cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መዝሙረ ተዋህዶ ዘኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 💠መዝሙሮች ና የመዝሙር ግጥሞች 💠ምስለ ስዕሎች በዚህ ቻናል ያገኛሉ አስተያየት ካለዎት @zgeorgis

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
223
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
+130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
በቅርብ ቀን በ Deacon Yohans official Link :- https://www.youtube.com/@DeaconYohansOfficial
إظهار الكل...
2👍 1🥰 1
ዕርገት ማለት ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡ በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡-‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉንእነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡ በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችንለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየአዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ‹አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው›፤›› በማለት ቅዱስ ወንጌልን መሠረት ባደረገ ኃይለ ቃል ጌታችን ወደ ሰማይ ስለ ማረጉና ለሐዋርያት አምላካዊ ትእዛዝ ስለ መስጠቱ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡ @onlythecross
إظهار الكل...
3
إظهار الكل...
ተሰምተው የማይጠገቡ የቅድስት አርሴማ መዝሙሮች @21media27 @-mahtot @-mahtot @zegiorgis

@21media27 @-mahtot @Merkorewostube @Kendilmedia #ethiopian #duet #begena #orthodox #mezmur #habesha #abelmekbib #zegiorgis #orthodoxmezmur

Photo unavailableShow in Telegram
በቅርብ ቀን 🔴አዲስ ዝማሬ 🔴 "አላውቀውም ብዬ" ዘማሪ ዲ/ን ዮሐንስ መሐመድ @onlythecross
إظهار الكل...
3
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ የናታኒም መንፈሳዊ ማህበር tiktok account https://www.tiktok.com/@john.t2004?_t=8mhXJqOpTjU&_r=1
إظهار الكل...
13ቱ ሕማማተ መስቀል  🥺🥺🙏 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካር 1 ,ሳዳር በሚባል ችንካር ቀኝ እጁ ቸነከሩት 2, አላዳር በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 3, ዳናት በሚባል ችንካር ሁሉቱን እግሩ ቸነከሩት 4, አዴራ በሚባል ችንካር ማህል ልቡኑ ቸነከሩት 5, ሮዳስ በሚባል ችንካር ደረቱን       አምስቱ የእመቤታችን ሀዘናት 1 , ከአምስቱ አደን አይሁድ እንዲገሉት በቤተ መቅደስ ስምኦ ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው ሉቃስም ምዕራፍ 2፥ 34- 5 2, ኛ ሁለተኝ ውም ሥስት ቀን በቤተ መቅደስ ባጣሁህ ጊዜ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 41 48 3, ኛ በሥስተኛው እጅህን እግርህን አስረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፍት ባሰብሁ ግዜ ነው ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 1 4,  በዕለተ አርብ እራቁትህን ቸንክረው በሁለቱ ወንበዴ መካከል እንደሰቀልኩ ባሰብሁ ጊዜነው አለች ዮሐን ምዕራፍ 19 17 22 5, ኛ ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳደርህ ባሰብሁ ጊዜ ነው ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 38 42 ከብርሃነ ትንሳኤው ያድርሰን የእግዚአብሔር ቸርነት የእመ ብርሃን ምልጃ አይለየን አሜን @onlythecross
إظهار الكل...
👏 4
◾️ ◾️ ◾️           ሕ ማ ማ ት “ ናይናን ፤ እብኖዲ ፤ ታኦስ        ማስያስ ፤ ትስቡጣን "              *★★★* እኒህም ቃላት ከዕለተ ሰኞ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ዓርብ ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሲነበብ በሚከርመው ግብረ ሕማማት በተባለው ነገረ ሕማማቱን መዝግቦ ካስቀመጠው ዝነኛ የቤተክርስቲያን መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው የሚገኙና ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ እንደወረደ ሳይለወጡ ተጽፈው የምናገኛቸው የዕብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ናቸው። ••• ★ ናይናን ናይናን የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም በግዕዙ “መሐረነ” በአማርኛው “ማረን” ማለት ነው፡፡ ••• ★ እብኖዲ እብኖዲ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው ★ ታኦስ ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ ጌታ፣ አምላክ” ማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናን” ማለትም በአማርኛ ትርጉሙ “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡ ★ ማስያስ ማስያስ ማለትም የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙም በእነርሱ ቃል “ መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም ” መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው። ★ ትስቡጣ “ዴስፓታ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ደግ ገዥ” ማለት ነው። ••• በአቅራቢያችን ቤተክርስቲያን ባይኖርም ሰዓት እየጠበቅን እንዲህ እያልን የጌታን ሕማሙን እያሰብን አቅማችን በፈቀደ መጠን ባለንበት ስፍራ እንዲህ እያልን እንስገድ። ••• •ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን #እብኖዲ #ናይን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን #ታኦስ ናይን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን #ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ  ናይን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያ ላይሶን •ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን #ትስቡጣ ናይን ኪርያ ላይሶን ••• እንበለ ደዌ ወህማም እንበለ ጻማ ወድካም ለብርሃነ ትንሣኤሁ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በሰላም ያለ ደዌና ያለህማም ያለጻእርና ያለድካም ለብርሃነ ትንሳኤው ያድርሰን ያድርሳችሁ። @onlythecross
إظهار الكل...
👍 3👏 1
✞ ሆሣዕና እምርት ✞ ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት(፪) ቡርክት እንተ ትመጽእ መንግስት(፬) ትርጉም:-የታወቀችይቱ የድኅነት ቀን የምትመጣይቱ የአባታችን የዳዊት መንግስት ቡርክት ናት ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
إظهار الكل...
ሆሣህና እምርት .mp31.12 MB
የዘመን ፍጻሜ.mp32.12 MB
ሆሣዕና በአርያም.mp39.35 KB
Encoderbot file id5559095 24k.m4a6.59 KB
ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው.mp34.66 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.