cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

ይህ የቴሌግራም ቻነል የእግር ኳስ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተለይ ለእንግሊዙ የለንደን የእግር ኳስ ክለብ ቼልሲ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ያቀርባል! አላማችን ኢትዮጵያዊያን የቼልሲ ደጋፊዎች ጥራት ያለው እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እንዲሁም ስለሚደግፉት ክለብ አኩሪ ታሪክ፣ ጠንካራ ማንነት፣ የድል አድራጊነት ባህል ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መስራት ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 165
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-1230 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የክረምቱ የመጀመሪያው ፈራሚ ቶሲን አድራቢዮ በነፃ ዝውውር ከፉልሃም ወደ ቼልሲ መምጣቱ ይፋ ሆኗል። እንኳን ደህና መጣህ! ይህን ዝውውር እንዴት አገኛችሁት?
إظهار الكل...
11👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ ሰማያዊ ኤንዞ ማሬስካ! “በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ ክለቦች አንዱ የሆነውን ቼልሲን መቀላቀል ለማንኛውም አሰልጣኝ ህልም ነው። በዚህ አጋጣሚ በጣም የተደሰትኩት ለዚህ ነው። የክለቡን የስኬት ባህል የሚያስቀጥል እና ደጋፊዎቻችንን የሚያኮራ ቡድን ለመስራት ጥሩ ብቃት ካላቸው ተጫዋቾች እና ሰራተኞች ጋር በጋራ ለመስራት ጓጉቻለሁ" ኤንዞ ማሬስካ ቼልሲዎች ጣሊያናዊውን ወጣት የእግር ኳስ ባለሟል ዋና አሰልጣኛቸው አድርገው መቅጠራቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል። እንኳን ደህና መጣህ!! መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ!!
إظهار الكل...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
ማሬስካ ወደ ቼልሲ? ቼልሲዎች ጣሊያናዊውን የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን በዋና አሰልጣኝነት ሊቀጥሩት ከጫፍ መድረሳቸውን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ዘግቦታል። ማሬስካ በቼልሲ የሚሳካለት ይመስላችኋል?
إظهار الكل...
👍 10👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከብራይተን እንደገና? ግርሃም ፖተር ብራይተንን ጥሩ ኳስ የሚጫወት ቡድን አድርጎት ስለነበር በቼልሲ ባለቤቶች ቼልሲን እንዲያሰለጥን እድል ተሰጥቶት ነበር፣ አልተሳካለትም እንጂ። ምክንያቱም ብራይተን እና ቼልሲ ሁለት በጣም የተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ ክለቦች በመሆናቸው ነው። የፖቼቲኖም ቅጥር ተመሳሳይ ነው። አሁን ደግሞ ዲ ዘርቢም በብራይተን የሰራውን ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው የቼልሲ ባለቤቶች በቼልሲ እድሉን እንዲሞክር እድል ሊሰጡት እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው። አዲሶቹ የቼልሲ ባለቤቶች አሰልጣኝ የሚቀጥሩት በጥናት ላይ ተመስርተው ሳይሆን በእድልና በግምት (በ "ደስ አለኝ - መሰለኝ" እንደሚባለው) ይመስላል። ለዚህም ማሳያው በሁለት አመቱ ውስጥ ቀጥረው ያሰናበቷቸውን እና አሁን ለመቅጠር የመጨረሻ እጩ ሆነው የቀረቡትን አሰልጣኞች መመልከት ይቻላል። ጥሩ ባለሙያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ናቸውም። ይሁን እንጂ አንዳቸውም በቼልሲ የልዕቀት ደረጃ ላይ የሚገኙ እንዳልሆኑ ግልፅ ነው። በቼልሲ ያለውን ጫና (ዋንጫ አላልኩም) ለመቋቋማቸው ምንም ማረጋገጫ የለም። ሊቋቋሙትም ላይቋቋሙትም ይችላሉ፣ እድላቸውን ይሞክራሉ። ከሆነላቸው ጥሩ ነው፣ ካልሆነላቸው ይሰናበታሉ። አሁን የሚቀጠሩት አልሆን ብሏቸው ሲሰናበቱ ደግሞ ሌሎች ወጣት "ታለንት" ያላቸው አሰልጣኞች ታላቁን ቼልሲ የማሰልጠን እድሉን እንደሚያገኙ ይጠበቃል። ዲ ዘርቢ እድሉን ቢያገኝ በቼልሲ የሚሳካለት ይመስላችኋል?
إظهار الكل...
👍 6
ፖቼቲኖ ለምን ተሰናበተ? ፖል ሜርሰን የፖቼቲኖን የስንብት ውሳኔ በተመለከተ እንዲህ ብሏል "ይሄ እብደት ነው፣ ስለ ፖቼቲኖ መሰናበት የምሰማውን ነገር ማመን አልቻልኩም። ቡድኑን እያሻሻለው ነበር፣ የአውሮፓ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሎታል፣ ማንችስተር ዩናይትድን በልጦ 6ኛ ደረጃ እንዲይዝ አድርጎታል" ……………………… ………………………… ሁኔታዎች እንደሚጠቁሙት ፖቼቲኖ የተሰናበተው ባስመዘገበው ውጤት የተነሳ አይደለም። የሊጉን ዋንጫ ቢወስድም እነ ቶድ ቦሊ የማይታዘዛቸውን አሰልጣኝ በቼልሲ እንዲቆይ አይፈቅዱም። በሚታዘዛቸው ወቅትማ ክለቡ ቢወርድም እንደግፈዋለን እያሉ፣ በፕሮጀክታቸው እንድናምን ሲጎተጉቱን ነበር። አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? … ፖቼ መታዘዝ አቆመ ወይም አጉረምርሟል። በዋናነት ጋላጋር እና ቻሎባህ እንዲሸጡ አይፈልግም፣ ባለቤቶቹ ደግም በሁለቱ የአካዳሚ ተጨዋቾች ሽያጭ የሚያገኙት ገንዘብ ንፁህ ትርፍ በመሆኑ እንዲሸጡ ይፈልጋሉ። የፍላጎት ግጭቱን (conflict of interest) እነሱ አለቃ ስለሆኑ አሰልጣኙን በማሰናበት ለመፍታት ሞክረዋል። ቶማስ ቱኩልንም ያሰናበቱት የእኛን ፍላጎት አያከብርም ብለው ነው፣ የእነሱ ፍላጎት በቼልሲ ከፍተኛ ትርፍ ማጋበስ ነው። ተጨዋቾች የሚገዙት ከክለቡ ውጤት አንፃር ብቻ ሳይሆን ወደፊት ከሚያገኙት የሽያጭ ትርፍ አንፃር ነው። ፖቼቲኖ የተሰናበተው ከቼልሲ ውጤት አንፃር ቢሆን ኖሮ መሰናበት የነበረበት አሁን ሳይሆን ከ6 ወር በፊት ነበር። ያኔ የማንም መጫወቻ ሆኖ በየሳምንቱ ሲሸነፍና ደጋፊው ሲያዝን "በፖቼቲኖ እንተማመናለን፣ ከአሰልጣኙ ጋር የረጅም ግዜ ፕሮጀክት ነው ያለን፣ ደጋፊው ትዕግስት ሊኖረው ይገባል" እያሉ ያላግጡ ነበር። አሁን ደጋፊው በቡድኑ እንቅስቃሴ ተስፋ ማድረግ ሲጀምር የእነሱ ጥቅም ስለተነካ ብቻ በድንገት ያለምንም ማቅማማት በ30 ደቂቃ ንግግር ቶማስ ቱኩል ላይ የመዘዙትን የስንብት ሰይፋቸውን አወጡ። ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚሄዱበት ርቀት እና ቡድኑ ውጤት ሲያጣ የሚያሳዩት ገደብ አልባ ትዕስት የሰማይ እና የምድር ያህል ይራራቃል። አሁንም እየፈለጉ ያሉት የሚታዘዛቸውን ወጣት እና ልምድ የሌለው አሰልጣኝ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ደግሞ የበለጠ ልብ ይሰብራል። ይህ ምን የሚሉት መስፈርት ነው? ትልልቅ ፕሮፋይል ያላቸው አሰልጣኞችን የማይፈልጉት ስለማይታዘዟቸው ከመሆኑ በስተቀር ሌላ ምን ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል? … በዚህ አካሄዳቸው የምንወደው ክለባችን ባለቤቶች ቡድኑን ወደ ቀድሞ ክብሩ ይመልሱታል ማለት ዘበት ነው። ተጨዋቾች ውጤታማ ካልሆኑ ይሸጣሉ ወይ በውሰት ይሰጣሉ፣ አሰልጣኝም ቢሆን ካልሆነለት ይሰናበታል፣ የክለብ ባለቤት ክለቡን ሲያምስ ግን ምን ይደረጋል? … የቸገረ ነገር ነው የገጠመን፣ ቢሆንም ግን ይህም ይታለፋል!!
إظهار الكل...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ፖቸቲኖ እና ቼልሲ ተለያይተዋል! ቴሌግራፍ እንደዘገበው ቼልሲ እና ፖቸቲኖ በስምምነት ተለያይተዋል - አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ዛሬ ክለቡን መልቀቁ ታውቋል። ቼልሲዎች ፖቸቲኖን በወጣት አሰልጣኝ ለመተካት ውስጥ ለውስጥ ንግግሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን ፋብሪዚዮ ገልጿል። ባለፈው ሳምንት ሴስክ ፋብሪጋስ በኮብሃም ተገኝቶ ተጨዋቾቹን ማበረታቱ የፖቼቲኖን ቦታ ለመረከብ እንደታሰበ አመላካች ይሆን? በፖቼቲኖ መሰናበት ምን ተሰማችሁ? በማን ቢተካስ ትመርጣላችሁ??
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የጄምስን የክሮስ ችሎታ ያስታወሱት አይመስለኝም! "ከሪስ ጄምስ የተላከው ክሮስ በጣም ድንቅ ነው። ግብ ጠባቂው የክሮሱን አካሄድ ለማንበብ ሞክሮ ነበር፣ ነገር ግን የክሮሱ ጥራት ከፍ ያለ ስለነበር ኳሱን መረቡ ላይ ለማሳረፍ ለጃክሰን በጣም ቀላል ነበር። ኖቲንግሃሞች ጄምስ ክሮስ ሲያደርግ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ በደንብ የሚያውቁት ወይም የሚያስታውሱ አይመስለኝም፣ ቢያስታውሱ ኖሮ ያንን ያህል ክፍት ቦታ እንዲያገኝ አይፈቅዱለትም ነበር ብዬ አስባለሁ" ጄሚ ሬድናፕ
إظهار الكل...
🔥 19👍 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኤደን ሃዛርድ በመስከረም 2018 የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ካሸነፈ በኋላ ኮል ፓልመር የሚያዚያ 2024 በማሸነፍ የመጀመሪያው የቼልሲ ተጫዋች ሆኗል።
إظهار الكل...
👍 13 2
Photo unavailableShow in Telegram
የብራይተኑ ካይሴዶ እየመጣ ነው? "ሞይሰስ ካይሲዶ በቼልሲ የመጀመሪያ ጨዋታዎቹ ላይ በእውነት በጣም ደካማ አፈፃፀም ነበር ያሳይ የነበረው። እናም ሲጫወት ባየሁት ቁጥር "ያ ለብራይተን ሲጫወት በድንቅ እንቅስቃሴው የማውቀው ተጫዋች የት ሄደ?" እያልኩ ማሰብ ጀምሬ ነበር። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ሁኔታው እየተቀየረ እየተሻሻለ መጥቶ አሁን ላይ ቀደም ሲል በብራይተን የምናውቀውን አስደናቂውን ካይሴዶን የሚያስታውስ የእንቅስቃሴ ፍንጭ ማየት ጀምሬያለሁ" ጄሚ ሬድናፕ እናንተስ ምን ትላላችሁ?
إظهار الكل...
👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
ቻሎባህ - Jehovah Son ! በቼልሲ አካዳሚ አድገውም ይሁን ከሌላ ክለብ በወጣትነታቸው ያላቸው ያልተገለጠ እምቅ ችሎታቸው ከግምት ውስጥ ገብቶ በውድ ዋጋ ከተገዙ ተጨዋቾች መካከል እንደ ትሬቨር ቻሎባህ ብሩህ ግዜ ከፊቱ የሚጠብቀው ያለ አይመስለኝም። ከሶስት እና አራት አመት በኋላ ከአለማችን ምርጥ ተከላካዮች አንዱ እንደሚሆን የሚያሳዩ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉት። ተክለ ሰውነቱ፣ እይታው፣ እርጋታው፣ ስነ ምግባሩ፣ ከኳስ ጋር ያለው ምቾት፣ … እና ከምንም በላይ በጠንካራ የእምነት መሠረት ላይ የታነፀ ማንነት ስላለው በህይወቱ የሚገጥሙትን አስቸጋሪ ወቅቶች በፅናት የሚሻገርበት እሴቶች አሉት። ይህን ያልተገለጠ እምቅ ችሎታውን ለማውጣት የሚፈልገው ሁለት ነገሮች ግዜ እና እምነት የሚጥልበት አሰልጣኝ ናቸው። ዛሬ የብቃቱ ግማሽ ላይ አልደረሰም፣ ነገ እንደሚደርስ ግን መገመት ቀላል ነው። አያድርገውና ቼልሲዎች ቻሎባህን የሚሸጡ ከሆነ ወደፊት ሁላችንም የምንቆጭበት ይመስለኛል።
إظهار الكل...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ኦ ቲያጎ … 😢 የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ በዓለም እግር ኳስ ምርጥ ተከላካዮች መካከል አንዱ የሆነውን ቲያጎ ሲልቫን በአንድ አመት ኮንትራት ያስፈረመው በወርሃ ነሀሴ 2020 ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ቲያጎ ከቼልሲ ጋር አራት አመታት ቆይቶ እና ከ150 በላይ ጨዋታዎችን አድርጎ፣ በእንግሊዝ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፎ በውድድር አመቱ መጨረሻ በክብር ሊሰናበት እንደሆነ ይፋ ሆኗል። ባሰለፈቸው አራት አመታት ውስጥ ለክለቡ ያለውን ሁሉ ስለሚሰጥ ከቼልሲ ደጋፊዎች ጋር እድሜ ልክ የሚቆይ የስሜት ትስስርና ግንኙነት መፍጠር ችሏል። ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ በይፋ በገለፀበት ቃለ ምልልሱ እንዲህ ብሏል። "ደህና ሁኑ ብዬ እስከመጨረሻው መሰናበት አልፈልግም፣ ምክንያቱም አንድ ቀን በሆነ አይነት ሚና ልመለስ እንደምችል አስባለሁ። ወደ እዚህ ታላቅ ክለብ መመለስ እፈልጋለሁ" እኛም አንድ ቀን እንደምትመለስ እናምናለን፣ ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለን።
إظهار الكل...
15😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ቼልሲ ውስጥ የማፍርባቸው ተጫዋቾች አሉ" "ከቀድሞው የቼልሲ ቡድን ጋር በጣም ጠንካራ የስሜት ትስስር ነው ያለኝ፣ ክለቡን እወደዋለሁ። አሁን እየሆነ ባለው ነገር ስሜቴ ተጎድቷል። አብራሞቪች ቼልሲን በአለማቀፍ ደረጃ ስኬታማ ካደረገው በኋላ የእሱን መልቀቅ ተከትሎ በክለቡ ላይ እየደረሰ ያለው የውጤት ቀውስ የማይታመን ነው። በሮማን አብራሞቪች ከፍተኛ ጥረት የተገነባው የክለቡ ጠንካራ ማንነት በዚህ መንገድ ሲፈራርስ ዝም ብሎ መመልከቱ ተቀባይነት የለውም። አሁን ካለው የቼልሲ ስብስብ ቁልፍ ተጫዋቾች እነማን እንደሆኑ አላውቅም። በቡድኑ ውስጥ እንደዚህ ያሉ ቁልፍ የመሪነት ሚና ያላቸው ተጫዋቾች ያሉ አይመስለኝም። ጠንካራ እና ልምድ ያላቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአንድ ቡድን ውስጥ ከሌሉ መሰረታዊ ነገሮች ለማከናወን ራሱ በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛሬ ቼልሲ ያለበትን ሁኔታ እንዲህ ነው ብሎ መናገር ራሱ አይቻልም። በቡድኑ ውስጥ ብዙ የሚያሳፍሩ እና የክለቡን ታሪክ የማይመጥኑ ተጫዋቾች አሉ። ባለቤቶቹ ብዙ ገንዘብ አውጥተዋል፣ ነገር ግን አሁንም በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪ በርካታ ችግሮች አሉ፣ በየቦታው ችግር አለባቸው። ይህ ለምን ሆነ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። አሁን የሚሄዱበት አካሄድ ጥሩ አይደለም፣ ይህ ሁኔታ ሊቀጥል አይገባም። ይህ ሁኔታ ዝም ስለተባለ በራሱ ግዜ የሚስተካከል ነገር አይደለም። ችግሩ እየባሰ ከሄደ በመጨረሻም ቼልሲን ለማየት ማንም ፍላጎት አይኖረውም። በዚህ አካሄዳቸው ከቀጠሉ ቡድኑ እንደ ቀድሞው በሌሎች ቡድኖች ዘንድ መፈራቱ እና መከበሩ ይቀራል፣ በቅርቡ ይረሳል፣ ተራ ቡድን ይሆናል። እና ይህ ደግሞ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፣ ይህ ነገር በፍጥነት መቆም አለበት" ጉስ ሂዲንክ
إظهار الكل...
8👍 6🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
Capitain, Leader and Legend!! የቼልሲ የምንግዜም ምርጥ አምበል፣ መሪ እና ታሪካዊ ተጨዋች በመባል የሚታወቀው ጆን ቴሪ የፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። እንኳን ደስ አለህ በሉት! 💙🙌
إظهار الكل...
🔥 10👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የመረቡን ጀርባ ማግኘት ብቻ ነበር የጎደለን! "ደጋፊዎቻችን ለማስደሰት የቻልነውን ለማድረግ ወስነን ነበር፣ በቂ እድሎችንም አግኝተን ነበር። ይህንን ሽንፈት መቀበል ከባድ ነው። በጨዋታው ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል፣ የመረቡን ጀርባ ማግኘት ብቻ ነበር የጎደለን። አሁን ማድረግ ያለብን ከእንደዚህ አይነት መራር ልምዶች ለወደፊቱ መማር ነው" ትሬቮህ ቻሎባህ ……………………… በተያያዘ ዜና ቼልሲዎች ቻሎባህን የመሸጥ ፍላጎት አላቸው። ቼልሲ ቻሎባህን አሁን ቢሸጠው ይጠቀማል? ወይስ ቢቆይ ነው ክለቡ የሚጠቀመው? እኔ ቢቆይ እመርጣለሁ!
إظهار الكل...
🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
L e g e n d ! በሰማያዊው ማልያ እንዳያቸው ከምመኛቸውና ስላየኋቸው ከምደሰትባቸው እና የማልያውን ክብር በሚገባ ይመጥናሉ ብዬ ከማምንባቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ ቲያጎ ነው። ቼልሲ በአዲሶቹ የክለቡ ባለቤቶች እጅ ከገባ ግዜ ጀምሮ ደስተኛ አይደለም፣ በውስጡ አምቆ የያዘው ብዙ የተከፋባቸው ነገሮች እንዳሉ ግልፅ ነው፣ ግን ለክለቡ ደህንነት ሲል እንዲሁም ፕሮፌሽናል ስለሆነ ዝምታን መርጧል። በውድድር አመቱ መጨረሻ ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ ፍንጭ የሰጠ አስተያየት ሰቷል። "ውሳኔውን ወስኛለሁ፣ በቅርቡ ይፋ ይሆናል" ብሏል። ስንብቱ በደስታ እና በዋንጫ የታጀበ ቢሆን እመኝ ነበር። ያም ሆነ ይህ ቲያጎ የቼልሲ ሌጀንድ ነው!
إظهار الكل...
👍 6🥰 5
Photo unavailableShow in Telegram
ጨዋታውአልቆ ቲያጎ ያለቅሳል፣ ኖኒ ግን ይስቃል፣ ምንድነው የሆነው? ቼልሲ ተሸንፏል ወይንስ አሸንፏል? …………………………………………………………………………… በእርግጥ ቼልሲ ካለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ የገጠመው ችግር የተወሳሰበ እና ዘርፈ ብዙ ነው። የክለቡ ባለቤቶች ስለ እግር ኳስ ኢንደስትሪው ያላቸው አነስተኛ ወይም የተሳሳተ ግንዛቤ፣ የዳይሬክተሮቹ ደካማ ስፖርታዊ ውሳኔ የምልመላና የቅጥር ስትራቴጂ፣ አሰልጣኙ የክለቡን ደረጃ (ስታንዳርድ) የሚመጥን አለመሆኑ፣ በርካታ ልምድ የሌላቸው ተጨዋቾች መኖራቸው ዋና ዋና ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች በአጭር ግዜ የሚቀረፉ ባለመሆናቸው ክለቡ ላልተወሰኑ አመታት በውጤት ማጣት ውስጥ ሊቆይ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን ምናልባት የክለቡ ባለቤቶች የክለቡን ጉዳት ለመቀነስ እና በአጭር ግዜ ውስጥ ክለቡን ከውድቀት ለመታደግ የሚፈልጉ ከሆነ በመጪው ክረምት እንደ ኖኒ ማዱኬ አይነት ተሸንፈው ከተቀናቃኝ ጋር ተቃቅፈው የሚገለፍጡ እና የቼልሲን አርማ ለብሶ መሸነፍ ምንም አይነት ህመም የማይፈጥርባቸውን ተጨዋቾችን አሰናብቶ በምትካቸው ሽንፈትን የሚጠሉ፣ የመሪነት ችሎታ ያላቸው እና ለክለባቸው አርማ አና ክብር እስከመጨረሻው የሚታገሉ፣ የደጋፊውን ስሜት የሚያከብሩ ተጨዋቾች ማስፈረም አለባቸው። የቲያጎን እንባ ማየት ግን ልብ ይሰብራል 😢 💔 የእሱን የማሸነፍ ስሜት ባልተረዱ ልጆች ህልሙ መክሸፉ ያሳዝናል፣ የቲያጎ ስሜት የደጋፊው ስሜት ነፀብራቅ ነው!
إظهار الكل...
11👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ኒኮላስ ጃክሰን ወይስ ፖቼቲኖ? ዛሬ የቼልሲ ተጨዋቾች ለማሸነፍ እንደፈለጉና ያላቸውን ሁሉ ለመስጠት ቆርጠው እንደመጡ ከእንቅስቃሴያቸውና ከሰውነት ቋንቋቸው መረዳት ቀላል ነው። በእርግጥ የተገኙትን የጎል እድሎች ቢጠቀሙ ኖሮ ማሸነፍ የሚችሉት ጨዋታ ነበር። በጨዋታው ያለቀላቸውን እድሎች ያባከነው ጃክሰን ጎል አካባቢ ሲደርስና ከበረኞች ጋር ሲገናኝ እጅግ የበዛ የአቅም ውሱንነት አለበት፣ እግሩ ይዝላል፣ ግራ ይጋባል፣ ይደነግጣል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት አያውቅም፣ ይደክመዋል፣ ምናልባት የሚያገባ ከሆነ ስለሚያሳየው የደስታ አገላለፅ እያሰበ ይሆናል… እናም ፈፅሞ ከመጨረሻ አጥቂ የማይጠበቅ የቂላቂል ውሳኔ ይወስናል፣ ወይም ተከላካዮች ደርሰው ኳሱን ይወስዱበታል፣ ከዛ ይበሳጫል፣ ከተጨዋቾች ይጣላል፣ ቢጫ ያያል… ህይወት ይቀጥላል። ይሄው ነው በየሳምንቱ እና በየ90 ደቂቃው የሚደጋገመው የጃክሰን በጭንቀት የተሞላ ትርዒት። እሱ የሚችለውን ነው እያደረገ ነው ያለው፣ መቼም "በቃ አልሆነልኝም" ብሎ ራሱን እንዲቀየር አይጠበቅበትም። ይህን ማድረግ ያለበት አሰልጣኙ ነው፣ ጃክሰን ተቀይሮ የሚወጣው ምን ሲያደርግ ነው?… መቼ? … ወይስ መቼም አይቀየርም? አንዳንዴስ ተቀይሮ መግባት የለበትም? … እንደዚህ አይነት ዝቅ ያለ አፈፃፀም እያሳየ እና ጫና ውስጥ ሆኖ አየተጫወተ በየሳምንቱ ሙሉ 90 ማሰለፉ ለእድገቱ ጠቃሚ ነው? አሰልጣኞች ከነባራዊ ሁኔታዎች ተነስተው በቀጣይ ሊመጣ የሚችለውን ነገር በመገመት በሚሰሩት ስራ ነው ልዩነት የሚፈጥሩት። ፖቼቲኖ የጃክሰንን ሁኔታ (አመላካች መረጃዎች) ከግምት በማስገባት ሊከሰት የሚችለውን ነገር ቀድሞ በመገመት ልጁንም ክለቡንም ለመታደግ የተለያየ ዘዴ አለመጠቀሙ ይገርማል። ሁሌም አንድ አይነት ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኮል ፓልመር የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ መባል አለበት! "ኮል ፓልመር በማንችስተር ሲቲ ቢሆን እና አሁን በቼልሲ የሚያደርገውን ነገር ቢያደርግ ኖሮ ሁሉም ሰው የፕሪምየር ሊግ ምርጡ ተጫዋች ነው ይለው ነበር። ቼልሲዎች በአጠቃላይ መጥፎ የውድድር ዘመን ስላሳለፉ ምናልባት ኮከብ ተብሎ ላይመረጥ ይችላል። ነገር ግን እኔ መመረጥ እንዳለበት አምናለሁ:: ከዚህ ቀደም በሊጉ ምንም ልምድ የሌለው ተጨዋች በፕሪሚየር ሊጉ ላይ በዚህ መጠን ጎል ማስቆጠር ከቀለለው እና ማንፀባረቅ ከቻለ ክብሩን መውሰድ እንዳለበት ምንም ጥርጥር የለውም። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ ነው፣ የጨዋታ ቦታውም የፊት አጥቂ ሳይሆን ነው የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነትን እየመራ ያለው። እሱ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀብላል፣ የፍፁም ቅጣት ምቶችን የሚያስቆጥረው ተዝናንቶ ነው፣ ጨዋታው የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን እሱ ግን ፍፁም የተረጋጋ እና ምን ማድረግ እንዳለበት ቀድሞ የሚያውቅ አይነት ሰው ይመስላል" ሳም አላርዳይስ የቼልሲው ኮል ፓልመር ለምን የዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን ማሸነፍ እንዳለበት ሲናገሩ
إظهار الكل...
17
Photo unavailableShow in Telegram
Form is temporary but class is permannent. Chelsea Football Club is class!! የአንድ ሰሞን ብቃት ግዜያዊ ነው፣ ይመጣል ይሄዳል፣ ከፍ ያለ ደረጃ ግን ጥራት ነው ይለያል! የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ላቅ ያለ ደረጃ ያለው፣ ያልተደረገውን ያደረገ የለንደን ኩራት ነው።
إظهار الكل...
🔥 6 2
Photo unavailableShow in Telegram
አንቼሎቲ የቼልሲን ጨዋታ አስታውሰዋል!! ቼልሲዎች በቶማስ ቱኩል መሪነት በቻምፒየንስ ሊጉ በ2021 እና በ2022 ለሪያል ማድሪድ ፈተና ሆነውበት ነበር። በ2021 ቼልሲዎች ሪያል ማድሪድን በግማሽ ፍፃሜው ከቻምፒየንስ ሊግ አስወጥተውት ነው ዋንጫውን ያነሱት። በቀጣዩ አመት በ2022 በድጋሚ ተገናኝተው በመጀመሪያው ጨዋታ ቼልሲዎች በስታምፎርድ ብሪጅ 3-1 ቢረቱም በመልሱ ጨዋታ በርናባው ላይ 3-0 መርተው (አራተኛ ጎል አስቆጥረው በVAR ተሽሯል) ሪያል ማድሪድ ባለቀ ሰዓት ባስቆጠረው ጎል ጨዋታው ጭማሪ ሰዓት አስፈልጎት ማድሪድ በተሰጠው ተጨማሪ ሰዓት አንድ ጎል አግብቶ ጨዋታውን ማሸነፉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው። ትላንት ማንችስተር ሲቲን አሸንፈው ከቻምፒየንስ ሊጉ ካስወጡት በኋላ አንቼሎቲን "ተጨንቀው ነበር ወይ?" ተብለው ሲጠየቁ የቼልሲን ጨዋታ አስታውሰዋል። "ከቼልሲ ጋር የተጫወትን ግዜ ከመመራት ተነስተን ካሸነፍናቸው ከባድ ጨዋታ በኃላ እንዲህ አይነት ጭንቀት ውስጥ ገብቼ አላውቅም" ብለዋል።
إظهار الكل...
9
Photo unavailableShow in Telegram
አስቸጋሪው ተጋጣሚዬ ድሮግባ ነው!! “በጣም ከባዱ ተጋጣሚዬ? ያለምንም ጥርጥር ዲዲየር ድሮግባ ነበር። በተለይ በስታምፎርድ ብሪጅ ስንጫወት ከድሮግባ ጋር በተቃራኒ መጫወት እጅግ በጣም ከባድ ነበር። እሱ በጣም ጎበዝ እና ጠንካራ ነበር። አንዳንድ ጊዜ በትንሽ ንኪኪ የተጎዳ መስሎ አውቆ ሳጥኑ ውስጥ እየወደቀ ዳኞችን ያታልላቸዋል፣ ሲፈልግ ደግሞ ጥንካሬውን ተጠቅሞ በጉልበቱ ኳሱን እየሸፈነብህ ይጫወትና ድንቅ ጎል ያስቆጥር ነበር። በእርግጠኝነት ጠንካራውና አስቸጋሪው ተጋጣሚዬ እሱ ነው። በወቅቱ በተለይም ደግሞ በዩናይትድ የመጀመሪያ የስራ ዘመኔ ላይ እሱ በጣም አስደናቂ ነበር ብዬ አስባለሁ" ኔማኒያ ቪዲች
إظهار الكل...
🔥 10 5👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሁላችንም የዚህ ልጅ ባለ እዳ ነን! ዘንድሮ ፖቼቲኖ ስራውን ያላጣው በዚህ የ21 አመት ወጣት ነው። ዘንድሮ ቼልሲ ከሊጉ ያልወረደው እና አነ ቶድ ቦሊን ከከፍተኛ ክስረት የታደገው ይህ የ21 አመት ወጣት ነው። ዘንድሮ ቼልሲ በየጨዋታው እየተሸነፈ ደጋፊው አንገቱን እንዳይደፋ ያደረገው የ21 አመት ወጣት ነው። ወጣት ነው ግን ደግሞ ስሜታዊ አይደለም፣ ከጨዋታ በፊት አያወራም፣ ከጨዋታ በኋላም አይፎክርም፣ ሰለ ፀጉር አቆራረጡ አይጨነቅም። ሀላፊነቱን በየጨዋታው በዝምታ የሚወጣው ኮል ፓልመር የቼልሲ ክለብ በዝቅታ ውስጥ ያገኘው እንቁ ነው። የዛሬው የዝቅታ ዘመን አልፎ ከፍ ማለታችን አይቀርም፣ የፓልመር ውለታ ግን ሁሌም አይረሳም። እሱ የሁላችንም ባለእዳ ነው!!
إظهار الكل...
👍 17 11
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲዎች ከወጣቱ አልፊ ጊልክሪስት ጋር እስከ 2026 ድረስ የሚቆይ ኮንትራትተፈራርመዋል።
إظهار الكل...
🔥 8👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
የተጨዋቾቹ ምላሽ ሙያዊ ያልሆነ እና ኢፍትሃዊ ነው! "የቼልሲ ነገር አሰልቺ ነው፣ ስለነሱ ማሰብ ያደክማል። በ10 ተጨዋቾች የተጫወቱት በርንሌይ ጨዋታውን ማሸነፍ ነበረባቸው። ቼልሲዎች ላለመውረድ ከሚታገል ቡድን ጋር ሊያውም በስታምፎርድ ብሪጅ እንዲህ መሆኑ ያሳፍራል። ቡድኑ እንዲህ በየሳምንቱ እያሳፈራቸውም ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ እየሄዱ ጨዋታ ለሚያዩ እና በዝማሬ ለሚያበረታቱ ደጋፊዎች ከፍተኛ አድናቆት አለኝ፣ እንዲህ አይነት ታማኝነት ስላሳዩ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ። በቃራኒው የቼልሲ ተጨዋቾች የደጋፊውን ታማኝነት የሚከፍሉበት ምንም አቅም በውስጣቸው የላቸውም፣ በልባቸው ውስጥ ምንም ተነሳሽነት የለም፣ በአእምሯቸው ውስጥ ምንም ነገር የለም፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም አያውቁም። ይህንን ክለብ ለሚወዱና ለሚደግፉ ሰዎች የተጨዋቾቹ ምላሽ ሙያዊ ያልሆነ እና ኢፍትሃዊ ነው" ፍራንክ ለበፍ
إظهار الكل...
👍 19👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ማርቲን ኪውን ፓልመርን አሞካሽቶታል! "ኮል ፓልመር ገና የ21 አመት ወጣት ነው፣ ግን ያለው ድንቅ ተሰጥኦ፣ ጥሩ እይታ፣ መረጋጋት እና ከፍተኛ የሆነ የራስ መተማመን እድሜውን እንድትረሳው ያደርግሃል። በዩሮ 2024 እንግሊዝን ለምን መወከል እንዳለበት ለሰዎች ለማሳየት እና ለማሳመን የፈለገ ይመስላል። ፊል ፎደን በሲቲ እድል እስኪሰጠው ድረስ ለመጠበቅ ትዕግስት ነበረው፣ ነገር ግን ፓልመር ፈጣን እድገት ማድረግ ፈልጎ ስለነበር ሲቲን በግዜ ለቆ ቼልሲን ተቀላቅሏል። በሲቲ ከልጅነቱ ጀምሮ አሳደገው ለዚህ ያደረሱት ባለሙያዎች አሁን ፓልመር የቼልሲን ማሊያ ለብሶ ድንቅ ብቃቱን በየሳምንቱ ሲያሳይ ማየት ከባድ እንደሚሆንባቸው አስባለሁ" ማርቲን ኪውን
إظهار الكل...
15😁 12👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዘመናዊው የእግር ኳስ ኢንደስትሪ እንዴት እንደሚሰራ ልትረዳው ይገባል!! "ሮማን አብራሞቪች ማሸነፍን በጣም ይወድ ነበር፣ ሁለተኛ መውጣት ለእሱ መሸነፍ ነው። እሱ በቼልሲ ቤት በነበረበት ከመጀመሪያው አመት ጀምሮ የገነባው ጠንካራ ባህል ለሽንፈት ምንም አይነት ርህራሄ አልነበረውም። የክለቡ ባህል ዛሬም ነገም ማሸነፍ ነበር፣ ዛሬ እየተሸነፍንም ቢሆን ቡድን ገንብተን ነገ እናሸንፋለን የሚል አካሄድ እሱ ጋር ቦታ የለውም። በእሱ ዘመን የነበሩ የትኛውም የክለቡ አሰልጣኞች ካላሸነፉ እንደሚሰናበቱ በግልፅ ያውቁ ነበር። ወደ ክለቡ የሚመጡት ለማሸነፍ ብቻ እንደሆነ አውቀውት ነው፣ እናም ያደርጉታል። ብዙ ሰው ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ያስተዳደርበት የነበረው ማሸነፍ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ መንገድ ትክክለኛው መንገድ ነው ብሎ አያስብም ፣ ነገር ግን በ19 አመት ቆይታው የሰበሰበውን የዋንጫ ብዛት (22) እና የክለቡን አለምአቀፋዊ ተወዳጅነት እንዴት እንዳሻሻለው ስትመለከት መደነቅህ አይቀርም። ያላሸነፈው የውድድር አይነት የለም። እሱ ያሳካውን አይነት አስደናቂ ስኬት ለማግኘት በርካታ ገንዘብ ማውጣት ብቻ ሳይሆን ልክ እንደ ሮማን አብራሞቪች ዘመናዊው የእግር ኳስ ኢንደስትሪ እንዴት እንደሚሰራም ጭምር ልትረዳው ይገባል" የቀድሞ የቼልሲ ዳይሬክተር ክርስቲያን ፑርስሎው
إظهار الكل...
👍 19 3🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
አልሰማሁም! በዛሬው ጨዋታ ላይ በስቴዲየም የነበሩ የቼልሲ ተጓዥ ደጋፊዎች የጆዜ ሞሪንሆን እና የሮማን አብራሞቪች ስም እየጠሩ ሲዘምሩ ተደምጠዋል። ይህንኑ ክስተት ተከትሎ ከጨዋታው በኋላ ስለሁኔታው በጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበለት ፖቼቲኖ ሲመልስ፣ "ደጋፊው እንደዛ ማድረጉ ተነግሮኛል፣ ነገር ግን እውነት ለመናገር እኔ አልሰማሁም። ምን ማለት እንደምችል አላውቅም፣ ያለንበትን ሁኔታ ማመን አለብኝ፣ እንዲህ አይነት ነገር የተለመደ ነው። በጨዋታው ከመምራት ወደ 2-1 መመራት ሄደን ነበር። እና የእነሱ የብስጭት ስሜት ግልጽ ነው፣ ዋና አሰልጣኝ እንደመሆኔ ለውጤቱ መጥፋት እና ለደጋፊው ሀዘንና ብስጭት እኔም ከተጠያቂዎቹ አንዱ ነኝ" ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ
إظهار الكل...
👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲ የዛሬውን ስኬት ችላ ብለህ ስለነገ ብቻ የምታስብበት ክለብ አይደለም!! "አዲሶቹ የቼልሲ ባለቤቶች ወጣት ተጫዋቾችን በማስፈረም ከጥቂት አመታት በኋላ ጥሩ ቡድን እንሰራለን በማለት ክለቡ ከዚህ ቀደም ስኬት ያስመዘገበበትን መንገድ ለመቀየር ወስነዋል። ይህ አካሄድ ግን አይሆንም፣ አይቻልም። ምክንያቱም ይህ ቼልሲ ነው። የዛሬውን ስኬት ችላ ብለህ ስለነገ ብቻ የምታስብበት ክለብ በፍፁም አይደለም፣ ሁለቱንም አመጣጥነህ መሄድ አለብህ። ባለቤቶቹ ወደ ቼልሲ የመጡት በአሜሪካ ያገኙትን የስፖርት ንግድ ስኬታቸውን ተማምነው በአውሮፓም በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብ ለማግኘት ነው። ነገር ግን የአውሮፓ የእግር ኳስ ከአሜሪካ የተለየ ነው። በአውሮፓ እግር ኳስ ንግድ ብቻ አይደለም፣ ባህልም ጭምር ነው። ለአውሮፓ ክለብ ደጋፊዎች እግር ኳስ ሁሉ ነገራቸው ነው፣ በውጤቱ ዛሬን መደሰት ይፈልጋሉ፣ በክለባቸው ሽንፈት ወይም ድል የሚሰማቸው ሀዘን ወይም ደስታ ጥልቅ ነው፣ በማሸነፍ የሚያገኙት እርካታ ዛሬን በደስታና በተስፋ እንዲያልፉት ያስፈልጋቸዋል፣ ልክ እንደ መድሃኒት ነው። የቼልሲ ባለቤቶች ግን ይህንን እውነታ እንደተረዱ እርግጠኛ አይደለሁም" ፍራንክ ለበፍ እናመሰግናለን ፍራንክ !!
إظهار الكل...
👍 17🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እጆቹን ሲዘረጋቸው ትልልቅ ክንፎች ያሉት አካል ይመስላል! “ፔትሮቪች በጠባብ ቦታ ላይ በድንገት ተስፈንጥሮ በከፍታ የመዝለል (Plyometric ይባላል) ችሎታ አለው። ስለዚህ ይህን ችሎታውን ይበልጥ ካዳበረው የበለጠ ኃይለኛ እና ፈጣን ዝላይ ማድረግ እንደሚችል አውቃለሁ። ይህ ችሎታ ጥሩ አቅም ያላቸውን ግብ ጠባቂዎች የበለጠ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። ፔትሮቪች የማይታመን የማዳን ችሎታም አለው። የሰውነቱ መጠነ ቅርፅ ትልቅና ሰፊ ነው፣ እጆቹን ሲዘረጋቸው ትልልቅ ክንፎች ያሉት አካል ይመስላል፣ በዚህም አብዛኛውን የግቡን ክፍል መሸፈን ይችላል። ይህ ደግሞ ለአንድ በረኛ ትልቁ ወሳኝ ነገር ነው" የቀድሞ የቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬቨን ሂችኮክ
إظهار الكل...
11👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
አይተኬው ንጎሎ ካንቴ … አይደክሜው ንጎሎ ካንቴ … በዋጋ የማይተመነው እንቁ ንጎሎ ካንቴ …ፀባየ ሰናዩ ታታሪ ንጎሎ ካንቴ… Priceless …!! ሁሌም ትናፈቃለህ !!
إظهار الكل...
👍 13 5
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ዌምብሌ የምንሄደው ለማሸነፍ ነው!! "በካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ሊቨርፑልን አሸንፈን ለቼልሲ ዋንጫዎችን ማንሳት እንደምንችል ማሳየት እንፈልጋለን። ወደ ዌምብሌ የምንሄደው ይህንን ለማድረግ ነው" ኮልዊል
إظهار الكل...
👍 10 8
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲዎች በዌምብሌይ ያደረጓቸውን የመጨረሻዎቹን 6 የፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል። ❌️ 2022 የኤፍኤ ዋንጫ ፍፃሜ ❌️ 2022 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ ❌️ 2021 የኤፍኤ ዋንጫ ፍፃሜ ❌️ 2020 የኤፍኤ ዋንጫ ፍፃሜ ❌️ የ2019 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ ❌️ 2018 ኮሚኒቲ ሺልድ ⏳️ ለ7ኛ ጊዜ በመጪው እሁድ በካራባኦ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ሊቨርፑልን ይገጥማሉ።
إظهار الكل...
8👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዲሳሲ !! ፈረንሳዊው የቼልሲ ተከላካይ አክስኤል ዲሳሲ ትላንት ከማንችስተር ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ ከቼልሲ የመከላከያ ቀጠና ሳጥን ውስጥ 16 ኳሶችን በማፅዳት በክለቡ ያለፉት ስምንት አመታት ታሪክ የነበረውን አሻሽሎ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል። ጄሚ ካራገር ስለ ዲሳሲ የትላንቱ ብቃት ለስካይ ስፖርት ሲናገር “በዚህ የውድድር አመት ከዚህ የተሻለ የመከላከል ብቃት አላስታውስም። ዲሳሲ ዛሬ ያሳየው ብቃት ጆን ቴሪ የሚታወቅበትን አይነት ከፍተኛ የመከላከል ብቃት ነበር" ብሏል። ዲሳሲ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጡም ይታወቃል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ድሮግባ ለተከላካዮች ቅዠት ነበር!! "ዲዲየር ድሮግባ ለተከላካዮች ቅዠት ነበር። ድሮግባ ለፍጹምነት የቀረበ የ9 ቁጥር አጥቂ ባህሪ የተላበሰ ይመስለኛል። የማይታመን ፍጥነትና ሃይል ነበረው፣ በሁለቱም እግሮቹ እንዲሁም በግንባሩ መትቶ ግብ ማስቆጠር የሚችል፣ ከርቀት የሚያገኛቸውን የቆሙ ኳሶች እና የፍፁም ቅጣት ምቶችን ወደ ጎልነት የመቀየር ድንቅ ክህሎት ነበረው። በተለይ ቡድኑ የእሱን እርዳታ በሚፈልግበት አጋጣሚ ሁሉ ድሮግባ ሀላፊነቱን በሚገባ ይወጣ ነበር። ድሮግባ የአሁን ዘመን ተጨዋች ቢሆን ኖሮ የመሸጫ ዋጋው እጅግ ውድ ይሆን ነበር" ዋይኒ ሩኒ
إظهار الكل...
15👏 3👍 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲዎች ማንችስተር ሲቲዎችን ማጥቃት አለባቸው! "ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚጫወት ቡድን ውጤት ይዞ ለመውጣት የሚፈልግ ከሆነ አጥቅቶ ለመጫወት ድፍረት ሊኖረው ይገባል። ቼልሲዎችም በድፍረት ይህን ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ። የሲቲዎችን ጥቃት ፈርተው በመግባት ወደ ኋላ አፈግፍገው በራሳቸው ሜዳ ላይ ለመጫወት የሚወስኑ አይመስለኝም፣ ይህን ካደረጉ ምናልባት ምንም አይነት እድል አያገኙም። ምክንያቱም ማንችስተር ሲቲዎችን በመጨረሻው ሶስተኛ የሜዳህ ክፍል ላይ እንዲቆዩ የምትፈቅድላቸው ከሆነ ከነህይወት እንደሚበሉህ ይሰማኛል። እንደ ካይሴዶ፣ ኤንዞ እና ካላጋር ያሉ ተጫዋቾች ጨዋታውን በሙሉ በመከላከል መጫወትን አይወዱም። እነሱ ሙሉ ጨዋታውን ተከላክሎ የጨረስ ይጠላሉ ብዬ አስባለሁ፣ መከላከል ተፈጥሯዊ ሚናቸው ባለመሆኑ በተሳሳቱ ቁጥር መበሳጨታቸውና መናደዳቸው አይቀርም፣ እናም በመጨረሻም ተስፋ ይቆርጣሉ። እነሱ ራሳቸውን መሆነው እንዲጫወቱ ልትፈቅድላቸው ይገባል። እርግጥ ነው ምናልባት በአሁኑ ሰአት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለመፎካከር የሚችሉበት ደረጃ ላይ አይደሉም። ነገር ግን ፉክክሩን የሆነ ቦታ መጀመር አለባቸው። እናም ይህ ጥሩ እድል ነው ብዬ አስባለሁ። በተለይም ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ስላሸነፉ በተከታታይ ውጤታማ እየሆኑ በራስ መተማመናቸውን ለማሳደግ ሲባል ሲቲን ለማሸነፍ መጫወት አለባቸው " ሴስክ ፋብሪጋስ እናንተስ ምን ትላላችሁ? ዛሬ ቼልሲዎች ውጤት ይዘው ለመውጣት ምን አይነት የጨዋታ ስልት ይዘው መግባት አለባቸው?
إظهار الكل...
👍 12
Photo unavailableShow in Telegram
እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር! ጥያቄ - የቼልሲ ደጋፊዎች ይወዱኛል ብለህ ታስባለህ? ፖቸቲኖ - እውነቱን መናገር አለብኝ፣ ይወዱኛል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም እነሱ ቻምፒዮንስ ሊግን አሸንፈው ያውቃሉ፣ ፕሪሚየር ሊጉንም አሸንፈዋል፣ በእግር ኳስ ውድድር ያሉትን ሁሉም ዋንጫዎች ያሸነፉ ደጋፊዎች ናቸው። እኔ በስድስት እና ሰባት ወራት ውስጥ ምን የሚያስደንቅ ነገር አድርጌ ይወዱኛል?"
إظهار الكل...
"የአሁኑ ቼልሲ ያለፉት 20 አመታት የነበረውን ቼልሲ አይደለም። እንደዚህ ብለን ማሰባችንን ማቆም አለብን። ከዚህ በኋላ እንደበፊቱ አይነት ቼልሲ አይደለንም። ያለፈውን ማሰብ ትተን ወደፊት መጓዝ አለብን" ፖቼቲኖAnonymous voting
  • ልክ ነው
  • ተሳስቷል
0 votes
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ፖቼቲኖ ምን እያለን ነው? "የአሁኑ ቼልሲ ያለፉት 20 አመታት የነበረውን ቼልሲ አይደለም። እንደዚህ ብለን ማሰባችንን ማቆም አለብን። ከዚህ በኋላ እንደበፊቱ አይነት ቼልሲ አይደለንም። ያለፈውን ማሰብ ትተን ወደፊት መጓዝ አለብን" ማውሪዚዮ ፖቼቲኖ ………… …………… …………… ፖቼቲኖ ምን እያለን ነው? … ምን አይነት መልዕክት ማስተላለፍ ፈልጎ ነው? … ይህ ንግግሩ የቼልሲ ደጋፊዎችን በሁለት ጎራ ከፍሎ እያከራከረ ነው። ግማሹ ደጋፊ "ልክ ነው፣ የአሁኑ ቡድን ገና ወጣት እና አዲስ ፕሮጀክ ስለሆነ ከበፊቱ ጠንካራ ቡድን ጋር ሊነፃፀር አይገባም" ሲል ግማሹ ደግሞ "ያለፈው ቡድን ኩራታችን ነው፣ በፍፁም ልንረሳው አንችልም፣ የአሁኑም ቡድን መገንባት ያለበት በባለፈው ቡድን እሴት እና ጥንካሬ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት" ይላሉ። እናንተስ መልዕክቱን እንዴት ተረዳችሁት? እስኪ ሀሳባችሁን አካፍሉን። ፖቼቲኖ ልክ ነው ወይስ ተሳስቷል?
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
“ራምቦ” እያሉ ይጠሩኝ ነበር! "ቶማስ ቱኩል የቼልሲ አሰልጣኝ ሆኖ እንደመጣ የመሰለፍ እድል ሰጠኝ፣ እሱ ከመምጣቱ በፊት በነበረው አሰልጣኝ ስር በምፈልገው መጠን እየተሰለፍኩ ስላልነበር የቶማስ መምጣት ለእኔ ዳግም ውልደት ነበር። እንደውም ብዙ አሰልጣኞች ሊማሩበት ይችላሉ ብዬ የማስበውን አንድ ነገር አደረገ። ነገሩ ከታክቲክ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበረውም። ምን መሰለህ፣ የመጀመሪያውን ልምምድ ስንጨርስ በቀጥታ ወደ እኔ መጣና “ቶኒ እስኪ ስለራስህ ንገረኝ” አለኝ እልኸኛነቴ እና የማሸነፍ ጠንካራ ፍላጎቴን ከየት እንዳመጣሁት ለማወቅ ፈልጎ ነበር። በበርሊን-ኒውኮልን ስላደግኩ በአካባቢያችን ባለ ኮሮኮንቻማ ሜዳ ላይ እንዴት ጠንክሬ እጫወት እንደነበርና በዚህም የተነሳ ሁሉም ትልልቅ ልጆች “ራምቦ” እያሉ ይጠሩኝ እንደነበር በስሜት ተውጪ ነገርኩት። የልጅነት ትዝታዬን አጫወትኩት። ቶማስ እንደ አባት ነበር የቀረበኝ እና ስለ እኔ ለማወቅ ፈልጎ የጠየቀኝ። ያ ለእኔ ትልቅ ነገር ነበር፣ የመፈለግ ስሜት ተሰማኝ። ቶማስ የመሰለፍ እድሉን ሲሰጠኝ ብዙ መነሳሳት ስለነበረኝ ተመልሼ ወደ ተጠባባቂ ወንበር እንደማልመለስ አውቀው ነበር። እሱ ከመምጣቱ በፊት ስለ እኔ ብቃት የሚነገረው ነገር ትክክል አልነበረም። በተቃራኒው እኔ ለክለቡ እና ደረቴ ላይ ለለጠፍኩት አርማው 200% ያለኝን ሁሉ ለመስጠት ወስኜ ነበር። ለእኔ ከቼልሲ ጋር ያሳካሁት የሻምፒዮንስ ሊግ ድል ለዚህ ያልተቆጠበ ጥረቴና ልፋቴ የተበረከተ ውድ ስጦታ አድርጌ ነው የምቆጥረው። " አንቶኒዮ ሩዲገር
إظهار الكل...
👍 14 5