cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

مشاركات الإعلانات
392
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
-630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🛑ከአሸባሪነት ወደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የተቀየረው ሙስሊም " converted from lslam to Orthodox Christian ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲዳረስ 👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ 👉@enatachinmaryam 👉@enatachinmaryam 👉@enatachinmaryam
إظهار الكل...
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ሃሌ ሉያ በዘንዜከር ሀሳበተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ወዓመታቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ማቴዎስ ፍሥሐ ዜናዊ በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 በኀምሳ ወበኀምስቱ ምእት ኮነ ዓመተ ፍዳ ወዓመተ ኵነኔ ወበዕስራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ኮነ ዓመተ ምሕረት ዮም ሠረቀ ለነ ወርኃ መስከረም ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኃ ጥቅምት ቡሩክ በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 ዓመት ዓመት አይለየን! 🌼 ዘመኑን ይባርክልን! 🌼 ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን! 🌼 ሀገራችን ኢትዮጵያን ሕጻናት የሚያድጉባት፣ ወጣቱ የሚሠራባት፣ አረጋውያን የሚጦሩባት፣ ሀብታም የሚጸድቅባት፣ ደካማ የሚረዳባት፣ ካህኑ የሚቀድስባት ያድርግልን! 🌼 ለታመመ ምሕረቱን፣ ላጣ ማግኘቱን፣ ለተጣላ ስምምነቱን ይስጥልን! 🌼 ከመንበሩ ታቦቱን፣ ከመቅደሱ ካህኑን፣ ከጓሮው ጎመኑን አይለይብን 🌼 ክፉ እንዳያገኘን፣ መልካም እንዳያልፈን እመ ብርሃን አትለየን! 🌼 ያጠፋውን ይማርልን፣ ካጠፋንም ይማረን! 🌼 ድሃ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ የሚል መሪ ይስጠን! 🌼ዘመኑን መልካም፣ ያማረ፣ የተወደደ፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የሰላም፣ ዘመን እንዲሆን የአምላካችን ቸርነት፣ የእመ ብርሃን አማላጅነት፣ የመልአከ ብርሃናት ቅዱስ ራጉኤል ተራዳዒነት አይለየን። 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 እነሆ ዐዲስ ዓመት፤ ''እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!'' 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
إظهار الكل...
እንኳን ደስ ያላችሁ ውድ ተመራቂ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!!!
إظهار الكل...
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ቻናሉን ሰብስክራይብ ለማድረግ 200 ኢቲቢ አግኝቻለሁ፣ ሂዱና ሰብስክራይብ ለማድረግም ገንዘብ ያግኙ! ለሰጠህው አትኩሮት እናመሰግናለን! 👇
إظهار الكل...
ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ! 200 ETB
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 ) ------------ 11፤ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። 12፤ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። 13፤ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
إظهار الكل...
👏👏👏🌹🥀🌹🕊️💐🌹🕊️🌹🥀በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!ሰላም እንደምን አላችሁ ተወዳጆች ሆይ? እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር ፤ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም እንዳለ መጽሐፍ !እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜ ሳይለይ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ጉዟችንን የቀና አድርጎ ነገ የመጨረሻ የዓመቱን የጥዋት ጉዞ የወንጌል አገልግሎት እንፈጽማለን! አምላከ ቅዱሳን ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን በእውነት!!! 🕊️🕊️🕊️ምስጋና በቅድሚያ ፍጥረትን ፈጥሮ ለሚገዛ ፤በላይ በሰማያት በአፈ መላእክት በ24ቱ ካኽናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር እየተባለ 24 ሰዓት ለሚመሰገን የሰራዊት ጌታ ፤በታች በደቂቀ አዳም ውዳሴው አዲስ ለሆነ ኤልሻዳይ ፤ሰማይን ያለባለ ለዘረጋ ፤ምድርን በውሃ ላይ ያለ ካስማ ላጸና ፤ ከዋክብትን ፈጥሮ በስማቸው ለሚጠራ ፤ ነፋስን ያለ ድምፅ ለሚመራው ደመናን ያለ መሪ ለሚያስጉዘው ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው!!! -በሁለተኛ ደረጃ ብራብ አላበላችሁኝም ብጠማም አላጠጣችሁኝም የሚለው ቃል እንዳይፈፀምብን ብላችሁ ቃለ እግዚአብሔርን ለተራቡ እና ለተጠሙ ነፍሳት በመምከርም በመሰበክም እንቅልፍ እየተዋችሁ ስታገለግሉ ለከረማችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በላይ በሰማይ ቤታችሁን ሰርታችኋልና ዝግና ብለት በማይበላው ሌባም በማይሰርቀው በላይ በሰማይ ደጅ አከማችታኋልና እግዚአብሔር አምላክ በመጨረሻው የፍርድ ጊዜ"""ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግስቴን ውረሱ """የሚለውን የፍርድ ቃል ያሰማችሁ!!!🕊️🕊️🕊️ ሶስተኛ ምስጋና ቃለ ወንጌልን ፈልጋችሁ ሁሌም ትግሃ ሌሊት ወደ ቤተ እግዚአብሔር በመገስገስ ስትማሩ ስትወያዩ ለከረማችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እግዚአብሔር አምላክ "ትርፍ ዘይትን ይዘው ሙሽራውን እንደተቀበሉት አምስቱ ቆነጃጅት" እናንተንም ሁላችንም ሙሽራው እግዚአብሔርን የምትቀበሉ የምንቀበል ያድርጋችሁ ያድርገን! ለነገ 24/10/2015 ዓ/ም የመጨረሻ ትምሕርት! ነገ የሚሆነው ስብከት እና ምክር አዘል ትምሕርት ነው!!! እኔም እንደ አባቴ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እላለሁ ''''""""በጌታ የተቀበልኸውን አግልግሎት እንድትፈፅመው ተጠንቀቅ ቆላ4፥17"""""" እግዚአብሔር በቸርነቱ ለከርሞ ያገናኜን ይሰብስበን!!! 👏👏👏👏👏👏👏 THE END OF THE YEAR MORNING SPIRITUAL PREACH IS FOR TOMORROW👏👏👏👏👏👏 👏💐🌹🕊️💐🕊️🌹🥀🌹💐
إظهار الكل...
ሰላም እንደምን አላችሁ ተወዳጆች ሆይ?@ ለቀን 23/10/2015 መወያያ ስለ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ይሆናል@ ፩ኛ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ማለት ምን ማለት ነው? ፪ኛ ትንሣኤ ሙታን ያላቸው እነማን ናቸው?የሌላቸውስ እነማን ናቸው? ፫ኛ በመጨረሻው የትንሣኤ ጊዜ የመለከት ድምፅ ይነፋ ዘንድ ስልጣን የተሰጠው ከመላእክት አለቃ መካከል ማን ነው?ስንት ጊዜ የመለከት ድምፅ ይነፋል?በዚያን ጊዜስ የሙታን አነሳስ እንደምን ነው? ፬ኛ ጻድቃንን በግራ ኃጥአንን በቀኝ ያቆማቸዋል ሲል ለእግዚአብሔር ግራና ቀኝ አለው ማለት ነውን?ለምን? ፭ኛ ጻድቃንን በበግ ኃጥአንን በፍየል ይመስላቸዋል:ለምን መሰላቸው? ፮ኛ የገነትንና የመንግስተ ሰማይን ልዩነት፤የሲኦልንናየገሃነመ እሳትን ልዩነት አብራሩ? ፯ኛ የሰው ልጅ በመጨረሻው ዘመን የሚጠየቃቸው 6ቱ ቃላተ ወንጌል እነማን ናቸው? ምንጭ የማቴዎስ ወንጌል 25 ጀምሮ! -----ቅዳሜ የመጨረሻ የጥዋት ጉዞ ውውይት ----
إظهار الكل...
🌹🥀🕊️🕊️🕊️🌹🌺ሰላም እንደምን አላችሁ ተወዳጆች ሆይ? ለቀን 19/10/2015 መወያያ ጥያቄ ስለ አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ይሆናል! ፩ኛ አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የሚባሉት እነማናቸው? ፪ኛ ለምን ምስጢር ተባሉ?አዕማድ ማለትስ ምን ማለት ነው?ለምን አዕማድ ተባሉ? ፫ኛ የቅድስት ሥላሴን አንድነት እና ሶስትነት አስረዱ? ፬ኛ ምስጢረ ሥላሴ መቼ ተገለጠ? ፭ኛ ምስጢረ ሥላሴን የሚያስረዱ ተፈጥሮአዊ ምሳሌዎችን ዘርዝሩ? ለቀን 20/10/2015 ፩ኛ የቅድስት ሥላሴ ኩነታዊ ግብራቸው ምንድን ነው? ፪ኛ ምስጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው? ፫ኛ ከሶስቱ አካላት ሰው የሆነው ማነው? ፬ኛ ሰው መሆን ለምን አስፈለገ? ፭ኛ እውነት ሰዎቹ እንደሚሉት ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ """ፍጡር ወይም ነቢይ ነውን???"""" የቀጠለ ስለ ምስጢረ ጥምቀት ፮ኛ ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው? ፯ኛ ጥምቀት ለምን ያስፈልጋል? ፰ኛ ጌታ የተጠመቀበት ምክንያት ምንድን ነው?ለምን በውኃ ተጠመቀ? ለቀን 21/10/2015 ስለ ምስጢረ ቁርባን ፩ኛ ምስጢረ ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው? ፪ኛ ቁርባን መቼ ተመሰረት?በማን ተመሰረተ? ፫ኛ የቁርባን ምሳሌ በብሉይ ዘመን? ፬ኛ ቁርባን የሚያስፈልገው ለማን ነው?ከኃጢአት ንፁህ ለሆነ ሰው ወይስ ለኃጢአተኛ? ፭ኛ ሰው ወደ ምስሩ ከመቅረቡ በፊትና ከቆረበ በኋላ ያለው ስርዓት ምንድን ነው? ስለ ዓመታዊ ክብረ በዓል ፬ኛ ሰኔ 21 የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በምን ምክንያት ነው? ለቀን 22/10/2015 ስለ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ይሆናል ማሳሰቢያ ፡ -ጥያቄዎቹ የበዙት ቀን ስለሌለን ነው!!!-የዚህን ዓመት ውይይት በቀን 24/10/2015 ዓ/ም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እናጠቃልላለን!!!👏👏👏👏👏👏👏
إظهار الكل...
🥀🌹🌹🌹🌹🌹🕊️🕊️ሰላም እንደምን አላችሁ ተወዳጆች ሆይ? ለቀን 17/10/2015 ዓ/ም መወያያ ጥያቄ """""""በእንተ ነገረ ድኅነት""""""" 👇👇👇👇👇የፈጠረውን እና ያዳነውን የማያውቅ ትውልድ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ ሊጠራ እንዴት ይቻለዋል?በምንስ አንደበቱ አምላኬ ብሎ ሊጠራው ይችላል?የተደረገለትን የሚረሳ እና ያዳነውን የማያውቅ እርሱ ውለታ ቢስ ማለት አይደለምን?እንደ ምን ያለ ፍርድስ ይጠብቀው ይህን?👆👆👆👆👆 ፩ኛ ነገረ ድኅነት ማለት ምን ማለት ነው?፪ኛ እግዚአብሔር አዳምን ለምን ዕፀ በለስን እንዳይበላ ከለከለው? ፫ኛ ለአዳም መበደል ተጠያቂው ማን ነው? ፬ኛ አዳምን ሊያድነው የሚችለው ማነው?ምን ምን ነገሮችን ማሟላት አለበት? ለቀን 18/10/2015 ፭ኛ አዳምን ለምን ቅዱሳን መላእክት ፡አበው ፡ነቢያት ሊያድኑት አልቻሉም? ፮ኛ በነገረ ድኅነት ውስጥ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሚና(ድርሻ) ምንድን ነው? ፯ኛ ድኅነት የተፈፀመ እና ያልተፈጸመ ድኅነት ተብሎ ይከፈላል ታድያ ልዩነቱ ምንድን ነው? ፰ኛ ታዲያ በዚህ በተፈፀመ እና ባልተፈፀመ ድኅነት የሰው ልጅ ድርሻ ምንድን ነበር?አሁንስ ምንድን ነው ድርሻው? ማሳሰቢያ፥ሁላችሁም መጽሐፍትን አንባቢዎች ሁኑ! የዚህ የጥዋት ውይይት 6ቀን ብቻ ይቀረናል፤በነዚህ ቀናትም """""""" ኑ እግዚአብሔርን መውደድ እና መፍራት እንማማር""""""""!!! --እሁድ መነሻ ሰዓት10፡30 PM🌺🌺🌺🌹🍁🍁🍁
إظهار الكل...