cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB]

የ ኤልሳ[FB] ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል እነሆ ♥♥♥ በዚህ ቻናል የ ኤልሳ[FB]ን የስነ- ፅሁፍ ስራዎች በብቸኝነት እንዲሁም ሌሎች ውብ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ AMAZING QUOTES MIND QUESTIONS AND OTHERS! ግጥም ድርሰት አጫጭር አባባሎች ፍልስፍናዎች እና ሌሎችም! @fkerofficial ELSA[FB] OFFICIAL CHANNEL !

إظهار المزيد
Ethiopia4 667Amharic4 180الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
1 617
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-77 أيام
-4330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 43 ............. ወደኛ ሲዞር ደርቆ ቀረ አንዴ እኔን አንዴ ክርስቲን እያፈራረቀ አየን በእጄ የ ና አይነት ምልክት ስሰጠው ከሀሳቡ ነቅቶ ወደኛ መምጣት ጀመረ " ናኦዴ " ብሎ ሰላም አለኝ " ተዋወቁ ክርስቲ ትባላለች " አልኩት " ዮኒ ይባላል በጣም የምወደው ጓደኛዬና የስራ ባልደረባዬ ነው " አልኳት ወዲያው ፊቷን ፈገግ አድርጋ አየችው ስልኳን ጎምበስ ብላ አየችና " መመለስ ያለብኝ ስልክ ነው ይቅርታ " አለችና ተነስታ ወጣች ወዲያው ዮኒ ጎኔን እየገፋኝ " አንተ ትላንት ቀን ተከተልኳት ያልኩህ ልጅ እኮነች ትራፊኩ ያስመለጠኝ... ባለሀብት ያልኩህ ....ቆንጅዬዋ...እንደውም ጂፕ መኪና ውስጥ የነበረችው ቆይ እንዴት አገኘሀት ባለስልጣን ናት? የቢዝነስ ጉዳይ ነው ?... በምን አጋጣሚ ተገናኝታችሁ ነው? " እንዳወራ እድሉን ሳይሰጠኝ የጥያቄ ጋጋታ አወረደብኝ " በስራ ጉዳይ ነው ከለንደን ነው የመጣችው " አልኩት " የንጉሳውያን ቤተሰብ ዝርያ መሆን አለባት " አለኝ " ኧረ ሀበሻ ነች " አልኩት ወዲያው ተመልሳ መጥታ ስትቀመጥ " ተጫወቱ ቢንያምን የማወራው የግል ጉዳይ ስላለኝ ላናግረው " ብያቸው ቢንያም ብቻውን የተቀመጠበት ሶፋ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ " ቢንያም እንዴት ነህ" አልኩት የተሞላ ውስኪዬን ከብርጭቆዬ ላይ እየተጎነጨሁ " ደናነኝ እንዴት ነህ ናኦድ " አለኝ " ትላንት ከፊዮሪ ጋር ስለተፈጠረው ነገር ማወቅ እችላለሁ? " አልኩት " እኔ ምንም አላጠፋሁም ግን በቃ በጣም ቀረበችኝ እና ስታይል ለመቀየር የሸሚዜን ቁልፍ መፍታት ጀመረች ወደዚያው ፎቶግራፈሩ ፎቶ አነሳን እኔ ደግሞ የማፈቅራት ልጅ አለች ይሄ ፎቶ በምንም መልኩ እንዲደርሳት አልፈልግም ልጅቷ ደግሞ ከፊዮሪና ጋር ቅርብ ነች"' አለኝ እኔ የማላውቃት የፊዮሪ የቅርብ ሰው? " እና የፈለገ ቢሆን እንዴት በዛ ሁኔታ ጥለሀት ትወጣለህ ? " " አናዳኝ ነበር በጣም ... ግን አንተን እንዴት ሊያስቀይምህ ቻለ? " አለኝ " የስራ ባልደረባዬ የቅርብ ጓደኛዬም ጭምር ነች በምንም አይነት ሁኔታ እንድትከፋ አልፈልግም " አልኩት " አላወኩም ነበር " አለኝ " ነገ ይቅርታ ትጠይቃታለህ " አልኩት " እውነት ናኦድ ይሄ ከባድ ነው " አለኝ " ያ ከሆነ ከኔ ድርጅት ጋር ያለህን ስራ አስብበት ከ ክርስቲናም ጭምር " አልኩት " ኧረ... እሺ ይቅርታ " አለኝ " እሱን እኔን ሳይሆን ፊዮሪን ነው እንድትጠይቃት የምፈልገው " " እሺ እጠይቃታለሁ ግን ድጋሚ መስራት አልፈልግም " አለኝ " እሷ እስከፈለገች ድረስ ትሰራለህ ካልፈለገችህ አትሰራም.. ቢንያም እየጠየኩህ አይደለም እየነገርኩህ ነው " አልኩት " እሺ " አለኝ " ከዚህ ቦሀላ እሷን የሚያስከፋ ነገር ስታደርግ እኔን ማስቀየምህንም አብረህ አስብበት " አልኩት " እሺ ይቅርታ " አለኝ በመሀል ዞሬ ሳያቸው ክርስቲ እና ዮኒ እያወሩ ይሳሳቃሉ እብድ የሆነ ልጅ ምን እያላት ይሆን ? ወዲያው ስለፊዮሪ ጓደኛ ያወራኝ ትዝ አለኝ "በነገርህ የምታፈቅራትን ልጅ ግን አውቃታለሁ?" አልኩት " አዎ " አለኝ " ማናት? የ NF ድርጅት ባለቤት ፌቨን " አለኝ " ፌቨን ፌቨን ?" " ብዙ ቀን አብራችሁ አውቃለሁ ብዙ ቀን ፎቶዋ አለኝ እንደውም " አለና ስልኩን አውጥቶ ፎቶዋን አሳየኝ ተሳስቶም መሰለኝ " ፌቩ እኮ እኔ ድርጅት ውስጥ ነው የምትሰራው ፀሀፊዬ ነች " አልኩት " እንዴ እውነትህን ነው?... ስለሱ አላውቅም ነበር NF ድርጅት የሷ እንደሆነ እና ሌላ ስራ ስለምትሰራ ሉላን ወኪል አድርጋት እንደምትሰራላት አውቃለሁ አንተ ጋር ያውም ፀሀፊ ሆና እንደምትሰራ ግን አላውቅም ነበር " አለኝ " ሉላን እኮ ከዚህ በፊት ስለስራ ስናወራ የድርጅቱ ባለቤት እንደሆነች ነው የነገረችኝ " አልኩት " እኔንጃ እንግዲህ እኔ ይሄን ነው የማውቀው " አለኝ በጣም ግራ ገባኝ የሆነ ተልዕኮ ያላትም መሰለኝ ግን ደግሞ ፌቨን ሳውቃት በፍፁም መጥፎ ልጅ አይደለችም... ምን አይነት አላማ ይዛ ነው የድርጅትነት ባለቤት ሆና የኔ ፀሀፊ የሆነችው?.......... ይ... ቀ....... ጥ.......... ላ................ ል..................... @Fkerofficial
إظهار الكل...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 33 ................ዋናውን በር ማንኳኳት ጀመርኩ... ብዙም ሳትቆይ ከፈተችልኝ ልክ ሳያት ልቤ ሲረበሽ ይታወቀኛል... አቅፋ ሰላም ብላኝ ወደሶፋው ከመራችኝ ቦሀላ እሷ ከኪችን ምግቦቹን ወደ ጠረጴዛው ማውጣት ጀመረች... ፀጉሯን ወደኋላ አሲዛው ወርዶ ከወገቧ በላይ ደርሷል ከውስጥ ባደረገችው ጥብቅ ያለ ቦዲ ላይ ሰፊ ሸሚዝ ደርባበት ከታች ጥቁር ቬል ለብሳለች ብቻ አጠቃላይ አለባበሷ ባትዘንጥም ውበቷን የሚከልል አይደለም ስትጨርስ ራት ከበላን ቦሀላ ወደሶፋው ተመልሰን ወይን ቀድታ መጠጣት ጀመርን " ለግብዣው በጣም አመሰግናለሁ " አልኳት " ምንም አይደለም " አለችኝ ፈገግ እያለች " እውነት ለመናገር ውለታህ አለብኝ ማንም ሰው በዚህ ሰአት ለማያውቀው ሰው እንደዚህ አያደርግም እኔ ደግሞ ህይወቴን ሊያተርፍ የሚችል ዘመድም ቤተሰብም የለኝም በዚህ ሰአት አንተ ባትኖር እሞት ነበር " ካለችኝ ቦሀላ ሳምሶናይት ይዛ መጣች " እባክህ ተቀበለኝ ውለታህ እንቅልፍ እየነሳኝ ነው እኔ መልካምነትህ ይበቃኛል " ብላኝ ከፍታ ሰጠችኝ... ሳየው ሙሉውን ብር ነው 3ሚልዮን ብቻም አይመስልም "ምንድነው? " አልኳት " እባክህ እምቢ እንዳትለኝ " አለችኝ " መልካም ነህ ካልሽኝ ለምን መልካምነቴን ታረክሺብኛለሽ? ለምን ሰጥቶ የመቀበል ስሜት እንዲሰማኝ ማድረግ ፈለግሽ? እውነት ፊዮሪ ይሄን ካንቺ አልጠብቅም ነበር አዝናለሁ " ብያት ሳምሶናይቱን ዘግቼ ከቤቷ ወጣሁ ከሳሎኗ ትጠራኛለች ብዬ እርምጃዬን እየቆጠርኩ ነበር የወጣሁት ግን አልጠራችኝም... ባለመጥራቷ እየደነገጥኩ እና ግራ እየተጋባሁ ወደመኪናዬ ስሄድ " ናኦድ... ናኦድ " እያለች እየጠራችኝ ወጣች አቤት ሳልላት ፊቴንም ሳላዞር ቆምኩ ዞራ ከፊቴ መጥታ "እሺ በጣም ይቅርታ እውነት ያስከፋሀል ብዬ አልነበረም " አለችኝ "እሺ ችግር የለውም " አልኳት ፊቴን ሳልፈታ " እሺ እንግባ?" አለችኝ ክንዴን እየያዘች ዞሬ አብሪያት ገባሁና ነበርኩበት ጋር ተቀመጥኩ " እውነት እኔኮ በጣም ስለከበደኝ ነው " አለችኝ " እኔ ላንቺ ጥሩ ማድረግ አልችልም? " አልኳት " እሱማ ትችላለህ... ግን እኔ ምንም ሳላደርግ ከሰዎች መቀበልን ስላልለመድኩ ይከብደኛል እሺ ሌላ ምን ላድርግልህ የምትፈልገው ነገር አለ?" አለችኝ... ትህትናዋ ፍፁም የማላውቃት ፊዮሪ ሆነች ልበ ደንዳናዋን ፊዮሪ አጣኋት ሙሉ በሙሉ ወደትላንቷ ፊዮሪ የተመለሰችም መሰለኝ "አዎ አለ " አልኳት " ምን? " አለችኝ በጉጉት እየጠበቀች "መጀመሪያ ግን ምንም ቢሆን ልታደርጊልኝ ቃል ግቢልኝ" አልኳት " ምንም ቢሆን ማለት?... ብዙ ነገር አለኮ " አለች " አንቺን እስካልጎዳሽ ድረስ እሺ በይኝ " " እሺ... ካልጎዳኝ" " ፕሮሚስ?" እጄን እየዘረጋሁ " ፕሮሚስ" አለችኝ እጄን እየመታች "እሺ 2 ነገሮች እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ " አልኳት " ምን እና ምን?" "የመጀመሪያው ሲጋራ ማጨስ እንድታቆሚ " " ማለት ለምን?... ማለቴ ያ ላንተ ምን ይጠቅምሀል ? " "ቃል ገብተሻል " "በቀላሉ የሚተው ነገር እኮ አይደለም" " አውቃለሁ ግን በሂደት... ቢያንስ በአንድ ወር ውስጥ " "እሺ" አለችኝ " ስለዚህ ተስማምተናል " ስላት "አዎ 2ኛውስ ምንድነው ? " አለችኝ " ማጨስ የጀመርኩት በምክንያት ነው ብለሽኝ ነበር " "አዎ " " ሌላ ጊዜ እነግርሀለሁ ካልከሽኝ ታሪክ ጋር አንድ ላይ ንገሪኝ " ወዲያው ፊቷ ላይ የሀዘን ጥላ ሲያጠላ ይታያል.... መጠጥ ከቀዳች ቦሀላ ጠጥታ መሬት መሬት ማየት ጀመረች " እየጠበኩሽ ነው " አልኳት " እንደዚህ ለመሆኔ መጀመሪያው አንድ ሰው ነው " " ማነው እሱ? " " ናዖድ "..................... ይ.. ቀ..... ጥ....... ላ............ ል................. @fkerofficial
إظهار الكل...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 42 .............ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡብኝ ከክርስቲ ጋር ደግሞ ምን ይሰራል ? ገብተው ሰላም ብለውኝ ተቀመጡ ክርስቲና " አንዴ ቢኒ ከ ናኦድ ጋር ማውራት ያለብን ነገሮች አሉ እስከዛ ዘና በል " አለችው " እሺ " ብሎ እዚሁ ቦታ ቀይሮ መዝናናት ጀመረ " ቢንያምን የት ነው የምታውቂው ?" አልኳት " ታዋቂ ሞዴል አይደለ እሱን የማያውቅ ሰው አለ እንዴ? አንተንም እንዳገኝ የረዳኝ እሱ ነው " አለችኝ " ማለት የስራ ግንኙነት አላችሁ ወይስ? " " አይ ታዋቂ ሞዴል ስለሆነ ወደፊት ለስራችን ይጠቅመናል ብዬ ስላሰብኩ ነው " አለችኝ " ጥሩ " አልኳት " ምነው ደበረህ ? ካልፈለክ አይሰራም " አለችኝ " ያንቺ ቢዝነስ እኮነው ከኔ ቅሬታ ጋር ምን አገናኘው " " ይገናኛል እንጂ " " እንዴት ? " " ናኦድ... ለንደን እያለሁ በጣም ነበር ስላንተ የማስበው በሄድኩበት ሁሉ ስላንተ ነው የሚወራው በፎቶ እንኳን አላውቅህም ነበር የሆነ ቀን ከ ቪክቶሪያ ሴክሬት ካምፓኒ ጋር ስለስራ እያወራን ድንገት ያንተን ስም አንስተው ሲያወሩ ነው ከነሱም ጋር እንደምትሰራ ያወኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቶህን ያየሁት official ስብሰባ ላይ ነበር ስብሰባው ላይ ያልተገኙት ተብሎ ሲዘረዘር አቶ ናኦድ ከ ኢትዮጵያ ተብሎ በፕሮጀክተር " አለችኝ " ኦ የዛ ኮንግረስ አባል ነሻ... እና የቢዝነስ አይዲያ ይዘሽ ነዋ የመጣሽው " አልኳት " አዎ ካንተ ድርጅት ጋር መስራት እፈልጋለሁ ግን ከዛም በላይ የሆነ ጉዳይ ይዤ ነው የመጣሁት " አለችኝ " ምንድነው እሱ " " ፍቅረኛ አለህ " " አይ... ምነው ? " " ፎቶህን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየሁበት ቀን ጀምሮ ስላንተ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም ሳላውቅህ ሳላይህ ነው የተሸነፍኩልህ ለራሴ ህልም እና የማይሆን ነገር እንደሆነ ለመንገር ብዙ ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም.... ኢትዮጵያ የመጣሁት ከስራው በላይ እንቅልፍ የነሳኝን ጉዳይ ፈትቼ ለማረፍ ነው... ናኦድ ሳላውቅህ በስም ብቻ ማረከኝ ፎቶህን ሳይ ይበልጥ ተማረኩብህ ባካል ሳይህ ግን አልቻልኩም.... አፍቅሬሀለሁ " አለችኝ ቆንጆ እንደሆንኩ አውቃለሁ በተወሰነ መልኩም ተፅእኖ ፈጣሪ እና ታዋቂ ግን በዚህ ልክ ለንደን ድረስ ያውም ይቺን ልዕልት የመሰለች ቆንጆ የሚያሳስት ማንነት ይኖረኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ለምን ፍቅረኛ የለኝም አልኳት ? ከፊዮሪ ሌላ ሴት ማሰብ እንደማልችል እያወኩ... እርግጥ ነው ፍቅረኛ የለኝም... የስራ ጉዳይ ቢሆንስ ብዬ ነዋ... ከራሴ ጋር በሆዴ እያወራሁ እየጠጣሁ በመሀል ከሀሳቤ አቋረጠችኝ " አሁን ላይ ማውራት የነበረብኝ ነገር እንዳልሆነ አውቃለሁ ያገናኘን ስራ ነው በዛላይ በደምብ አልተግባባንም... ግን ጥያቄህን ለመመለስ ያክል ነው ለዚህ ነው የኔ ቢዝነስ ጉዳይ የሚመለከትህ" አለችኝ " መልካም... ከ ቢንያም ጋር መስራትሽ ያስደስተኛል አያስደስተኝም የሚለውን ሌላ ጊዜ እናወራበታለን ያንቺ የቢዝነስ ሀሳብ ምን ነበር? " አልኳት " ኧ... የኔ የልብስ ብራንድ የራሱ የሆኑ ምርቶች አሉት እነሱን import እንድታደርግልኝ እና በወኪልነትም ጭምር ኢትዮጵያ ውስጥ እንድታከፋፍልልኝ እፈልጋለሁ ይሄን ስራ ደግሞ በአመታዊ የኮንትራት ቢዝነስ እንደምትሰራ ስለሰማሁ የቀጣዩን አመት ውል ከኔ ካምፓኒ ጋር እንድታደርግ እፈልጋለሁ " አለችኝ " አዝናለሁ ያልሽው ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ ቅርብ ጊዜ ሁለት ወር ከማይሞላ ጊዜ በፊት ከሌላ ድርጅት ጋር ተዋውዬ ጨርሻለሁ " አልኳት "ኦ እውነት ? " አለችኝ " አዎ" " ሌላ ባንተ ዙሪያ ያለ የምታውቀው ድርጅት አለ? " አለችኝ " እስኪ ልሞክር " አልኳት በዝምታ መጠጣት ጀመርን በጣም ቆንጆ ናት አለባበሷ ደግሞ ከምንም በላይ ግን ሁሉም ውበቷ ተደምሮ እንኳን የፊዮሪን ሩብ በልቤ ላይ ሚዛን አይደፋም ይሄን እያሰብኩ እያየኋት ድንገት ዮኒ መጣ ልክ የቪአይፒውን ክልል እንደተቀላቀለ አይኑ ቢንያም ላይ ነው ያረፈው በቁሙ ሰላም ብሎት ወደኛ ሲዞር ደርቆ ቀረ........ ይ.. ቀ..... ጥ........ ላ............. ል.................. @fkerofficial
إظهار الكل...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 41 ............ወዲያው ወደሳሎን አይኗን እያሻሸች መጣች ስታየኝ በጣም ደነገጠች " እ.. እንዴ ናኦድ ..." አለችኝ የአግራሞት ፈገግታ ፈገግ እያለች " ወዬ " አልኳት " እዚህ አድረህ ነው? " አለችኝ " አዎ " አልኳት " ማታ ደክሞህ መሆን አለበት " አለችኝ " አዎ ያው ሰካራም ጠባቂ ያስፈልገዋል ብዬ ነው " አልኳት "what? ሰክሬ ነበር? " አለችኝ ሳቋ እየመጣ " ስካርስ ቢሉሽ ስካር ነው? " አልኳት " ምን አደረኩ በናትህ? " አለችኝ " ስትሰክሪ ምንድነው የምታደርጊው" አልኳት " ሰክሬ አላውቅም " አለችኝ " ሀሀሀ ኧረ ቀልድ " " እውነት ሞቅ ሊለኝ ይችል ይሆናል እንጂ በፍፁም ሰክሬ አላቅም " አለችኝ እውነትም ሳስበው መጀመሪያ መጠጥቤት ያገኘኋት ቀን ያን ሁሉ ጠጥታ ትንሽ እንኳን ወልገድ አላለችም ነበር... ምናልባት ሻት ማድረጓ እንደሆነ ብዬ አሰብኩ " እና ትላንት ምን ተገኝቶ ነው?" አልኳት " ያ ቢንያም ነዋ " አለችኝ " በይ በይ ... ንዴት በእንቅልፍም አይወጣልሽም እንዴ? " አልኳት " ሀሀሀ እሺ ትቼዋለሁ" አለች " ሰአቱ እየሄደ ነው ስራ መግባት አለብኝ " አልኳት " ቆይ እንጂ ቁርስ ብላ " አለችኝ " ደርሷል ?" አልኳት " ኧረ አሁን ገና ነው የተነሳሁት ግን አይቆይም 5 ደቂቃ ብቻ አለችኝ " እውነት ለመናገር እርቦኛል ግን ላስለፋት አልፈለኩም " ችግር የለውም ሌላ ቀን " ብያት ጫማዬን አጥልቄ ወጣሁ ከዋናው በር እንደወጣሁ ነበር መኪናዬን ከአጥር ውጪ እንዳቆምኩ ሳላስገባው ማደሬ ትዝ ያለኝ እሷ ነበረች እኔ የሰከርነው ብዬ በራሴ ፈገግ አልኩ ስልኬን አውጥቼ ሳየው ባትሪ ዘግቷል ወዲያው ዮኒ ትዝ አለኝ ከአጥር ውጪ ወጥቼ መኪናዬን አስነስቼ መጀመሪያ ቤት ሄድኩ ስልኬን ቻርጅ ሰክቼ ወደ እንግዳ መኝታ ክፍል ስሄድ ዮኒ ብርድልብሱን ሳይገልጥ ጫማውን ሳያወልቅ እግሩ ከጉልበቱ በታች አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከላይ ተኝቷል መስኮቱም አልተዘጋም ቀሰቀስኩት እና ወዲያው እንደነቃ ተነስቶ አወራኝ " ናኦድ ምን ሆነህ ነው ? ስልክህ እኮ አይሰራም እዛው አድረህ ነው? ደናነህ? " አለኝ " አዎ እምዳጋጣሚ አላየሁትም ነበር ስልኬ ዘግቶ ነው ጠዋት ነው መዝጋቱንም ያየሁት " አልኩት " ስጠብቅህ ነበር እኮ ሌሊት ድረስ መቼ እንቅልፍ እንደወሰደኝም አላውቅም " አለኝ "ይቅርታ በጣም " አልኩት " እንዴት ነበር ግን በምን ምክንያት አደርክ እደር አለችህ? " አለኝ " አይ.. በጣም ተናዳ ሰክራ ነበር " አልኩት " በምን ነግራሀለች?" አለኝ " ቢንያም በጣም አናዷታል አወራዋለሁ " አልኩት " ምን አድርጎ " አለኝ የነበረውን ነገር በሙሉ ነገርኩት " ይገርማል ቢንያም ፊዮሪ ላይ ኮራ ነው የምትለኝ ?" "እሷ እኮ በሌላ ነገር አላሰበችውም ራሱን ሲቆልል ነው " አልኩት " በሷ መነካት አግኝቶ ነው እንዴ?" አልኩት " እኮ " " እና ግን እንዴት ነው ሰክራለች ብለኸኝ ነበር..." አለኝ " አዎ ተናዳ ጠጥታ ነበረ" " ታዲያ የት አደረች? " አለኝ " ቤቷ ነዋ " " ቤቷማ ቤቷ ነው እንኳን እሷ አንተም አድረህበታል... ክፍሉን ነው ያልኩህ " " መኝታ ክፍሏ ነዋ እኔ እኮነኝ ያስተኛኋት " " ወንዳታ ... እና እንዴት ነው ምንም አልተፈጠረም ? " አለኝ " ምን አስበህ ነው.. ኧረ ሳሎን ነው የተኛሁት " " እ? " አለኝ " አዎዋ አስተኛኋት በሩን ቆልፌ ተኛሁ " አልኩት " በል ከዚህ በላይ ከቆየን በጣም ታስቀይመኛለህ " አለኝ " ስለሱ ጉዳይ እኮ አውርተንበት ጨርሰናል " አልኩት " እኔ የምለው ግን አባቷ ነህ?" " በምን እድሌ አልኩት" " ከቆየሁ ታናድደኛለህ ብዬህ ነበር " አለኝና ወጣ " ማታ እተለመደው ቦታ እንገናኝ " አልኩት ጮክ ብዬ " እንደዋወል " ብሎኝ መኪናው ውስጥ ገባ ስራ ቦታ ስሰራ ውዬ ክርስቲን ለማታ የቀጠርኳት የኔና የ ዮኒ የተለመደ ቪአይፒ ቦታ ሄጄ ተቀመጥኩ ወዲያው ብዙም ሳትቆይ ቢንያም እና ክርስቲ አብረው መጡ ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡብኝ ከክርስቲ ጋር ደግሞ ምን ይሰራል ?....................... ይ.. ቀ.... ጥ...... ላ.......... ል............... @fkerofficial
إظهار الكل...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 40 ..........."ፊዮሪ " የሚለው ንቅሳቴ ትዝ ሲለኝ በድንጋጤ ክው አልኩ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ዞሬ አይኗን ማየት አቃተኝ ግን ሳስበው ዞሬ ከምቀር ፊቴን አዙሬ ባስቀይስ ይሻለኛል ብዬ ወዲያው ፊቴን ወደሷ ሳዞር ፊቷ ላይ ምንም አዲስ ነገር አላየሁም አላየችውም ማለት ነው? " ቶሎ ልበስ " ብላኝ ወጣች ከወጣች ቦሀላ ትከሻዬን ሳየው ለካ ከተነቀስኩበት ጀርባዬ አቅጣጫ ሸሚዜን አንጠልጥዬበት ነበር.. እፎይ ብዬ ልብሴን ለብሼ ወጣሁ ስወጣ ቢሮ ማንም የለም ፊዮሪ ብቻዋን ቆማለች " ጨርሰናል... በጣም ነው የማመሰግነው ናኦዴ " ብላ መጥታ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት " ቤት እንሂድ? " አለችኝ ከእቅፌ እየወጣች " እሺ " ብያት ተያይዘን በየራሳችን መኪና ወደሷ ቤት ሄድን... ውስጥ እየገባን ስልኬ ጠራ የማላውቀው ስልክ ነው አነሳሁት " ሄሎ ናኦድ " የሴት ድምፅ ነው " አቤት ? " " ደናነህ?" " ይመስገን ማን ልበል " አልኳት " ክርስቲ ነኝ " አለችኝ " ክርስቲ እንዴት ነሽ?" " አለሁልህ አሁን ፈልጌህ ነበር እንገናኝ ? " አለችኝ " አሁን እንኳን አልችልም " " ለምን ? " አለችኝ " የግል ፕሮግራም አለኝ ነገ መሆን አይችልም? " አልኳት " እሺ በቃ " " እሺ ደናደሪ " " አሜን " ብላኝ ዘጋችው ፊዮሪ እራት አቅርባ ከበላን ቦሀላ ውስኪ ከፍታ መቅዳት ጀመረች " ታቃለህ ግን ማንም እንደዚህ ንቆኝ አያውቅም " አለችኝ " አልገባኝም " አልኳት " ቢንያም ነዋ " አለችኝና ሙሉ ብርጭቆውን ሙሉውን በአንድ ትንፋሽ ግጥም አደረገችው ... ደነገጥኩ " ቆይ እኔ... ባስበው እራሱ አንሼበት ነው? እንደዛ እየተመናጨቀ የወጣው?" አለችና ሁለተኛ ሻቷን ግጥም አደረገችው " በቃሽ በቃሽ " ብዬ ልትቀዳ ስትል ልከለክላት ሞከርኩ እጄን ወደዛ ገፍታ ድጋሚ ቀዳች " ልጠጣ እንጂ ቤቴ አደል እንዴ ? " አለችኝ " ፎቶግራፎቹን ኢሜይል አድርገሻል? " አልኳት " እሱ የኔ ሳይሆን የ ኤደን ስራ ነው ፎቶግራፈሩ ደግሞ ይልክላታል " አለችኝ አፏ መኮላተፍ ጀምሯል በዛ ላይ አንድ ብርጭቆ ሙሉውን ግጥም አድርጋ ጠጣችውና " ሰው እ..እንዴት የሸሚዝ ቁልፌ ተነካ ብሎ እንደዛ ይሆናል.. ደሞኮ.. ያረኩት.. ቆ.. ቆይ ላሳይህ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ሶፋውን እየተደገፈች መጥታ አጠገቤ በጣም በቅርበት ተቀምጣ " እንደዚህ እኮነው የፈታሁት " እያለች ሸሚዜን የደረት ቁልፍ መክፈት ጀመረች... ስካሯን ከመንገዳገዷ በላይ የንግግሯ ቃላቶች መያያዝ ይናገራል የሸሚዜን ቁልፍ እስከ እምብርቴ ድረስ ከፈታችው ቦሀላ " እንደዚህ እኮነው የፈታሁት " አለችኝ በአግራሞት ዝም ብዬ አየኋት ሰው እንዴት ሲሰክርም ያምርበታል? " እ... ይሄ ያስቆጣል? " አለችኝ " አያስቆጣም " አልኳት " እኮ.. እኮ አያስቆጣም " ብላ አቀፈችኝና ደረቴን ተደግፋ ጋደም አለች አቅፌ ፀጉሯን እያሻሸኋት ጥቂት ጊዜ በዝምታ ቆየን... ቀና ብዬ የግድግዳ ሰአቱን ሳይ ሰአቱ መሽቷል " ፊዮሪ " አልኳት መልስ አልሰጠችኝም " ፊዮሪ.... ፊዮሪ መሽቷል ልሂድ " አልኳት መልስ የለም አንገቴን አጎምብሼ ሳያት እንቅልፍ ወስዷታል ቀስ ብዬ ከደረቴ ላይ አንስቻት ትራስ ካስደገፍኳት ቦሀላ መኝታ ክፍሏን ከፍቼ ገብቼ አልጋዋን ገልጬ አቅፌ ይዤ አስገብቼ አስተኝቻት ልወጣ ስል ትዝ ሲለኝ በሯን ማንም ከውስጥ አይቆልፈውም የማደርገው ግራ ገባኝ ሳስበው ትቻት ሄጄ የሆነ ነገር ሆና ከሚፀፅተኝ እዚሁ ስጠብቃት ባድር ይሻለኛል.... በሩን ከውስጥ ቆልፌ ኮቴን አውልቄ ከወገቤ በታች እግሬን ለብሼው ተኛሁ... . . . ጠዋት ስነቃ ማንም የለም ሰአቴን ሳይ 1:30 ይላል የሰው ኮቴ ተሰማኝ ፊዮሪ ተነስታለች ማለት ነው... ወዲያው ወደሳሎን አይኗን እያሻሸች መጣች ስታየኝ በጣም ደነገጠች........... ይ.. ቀ.... ጥ...... ላ........... ል............... @fkerofficial
إظهار الكل...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 39 .............ወዲያው ፊዮሪ ተከትላው ወጥታ በር ላይ ቆመች ሁለተኛውን በር ከፍቶ ሳይወጣ ማውራት ጀመረች " ሂዳ አንተ ብቻ አይደለህም እኮ ሞዴል " አለችው በንዴት ጉንጯ ቀልቷል " ምንድነው ፊዮሪ " አልኳት "በጣም አበዛው ስራ እኮነው የያዝነው " አለች " ምን ሆኖ ነው" አልኳት " ሰው የሸሚዜን የደረት ቁልፍ ለምን ነካሽ ብሎ እንደዚህ ይሆናል እንዴ?" ስራ አይደል እንዴ የያዝነው?" አለች " ማለት የምን ስራ? " አልኳት " ዛሬ ምሽት ፎቶ አንስተን ወደውጪ የምንልካቸው ዲዛይኖች አሉ እሱ ደግሞ ውጪ ድረስ ሄዶ ስለተወዳደረና ስለሚያውቁት በዛላይ የሰውነት አቋሙ ስለሚያምር ነው የመረጥኩት... ማን ስለሆነ ነው እሱ የሸሚዜን ቁልፍ ነካሽ ብሎ እንደዚህ የሚሆነው ፊዮሪና እኮነኝ ስራ ስለሆነ እንጂ ቢለምነኝ እንደማላደርገው ያውቃል " አለችኝ ወዲያው አንድ ሴት ቦርሳዋን ይዛ ከውስጥ ወጥታ " ይቅርታ ፊዮሪና እኔ የምሰራው በቢንያም ስር እንደሆነ ታውቂያለሽ ምንም ማድረግ አልችልም " ብላት ወጣች ፊዮሪ ወደውስጥ ስትገባ ተከተልኳት በቢሮዋ ውስጥ አልፋ ሌላ በር ከፍታ ገባች ተከትያት ስገባ በጣም የሚያምር የፎቶ ስቱዲዮ ነበር አንድ ሴት ሜካፕ ይዛ ቆማለች አንድ ወንድ ደግሞ ካሜራ ይዟል... እንደዚህ የሚያምርና ሚስጥራዊ ቦታ ያለ ስቱዲዮ ገጥሞኝ አያውቅም በጣም ያምራል ወደ 10 የሴትና የወንድ ልብሶች በልብስ ማንጠልጠያ ተንጠልጥለዋል.... አይታቸው ተመልሳ ወደቢሮዋ ወጣች ተከትያት ወጣሁ በንዴትና በጭንቀት ቢሮ ወምበሯ ላይ ተቀመጠች " መጀመሪያ አንቺ ተረጋጊ " አልኳት " እንዴት ነው የምረጋጋው ቀብድ 20,000 ዶላር የተቀበልኩበት ስራ ኮነው ዛሬ ካልላኩላቸው አያምኑኝም ማታ ኢሜይል እንዳደርግላቸው ከሳምንት ጀምሮ ነግረውኛል " አለችኝ " ናኦድ " አለችኝ መልሳ " ወዬ " አልኳት " እባክህ እምቢ እንዳትለኝ " አለችኝ " ምንድነው " አልኳት " እባክህ አንተ የወንዱን ሞዴል ስራልኝ " አለችኝ በተስፋ አይን ተነስታ አጠገቤ ቆማ እያየችኝ "እ?" አለችኝ መልስ ስታጣ አይን አይኔን እያየች... ወዲያው ዮናስ የትም ቢሆን ልብስህን እንዳታወልቅ ያለኝ እና ንቅሳቴ ትዝ አለኝ " ፊዮሪ እንደሱ እንኳን አይሆንም " አልኳት " ለምን? " አለችኝ " አይሆንም... ብሩን ግን ልከፍልልሽ እችላለሁ " አልኳት " ብሩን አይደለም እኔኮ ሌላ የውጪ ደምበኛ የለኝም " አለችኝ "ሌሎች ብዙ ብራንቾች ላገናኝሽ እችላለሁ " አልኳት " እሺ ተወው በቃ " ብላኝ አይኗ እምባ አቀረረ እንደዛ የምሳሳለት አይን ድጋሚ በኔ ምክንያት እምባ አግቶ ሳየው የምገባበት ጠፋኝ... ወደራሴ አስጠጋኋትና ደረቴ ጋር አስጠግቼ አቀፍኳት እምባዋን እየጠረኩ ባንድ እጄ ፀጉሯን እያሻሸሁ " እሺ... እሺ በቃ ..." አልኳት ከደረቴ ላይ ፈንጠር ብላ ተነስታ እምባ ባጨማለቀውና ደስታ በሚያስተጋባው ፊቷ እያየችኝ " እውነት?" አለችኝ " አዎ... ግን ሴትም ሞዴል የለሽም እኮ " አልኳት " ችግር የለውም ራሴ ሰራቸዋለሁ " አለችኝ የሴቷን የሞዴሊንግ ቦታ የምትሸፍነው እሷ እንደሆነች ሳውቅ ነው ሊያመልጠኝ የነበረው እድል የገባኝ ውስጥ ገብተን ሜካፕ ባለሙያዋ ይዛት ገባች እኔ እዛው ከላይ የሚቀየረውን አንዱን ልብስ ቶሎ ሳትመጣ ቀይሬ ከስርም ሱሪዬን ቀየርኩ ደስ የሚለው የወንድም የሴትም ልብስ መቀየሪያ ክፍል መኖሩ ነው ቀይሬ ላይ የለበስኩትን አንገቴ ድረስ ቆልፌ ወጣሁ ፊዮሪ ትንሽ ቆይታ ከሚያምርና በላባ ከተሞላ ልብስ ጋር ልእልት መስላ ወጣች ሳያት እንደ አዲስ ደነገጥኩ ከሜካፑ ጋር ይሁን... ብቻ አላውቅም እንደዚህ አምሮባት አይቻት አላውቅም እሷም አይታኝ " ዋው! የደረት ቁልፍህን ክፈተው " አለችኝ " እኔኮ ብትከፍቺልኝም.. አልነሳም ብዬ አልወጣም " አልኳት እየሳቀች መጥታ ተራ በተራ ከፈተችልኝ "ኧረ ፐለው... እንደዚህ አቋም እንዳለህ አላውቅም ነበር " አለችኝ " አመሰግናለሁ አለቃዬ " አልኳት ፈገግ ብላልኝ በተለያየ ልብስ በተለያየ ስታይሎች ፎቶ ተነሳን አንዳንዶቹ ስታይሎች እኔና እሷን ከመጠን በላይ ስለሚያቀራርቡ ፈትነውኝ ነበር... እንደምንም ጨርሰን ልብሴን ከስር ለብሼ ከላይ ሸሚዜን አጊንቼው ትከሻዬ ላይ አድርጌው ኮቴን ከልብሶቹ መሀል እየፈለኩ ከላይ ሳልለብስ ድንገት ፊዮሪ ከኋላዬ መጣች ጀርባዬ ላይ ያለው "ፊዮሪ" የሚለው ንቅሳቴ ትዝ ሲለኝ በድንጋጤ ክው አልኩ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ዞሬ አይኗን ማየት አቃተኝ .............. ይ.. ቀ..... ጥ....... ላ............ ል................ @fkerofficial
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.