Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
الذهاب إلى القناة على Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
إظهار المزيد3 586
المشتركون
-124 ساعات
-17 أيام
+5430 أيام
أرشيف المشاركات
🟡የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??ሶስት(3) አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques A) ሜካኒካል ውስጥ :- 1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው:: 2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን 3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር ፀባይ ማግኘት እንችላለን B) ኬሚካል :- 1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡ 2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡ 3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡ C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:- 1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው 2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው 3. Dynamic Stabilization ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል:: ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡ ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡ 4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡ የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤ ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡ ቻናሉን አጋሩ! Share➡️ይደረግ! @con_site 🏗
🟡የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??ሶስት(3) አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques A) ሜካኒካል ውስጥ :- 1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው:: 2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን 3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር ፀባይ ማግኘት እንችላለን B) ኬሚካል :- 1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡ 2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡ 3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡ C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:- 1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው 2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው 3. Dynamic Stabilization ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል:: ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡ ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡ 4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡ የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤ ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
በውስጥ የደረሰን ጥቆማ
መንግስት ካደራጃቸው ማህበር አንዱን ውስጥ ተቀጥሬ ያየሁት ጉድ የሚመለከተው ሰው ብናገር ደስ ይለኝ ነበር።
አንድ ስሙን መግለፅ የማልፈልገው ማህበር ( የማህበሩ ዋና ባለቤት ) የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ የአንድ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ግንባታ ኮንትራት ወስዶ አማካሪው እና ኮንትራክተሩ በሙስና ተነጋግረው በግንባታው ላይ ዲዛይኑ ሚያዘው መስረት ከ120 ኪሎግራም ብረት ግማሹ ተቀንሶ 60 ኪሎ ያህል አስገብተው የሽንት ቤቱ ግራውንድ ኮንክሪት ተሞላና ተጠናቀቀ።
እኔ የምለው ምንም የማያውቁ ህፃናት ሽንት ቤቱ ተደርምሶ እንዳያልቁ መልክቴ ነው።
📍ቦታው ፡ አቃቂ ክ/ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ አለም ባንክ ፣ ፊታውራሪ አባይነህ አንደኛና ሁለተኛ (ከ 1 - 8 ) ትምህርት ቤት
ለሚመለከተው ኣካል በማጋራት አደጋ ከማድረሱ በፊት ልናጋራው ወደድን🤚
Detailed_Calculation_Concrete_Mix_Design_1723208991.pdf3.30 KB
የግንባታ ዝርዝር የአገልግሎት ስታንዳርዶች እዚህ ያገኛሉ!
🟡በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/🏗በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም #ግዚያዊ_ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ_ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡ ግዚያዊ_ርክክብ/ProvisionalAcceptance/ ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡ እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡ በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡ ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡ እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡ የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period) የመድህንነት_ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡ ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡ በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡ ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/ በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡ የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት (definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡ የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
+3
ማስታወቂያ:-NAYHAf Construction Metal Trading- አቅራቢ🏗 ጥራትና ታማኝነትን የተላበሰ አገልግሎት" ከደንበኞች አብዛኛሆቻችሁ ታውቁታላችሁ
መገኛ አድራሻው ቦታ:-📍- ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ
ስልክ ቁጥር:-🔺📞+251- 944454610 🔺📞+251- 952730999 #LTZ 28 #LTZ 38 #LTZ 48 #CHS ከ ባለ 12mm ጀምሮ .... #RHS #I BEAM #U CHANNEL #H BEAM #Mesh Wire #የ ኣጥር ሽቦ #Galvanized Pipe #Angle #Aluminium Sheet #D ብረት#8 ቁጥር #ፌርሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ! ስትፈልጉ በቀጥታ ይደውሉ.. .
" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጨረታና በዕጣ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባልገቡት ባለንብረቶች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋቃ።
የኮርፖሬሽንኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
- ከታኅሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ወደ ቤታቸው የገቡና ያልገቡትን የመለየት ሥራ ተጀምሯል።
- ከመስከረም 20 ቀን እስከ በጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የቤት ባለንብረቶች እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ነበር በድጋሚ ቀነ ገደቡን በማራዘም እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለንብረቶች እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር።
- ባደረገው ምልከታ ወደ ቤታቸው የገቡ፣ ያከራዩና በዕድሳት ላይ የሚገኙ አሉ።
- የተቀመጠው ቀነ ገደብ በመጠናቀቁ በሁሉም ሳይቶች የመለየት ሥራ ይጀመራል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዕጣ ተላልፎባቸው ቤታቸው ያልገቡትን ባለንብረቶች፣ ቤቶቹን ምን ለማድረግ ታስቧል ? ለሚለው ጥያቄ " ቀነ ገደቡ በቅርቡ በመጠናቀቁና ወደ ቤታቸው ያልገቡበትን ማለትም ፦
° በሕይወት አለመኖር፣
° መግባት አለመፈለግ፣
° በአገር ውስጥ አለመኖር፣
° በሕግ በተያዙ ጉዳዮችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መሆኑን ማጣራት ይደረጋል " ብለዋል፡፡
በዕጣና በጨረታ ተላልፈው ባለቤቶቻቸው ያልገቡባቸው ቤቶች ምን ያህል ናቸው ? ለሚለው ጥያቄ " መጠናቸው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሳይቶች እንደሚገኙ፣ ቁጥራቸውን ግን ይህን ያህል ነው ለማለት ያስቸግራል " ሲሉ መልሰዋል።
" ዋናው ነገር የቁጥር ጉዳይ አይደለም፤ ክፍት በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውንና ከተለያዩ ሳይቶች በርካታ አቤቱታዎች ለኮርፖሬሽኑ እየደረሱ በመሆኑ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " ያሉ ሲሆን " ባለቤቶቹ ያልገቡባቸው ቤቶች ከተለዩ በኋላ በቅርቡ ውሳኔ ይሰጣል " ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ፣ በሕግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው ከማቋረጥ ባለፈ በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ሕገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
መረጃውን ከሪፖርተር ጋዜጣ ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia
🟡QUANTITY SURVEYINGየብዛት ዳሰሳ ማለት በአጠቃላይ ቁሶች ዝግጅት እና መጠን ለግንባታ ፕሮጀክቶች መለካት QUANTITY SURVEYING የተለያዩ ስራዎችን ሊሸፍን ይችላል:- ✔️የዝርዝር ዝግጅት ✔️የኮንስትራክሽን ስራዎች መለኪያዎችን መውሰድ ✔️በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የግምታዊ ወጪ ግምት ዝግጅት የዝርዝር ወጪ ግምትን በተለያዩ ደረጃዎች ማዘጋጀት:- ➡️የንብረት ግምት የQUANTITY SURVEYING ዓላማ:- ደንበኛው ትክክለኛውን የስራ መጠን እና የሚፈለገው በጀት እንዲገመግም። ወጥ የሆነ የቁጥር መለኪያ በማቅረብ የጨረታዎችን ትክክለኛ ዝግጅት ለማገዝ። የተከናወነውን ሥራ ትክክለኛ ዝርዝር ለመስጠት። የክፍያ ማረጋገጫን ለማገዝ። የሚፈለገውን የሥራ መጠን ግንዛቤ ለመስጠት።
Manual for Materials List Preparation.docx0.96 KB
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
