cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሩዋድ የበጎ አድራጎት እና መረዳጃ ማሀበር®

ጉዞ ወደ ከፍታ ☆መረጃ ለማግኘት telegram:- @buki1453 @Esoo_017 @Abunehyan1

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
391
المشتركون
-124 ساعات
-37 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

° ' ቀብር ውስጥ ያለው ሰውዬ በጣም የሚመኘው ነገር ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ ' ብለው እኮ ጠየቁ ተከታዮቻቸውን 😔 ~ ' በጣም የሚመኘው ነገር ሁለት ረከዓ መስገድ ነው ብለን እናስባለን ' አሏቸው ። ~ ' እሺ እሱ አልቻለም እናንተ ስገዱ ' አሉን😔 ~ ይሄ ሰውዬ አልቻለም እድል የለውም አይደል እንዴ ? ~ እናንተ እኮ እድል አላችሁ 🥹 << ቀብለ ፈወዋቲል ዐዋን >> ጊዜው ከማለፉ በፊት… በቃ እናንተ ተጠቀሙበት ¡¡
إظهار الكل...
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ ጉዳዮቻችንን ለማስፈፀም ወደ ሰዎች ስንደውል "የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም…!" …"የደወሉላቸው ደንበኛ ቴሌፎን ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም!"…የሚሉ የኦፕሬተር ድምፆች አሰልችተውናላ? በቃ ለነሱ ብዙም ቦታ አንስጥ... ወደ ጌታችን የምናደርገው ጥሪ ከመሰል መሰናክሎች የጠራ በመሆኑ እንደሰት…መቆራረጥ የሌለው…ፈጣንና ቀልጣፋ ነው…!!🤌🏼 ጌታችን አሁን አልገኝም አይልም..አለሁ….."ለምኑኝ እቀበላችሗለሁ" እንጂ!! መስመሩ በአለም ህዝቦች በጠቅላላ እና በአንድ ሰዓት ጥሪ ቢደረግበት እንኳን ተይዟል አይለንም…!!!..ሁሌም 24 ሰዓት ክፍት ነው በዛ ላይ ወጪ የለውም.......!! . ከእኛ የሚጠበቀው የቂን የተባለውን ሲም ካርድ ተጠቅመን ወደርሱ መደወል ብቻ ነው…🤳🏽ጌታህ የአንተን ጥሪ ሁሌም ይቀበላል…እንደውም ኔትወርኩ የበለጠ ነፃ የሚሆንበትን እና ጥሪህ በፍጥነት ተሰሚነት የሚያገኝባቸውን ተጨማሪ የአየር ሰዓታት አመቻችቶልሃል!!♥♥ለይለቱል ቀድር የእድሉ ተጠቃሚ እንሁን…ታድያ ዱዓ ስታደርጉ እኔንም አትርሱኝ ዱኣ አድርጉልኝ!
إظهار الكل...
●▬▬๑۩የኛ ነቢይ ሙሃመድﷺ۩๑▬▬● << የቂያማ እለት የኔን አማላጅነት የማግኘት ቅድሚያ ያለው ሰለዋትን በብዛት ያወረደ ሰው ነው ። >> ብለዋልና ሰለዋት በማብዛት አላህ ሱብሀነ ወተዓላ የነቢዩን ሙሀመድ ﷺ ሸፈዓ እንድናገኝ ያድርገን ። ●▬▬๑۩የኛ ነቢይ ሙሃመድﷺ۩๑▬▬●
إظهار الكل...
አሞራው በሰማይ ላይ❤️ ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት «ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት «አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ። በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ··· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ «አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ ከሞት ዳንን። አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ። ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ በማለት አዘዟት።
إظهار الكل...
የነብዩ ሙሃመድ ﷺ ታሪክ●                   ክፍል 5       ዝግጅት:- አብዱ  ሙሰማ ሀሰን ነብዩ صلى الله عليه وسلم በዚያ በጃሂሊያው ዘመን ራሱ ከወንጀል የተቆጠቡ ነበሩ።  በየትኛውም አስፀያፊ ስነምግባር አልተዘፈቁም። ክህደትና ውሸት አልፈፀሙም፤ ሙዚቃ አላዳመጡም። ቁማር አልተጫወቱም። ዝሙት ላይ አልወደቁም። እርቃናቸውን አልታዩም። ዐረፋን በመተው ሙዝደሊፋ ላይ አልቆሙም። ጣኦትን አልተሳለሙም። ለጣኦት የታረደንም ይሁን የአላህ ስም ያልተጠቀሰበትን እርድ አልበሉም። ከዕባ በጎርፍ በመጎዳቱ ምክንያት ሙሽሪኮቹ ከዕባውን አፍርሰው በሚገነቡበት ወቅት የ35 አመቱ ሙሀመድصلى الله عليه وسلم  ድንጋይ እየተሸከመ ያቀርብ ነበር። ሙሽሪኮቹም ከዕባውን ገንብተው ሲያጠናቅቁ ሀጀረል አስወድን የትኛው ጎሳ ከቦታው ላይ ያስቀምጠው በሚል በመካከላቸው ጭቅጭቅ ተፈጠረ። መጀመሪያ የደረሰ ሰው ይፍረድልን ብለው ተስማሙ። ድንገት ሙሀመድ ከውጭ ከተፍ አለ። ታማኙ ሰው መጣ ብለው ጮሁ። ሙሀመድም ጋቢ መሳይ ልብስ አምጡ አላቸውና ሀጀረል አስወድን ከጋቢው ላይ አስቀምጦ ሁሉም ጎሳ የጋቢውን ጫፍ በመያዝ ወደከዕባው እንድወስዱት ካስደረገ በኋላ ከልብሱ ላይ አንስቶ ቦታው ላይ አስቀመጠው። በዚህም ከፀብ ታደጋቸው። እነሱም የነብዩን ብልህነት ተገነዘቡ። ሀጀረል አስወድ ከጀነት ነጭ ሆኖ እንደወረደና በሰው ልጆች ወንጀል ተፅእኖ ምክንያት እንደጠቆረ የሚጠቁም ሀዲስ አለ። ነብዩ صلى الله عليه وسلم  ከመላካቸው በፊት ዐረቡ ዐለም እጅግ በጣም በከፋ የአሰተሳሰብ ኋላቀርነት ተዘፍቆ ነበር።በዚያ በጃሂሊያው ዘመን ድንጋይ እየተመረጠ ይመለካል። ዝሙት እንደክብር መገለጫ በይፋ ይፈፀማል። አራጣ በሰፊው ተንሰራፍቷል። ጎረቤት ይበደላል። በክት (የሞተ እንስሳ) ይበላል። ዝምድና መቁረጥ የተለመደ ባህል ነው።ጠንካራው የደካማውን ይቀማል። ሴት መውለድ ያስኮንናል። ከተወለዱም ከነህይወታቸው ይቀበራሉ። ድህነት ተፈርቶ ልጅ ይገደላል። አስካሪ መጠጥ የህዝቡ መለያ ነው። ባል ሚስቱን ሂጂና ከእከሌ  አርግዘሽልኝ ነይ ብሎ ይልካል። ባጭሩ ዐብደላህ ቢን ዐባስ  رضي الله عنه እንደገለፀው የዐረቦችን መሀይምነት ለማወቅ የፈለገ በ አንዓም ምእራፍ ውስጥ ከአንቀፅ 130 ጀምሮ የተጠቀሰውን ታሪካቸውን ማስተዋሉ በቂ ነው። ነብያቶች ባጠቃላይ  በህይወት ባሉበት ጊዜ የሙሀመድ ነብይነት ካጋጠማቸው የእሱ ተከታይ እና አጋዥ  ሊሆኑ ቃል ገብተዋል። እያንዳንዱ ነብይም ለተከታዮቹ ስለ ሙሀመድ ሳይናገር አላለፈም።  በትክክለኛው ተውራትና ኢንጅል ውስጥ ሙሀመድ በመገለጫዎቹም ብቻ ሳይሆን በስሙም  መጠቀሱ ለዚህ ግልፅ ማሳያ ነው።እንደ ወረቃ፣በሂራ፣ አቡ ተይሃን፣ ዐብደላህ ቢን ሰላም፣ ከዕቡ አልአህባር ፣ዐብደላህ ቢን ዐምር፣ የዐሙሪያው መነኩሴ እንድሁም የሩሙ ንጉስ ( ሂረቅል)  አይነት የመፅሀፉ ባለቤቶች ስለሙሀመድ ምስክርነት መስጠታቸው  ይሄንኑ አረጋጋጭ ነው። ሊላኩ አካባቢ ደግሞ የሙሀመድ መምጣት ወሬ በሰፊው ተሰራጨ። ጠንቋዮች ሳይቀሩ ስለሙሀመድ صلى الله عليه وسلم መተንበይ ጀምረው ነበር። ታዲያ የዚህ ወሬ መሠራጨት አንዳንዶች ሙሀመድን ዝግጁ ሆነው እንድጠብቁ ጥሩ እድል ፈጥሮላቸዋል። አንሷሮች እስልምናን እንድቀበሉ ፈር የቀደደላቸውም ይሄው ወሬ ነበር። ሰልማንም رضي الله عنه የመነኩሴውን ጥቆማ ተከታትሎ ሰለመ። ነብይ ከመሆናቸው በፊት ድንጋይ ሰላምታ እንደሚያቀርብላቸው፣ በህልም የሚያዩት ነገር  በተመሳሳይ መልኩ በእውን እንደሚከሰት፣ የሆነ ወጣ ያለ ድምፅ እንደሚሰሙ እና ያልተለመደ ብርሃን እንደሚመለከቱ ተናግረዋል። ኋላ ላይ ደግሞ ከሰዎች ራቅ ማለትን ወደዱና ለቀናቶች የሚሆንን ስንቅ በመያዝ ወደ ሂራእ ዋሻ እየሄዱ ያመልኩ ጀመር። ከእለታት በአንዱ  ሰኞ በዋሻው ውስጥ እንዳሉ መላኢካው ጂብሪል በልብስ ጠቅልሎ ከጨመቃቸው በኋላ አንብብ አላቸው። ማንበብ አልችልም ብለው መለሱ። ከሶስተኛው ምልልስ በኋላ ከመጀመሪያዋ የቁርአን ምእራፍ (የ ዐለቅ ምእራፍ) አምስቱን አንቀፆች አነበበላቸው። በአብዛኛዎቹ ቀደምቶችና ተከታዮቻቸው አቋም መሠረት መጀመሪያ የወረደው የቁርአን ምእራፍ የዐለቅ/ቀለም ምእራፍ ሲሆን ከእሷም ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 5 አንቀፆቸ ናቸው። ነብዩም صلى الله عليه وسلم በክስተቱ ተደናግጠው እየተንቀጠቀጡ ኸዲጃ  رضي الله عنها ዘንድ ደረሱ። ሸፍኑኝ ሸፍኑኝ አሉ። በልብስ ሸፈነቻቸው። ቀጥለውም አሁንኳ ለነፍሴም ስጋት እያደረብኝ ነው። እብደትም እንዳያጋጥመኝ እየሰጋሁ ነው አሏት። ኸዲጃ رضي الله عنها ግን ኧረ ፍፁም! አንተ ለዚህ የምትገባ ሰው አይደለህም ብላ መልካም ጎኖቹን ከጠቃቀሰች በኋላ ለማንኛውም እስኪ ወደ አጎቴ ልጅ ወረቃ ጋር ልውሰድህ ብላ አስመከረቻቸው። ወረቃም ሙሀመድን ያጋጠመው ሙሳን ያጋጠመው አይነት እንደሆነ፣ ከሀገር እንደሚባረርም ጠቁሞ በሚሰደድበት ወቅት በህይወት ካለ ጠንከር ያለ እገዛ እንደሚያደርግለትም ነገረው። ወረቃ ቢን ነውፈል رضي الله عنه ሙሀመድ صلى الله عليه وسلم   መልእክተኛ ከመሆናቸው በፊትም ቢሞት በነብይነታቸው ግን አምኖ ነበር። ሸይኽ አልባኒ ትክክለኛ ባሏቸው  ሀዲሶችም ወረቃ የጀነት መሆኑ ተጠቁመዋል። ከቀደምቶች ኢማሙ ጦበሪ ፣በገውይ፣ ኢብኑ ቃኒዕ እንድሁም ከዘመናችን መሻይኾች ሸይኽ ዑሰይሚንና ሸይኽ ፈውዛን ከወንዶች የመጀመሪያው አማኝ ወረቃ እንደሆነና እና ከሶሃቦችም እንደሚመደብ ይጠቅሳሉ። በመጀመሪያው የቁርአን ምእራፍ ነብይነታቸው ከታወጀ በኋላ ለተወሰኑ ጊዜያቶች ራእዩ ተቋረጠ። ነብዩም صلى الله عليه وسلم  በመቋረጡ ምክንያት ከባድ ሀሳብ ገባቸው። ከእለታት አንድ ቀን ቆመው በነበሩበት ሰአት የሆነ ድምፅ ሰሙ። ቀጥ ብለው  ሲመለከቱ ያኔ በሂራእ ዋሻ የታገላቸውን መላኢካ በሰማይና በመሬት መካከል በኩርሲይ ላይ ተቀምጦ አዩት። በመጀመሪያው ቀን የደረሰባቸውን ትግል (ጭንቀት) አስታወሱና በድንጋጤ  ቤት ገብተው ሸፍኑኝ ሸፍኑኝ አሉ። እንደተሸፋፈኑም የሙድደሲር ምእራፍ ወረደላቸው። አንተ ተሸፋፋኙ ሆይ። ተነስና አስጠንቀቅ.... የሚል ትእዛዝ ደረሳቸው። ይቀጥላል....... ቀጣይ ይትሉ ❤️           ©Hisnul_Muslim99
إظهار الكل...
✅እግዚአብሄር :– እኔ ሰው አይደለሁም።( ሆሴዕ 11:9 ) ✅ኢየሱስ :– እኔ ሰው ነኝ።(ዮሐንስ ወንጌል 8:40 ) ( ትንቢተ ሆሴዕ 11:9 ) እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ እንጂ #ሰው_አይደለሁምና፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰው ነኝ ይላል (የዮሐንስ ወንጌል 8:40 ) ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ:: ነገር ግን ነገር ግን........ ኢየሱስ ሰው ነኝ አምላክ አይደለሁም እያለ እየተማፀናቹ እናንተ ግን አይ  ኢየሱስ አምላክ ነህ፣ ጌታ ነህ፣ ፈጣሪ ነህ ወዘተ..... ብላችሁ የምታመልኩት ከሆነ ይህን መልዕክት በአንደበቱና በግልፅ  አስቀምጦላቹሃል፣ የማቴዎስ ወንጌል 7 ፣ 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ #ጌታ_ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥#የሚለኝ_ሁሉ_መንግሥተ_ሰማያት_የሚገባ_አይደለም። 22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23 የዚያን ጊዜም። #ከቶ_አላወቅኋችሁም፤ #እናንተ_ዓመፀኞች፥  #ከእኔ_ራቁ_ብዬ_እመሰክርባቸዋለሁ። ስለዚህ ኢየሱስን ምትወዱት ከሆነ ቃሉንና ምክሩን ስሙ! ከፊቴ ጥፉ አላውቃችሁም እላቹሃለው እያላቹ ነው። በወንጌል ካላፈሩ እስኪ ሼር አድርጉት ይህ 100% ከመፅሀፍ ቅዱስ ከ (ወንጌል) ስለወጣ ሁሉም #ክርስቲያን  #ሼር ያድርገው። 📱 “እየሱስ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የፈጣሪ መልእክተኛ”  ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ 💥1• “የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የኣብ ነው እንጂ የኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 14:24) ✋ የማን ነው ኣለ? ••••• የላከኝ የኣብ√ በዚህ ጥቅስ መሰረት ወልድ( እየሱስ) የኣብ መልእክተኛ ነው። 💥 2• “እኔ ከራሴ ኣንዳች ላደርግ ኣይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳሎ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ኣልሻምና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:30) ✋ የማን ፈቃድ ኣለ? ••••• የላከኝን√ ማነው የላከው? እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ኣምላክን የሚልክ ደግሞ ማነው? ኣምላክ ይልካል ወይስ ይላካል? 💥 3• “ቃሌን የሚሰማ የላከኝም የሚያምን የዘላለም ሂወት ኣለው”( የዬሐንስ ወንጌል 5:24) ✋ ማንን የሚያምን ኣለ? ••••••• የላከኝን√ ማነው የላከው? 💥 4• “ኢየሱስም ጮኸ እንዲህም ኣለ በኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 12:44) ✋ በኢየሱስ ማመን በማን ማመን ነው? •••••• በላከው√ ማነው የላከው? 💥 5• “እኔ ከራሴ ኣልተናገርሁምና ነገር ግን የላከኝ ኣብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 12:49) ✋ እዚህ ላይ ደግሞ ” የላከኝ ኣብ” በማለት የኣብ መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ተናግርዋል። 💥6• “የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 8:26) ✋ ኢየሱስን የላከ እውነተኛው ማነው? 💥 7• “የላከኝም ኣብ ሰለኔ ይመሰክራል”( የዬሐንስ ወንጌል 8:18) ✋ማን ኣለ? ••••• የላከኝ ኣብ√ 💥8• “ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም ኣላቸው ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ 7:16) ✋ ትምህርቱ ከማን ነው?•••••ከላከው√ ማነው የላከው? 💥 9• “እኔም በራሴ ኣልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 7:28) ✋ ኢየሱስን የላከ የማይታወቅ እውነተኛው ማነው? 💥 10• “እኔንም የጣለ የላከኝም ይጥላል”( ሉቃስ ወንጌል 10:16) ✋የላከኝን? ማነው የላከው? 💥11• “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር ኣልተላክሁም ኣለ”( ማቴዎስ 15:34) ✋ወደ እስራኤል መልእክተኛ ኣድርጎ የላከው ማነው? 💥12• “ኣንተም እንደላክኸኝ ኣመኑ”( የዬሐንስ ወንጌል 17:8) ✋ማነው የላከው? 💥13• “ይህ የማደርገው ስራ ኣብ እንደላከኝ ስለኔ ይመሰክራልና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:36) ✋ኣብ እንደላከኝ በማለት መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ይናገራል። 💥14• “የላከኝ ኣብም እርሱ ስለኔ መስክሮዋል”( የዬሐንስ ወንጌል 5:37) ✋ምን ያደረገኝ ኣብ? •••••••• የላከኝ√ 💥15• “እኔ ከእግዚኣብሄር ወጥቼ መጥቻለሁና እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ ኣልመጣሁም”( የዬሐንስ ወንጌል 8:42) ✋ከእግዚኣብሄር የተላከ መልእክተኛ መሆኑን ይነግረናል። 💥16• “ባሪያ ከጌታው ኣይበልጥም መልእክተኛም ከላከው ኣይበልጥም” ( የዬሐንስ ወንጌል 13:16) መልእክተኛው ማነው? ላኪውስ ማነው? 💥17• “ኣብ እንደላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኃለሁኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 20:21) ✋ኣብ እንደላከኝ በማለት የኣብ መልእክተኛ እንደሆነ በግልፅ ነግሮናል።
إظهار الكل...
👍 2
( ﺍللَّهُمَّ ﺻَﻞِّ ﻋَﻠَﻰ ﺳَﻴِّﺪِﻧَﺎ مُحَمَّدٍ ﻋَﺒْﺪِﻙَ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻚَ ﺍلنَّبِيِّ ﺍﻷُﻣِّﻲ ﻭَﻋَﻠَﻰ ﺁﻟِﻪِ ﻭَﺻَﺤْﺒِﻪِ وَسَلِّمْ تَسْلِيماً ) Selewat to be said 80 or 100 times on Friday after asr. ጁሙዐ ከአስር ቡሀላ 80 ወይም 100 ጊዜ የሚደረግ ሰለዋት
إظهار الكل...
ክብር ለሴቶች . 1⃣. ባል በሚስቱ ላይ ከወሰለተ ቅጣቱ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መወገር ነው፡፡ 2⃣. 2ኛ ሚስት አግብቶ እኩል ካላስተዳደር የትንሳኤ ቀን ወደ ጎን ተጣሞ ይቀሰቀሳል፡፡ 3⃣.ጥሎሽ ይህን ያህል እሠጣታለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ካልሠጠ እሱ ሌባ ነው፡፡ 4⃣. የፈታት አንደሆነ ከሠጣት ነገር ዉስጥ አንዳችም ነገር መውሰድ የለበትም፡፡ አሳፋሪ ነው አትውሰዱ ይላል ቁርኣን፡፡ 5⃣. የዉርስ መብቷን የማይሠጣት ከሆነ የአላህን ድንበር ተላለፈ፡፡ የአላህን ድንበር የሚተላለፍ ራሱን ምንኛ በደለ!፡፡ 6⃣ ሴትን ልጅ በመምታት ይሁን በሌላ ነገር ያዋረዳትና ዝቅ ያደረጋት እሱ የተዋረደ ነው፡፡ 7⃣. ከአራትወር በላይ ጥሏት የጠፋ እንደሆነ የመለያየት መብት አላት፡፡ 8⃣. እንደ እናቱ ሊያያት አይገባም፤ ጀርባውን መስጠትና ፍራሹን መለየትም የለበትም፡፡ 9⃣. ‹አልቀርብሽም አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ነሽ› ካላት በኋላ ቃሉን ማጠፍ ከሳበ ለቅጣቱ ስልሳ ቀናትን መፆም ይኖርበታል፡፡ 🔟. የጠላት እንደሆነም ይታገስ፡፡ በጠሉት ነገር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገር ሊኖር ይችላልና ይላል ቁርአን ፡፡ 1⃣1⃣. አንደኛውን ባህሪዋን ቢጠላ ሌላውን ይውደድላት፡፡ ሰው ሆኖ ሙሉ የለምና፡፡ 1⃣2⃣ የፈታት እንደሆነም መልካምነቷን አይርሳ፡፡ ትዝታ አያረጅም፡፡ ምንም እንኳ የሆነ ጊዜ ጥሩ ትንፋሽ ተለዋውጠዋልና፡፡ 1⃣3⃣. በፍቺ ከተለያዩ ልጆቿን አይከልክላት፡፡ ቀለባቸውንም በትክክል ይስጣት ፡፡ 1⃣4⃣. ሴት ልጅ በሀብት ንብረቷ ሙሉ ባለመብት ናት፡፡ መፀወተች፣ ነገደችበት መብቷ ነው፡፡ በሷ ገንዘብ ባሏ አያገባውም፡፡ 1⃣5⃣ ድንበር ያለፈባት ሰው በተመሳሳይ መልኩ መቀጣት ይኖርበታል፡፡ 1⃣6⃣. ባሏን የምትታዘዘው በመልካም ነገር ያዘዛት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን በማመፅ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡ 1⃣7⃣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የበኑ ቀይኑቃዕ ጎሣዎች ላይ የዘመቱት በሴት ልጅ ክብር ምክንያት ነው፡፡ 1⃣8⃣. ከሷ መከላከል የመስዋእትነት ደረጃ አለው፡፡ 1⃣9⃣. ኸሊፋ አል-ሙዕተሲም ዐሙሪያ ድረስ ጦራቸውን ያዘመቱት ስለሷ መነካት እልህ ብለህ ነው፡፡ (ይህን ታሪክ ፈልጋችሁ አንብቡ፡፡) 2⃣0⃣. በዉሸት በዝሙት የወነጀላት የሰማኒያ ጅራፍ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ 2⃣1⃣. እሷን ማስተማር ግዴታ ነው፡፡ በመልካም ሁኔታ ማሳድግ የጀነት መግቢያ መንገድ ነው፡፡ 2⃣2⃣ ከእናቶች እግር ሥር አትነሱ፡፡ ጀነት በእግራቸው ሥር ነውና፡፡ 2⃣3⃣. እናት ከአባት በሦስት ደረጃዎች የበለጠች ናት፡፡ አል-ዐሪፊ እንደፃፉት… ራሳችሁ በድላችሁ፣ መብቶቻቸውን ሰርቃችሁ እስልምና ሴቶችን ይበድላል አትበሉ።💞💞💞
إظهار الكل...
👍 1