ነገ ከጳውሎስ ደቀ መዛመርት አንዱ ወደዚች አገር ይመጣል እርሱም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቅሻል። በማግሥቱም ያ ሐዋርያ መጥቶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃት። በሦስተኛውም ቀን እንደቀጠረቻቸው አባቷና እናቷ መጡ እርሷም እንዲህ አለቻቸው "እኔ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ"። ❤ አባቷም ሰምቶ በእርሷ ላይ ተቆጣ ወደ ከተማው መካከልም አውጥተው በጐዳና ላይ እንዲጥሏትና በፈረሶች እግር እንዲአስረግጧት አዘዘ። ወታደሮችም ንጉሥ አባቷ እንዳዘዘ አደረጉባት ግን ምንም ምን ክፉ ነገር ከቶ አልደረሰባትም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አባቷና እናቷ በአዩ ጊዜ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ መንግሥታቸውንም ትተው ለርሷ ወደተሠራው አዳራሽ ሔደው በውስጡ ተቀመጡ። ❤ በጐረቤታቸው ያለ ንጉሥም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ርሳቸው መጥቶ ወደ መንግሥታቸው እንዲመለሱ ተናገራቸው። እነርሱም አልፈለጉም እርሱም መንግሥታቸውን ያዘ ቅድስት ኄራኒንም ይዞ አሠቃያት ከዚያም አንበሶችን፣ እባቦችን በላይዋ ሰደደ ምንም አልቀረቧትም ። ሁለተኛም በመጋዝ መገዛት በአንገቷም ውስጥ ታላቅ ደንጊያ አሥሮ ከባሕር ጣላት የክብር ባለቤት ጌታችንም ከዚህ ሁሉ አድኖ ያለ ጥፋት በጤና አሥነሣት። ❤ ከዚህም በኋላ እርሷን ያጠመቀ ሐዋርያን አባቷ ጠርቶ ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ ቊጥራቸውም ሦስት መቶ ሆነ ከዘመዶቹና ከሀገር ሰዎችም ብዙዎች ተጠመቁ። ❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ኑማርያኖስ የቅድስት ኄራኒን ዜናዋን ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ቀላኒካ ወደሚባል አገር ወሰዳት። በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በበሬ አምሳል በተሠራ የነሐስ በርሜል ውስጥ ዘጋባት የክብር ባለቤት ጌታችንም ያንን በሬ ሰብሮ ቅድስት ኄራኒን ያለ ጥፋት በጤና አወጣት። ❤ ከዚህም በኋላ ኑማርያኖስ ሙቶ በርሱ ፈንታ ሳፎር ነገሠ እርሱም የቅድስት ኄራኒን ዜና በሰማ ጊዜ ወደ ርሱ አስቀርቦ በእጁ ውስጥ በአለ በታላቅ ጦር ወጋትና ነፍሷን አሳለፈች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሞተ አስነሣት። ንጉሥ ሳፎርም በአየ ጊዜ እጅግ አደነቀ ሰገደላትም በጌታችን ኢየሱስም አመነ ። ከእርሱም ጋራ ከሀገር ሰዎች ብዙ ወገኖች አመኑ ቁጥራቸውም ሠላሳ አንድ ሺህ ሆነ። ❤ ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አባቷና እናቷ ዐረፉ እርሷን ግን አምላካዊት ኃይል ተሸከመቻት ወደ ኤፌሶን አገርም አድርሳት በዚያ ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገች። ❤ በፋርስ ነገሥታት በመቄዶንያ፣ በቀላኒካና በቊስጥንጥንያ ነገሥታት ፊት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከመሰከረች በኋላ ወደ ወደደችው ክርስቶስ ሔደች። የድልና የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያዊቷ ሰማዕት በቅድስት ኄራኒ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 21 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለኄራኒ ከመ ትርጓሜሁ ለስማ። ምሥጢረ ጥምቀት ዘርእየት አምሳለ ዕፀ ዘይት በንዋማ። ሶበ ነይሩ ኪያሃ በጽንዐ ሃይማኖት ቀዊማ። ወሶበ ኢክህለ ሙቃሔ ወእግረ ፈረስ ያሕምማ አሠረ ዚአሃ ተለው አቡሃ ወእማ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ21። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። + + + ❤ የዕለቱ የቅ ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥25-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1-1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-18። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 22:23-34 "ወበይእቲ ዕለት መጽኡ ኀቤሁ ሰዱቃውያን" - "በዚያን፡ቀን፦ትንሣኤ፡ሙታን፡የለም፡የሚሉ፡ሰዱቃውያን፡ወደ፡እርሱ፡ቀረቡ፥እንዲህም፡ብለው፡ጠየቁት፦መምህር፡ሆይ፥ሙሴ፡አንድ፡ሰው፡ልጅ፡ሳይወልድ፡ሲሞት፡ወንድሙ፡ሚስቱን፡አግብቶ፡ለወንድሙ፡ዘር፡ይተካ፡አለ። ሰባት፡ወንድማማች፡በእኛ፡ዘንድ፡ነበሩ፤ፊተኛውም፡ሚስት፡አግብቶ፡ሞተ፥ዘርም፡ስለሌለው፡ሚስቱን፡ለወንድሙ፡ተወለት፤ እንዲሁ፡ደግሞ፡ሁለተኛው፡ሦስተኛውም፥እስከ፡ሰባተኛው፡ድረስ። ከሁሉም፡በኋላ፡ሴቲቱ፡ሞተች። ሁሉ፡አግብተዋታልና፥በትንሣኤ፡ቀንስ፥ከሰባቱ፡ለማናቸው፡ሚስት፡ትሆናለች? ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦መጻሕፍትንና፡የእግዚአብሔርን፡ኃይል፡አታውቁምና፡ትስታላችሁ። በትንሣኤስ፡እንደእግዚአብሔር፡መላእክት፡በሰማይ፡ይሆናሉ፡እንጂ፡አያገቡም፡አይጋቡምም። ስለ፡ትንሣኤ፡ሙታን፡ግን፦እኔ፡የአብርሃም፡አምላክ፥የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡ነኝ፡የሚል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡እናንተ፡የተባለውን፡አላነበባችሁምን፧የሕያዋን፡አምላክ፡ነው፡እንጂ፡የሙታን፡አይደለም። ሕዝቡም፡ይህን፡ሰምተው፡በትምህርቱ፡ተገረሙ። ፈሪሳውያንም፡ሰዱቃውያንን፡ዝም፡እንዳሠኛቸው፡በሰሙ፡ጊዜ፡አብረው፡ተሰበሰቡ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.41 KB

20/12/2012 ዓ.ም (፳/፲፪/፳፻፲፪ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ነጽረኒ ወስምዐኒ እግዚኦ አምላኪየ። አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት። ወከመ ኢይበሉኒ ጸላዕትየ ሞዕናሁ። መዝ. 12፥3 🕯 ትርጉም አቤቱ አምላኬ እየኝ ስማኝም። ጠላቴ አሸነፍኹት እንዳይል። የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለ፯ቱ ደቂቅ እለ ኀብኦሙ እግዚአብሔር ውስተ በኣት ወወሀቦሙ ንዋመ ጥዑመ እስከ ፫፻፸ወ፪ ዓመት፤ እለ አስማቲሆሙ አርከሌዶስ ዲኦሚዶስ አውጋንዮስ፣ ድሜጥሮስ፣ በርናጥዮስ፣ ከእስጢፋኖስ፣ ኪራኮስ ሰማዕታት እለ ክርስቶስ"። ትርጉም፦ እግዚአብሔር በዋሻ ውስጥ የሰወረራቸው፤ እስከ 372ዓመት ድረስ ጥዑም እንቅልፍን የሰጣቸው በክርስቶስ ሰማዕት ለኾኑ ስማቸው አርከሊዶስ ዲኦሚዶስ አውጋንዮስ፣ ድሜጥሮስ፣ በርናጥዮስ፣ ከእስጢፋኖስ፣ ኪራኮስ ለኾነ ለሰባቱ ሕፃናት ሰላምታ ይገባል። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዘመናት አንቀላፋተው በንጉሥ በቴዎዶስዮስ ዘመን ተነስተው ትንሣኤ ሙታን ለሰበኩ በከሀዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ዘመን ለነበሩ ከኤፌሶን ሀገር ለሆኑ ለሰባቱ ደቂቅ ለዕረፍት በዓላቸውና ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለትንሣኤዋና ለዕርገቷ አምስተኛ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከቅድስት ሄዛዊ ከመታሰቢያዋ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅዱሳን ሰባቱ ደቂቅ፦ እሊህም ስማቸው መክሲሞስ፣ ታሙኪሮስ፣ መርዳዲሞስ፣ ዮሐንስ፣ ቆስጠንጢኖስ፣ ዝሚና ዲዮናስዮ ናቸው። ንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ውስጥ በመዛግብቱ ላይ የሾማቸው ነበሩ። አምልኮ ጣዖትንም በአወጀ ጊዜ ጣዖትን በማምለክ ሥራ አልተሳተፉም። እሊህንም ቅዱሳን በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ይዞም አሠራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ለመሔድ በፈለገ ጊዜ እስከ ሚመለስ ድረስ ፈትቶ ለቀቃቸው ምናልባት ከምክራቸው ቢመለሱ ብሎ በልቡ አስቦ። ከዚህም በኋላ እሊህ ቅዱሳን ለረከሱ ጣዖታት እንዳይሰግዱ የጭፍራነት ሥራቸውን ትተው በተራራ ውስጥ ወደአለ ዋሻ ሒደው በዚያ ተሠወሩ። የዋሻውን አፍ ዘጉ ከእሳቸውም ጋራ በንጉሥ ዳኬዎስ ስም የተቀረጸ ብር ነበር። ከእርሳቸውም አንዱም አንዱ በየተራቸው ወጥቶ ምግባቸውን ገዝቶ ወደእሳቸው ይመለስ ነበር። ዳኬዎስም ከሔደበት እንደተመለሰ በሰሙ ጊዜ የዋሻውን ደጃፍ ዘግተው ተኙ። ❤ የእሊህንም ቦታቸውን የሚያውቅ አማኒ የሆነ ከጭፍሮች ውስጥ አንድ ሰው ነበረ ወደ ከተማ ሲወጡ ያገኛቸው ዘንድ ጠበቃቸው ባልመጡም ጊዜ ተነሥቶ ወደ ዋሻቸው ሔደ። ዋሻዋንም ከውስጥ እንደ ዘጓት ሁና አገኛት እነርሱም በረሀብ የሞቱ መሰለው ታላቅም የደንጊያ ሠሌዳ አምጥቶ ከእሳቸው የሆነውን ገድላቸውን ጽፎ በቀዳዳ ወደ ዋሻው ውስጥ አስገባው። እሊህም ቅዱሳን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዘመናት አንቀላፉ ዳኬዎስም ሙቶ እስከ ቴዎዶስዮስ ብዙ ነገሥታት ነገሡ። ❤ በዚህም ምእመን ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዎች ተነሥተው ብዙዎች ተከተሏቸው። በዚያንም ጊዜ እሊህን ቅዱሳን ሰባቱን ደቂቅ እግዚአብሔር አነቃቸው ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ግልጽ ያደርግ ዘንድ። ❤ ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው አንዱ ምግባቸውን ሊገዛ የከሀዲ ዳኪዎስንም ወሬ ይሰማ ዘንድ ብር ይዞ ወጣ ወደ ከተማም በገባ ጊዜ የከተማዋ ሁኔታ ተለወጠበት። በከተማውም በር መስቀሎችን አየ በየቅጽሮቿም የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ስሙን ያለ መፍራት ሲጠሩ ሰማ አንዱንም ሰው"ይች አገር ኤፌሶን አይደለችምን?" ብሎ ጠየቀ እርሱም "አዎን ናት" አለው። ያንንም ብር አውጥቶ ለባለ ሱቁ ሰጠው ምግባቸውን ይሸጥለት ዘንድ ባለ ሱቁም ያን ብር ተመለከተው የንጉሥ ዳኬዎስም ስም ተቀርጾበት አገኘውና ያንን ሰው ይዞ "በአንተ ዘንድ የተሸሸገ መዝገብ አለ ይህ ምልክት ከአንተ ተገኝቷልና" አለው። ❤ እንዲህም ሲጣሉ ወደእርሳቸው ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እንዲህም ብለው ጠየቁት "አንተ ከወዴት ነህ?" "ከዚች አገር ነኝ" አላቸው። "ማንን ታውቃለህ" አሉት እርሱም "ዕገሌንና ዕገሌን" አላቸው ከዘመን ብዛት የተነሣ የጠራቸውን ሰዎች የሚያውቃቸው የለም። ስለዚህም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ወደ ዳኞችና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ቴዎድሮስ ወደ ንጉሥ ቴዎዶስዮስም አቀረቡት። ንጉሡና ኤጲስቆጶሱም "ከአንተ የሆነውን እውነቱን ንገረን ከወዴት አገር ነህ" አሉት። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው "እኛ ሰባታችን የከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ነን እርሱም ወጥቶ ወደ ሌላ አገር በሔደ ጊዜ ከአንዷ ዋሻ ውስጥ ገብተን የዋሻዋን በር ዘግተን ተኛን"። እነሆ ስንነቃ የምንመገበውን ምግብ እገዛ ዘንድ ላኩኝ። ❤ ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ በሰሙ ጊዜ ተነሥተው ወደዚያ ዋሻ ከእርሱ ጋራ ሔዱ ከእርሳቸውም ጋራ ብዙ ሕዝቦች አሉ ቅዱሳኑንም ተቀምጠው አገኙአቸው። የዘመኑም ቁጥር በውስጡ የተጻፈበትን በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን የሆነውን ሠሌዳውን ወድቆ አገኙት ዘመኑም ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት እንደሆነ ታወቀ። ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉትም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው ትንሣኤ ሙታን እንዳለ አመኑ። እሊህ ሰባቱ ደቂቅንም በጠየቋቸው ጊዜ ከእርሳቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩአቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ተኙ። ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ንጉሥም የወርቅ ሣጥን ሠራላቸው በሐር ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው። ከሥጋቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የእሊህም የሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ሰብዓተ ዕደው። እለ ኮኑ ቅድመ ዘበሃይማኖት ስንዕወ። አዝማነ ዕልወት ይኅልፋ እለ አጽምዑ ብጽወ። ማዕዖ በዓቶሙ በሥምረተ አምላክ ተርኅወ። ነቂሖሙ ህየ ይግበሩ ፍናው"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 20። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ነጽረኒ ወስምዐኒ እግዚኦ አምላኪየ። አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት። ወከመ ኢይበሉኒ ጸላእትየ ሞዕናሁ"። መዝ 12፥3 ወይም መዝ 44፥9-10። የሚነበቡ መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥31-51፣ ያዕ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 23፥22-ፍ.ም። የሚበበው ወንጌል ማቴ 22፥23-34 ወይም ሉቃ 1፥39፥57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የትንሣኤዋና የዕርገቷ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 27:50-57፡ "ወጸርሐ ካዕበ ኢየሱስ በዐቢይ ቃል" - "ኢየሱስም፡ሁለተኛ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡ተወ። እነሆም፥የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከሁለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡ተናወጠች፥አለቶችም፡ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም፡ተከፈቱ፥ተኝተው፡ከነበሩትም፡ከቅዱሳን፡ብዙ፡ሥጋዎች፡ተነሡ፤ ከትንሣኤውም፡በኋላ፡ከመቃብሮች፡ወጥተው፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ገቡና፡ለብዙዎች፡ታዩ። የመቶ፡አለቃም፡ከእርሱም፡ጋራ፡ኢየሱስን፡የሚጠብቁ፡መናወጡንና፡የሆነውን፡ነገር፡አይተው፦ይህ፡በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡ብለው፡እጅግ፡ፈሩ። ኢየሱስን፡እያገለገሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ብዙ፡ሴቶች፡በሩቅ፡ሆነው፡ሲመለከቱ፡በዚያ፡ነበሩ፤ ከእነርሱም፡መግደላዊት፡ማርያምና፡የያዕቆብና፡የዮሳ፡እናት፡ማርያም፡የዘብዴዎስም፡የልጆቹ፡እናት፡ነበሩ። በመሸም፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡የተባለው፡ባለጠጋ፡ሰው፡ከአርማትያስ፡መጣ፥እርሱም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡ነበረ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.66 KB

19/12/2012 ዓ.ም (፲፱/፲፪/፳፻፲፪ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯y🕯🕯 በእግዚአብሔር እሴብሕ ቃልየ። በእግዚአብሔር ይከብር ዘነበብኩ። ወበእግዚአብሔር ዘነበብኩ ተወከልኩ ኢይፈርህ ምንተ ይሬስየኒ ሰብእ። መዝ. 55፥10 🕯 ትርጉም በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ። በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ። በእግዚአብሔር ታመንሁ፥አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 1:39-57፡ "ወተንሥአት ማርያም" - "ማርያምም፡በዚያ፡ወራት፡ተነሥታ፡ወደ፡ተራራማው፡አገር፡ወደ፡ይሁዳ፡ከተማ፡ፈጥና፡ወጣች፥ ወደዘካርያስም፡ቤት፡ገብታ፡ኤልሳቤጥን፡ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም፡የማርያምን፡ሰላምታ፡በሰማች፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኗ፡ውስጥ፡ዘለለ፤በኤልሳቤጥም፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሞላባት፥ በታላቅ፡ድምፅም፡ጮኻ፡እንዲህ፡አለች፦አንቺ፡ከሴቶች፡መካከል፡የተባረክሽ፡ነሽ፥የማሕፀንሽም፡ፍሬ፡የተባረከ፡ነው። የጌታዬ፡እናት፡ወደ፡እኔ፡ትመጣ፡ዘንድ፡እንዴት፡ይሆንልኛል? እነሆ፥የሰላምታሽ፡ድምፅ፡በጆሮዬ፡በመጣ፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኔ፡በደስታ፡ዘሏልና። ከጌታ፡የተነገረላት፡ቃል፡ይፈጸማልና፥ያመነች፡ብፅዕት፡ናት። ማርያምም፡እንዲህ፡አለች፦ ነፍሴ፡ጌታን፡ታከብረዋለች፥መንፈሴም፡በአምላኬ፡በመድኀኒቴ፡ሐሴት፡ታደርጋለች፤ የባሪያዪቱን፡ውርደት፡ተመልክቷልና።እንሆም፥ከዛሬ፡ጀምሮ፡ትውልድ፡ሁሉ፦ብፅዕት፡ይሉኛል፤ ብርቱ፡የሆነ፡እርሱ፡በእኔ፡ታላቅ፡ሥራ፡አድርጓልና፤ስሙም፡ቅዱስ፡ነው። ምሕረቱም፡ለሚፈሩት፡እስከ፡ትውልድና፡ትውልድ፡ይኖራል። በክንዱ፡ኃይል፡አድርጓል፤ትዕቢተኛዎችን፡በልባቸው፡ዐሳብ፡በትኗል፤ ገዢዎችን፡ከዙፋናቸው፡አዋርዷል፤ትሑታንንም፡ከፍ፡አድርጓል፤ የተራቡትን፡በበጎ፡ነገር፡አጥግቧል፤ባለጠጋዎችንም፡ባዷቸውን፡ሰዷቸዋል። ለአባቶቻችን፡እንደ፡ተናገረ፥ለአብርሃምና፡ለዘሩ፡ለዘለዓለም፡ምሕረቱ፡ትዝ፡እያለው፡እስራኤልን፡ብላቴናውን፡ረድቷል። ማርያምም፡ሦስት፡ወር፡የሚያህል፡በእርሷ፡ዘንድ፡ተቀመጠች፡ወደ፡ቤቷም፡ተመለሰች። የኤልሳቤጥም፡የመውለጃዋ፡ጊዜ፡ደረሰ፥ወንድ፡ልጅም፡ወለደች።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.41 KB

19/12/2012 ዓ.ም (፲፱/፲፪/፳፻፲፪ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ፡፡ መዝ. 44፥9 🕯 ትርጉም በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና። ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ ስሚ፤ እዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 27:50-57፡ "ወጸርሐ ካዕበ ኢየሱስ በዐቢይ ቃል" - "ኢየሱስም፡ሁለተኛ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡ተወ። እነሆም፥የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከሁለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡ተናወጠች፥አለቶችም፡ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም፡ተከፈቱ፥ተኝተው፡ከነበሩትም፡ከቅዱሳን፡ብዙ፡ሥጋዎች፡ተነሡ፤ ከትንሣኤውም፡በኋላ፡ከመቃብሮች፡ወጥተው፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ገቡና፡ለብዙዎች፡ታዩ። የመቶ፡አለቃም፡ከእርሱም፡ጋራ፡ኢየሱስን፡የሚጠብቁ፡መናወጡንና፡የሆነውን፡ነገር፡አይተው፦ይህ፡በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡ብለው፡እጅግ፡ፈሩ። ኢየሱስን፡እያገለገሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ብዙ፡ሴቶች፡በሩቅ፡ሆነው፡ሲመለከቱ፡በዚያ፡ነበሩ፤ ከእነርሱም፡መግደላዊት፡ማርያምና፡የያዕቆብና፡የዮሳ፡እናት፡ማርያም፡የዘብዴዎስም፡የልጆቹ፡እናት፡ነበሩ። በመሸም፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡የተባለው፡ባለጠጋ፡ሰው፡ከአርማትያስ፡መጣ፥እርሱም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡ነበረ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.66 KB

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 1:39-57፡ "ወተንሥአት ማርያም" - "ማርያምም፡በዚያ፡ወራት፡ተነሥታ፡ወደ፡ተራራማው፡አገር፡ወደ፡ይሁዳ፡ከተማ፡ፈጥና፡ወጣች፥ ወደዘካርያስም፡ቤት፡ገብታ፡ኤልሳቤጥን፡ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም፡የማርያምን፡ሰላምታ፡በሰማች፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኗ፡ውስጥ፡ዘለለ፤በኤልሳቤጥም፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሞላባት፥ በታላቅ፡ድምፅም፡ጮኻ፡እንዲህ፡አለች፦አንቺ፡ከሴቶች፡መካከል፡የተባረክሽ፡ነሽ፥የማሕፀንሽም፡ፍሬ፡የተባረከ፡ነው። የጌታዬ፡እናት፡ወደ፡እኔ፡ትመጣ፡ዘንድ፡እንዴት፡ይሆንልኛል? እነሆ፥የሰላምታሽ፡ድምፅ፡በጆሮዬ፡በመጣ፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኔ፡በደስታ፡ዘሏልና። ከጌታ፡የተነገረላት፡ቃል፡ይፈጸማልና፥ያመነች፡ብፅዕት፡ናት። ማርያምም፡እንዲህ፡አለች፦ ነፍሴ፡ጌታን፡ታከብረዋለች፥መንፈሴም፡በአምላኬ፡በመድኀኒቴ፡ሐሴት፡ታደርጋለች፤ የባሪያዪቱን፡ውርደት፡ተመልክቷልና።እንሆም፥ከዛሬ፡ጀምሮ፡ትውልድ፡ሁሉ፦ብፅዕት፡ይሉኛል፤ ብርቱ፡የሆነ፡እርሱ፡በእኔ፡ታላቅ፡ሥራ፡አድርጓልና፤ስሙም፡ቅዱስ፡ነው። ምሕረቱም፡ለሚፈሩት፡እስከ፡ትውልድና፡ትውልድ፡ይኖራል። በክንዱ፡ኃይል፡አድርጓል፤ትዕቢተኛዎችን፡በልባቸው፡ዐሳብ፡በትኗል፤ ገዢዎችን፡ከዙፋናቸው፡አዋርዷል፤ትሑታንንም፡ከፍ፡አድርጓል፤ የተራቡትን፡በበጎ፡ነገር፡አጥግቧል፤ባለጠጋዎችንም፡ባዷቸውን፡ሰዷቸዋል። ለአባቶቻችን፡እንደ፡ተናገረ፥ለአብርሃምና፡ለዘሩ፡ለዘለዓለም፡ምሕረቱ፡ትዝ፡እያለው፡እስራኤልን፡ብላቴናውን፡ረድቷል። ማርያምም፡ሦስት፡ወር፡የሚያህል፡በእርሷ፡ዘንድ፡ተቀመጠች፡ወደ፡ቤቷም፡ተመለሰች። የኤልሳቤጥም፡የመውለጃዋ፡ጊዜ፡ደረሰ፥ወንድ፡ልጅም፡ወለደች።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨