cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ድንቃ ድንቅ ኢስላማዊ ወጎች👌👌

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ድንቅ ኢስላማዊ ወጎችን እንዲሁም ለናንተ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ኢስላማዊ ታሪኮች እናቀርብላችኋለን

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
199
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

00:46
Video unavailableShow in Telegram
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤) «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦) «ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም። ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን።
إظهار الكل...
የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ ~ ~ ~~ ~ ~ 1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም] 2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው”  ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው”  ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570] 5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!”  ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403] 7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)”  ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ተጠንቀቅ! 1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644] 3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡ ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡ 1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡ 3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡ 4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡ 5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡ 6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡ @yasin_nuru @yasin_nuru
إظهار الكل...
የአላህን እዝነት ተመልከቱ!! 🍂ከቁርኣን አንድ ሀርፍ የቀራ ሰው 10 አጅር ያገኛል። «አሊፍ፣ ላም፣ ሚም» ያለ ሰው 30 አጅር ያገኛል። 🍂«ቁል ሁወ‘ላሁ አሀድ»ን የቀራ ሰው የቁራኣንን 1/3 እንደቀራ ይፃፍለታል። 🍂ሰላሳ አያዎችን ያላትን «ሱረቱል ሙልክ»ን የቀራ ሰው… ታማልድለታለች፣ ወንጀሉም ይማራል። 🍃አላህን ሚያስታውስ ሰው አላህ ያስታውሰዋል። 🍃በአላህ መንገድ ከመግደልና ከመገደል በላይ ዚክር ማድረግ በላጭ ነው። 🌴ሱብሀነላህ፣ አልሀምዱሊላህ፣ ክኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር… ፀሀይ ከወጣባቸው ቦታዎች ባጠቃላይ በላጭ ናቸው። የጀነት ተክሎችም ናቸው። 🍃100 ጊዜ ሱብሀነላሂ ወቢሀምዲሂ ያለ ሰው… ወንጀሉ የበህር አረፋ ቢያህል እንኳን ይማርለታል። 🍃100 ጊዜ ‘ላ ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይዒን ቀዲር’ ያለ ሰው… 10 ባሪያ ነፃ እንዳወጣ ይያዝለታል። 100 ወንጀል ይማርለታል፣ 100 ምንዳ ያገኛል፣ ከሸይጣን ይጠበቃል፣ ማንም የሱን ያህል ምንዳ አያገኝም እሱ ያለውን ያህል ያለ ወይም ከሱ በላይ ያለ ሰው ሲቀር። 🌴‘ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ’ የጀነት ተክል ነው። በነቢዩ ላይ አንዲትን ሰለዋት ያወረድ አላህ በሱ ላይ 10 ያወርዳበታል። 🌼ውዱእን አስውቦ ያደረገ ሰው ወንጀሉ ይማርለታል። ፊቱን ሲታጠብ በአይኑ ያየው ወንጀሉ ይገርፋል። እጁን ሲታጠብ በጁ የሰራው ይወጣል፣ እግሩን ሲታጠብ በእግሩ ወደ ወንጀል የሄደበት ወንጀሉ ይጠራል። (ከወንጀል ጠርቶ እስኪወጣ ድረስ።) 🌼ቤቱ ውድዕ አድርጎ ወደ መስጂድ የሚሄድ ሰው በአንድኛው እርምጃው ወንጀሉ ይታበሳል፣ በሌላኛው አጅር ይፃፍለታል። ውዱኧን፣ ኩሹኧን፣ ሩኩኣን አስተካክሎ ዋጂብ ሰላትን የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳለ ይማርለታል። (ከባኢሮች ሲቀሩ።) 🌼ውዱእ ሳይፈታ እዛው የሰገደበት ቦታ ላይ የዘወተረ ሰው… መላኢካዎች ምህረትን ይጠይቁለታል። ‘አላህ ሆይ! ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት!’ ይላሉ። 🌼ኢሻን በጀመኣ የሰገደ ሰው ሌሉትን ግማሽ እንደቆመ ይፃፍለታል፣ ፈጅርን በጀመኣ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደሰገደ ይፃፍለታል። በፈጅርና በኢሻ ውስጥ ያለን ምንዳ ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ በእንብርክካቸውም ቢሆን ይመጡ ነበር። 🌼የፈጅር ሱና ከዱንያን ውስጡ ካለው ነገር ባጠቃላይ በላጭ ናት። 🌼በአላህ ላይ ምንዳውን ተሳስቦ ለይልን የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳል ይሰረያል። ⚡️ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው… የፆሚን ምንዳ ያገኛል። @anbeb_islamic
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ! በማእከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጅድ ኢማም የሆኑት ሸኽ ሲራጅ ተገደሉ! ... በማእከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸኽ ሲራጅ መግሪብ ሰላት ሰግደዉ ከመስጂድ ሲወጡ በታጣቂዎች ተይዘዉ ከሄዱ በሃላ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበዉ መገደላቸውን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ገልፀዋል። ... ሸኽ ሲራጅ በዛዉ መስጅ ለረጅም አመት ደረሳዎችን እስከዛሬዋ እለት ያቀሩ የነበሩ ሲሆን መግሪብን አሰግደዉ ሲወጡ ታጣቂዎቹ እየጎተቱ የወሰዷቸዉ መሆኑና ይህን የሀገር ሽማግሌ የሁሉ አባት የሆኑት የመስጅድ ታላቁን ሸኽ ገድለዉ ጥለዋቸዉ እንደሄዱ የክልሉ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። .. ©ሀሩን ሚዲያ
إظهار الكل...
አስኳላቸው 🏵 💡:ኢስላም ዐቂዳ ነው ፤ #አስኳሉ ተውሒድ ነው። 💡:ዒባዳ ነው ፤ #አስኳሉ ኢኽላስ ነው። 💡:መኗኗር ነው ፤ #አስኳሉ እውነተኝነት ነው። 💡:ስነ - ምግባር ነው ፤ #አስኳሉ እዝነት ነው። 💡:ህግ ነው ፤ #አስኳሉ ፍትህ ነው። 💡:ሥራ ነው ፤ #አስኳሉ ጥራት ነው። 💡:አደብ ነው ፤ #አስኳሉ ትህትና ነው። 💡:መስተጋብር ነው ፤ #አስኳሉ ወንድማማችነት ነው። 💡:ሥልጣኔ ነው ፤ #አስኳሉ ሚዛናዊነት ነው። ┊  ┊  ┊  ┊ ┊  ┊  ┊  ✿ ┊  ┊  ❀ 📗 ┊  ✿ 🔗 ❀ Muslimchannel2.t.me
إظهار الكل...
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
إظهار الكل...
✍️#በሕይወትህ_ዘመን_ይህን_አስብ!" #ደስታና_መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱም በመጠንና በእርጋታ ተቀበላቸው እንጂ በደስታ ጊዜ ፈንጠዝያ በመከራ ጊዜ ደግሞ መጨነቅ አታብዛ። #ደስተኛ_ሆነህ መኖር ከፈለግክ ልብህን ከጥላቻ እንዲሁም አእምሮህን ከጭንቀት ነፃ አድርግ። #ኑሮ_እንድታለቅስ_መቶ ምክንያቶችን ከሰጠችህ፤ አንተ ደግሞ ፈገግ ለማለት ሺህ ምክንያቶችን ደርድርላት። #በዚህ_ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፤ ከፀጥታ ሰላምና እረፍት የሚገኝ መሆኑን አትዘንጋ። #አሁን_እያለፍክበት_ያለው_ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድልህን እንድታማርር እያደረገህ ይሆናል፤ ☞ነገ የሚመጣውን ግን አታውቅም፤ ☞የአንተ ችሎታና ጥበብ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበል እና ነገን ለአላህ መተዉ ነው። #ቻናላችንን_ሼር_ያድርጉ 👇👇 @Alif_islamic_posts @Alif_islamic_posts
إظهار الكل...
ክብር ለሴቶች . 1⃣. ባል በሚስቱ ላይ ከወሰለተ ቅጣቱ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መወገር ነው፡፡ 2⃣. 2ኛ ሚስት አግብቶ እኩል ካላስተዳደር የትንሳኤ ቀን ወደ ጎን ተጣሞ ይቀሰቀሳል፡፡ 3⃣.ጥሎሽ ይህን ያህል እሠጣታለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ካልሠጠ እሱ ሌባ ነው፡፡ 4⃣. የፈታት አንደሆነ ከሠጣት ነገር ዉስጥ አንዳችም ነገር መውሰድ የለበትም፡፡ አሳፋሪ ነው አትውሰዱ ይላል ቁርኣን፡፡ 5⃣. የዉርስ መብቷን የማይሠጣት ከሆነ የአላህን ድንበር ተላለፈ፡፡ የአላህን ድንበር የሚተላለፍ ራሱን ምንኛ በደለ!፡፡ 6⃣ ሴትን ልጅ በመምታት ይሁን በሌላ ነገር ያዋረዳትና ዝቅ ያደረጋት እሱ የተዋረደ ነው፡፡ 7⃣. ከአራትወር በላይ ጥሏት የጠፋ እንደሆነ የመለያየት መብት አላት፡፡ 8⃣. እንደ እናቱ ሊያያት አይገባም፤ ጀርባውን መስጠትና ፍራሹን መለየትም የለበትም፡፡ 9⃣. ‹አልቀርብሽም አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ነሽ› ካላት በኋላ ቃሉን ማጠፍ ከሳበ ለቅጣቱ ስልሳ ቀናትን መፆም ይኖርበታል፡፡ 🔟. የጠላት እንደሆነም ይታገስ፡፡ በጠሉት ነገር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገር ሊኖር ይችላልና ይላል ቁርአን ፡፡ 1⃣1⃣. አንደኛውን ባህሪዋን ቢጠላ ሌላውን ይውደድላት፡፡ ሰው ሆኖ ሙሉ የለምና፡፡ 1⃣2⃣ የፈታት እንደሆነም መልካምነቷን አይርሳ፡፡ ትዝታ አያረጅም፡፡ ምንም እንኳ የሆነ ጊዜ ጥሩ ትንፋሽ ተለዋውጠዋልና፡፡ 1⃣3⃣. በፍቺ ከተለያዩ ልጆቿን አይከልክላት፡፡ ቀለባቸውንም በትክክል ይስጣት ፡፡ 1⃣4⃣. ሴት ልጅ በሀብት ንብረቷ ሙሉ ባለመብት ናት፡፡ መፀወተች፣ ነገደችበት መብቷ ነው፡፡ በሷ ገንዘብ ባሏ አያገባውም፡፡ 1⃣5⃣ ድንበር ያለፈባት ሰው በተመሳሳይ መልኩ መቀጣት ይኖርበታል፡፡ 1⃣6⃣. ባሏን የምትታዘዘው በመልካም ነገር ያዘዛት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን በማመፅ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡ 1⃣7⃣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የበኑ ቀይኑቃዕ ጎሣዎች ላይ የዘመቱት በሴት ልጅ ክብር ምክንያት ነው፡፡ 1⃣8⃣. ከሷ መከላከል የመስዋእትነት ደረጃ አለው፡፡ 1⃣9⃣. ኸሊፋ አል-ሙዕተሲም ዐሙሪያ ድረስ ጦራቸውን ያዘመቱት ስለሷ መነካት እልህ ብለህ ነው፡፡ (ይህን ታሪክ ፈልጋችሁ አንብቡ፡፡) 2⃣0⃣. በዉሸት በዝሙት የወነጀላት የሰማኒያ ጅራፍ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ 2⃣1⃣. እሷን ማስተማር ግዴታ ነው፡፡ በመልካም ሁኔታ ማሳድግ የጀነት መግቢያ መንገድ ነው፡፡ 2⃣2⃣ ከእናቶች እግር ሥር አትነሱ፡፡ ጀነት በእግራቸው ሥር ነውና፡፡ 2⃣3⃣. እናት ከአባት በሦስት ደረጃዎች የበለጠች ናት፡፡ አል-ዐሪፊ እንደፃፉት… ራሳችሁ በድላችሁ፣ መብቶቻቸውን ሰርቃችሁ እስልምና ሴቶችን ይበድላል አትበሉ።💞💞💞 @yasin_nuru @yasin_nuru
إظهار الكل...
ሴቶች.... ና ዕድሜ      ሰውየው አራት ሚስቶች አሉት ፤ ሚስቶቹ ቅሬታ ነበራቸውና ተመካክረው ፍርድ ቤት ከሰሱት ፤ በቀጠሮውም መሰረት ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛው ክሳቸውን ለመስማት ከአራታችሁ በእድሜ ታላቅ የሆነችዋ ቀድማ ቅሬታዋን ታሰማ አላቸው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ በፀጥታ ተዋጠ ፤ ክሱን የሚያሰማ ጠፋ ፤ ፋይሉም ተዘጋ ።
إظهار الكل...
❌Mother's Day❌      ➲ «ቀን የላትም እናት» ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻ የእዝነት የደግነት የፍቅር ተምሳሌት፡ የማማ ውለታ መች ይረሳል ቀን ሌት፡ ምን አይነት ቅዠት ነው እንደት አይነት ስሌት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ አንድ ቀን አስቦ አመት ሙሉ መርሳት፡ ከእውነት መሸሽ ነው ሰወችን ማሳሳት፡ የአሏህን አደራ ትዕዛዙን አራክሰን፡ የእናትን ትውስታ በአንድ ቀን መወሰን፡ አጉል ፍልስፍናን ከነጮች ተውሰን፡ ይህ አይነቱ ቅዠት የት ነው የሚያደርሰን!? 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ በስልጣኔ ስም ጠልፎን መጥፎ ንዝረት፡ ጀነት በእግሮቿ ስር ለሆነላት ፍጥረት፡ ለርሷ ማስታወሻ አንድ ቀን መመስረት፡ አያዋጣም ተውት ፍፃሜው ነው ክስረት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ሐቋን እያሟላህ ታዘዛት ይልቅስ፡ ከቀብር ስትገባ ነገ እንዳታለቅስ፡ በድሎኛል ብላ እማዬ እንዳትወቅስ፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ራስክን አዘጋጅ ለመልካም ትብብር፡ በማንኛውም ቀን እናትህን አክብር፡ ስሜት ተከትለህ ለሸይጧን አትገብር፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ የደስታ የፍቅር የፅናት መልክ ናት፡ ማዕረጓን ከፍ አርጎ አሏህ ያገነናት፡ ታስቦ የሚውል ቀን የላትም እናት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ✍️በኑረዲን አል አረቢ➊❹❹❹
إظهار الكل...