ሰዋስው ☘☘☘☘
الذهاب إلى القناة على Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
إظهار المزيد1 161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 161
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል። ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉአን። ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ። መዝ 67፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥1-14።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ። ወይሴብሑ ለስምከ። መዝራዕትከ ምስለ ኃይል"። መዝ 88፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥23-30፣ 2 ጴጥ 1፥15-ፍ.ም እና የሐ ሥራ 7፥44-54። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥28-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላችን ለመድኃኒታች ለኢየሱስ ለክርስቶስ ከዘጠኙ ዐበይት በዓል ለአንዱ ለሆነው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ለሙሴ ለኤልያስ ለሐዋርያት ለጴጥሮስ ለያዕቆብና ለዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዓልና በሰላም፡አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ከልደቱ፣ ከብንያምም ከመታሰቢያው፣ ከተጋዳይ ከአባ ጋልዮን ከዕረፍቱና በሰማዕትነት ከዐረፈች ከቅድስት ኦፍራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን ደብር ዘሠምሮ የኀድር ውስቴቱ እግዚአብሔር አማን ተሰብሐ በደብረ ታቦር"። ትርጉም፦ ደብረ ታቦር የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?አለ ፤ እግዚአብሔር በውስጡ ሊያድርበት በወደደው በደብረ ታቦር ተራራ በእውነት ተገለጠ (ተመሰገነ)። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ቅዱሳን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
❤ ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
❤ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት።
❤ ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና።
❤ እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነነቱ የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"።
❤ ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
❤ ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ያስነሳቸው ማንም አይችልም።
❤ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
❤ የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ።
❤ ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
❤ እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት። ሰው ካልሆ በበረት እንዴት አስተኙት አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
❤ ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ።
❤ ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ተጋዳይ አባ ጋልዮስ፦ ይህም በቀንና በሌሊት ጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጎልማሳ ሆኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጪ አልወጣም ከማህበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።
❤ ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት "እኛ ተሰውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋር ልንወስድህ ወደን ወደ አንተ መጣን" ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደ ማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሯቸው ሔደ።
❤ ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጡለት እነርሱም የዳዊት መዝሙር ያገቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁቱ በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእነርሳቸው ጋር ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእርሳቸው ጋር አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።
❤ ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው "ወዴት ነበርክ" አለው እርሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ ነሐሴ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጋልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የነሐሴ 13 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ። ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዳሴ። አመ ገበርከ በታቦር እግዚኦ ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። ኤልያስ መንገለ ቆመ ወኀበ ሀለወ ሙሴ። ዘመለኮትከ ወልደ ከሠትከ ሥላሴ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ13።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ጌታችን ልክ በደብረ ታቦር ጌታችን ልክ ለእነ ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠላቸው ሁሉ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለአባታችን ለአቡነ ሊቃኖስም እንዲሁ በበዓታቸው በደብረ ቆናጽል ገዳም ሣሉ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ ለአሳያቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ በዚች ቀን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በሀገራችን በሚገኘው በደብረ ቆናጽል ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል። የተገለጠውም እንደነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፋንታ የለተሰወሩት ለአቡነ ሊቃኖስ ነው።
❤ አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ "ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ" በማለት ይገልጸዋል፡፡ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡
❤ የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡
❤ ጌታችን ነሐሴ 13 ቀን ልክ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በዚህ በፎቶው ላይ በሚታየው በአቡነ ሊቃኖስ ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል።
❤ አቡነ ሊቃኖስ በደረቅ ጭንጫ ላይ ውሃ በተአምራት አፍልቀው ለቅዳሴ ማይ ጸሎት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ አቡነ ሊቃኖስም እንደ መሴ ከጭንጫ ላይ ያፈለቁትን ውሃ በወንፊት አድርገው ለአቡነ ገሪማና ለአቡነ ጰንጠሌዎን ይልኩላቸዋል፡፡ ከዳግማዊው ሙሴ ከአቡነ ሊቃኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ሳልፆም ሊፈሰክ ነው።
አይ የኔ ነገር
እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር"
የንሰሀ ህይወት ይስጠን!
https://t.me/Eotcw
1 161
ሌሎች የደብረ ታቦር ግጥም ጭውውት ለማግኘት ከላይ ያለውን forward በመንካት የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
ማዕተቤን አልበጥስም
ደብረ ታቦር
ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ
እውነት ብርሃንን አጥልቀሽ
ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ
አንቺ የምሥጢር ሥፍራ
የመለኮት ብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምሥጢር
ልቆ የታየብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ከአድማሳት ከፍ ከፍ ብሎ
የስምሽ ተረፈ ውሉ
የተዘከረው በዓለሙ
ምን ይሆን ወርቅ ሰሙ?
ምን አገኘሽ ያኔ ታቦር
እንዲያ ተከፍቶ የብርሃንሽ በር
የክብሩ ግርማ የዋጠሽ
እኮ ማን ነው የረገጠሽ?
ጌታሽ ነው አሉ ስሰማ
ከተራራሽ አናት ማማ
የብርሃን ጉንጉን ሸማ
ያጎናፀፈሽ በግርማ
ግሩም እኮ ነው!
ከተራሮች አንቺን መርጦ
ከነአባቱ ተገልጦ
ደጅሽን ሳይንቅ ማክበሩ
እንዴት እንዴት ይሆን ምሥጢሩ?
ይህንንም ደግሞ ዳዊት
ተናግሯል አሉ በትንቢት
ታቦር ወአርሞንኤም በሚል ቅኔ
በስሙ ተደሰቱ ያኔ
እያለ ዘመረ በክብር
የዚህችን ተራራ ምሥጢር
ያ ልበ አምላክ ዳዊት
የተናገረው ትንቢት
ለካ ይህ ኖሯል ግቡ
ደጅሽ በብርሃን ማበቡ
ኧረግ! አንቺስ ታድለሻል
የማይቻለውን ችለሻል
እሳተ መለኮትን ይዘሻል
ለመሆኑ እንዴት ቻልሽው ታቦር
ያን እውነተኛ ፍቅር?
ከመንበሩ የሳበው ንጉሥ
በብርሃን ሠረገላው ሲፈስ
መሠረትሽ ሳይናጋ
ባለበት ቆሞ የረጋ
ምን ይሆን ምሥጢሩ የፅናትሽ
በፊቱ ቆመሽ መታየትሽ?
ልብሱ ነጭ ሆኖ በረድ
አብም ከሰማይ ሲወርድ
ዙሪያው በክብር ደመና
ተመልቶ በብርሃን ፋና
ሙሴ ከመቃብሩ ተጠርቶ
ኤልያስ ከብሄረ ሕያዋን መጥቶ
በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው
ሲወያዩ ላስተዋለው
ምን ይመስል ይሆን ገጹ?
የብርሃን መለኮት መገለጹ
ደግሞ የሐዋርያቱ
የእነዚያ የሦስቱ
ሲጋልቡ ርደው
እንደ ቄጤማ ወርደው
ከሰሩ የተነጠፉቱ
ምንድን ይሆን ምክንያቱ?
ጴጥሮሰማ ተሽብሮ
ናላው በድንጋጤ ዞሮ
ለእያንዳንዳችሁ በጋራ
ሦስት ዳሶችን እንስራ
ብሎ በዚያች የብርሃን እልፍኝ
የዘለዓለም ደስታን ሊያገኝ
አስቦ በቅጽበት መመኘቱ
ገርሞትም አይደል ክስተቱ
የብርሃን ፀዳል ድምቀቱ?
እኮ እንደምን አይገርመው
ሙሴና ኤልያስ ቆመው
ክብሩን ሲያውጁ እያዩ
ማነው የሙሴን አምላክ ሙሴ ባዩ?
ሲል ሙሴ ባሕር ከፋዩ
የኤልያስንስ ክብር ጌታ
አውርደውት ከሰው ተርታ
ኤልያስ ባዮቹ እነማን ናቸው?
ሲል ኤልያስ ገርሟቸው
ይህን ሲሰሙ ሐዋርያቱ
በድንጋጤ ሲመቱ
ደግሞ ወርዶ አባቱ
ልጄን ስሙት በማለቱ
በፍርሃት ማዕበል ሲንገላቱ
ይህ ሁሉ ምስጢር መታየቱ
በአንቺም አይደል ታቦር
መገለጹ የሦስትነት ምስጢር
ጥንትስ ታሪክሽ ተዘክሮ
መቼ ያልቅና ተነግሮ
እንዲያው ድንቅ
እንበል እንጂ ድንቅ ድንቅ!
የብርሃንሽ ሰንደቅ
ከአድማሳት ልቆ ሲደምቅ
ክብር እንበልሽ ክብር!ክብር!
አንቺ እውነተኛ የምስጢር በር
የሥሉስ ቅዱስ ነገር
የተገለጸብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ያበራሽ ይብራ ስሙ ይግነን
ዛሬም ለእኛ ብርሃን ይሁነን
ገኖ ያግነን በፈቃዱ
በራ ይሁንልን መንገዱ
ክብሩም ከፍ ከፍ ወደ ላይ
ከሰማየ ሰማያት በላይ
እንዲሁም በምድር በቀላይ
የአምላካችን አዶናይ
ክብርሽ ዛሬም ነገ ይነገር
መሆንሽ እውነተኛ የብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምስጢር
የተገለጠብሽ መንደር ደብረ ታቦር!!!
ወስበሐት ለእግዚአብሔር።
https://t.me/Eotcw
1 161
በደብረ ታቦር
መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ
በተቀደሰው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት
ዮሐንስ ጴጥሮስን ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አንሥቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮቱ በብርሃን ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ሰሙት እስከ ዘለዓለም
ሕይወት በእርሱ ነው ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።
ከዲ/ን ቃለ አብ ሲሳይ
https://t.me/Eotcw
1 161
#ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)
ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡
በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤ የደመቀ የጎላ ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው፡፡ የችቦ ማብራት ቱፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ተራራው ከገሊላ ባህር በስተ ምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል፤ መሳ.4 ÷6-14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤ ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ሌሎች ኤልያስ ነው፤ ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ ነው
ይላሉ ብለውት ነበር፤ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ’’ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስደስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦሥቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን
ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርሀን አሳየኝ ብሎት ነበር (ዘጸ. 33÷17-23) ጌታችን ግን በሕይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል ፡፡
ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለአለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል፡፡
ከዚያም ደመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው አርሱን ስሙት" ሲል መሰከረ፡፡ ማቴ 17÷ 2 ሉቃ 9÷29፡፡
እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖቴ ኩራቴ
ከዲ/ን ቃለ አብ ሲሳይ
https://t.me/Eotcw
1 161
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ስርአተ ማህሌት ዘበዓለ ደብረ ታቦር
🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇🎇
ሥርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCW
መልክአ ሥላሴ፦
ሥላሴክሙ ሥላሴ ይረስየኒ መካነ፤ድኅረ ተዋሓድኩሰ ዘሥላሴሁ ብርሃነ፤ዮርዳኖስክሙ ዝየ እስመ ኵለንታየ ኮነ፤ኢየኀሥሥ እምዮርዳኖስ ሰማዕተክሙ ምእመነ፤ወኢይትሜነዮ ለታቦር እስመ ታቦር አነ።
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
ሰላም ለከ ኦ ደብረ ታቦር፤ዘአስተርአየ ላዕሌከ ትእምርተ መንግስት ህየ ንሰግድ ኩልነ፤ኀበ ተሰብሐ እግዚእነ
@EOTCWW
ወረብ፦
ሰላም ለከ ኦ ደብረ ታቦር ዘአስተርአየ ላዕሌከ ትእምርተ መንግስት/2/
ህየ ንሰግድ ኩልነ ኀበ ተሰብሐ እግዚእነ/2/
@EOTCW
@EOTCW
ነግሥ
ዳዊት ነቢይ እምነ አድባራት አልዓላ ፤አምሳለ ኪሩብ አስተማሠላ ፤አመ ወአለ ባቲ ክርስቶስ ርእሰ መሐላ ፤በደብረታቦር ካልዕተ ጸናፊ ጌልጌላ ፤ናሁ ተመነየ በማዕከላ ጴጥሮስ ከመ ይሣርር ሠቀላ ።
@EOTCWW
ዚቅ፦
ደብር ዘበእንቲአሁ ጸርሐ፤ዳዊት ነቢይ እንዘ ይብል፤ወሰምዐኒ እምደብረ መቅደሱ
@EOTCWW
@EOTCWW
መልክአ ፍልሰታ፦
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ስቡሐ ዘተሰብሐ፤እምነ ፀሐይ ወወርህ ስነ ስብሐትኪ አብርሃ ፤ እንበሌኪ ድንግል ወእንበለ ወልድኪ በኩረ ፍስሐ ፤ አልቦ ለሞት ማዕሰሪሁ ዘፈትሐ፤ ወሙታነ በሲኦል አንቅሐ።
@EOTCWW
ዚቅ፦
እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን
@EOTCWW
@EOTCWW
መልክዐ ኢየሱስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሓላ ዘኢይሔሱ፡ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሡ፡ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፡ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።
@EOTCWW
@EOTCWW
ዚቅ
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ ወይሴብሑ ለስምከ ዮም ታቦር
@EOTCW
ወረብ፦
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ በስመ ዚአከ/2/
ወይሴብሑ ለስምከ ይሴብሑ ለስም/2/
@EOTCW
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለልሳንከ በደብረ ታቦር ዘአልኆሰሰ፡ለብርሃን ዐቢይ እስከ ጽላሎቱ ተሐውሰ፡ ነበልባለ እሳት ክርስቶስ ዘተዋሐድከ ጳጦሰ፡በዋዕየ ፍቅርከ ከመ ሥርወ አእዋም የብሰ፤ውሣጤ ሕሊናየ ነደ ወልብየ ጤሰ።
@EOTCW
ዚቅ
ወሪዶሙ እምደብር እም ደብረ ታቦር አዘዞሙ ኢይንግሩ ዘርእዩ በደብር እስከ አመ ይትፈጸም በዕድሜሁ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ወሪዶሙ እምደብር እምደብር እምደብረ ታቦር ኢይንግሩ ዘርእዩ በደብር /2/
እስከ አመ ይትፈጸም በዕድሜሁ ይትፈጸም/2/
@EOTCWW
@EOTCWW
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለሰኰናከ እንተ ይስተጋብእ ኩሎ፡ ኃበ ኅደገ ወቀጽዐ ውስተ ሠሌዳ ኰኩሕ ሥዕሎ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመልአከ ዓለም ዘትትቤቀሎ፡ ስብሐቲከ እርአይ እግዚኦ እምቅድመ ዓለማት ዘሀሎ፤መንጦላዕተ ዓይንየ ቅላዕ ወአብርህ ጸዳሎ።
@EOTCWW
ዚቅ
ስብሐቲሁ ዘእምሃቤሁ ወውዳሴሁ እምዚአሁ አኃዜ አለም ለሊሁ ሰይፈ በቀል ውስተ እዴሁ ፍትሐ ግፉዓን ይወጽእ እምጽሩሕ
@EOTCWW
ወረብ
አሐዜ አለም ዘእምሃቤሁ ስብሐቲሁ ወውዳሴሁ እምዚአ/2/
ሰይፈ በቀል ውስተ እዴሁ ፍትሐ ግፉአን እምጽሩይ ህይወት/2/
@EOTCWW
@EOTCWW
መልክአ ኢየሱስ
እምኩሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፡ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፡ ተሰብኦተከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፡ ያንኰ ርኩር ታሕተ ደይን ግዱፈ ከዊኖ
@EOTCWW
@EOTCWW
ዚቅ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ነአምን ዘንተ ሥላሴ አሐዱ ውእቱ አምላክ ፍጹም ዘእምኔሁ ለአብ ወወልድ ተወልደ በአምሳለ ዚአሁ ኅቡር ህላዌሁ ነአምን ንሕነ ነአምን።
@EOTCWW
ወረብ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ/2/
አሐዱ ውእቱ አምላክ ፍፁም አሐዱ ውእቱ/2/
@EOTCWW
@EOTCWW
ምልጣን:-
ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል ለምንት ይትነሥዑ አድባር ርጉዓን ደብር ዘሠምሮ የኀድር ውስቴቱ እግዚአብሔር አማን ተሰብሐ በደብረ ታቦር።
@EOTCWW
አመላለስ፦
አማን በአማን ተሰብሐ"አማን በአማን"/2//2/
ተሰብሐ በደብረ ታቦር/4/
@EOTCWW
ወረብ፦
ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል ለምንት ይትነሥዑ አድባር ርጉዐን /2/
ደብር ዘሠምሮ የሐድር ውስቴቱ እግዚአብሔር/2/
@EOTCWW
@EOTCWW
እስመ ለዓለም
ወተወለጠ ራዕዮ በቅድሜሁ ወአልባሲሁኒ ኮነ ጸአዳ ከመ በረድ ይቤሎ ጴጥሮስ ለኢየሱስ ሊቅ ንንበር ዝየ ወንግበር ሠለስተ ማህደረ፤ማ-አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ፤ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማህደረ።
@EOTCWW
አመላለስ፦
አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ/2/
ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማህደረ/4/
@EOTCWW
@EOTCWW
ወረብ፦
ወተወለጠ"ራዕዮ በቅድሜሁ"/2/ /2/
ወአልባሲሁኒ ኮነ ጸአዳ ከመ በረድ/2/
https://t.me/Eotcw
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
