cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

ይህ የቴሌግራም ቻነል የእግር ኳስ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተለይ ለእንግሊዙ የለንደን የእግር ኳስ ክለብ ቼልሲ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ያቀርባል! አላማችን ኢትዮጵያዊያን የቼልሲ ደጋፊዎች ጥራት ያለው እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እንዲሁም ስለሚደግፉት ክለብ አኩሪ ታሪክ፣ ጠንካራ ማንነት፣ የድል አድራጊነት ባህል ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መስራት ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 155
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-97 أيام
-1830 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የተሰበረውን ቼልሲ መጠገን ይችላሉ "ጆዜ ሞሪንሆ በግዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ሊመጣ እንደሚችል እና እሱ ደግሞ ጆን ቴሪን በረዳትነት ሊያመጣው እንደሚችል የሚወራውን ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። ይህ ነገር እውነት ሆኖ ማየት ቢቻል እንዴት ጥሩ ነበር፣ ነገር ግን ይሆናል ብሎ ማሰቡ ራሱ አስደሳች ነገር ነው። ሁለቱም ጠንካራ የቼልሲ ማንነት ስላላቸው ልምዳቸው ተጨምሮበት ቡድኑን ወደ ቀድሞው አስፈሪ ባህሪው ይመልሱት ነበር። በአሁኑ ሰአት ቼልሲ ማለት የተሰበረ ቡድን ነው፣ እና እነዚህ ሁለት ሰዎች ከመጡ ስብራቱን ሊጠግኑለት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ" አማኑኤል ፐቲት
إظهار الكل...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
በፖቸቲኖ ላይ ያለው ጫና እየጨመረ ነው! የቼልሲ ክለብ ባለቤቶች አሁንም ማውሪሲ ፖቼቲኖን ለማባረር አልወሰኑም። ነገር ግን በቀጣይ ያሉ ጨዋታዎች ውጤት የማይቀየር ከሆነ አሰልጣኙን ስለማሰናበት ያስባሉ። ሲል ፋብሪዚዮ ሮማኖ ገልጿል። ጥያቄው እስካሁን የተሰጠውን ግዜ ተጠቅሞ ተስፋ ሰጪ ነገር ማሳየት ያልቻለን አሰልጣኝ በቀጣዮቹ ጥቂት ጨዋታዎች ካላሸነፈ አሰናብተዋለሁ ብሎ ማሰብ በራሱ የተምታታ አቋም ነው። አሁን ያለው ቼልሲ ቀጣዮቹን ጨዋታ በአጋጣሚ ቢያሸንፍ ጥሩ ሆነ ማለት ይቻላል? ማሰናበት ካስፈለገ ቶሎ ወስኖ ማሰናበት አልያም በአቋማቸው ፀንተው በማንኛውም ሁኔታ አቆይቶ የሚሆነውን ማየት ነበረባቸው። ግራ የገባ ነገር ነው!
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ እግር ኳስ እንጂ የአሜሪካ ቤዝቦል አይደለም! "ከጅምሩ ጀምሮ የቼልሲ ባለቤቶች ትክክለኛና ልምድ ያላቸውን የእግር ኳስ ባለሙያዎችን አይሰሙም፣ አይፈልጉም። ቶድ ቦሊ ወደ ቼልሲ እንደመጣ ራሱን የክለቡ ግዜያዊ የእግር ኳስ ዳይሬክተር (የስፖርት ዳይሬክተር) አድርጎ መሾሙን አስታውሳለሁ፣ በእውነት ይህን ማመን ይከብዳል። አዝናለሁ፣ ይሄ ማለት እኮ ልክ አሌክስ ፈርጉሰንን ወደ አሜሪካ ወስዶ የ ኤል.ኤ ዶጀርስ የቤዝቦል ቡድንን መሾም ማለት ነው፣ ይህ በፍፁም ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም። ቶድ ቦሊ በአሜሪካ የዶጀርስ ቆይታው ተሳክቶለት ይሆናል፣ ነገር ግን እያወራን ያለነው ስለ እንግሊዝ እግር ኳስ እንጂ ስለ አሜሪካ ቤዝቦል አይደለም" ግርሃም ሱነስ
إظهار الكل...
👍 5🤯 3
Photo unavailableShow in Telegram
የ ጨ ዋ ታ ቀ ን !! 💙 ዛሬ ቀን 11 ፡ 00 ሰዓት 💙 የፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ 💙 ቼልሲ ከዎልቭስ 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የየካቲት ወር ጨዋታዎች! በያዝነው ወር (የካቲት) ውስጥ ብቻ ቼልሲዎች 5 ጨዋታዎችን ያደርጋሉ። 3 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከዎልቭስ፣ ከፓላስ እና ማንችስተር ሲቲ ጋር፣ 1 የኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታ ከአስቶን ቪላ ጋር እንዲሁም የካራባኦ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ከሊቨርፑል ጋር ያከናውናሉ። መልካም እድል ለሰማያዊዎቹ!!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞው የቼልሲ ተጨዋች ፍራንክ ለበፍ የቼልሲ ተጨዋቾች ከሊቨርፑል ጋር ሲጫወቱ ባሳዩት ደካማ አቋም ክፉኛ ተችቷቸዋል። "ከንኩንኩ በስተቀር የቼልሲ ተጨዋቾች በሙሉ በከፍተኛ ደረጃ ለመጫወት የሚያስችል ብቃት የላቸውም፣ ወይም እያሳዩ አይደለም። አሁን በሚያሳዩት ብቃት መጫወት የሚችሉት በሊጉ ወገብ ወይም አጋማሽ ላይ ለሚገኙ ክለቦች ነው። በሊቨርፑሉ ጨዋታ ንኩንኩ ተቀይሮ ሲገባ ትልልቅ ተጨዋቾች እንዴት እንደሚጫወቱ አሳይቷል። ሌሎቹ ተጨዋቾች ግን በቼልሲ ደረጃ የሚገኙ አይደሉም፣ መካከለኛ ደረጃ ተጨዋቾች ናቸው" ፍራንክ ለበፍ ትስማማላችሁ?
إظهار الكل...
13👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የ ጨ ዋ ታ ቀ ን !! 💙 ዛሬ ምሽት 4 ፡ 45 ሰዓት 💙 የኤፍ ኤ ዋንጫ 4ኛ ዙር ጨዋታ 💙 ቼልሲ ከአስቶን ቪላ 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!! 💙 እየተወያየን፣ እየተማማርን፣ እየተዝናናን ቼልሲን አብረን እንደግፍ!! 💙 የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ 👇🏿 https://www.youtube.com/@TBPSK
إظهار الكل...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
የካራባዎ ዋንጫ ፍፃሜ! በደርሶ መልስ ውጤት ሚድልስብሮን 6 -2 በማሸነፍ ቀድመው የፍፃሜው ተፋላሚ መሆናቸውን ያረጋገጡት የቼልሲዎች የፍፃሜ ተጋጣሚ ሊቨርፑሎች መሆናቸው ተረጋግጧል። ትላንት ምሽት ከፉልሃም ብርቱ ፉክክር የገጠማቸው ሊቨርፑሎች በድምር ውጤት 3-2 በማሸነፍ ለዌምብሌዩ የፍፃሜ ጨዋታ የደረሱ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች የዛሬ 3 አመት በዚሁ መድረክ ላይ ተገናኝተው ሊቨርፑል የዋንጫ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ነው። የፍፃሜው ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን የግዜ አቆጣጠር የካቲት 17፣ 2016 ዓ.ም እሁድ የሚከናወን ይሆናል።
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሴዛር ካሳዴይ ይመለሳል!! ቼልሲዎች በውሰት ውል ለሌስተር ሲቲ ሰጥተውት የነበረውን ወጣት ጣሊያናዊው አማካኝ ሴሳሬ ካሳዴይን የውሰት ውሉን አቋርጦ እንደመለስ መወሰናቸው ታውቋል። እንደተመለሰም በማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የመጀመሪያ ቡድን ውስጥ እንደሚካተትና ልምምድ ማድረግ እንደሚጀምር ተገልጿል። ካሳዴይ የሻምፒዮንሺፑ መሪ ለሆነው ሌስተር ሲቲ 25 ጨዋታዎችን አድርጎ 3 ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወቃል። ብዙ የቼልሲ ደጋፊዎች ቼልሲ በቅደመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ባሳየው ድንቅ አቋም ምክንያት በልጁ የመመለስ ውሳኔ ደስተኛ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
إظهار الكل...
👍 10
ጆዜሞሪንሆ ከሮማ ጋር መለያየቱን ተከትሎ በድጋሚ ቼልሲን ሲያሰለጥን ማየት ትፈልጋላችሁ??Anonymous voting
  • አዎ እፈልጋለሁ
  • አይ አልፈልግም
0 votes
Photo unavailableShow in Telegram
ጆዜ ሞሪንሆ እና ሮማዎች በድንገት መለያየታቸው ይፋ ሆነኗል። ቀጣዩ የጆዜ ክለብ ማን ይሆን? ጆዜን በድጋሚ ቼልሲን ሲያሰለጥን ማየት ትፈልጋላችሁ??
إظهار الكل...
👍 10
እንደ ማት ሎው ዘገባ ከሆነ ቼልሲዎች በሳውዲ አረቢያ ሊግ ከሚጫወቱ ተጨዋቾች መካከል በካሪም ቤንዜማና በፈርሚንሆ አይነት ደረጃ ያለው ሁነኛ አጥቂ ቀሪው የውድድር አመት እስኪጠናቀቅ ድረስ በሚቆይ የውሰት ውል ለማስፈረም ይፈልጋሉ፣ ይህንን ለማሳካት እንቅስቃሴም ጀምረዋል። በእናንተ ምርጫ ከሁለቱ እጩዎች ለቼልሲ የፊት መስመር ችግር የተሻለ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው ማነው? ቤንዜማ ወይስ ፊርሚንሆ?Anonymous voting
  • ቤንዜማ
  • ፊርሚንሆ
0 votes
🔥 4😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
1
Photo unavailableShow in Telegram
ኦሊቪየ ጂሩ ? የሊቨርፑሉ የመሀል ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ በሊጉ በጣም ያስቸገረው ተጋጣሚ ማን እንደሆነ ተጠይቆ ሲመልስ፣ "ኦሊቪየ ጂሩ ይመስለኛል። እሱን በጨዋታዬ ሁልጊዜ እንደያዝኩት አስባለሁ፣ ሁሉን መንገድ ዘግቼበት በደንብ ተቆጣጥሬዋለሁ የሚል ስሜት ይሰማኛል፣ ነገር ግን ሁልጊዜም በሆነ መንገድ ወይም ክፍተት በኩል ጎል ማስቆጠር ይችላል። በጭንቅላቱ፣ በእግሩ፣ በጉልበቱ ወይም በሆነ የሰውነቱ ክፍል ተጠቅሞ በእኔ ላይ ጎል ደጋግሞ አስቆጥሯል" እናንተስ ስለ ኦሊቪየ ጂሩ ምን አይነት ትውስታ አላችሁ? አሁን ቼልሲ ካለበት የጨራሽ አጥቂ ችግር እና ጂሩ ለቼልሲ እየሰጠ ከነበረው አገልግሎት አንፃር ቼልሲዎች እሱን ማሰናበታቸው ትክክለኛ ውሳኔ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ?
إظهار الكل...
😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
ለፔትሮቪች የዛሬ ብቃት ከ10 ስንት ትሰጡታላችሁ? ልጁ ገና 24 አመቱ ነው፣ እርጋታውና ብስለቱ ግን ከእድሜው በላይ ነው። ቼልሲዎች ከፒተር ኦስጉድ እና ከፒተር ቼክ በኋላ ለረጅም ግዜ መረባቸውን በንቃት እና በታማኝነት የሚጠብቅላቸው ሁነኛ ግብ ጠባቂ ያገኙ ይመስላል። ቼልሲን ከ1964 -1974 በግብ ጠባቂነት ያገለገለው እና በብቃቱ የቼልሲ የምንግዜም ምርጥ በረኛ ተብሎ ከሚታወሰው እንግሊዛዊው ፒተር ኦስጉድ እና ከሌላኛው የክለቡ ድንቅ በረኛ ቼካዊው ፒተር ቼክ ጋር የሚቀራረብ አገልግሎት የመስጠት አቅም (potential) እንዳለው እያሳየ ነው። ፒተር ኦስጉድ ⏩ ፒተር ቼክ ⏩ ለፔትሮቪች ⏳ የስማቸው መቀራረብም ይገርማል!
إظهار الكل...
👏 19👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አስጨናቂውን ጨዋታ ቼልሲዎች 1ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፈዋል። ዋናው 3 ነጥቡ ነው የሚለው ሀሳብ ያስማማል!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኮል ፓልመር ባስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ጎል ቼልሲዎች ጨዋታውን አንድ ለዜሮ እየመሩ ወደ እረፍት አምርተዋል። የመጀመሪያውን 45 ደቂቃ ጨዋታ እንዴት አገኛችሁት?
إظهار الكل...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው ጨዋታ ፉልሃምን በብሪጅ የሚገጥሙት ቼልሲዎች አሰላለፋቸው ይህን ይመስላል። እንዴት አያችሁት? ውጤቱን ገምቱ! ድል ለሰማያዊዮቹ!!
إظهار الكل...
የ ጨ ዋ ታ ቀ ን !! 💙 ዛሬ ቀን 9 ፡ 30 ሰዓት 💙 የፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታ 💙 ቼልሲ ከ ፉልሃም 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!! 💙 እየተወያየን፣ እየተማማርን፣ እየተዝናናን ቼልሲን አብረን እንደግፍ!! 💙 የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ 👇🏿 https://www.youtube.com/@TBPSK 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!!
إظهار الكل...
👍 4
ጆን ቴሪ - አዲሱ ቼልሲ ያላየው የስኬት ሚስጢር ?? በቼልሲ የመልሶ ግንባታ ሂደት ውስጥ ከተሰሩት ትልልቅ ስህተቶች አንዱ ጆን ቴሪን በዋናው ቡድን ውስጥ በሆነ አይነት ሚና አለመጠቀማቸው ነው። ጆን ቴሪ በአዲሱ የቼልሲ የቡድን ግንባታ ላይ ለክለቡ ስኬታማ መሆን ከፍያለ ሚና መጫወት የሚችል ሁሉ ነገሩ ከሰማያዊዎቹ ጋር የተቆራኘ ሰው ነው። ለምሳሌ፣ አሁን ቼልሲ የአሸናፊነት ማንነቱን ቀስ በቀስ እያጣ ነው፣ ሁሉም የቡድኑ አባላት እና ባለቤቶቹ ለቼልሲ አዲስ ናቸው። ቴሪ ደግሞ የቼልሲ የአሸናፊነት ዘመን ምልክት ነው። ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ ከ50 አመት በኋላ ሲያሸንፍ የነበረው የመሪነት ሚና በክለቡ ታሪክ በደማቁ የተፃፈ ገድል ነው። ይህ ስኬቱ በቼልሲ ቤት የተለመዱ እና ከፍ ብለው የተሰቀሉ የጥራት እና የድል አድራጊነት ባህሎች ተጠብቀው መቀጠላቸውን የማረጋገጥ ሚና መጫወት እንዲችል ያደርገዋል። ለቼልሲ መጫወት ምን ማለት እንደሆነ ለማሳወቅ እና የአዳዲስ ተጫዋቾችን ሞራል ከፍ የሚያደርግ ጠንካራ ስብእና ያለው ሰው ነው። ክለቡ አንድ አሰልጣኝ ስራ ሲቀየር ውጤታማ የሽግግር እንዲኖረው አሰልጣኙን ለመርዳት እና ጠቃሚ መረጃን ለመስጠትም ከበቂ በላይ እውቀትም፣ ዝግጅትም፣ ፍላጎትም አለው። በእያንዳንዱ ክለብ ውስጥ ክለባቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ የሚወዱና በስሜትም ጭምር የተሳሰሩ ከጀርባ ሆነው የሚሰሩ በጣም አስፈላጊ ባለሙያዎች አሉ። በቼልሲ ቤት ጆን ቴሪ ለዚህ ሚና በጣም ተስማሚ ይመስለኛል። ችግሩ የቼልሲ ባለቤቶች ቼልሲን እንደ አዲስ መስራት እና ከዜሮ መጀመር እንጂ ያለፈ ስኬቱ ላይ መሰረት አድርገው ስኬቱን ማስቀጠል የሚፈልጉ አይመስልም። እንደ ቼልሲ ያለ እጅግ በጣም ስኬታማ ክለብን ያለፈ ጠንካራ ጎን ትቶ ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ መጀር ደግሞ ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። አሁን በቼልሲ ቤት እየሆነ ያለውም ይህው አላስፈላጊ የሆነ ጠንካራ ማንነት አፍርሶ አዲስ ማንነት የመፍጠር ውጤት አልባ ልፋት ነው።
إظهار الكل...
👍 6🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ዴቪድ ዳትሮ ፎፋና ወደ በርንሌይ! ዴቪድ ዳትሮ ፎፋና ከቼልሲ በውሰት ውል በርንሌይን ሊቀላቀል ነው። ቼልሲዎች አጥቂው የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ማግኘት አለበት ብለው ስላመኑ ነው ቀደም ሲል በውሰት ከሄደበት የጀርመኑ ክለብ ዩኒየን በርሊን የተጠራው። … … … ጥያቄ? በዴቪድ ዳትሮ ፎፋና እና በኒኮላስ ጃክሰን መካከል ያለው ወቅታዊ ብቃት (performance) ፣ ችሎታ (skill)፣ ልምድ (experiance) እና አቅም (potential) ምን ያህል ሰፊ ቢሆን ነው አንዱ የቼልሲ አንደኛ ተመራጭ አጥቂ ሌላኛው ደግሞ በውሰት ውል በየክለቡ የሚዞረው? ተወያዩበት!
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲዎች ከእረፍት በፊት በተቆጠረባቸው አንድ ጎል የመጀመሪያውን ጨዋታ ተሸንፈዋል። የመልሱ ጨዋታ በብሪጅ ስለሚካሄድ ውጤቱን ቀልብሰው የማለፍ እድላቸው አሁንም አልተሟጠጠም። በተለይ ፓልመር ዛሬ ጥሩ አልነበረም፣ ካይሴዶ ቀስ በቀስ ወደሚታወቅበት ብቃቱ እየተመለሰ ይመስላል። እናንተ ጨዋታውን እንዴት አገኛችሁት?
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በምሽቱ ጨዋታ ሚድልስብራን የሚገጥሙት ቼልሲዎች አሰላለፋቸው ይህን ይመስላል። እንዴት አያችሁት? ውጤቱን ገምቱ! ድል ለሰማያዊዮቹ!!
إظهار الكل...
1
Photo unavailableShow in Telegram
ጥያቄ ? ለቼልሲ ከተጫወቱ በርካታ ብራዚላዊያን መካከል የእናንተ ምርጡ ተጨዋች ማነው? ምርጫው በፎቶው ላይ ያልተካተቱትንም ይጨምራል።
إظهار الكل...
1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢያን ማትሰን ወደ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ! ኢያን ማትሰን በውሰት ውል ወደ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከመሄዱ በፊት ከቼልሲ ጋር እስከ ሰኔ 2027 ድረስ የሚቆይ አዲስ የኮንትራት ውል ይፈራረማል። ከፊርማው በኋላ ማትሰን ዛሬውኑ (ማክሰኞ) ወደ ጀርመን እንደሚጓዝና ነገ ረቡዕ የህክምና ምርመራውን አከናውኖ በይፋ ዶርትሙንዶችን ይቀላቀላል። የውሰት ውሉ የሚቆየው እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ይሆናል። ማትሰን መልካም ግዜ መዶርትሙንድ እንዲያሳልፍ ተመኘን!
إظهار الكل...
1
Photo unavailableShow in Telegram
የ ጨ ዋ ታ ቀ ን !! 💙 ዛሬ ምሽት 5 ፡ 00 ሰዓት 💙 የካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ (የመጀመሪያ ጨዋታ) 💙 ሚድልስብሮ ከቼልሲ 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!! 💙 እየተወያየን፣ እየተማማርን፣ እየተዝናናን ቼልሲን አብረን እንደግፍ!! ………………………………………………… 💙 የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ 👇🏿 https://www.youtube.com/@TBPSK
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ማይክል ሄንዝ ጎልዲንግ! እ.ኤ.አ. በግንቦት 23 2006 የተወለደውና የአማካይ መስመር ተጫዋች የሆነው የ17 አመቱ እንግሊዛዊ ታዳጊ ማይክል ሄንዝ ጎልዲንግ ለቼልሲ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከፕረስተን ጋር በተደረገ የኤፍ ኤ ዋንጫ ግጥሚያ ላይ አድርጓል። Remember the name!
إظهار الكل...
🔥 14
Photo unavailableShow in Telegram
4 ! ቼልሲዎች ከእረፍት መልስ ባስቆጠሯቸው አራት ጎሎች 4 ለ 0 አሸንፈው ወደ አራተኛው ዙር አልፈዋል!
إظهار الكل...
11
Photo unavailableShow in Telegram
ጨዋታው በዜሮ አቻ ወደ እረፍት አምርቷል። የመጀመሪያውን 45 ደቂቃ ጨዋታ እንዴት አገኛችሁት?
إظهار الكل...
🌚 6
Photo unavailableShow in Telegram
ቲሞ ወደ ቶትንሃም? የቀድሞው የቼልሲ አጥቂ ቲሞ ቨርነር በያዝነው የጥር የዝውውር መስኮት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ሊዛወር ይችላል ተብሎ ሲነገር ቢቆይም አሁን ላይ ከጀርመን እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት በዚሁ የዝውውር መስኮት ቶተንሃምን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ በውሰት ውል ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል። ቨርነር በዚህ የውድድር አመት በቡንደስሊጋው በስምንት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ከአርቢ ላይፕዚግ ጋር እስከ 2026 ክረምት ድረስ የሚያቆይ ውል አለው። ቲሞ በቼልሲ የታሰበውን ያህል ስኬታማ ባይሆንም በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ ግን በጣም ተወዳጅ ነው። እናንተ ስለ ቲሞ ያላችሁ ስሜት ምን አይነት ነው? ለአጭር ግዜም ቢሆን እሱን በቶትንሃም ማሊያ ሲጫወት ማየቱ ምን አይነት ስሜት ይፈጥር ይሆን?
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው ጨዋታ ፕረስተንን የሚገጥሙት ቼልሲዎች አሰላለፋቸው ይህን ይመስላል። እንዴት አያችሁት? ውጤቱን ገምቱ! ድል ለሰማያዊዮቹ!!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የ ጨ ዋ ታ ቀ ን !! 💙 ዛሬ ምሽት 2 ፡ 30 ሰዓት 💙 የኤፍ ኤ ዋንጫ 3ኛ ዙር ጨዋታ 💙 ቼልሲ ከፕረስተን 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!! 💙 እየተወያየን፣ እየተማማርን፣ እየተዝናናን ቼልሲን አብረን እንደግፍ!! 💙 የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ 👇🏿 https://www.youtube.com/@TBPSK 💙 የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል 👇🏿 https://t.me/beakal_chelsea 💙 ድል ለሰማያዊው ኩራት ቼልሲ!!
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች! 💙 ቼልሲዎች የቶትንሃም ሆትስፐርስ እና የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የሆነውን ፈረንሳዊ ተከላካይ ዣን ክሌር ቶዲቦን ይፈልጋሉ። ቼልሲዎች ቶዲቦ ላይ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ቢሆንም ክለቡ ኒስ ግን በጥር ወር ለመሸጥ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ዴይሊ ሜል ዘግቧል። 💙 ቼልሲዎች ታዳጊውን አሌክስ ማቶስን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ በሻምፒዮንሺፕ ለሚወዳደረው ክለብ ሀደርስፊልድ ታውን በውሰት ለመስጠት መስማማታቸውን ዘ አትሌቲክስ ዘግቦታል። 💙 ታዳጊው የቼልሲ ተጨዋች ዛክ ስተሪጅ በፒተርቦሮ ዩናይትድ ያለው የውሰት ጊዜ ከተቋረጠ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ቼልሲ መመለሱን ዘ አትሌቲክስ ዘግቦታል። 💙 በውሰት ውል ኒውካስትልን የተቀላቀለውና በአሰልጣኝ ኤዲ ሃው ቋሚ አሰላለፍ ለመግባት እየተቸገረ ያለው ሉዊስ ሀል በኒውካስል ለመቆየት መዘጋጀቱ በዴይሊ ቴሌግራፍ ተዘግቧል። 💙 ቼልሲዎች የቤኔፊካውን ተከላካይ አንቶኒዮ ሲልቫን ለማዘዋወር ቅደመ ዝግጅት እያደረጉ ነው ሲል ዘ ሰን መረጃውን አጋርቷል። 💙 ትሬቮህ ቻሎባ ምንም እንኳን የጉዳት ችግር ቢገጥመውም በዚህ የጥር ወር ቼልሲን ሊለቅ ይችላል። ባየር ሙኒክ የትሬቮህ ቻሎባህ ፈላጊ ሲሆን ሁኔታውን ለረጅም ግዜ ሲከታተል መቆየቱ ይታወቃል።
إظهار الكل...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ፓልመር! በታህሳስ ወር ብቻ አራት ግቦች ያስቆጠረውና ሁለት የጎል ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለው ወጣቱ ኮል ፓልመር የታህሳስ ወር የፕሪምየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ለመሆን በእጩነት ተመርጧል።
إظهار الكل...
17👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች 💙 ብራዚላዊው የቼልሲ ተጨዋች አንድሬ ሳንቶስ የውሰት ውሉን አቋርጦ ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ቼልሲ መመለሱ ታውቋል። የውሰት ውሉ እንዲቋረጥ የተደረገው ሳንቶስ በውል ስምምነቱ መሰረት በቂ የመጫወት እድል ባለማግኘቱ እንደሆነ ታውቋል። 💙ኮኖር ጋላገር በያዝነው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ቼልሲን እንደማይለቅ ተዘግቧል። 💙 ሰሞኑን በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ አድናቆት እየተቸረው ያለው ወጣቱ አልፊ ጊልክሪስት የብዙ ክለቦችንም ትኩረትና ፍላጎት እየሳበ ነው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ ቼልሲዎች ወጣቱን በውሰትም ሆነ በግዢ ለማዘዋወር የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ አይደሉም። ወጣቱ ባለፈው የውድድር ዘመን የቼልሲ ከ21 አመት በታች ቡድን አምበል የነበረ እና በውድድሩ ላይ የወቅቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት በእጩነት ቀርቦ እንደነበር ይታወቃል።
إظهار الكل...
👍 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶርትሙንዶች በተከፈተው የጥር የዝውውር መስኮት ኢያን ማትሰንን ለማዘዋወር ከቼልሲዎች ጋር መነጋገር ጀምረዋል። ቼልሲዎች ለከማትሰን ሽያጭ 30 ሚሊየን ፓውንድ ለማግኘት መወሰናቸው የታወቀ ሲሆን ይህም ውሳኔ የዝውውር ድርድሩን ለዶርትሙንዶች አስቸጋሪ እንደሚያደርግባቸው ተዘግቧል። በሌላ መረጃ የቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ የሃኪም ዚያሽን የውሰት ውል ለማራዘምም ሆነ ተጨዋቹን በግዢ ለማዘዋወር ፍላጎት ስለሌለው ዚያሽ ወደ ቼልሲ እንደሚመለስ ይጠበቃል።
إظهار الكل...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ጥር 1 - 2024! ዛሬ በጀመረው የአዲሱ የፈረንጆች አመት 2024 የመጀመሪያ ወር ውስጥ ብቻ ቼልሲዎች 5 ጨዋታ ያደርጋሉ። 2 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከፉልሃምና ከሊቨርፑል ጋር፣ 2 የካራባኦ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ከሚድልስብሮ ጋር እንዲሁም 1 የኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታ ከፕረስተን ጋር ያከናውናሉ። ቼልሲዎች ስንት ጨዋታዎች በድል ያጠናቅቃሉ? የትኞቹን? ለአንድ ወር የሚቆየው የጥር የዝውውር መስኮቱም ዛሬ ተከፍቷል። ቼልሲ እነማንን አስፈርሞ፣ እነማንን ያሰናብታል? ወይም በውሰት ይሰጣል የሚለውን መረጃ ለማግኘት ደጋፊዎች በጉጉት ይጠብቃሉ። አብራችሁን ሁኑ፣ እንደተለመደው ተአማኒነታቸው የተረጋገጡ መረጃዎችን በጥራትና በትኩሱ እናደርሳችኋለን።
إظهار الكل...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ጋላገር ፓልመርን አሞካሽቶታል! "ኮል ፓልመር ምርጥ ተጫዋች ነው፣ ለሁሉም ሰው በግልፅ የሚታይ ችሎታና ተሰጥኦ አለው። ከኳስ ጋርም ሆን ያለ ኳስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በጣም ድንቅና ውጤታማ ነው። ወደ ቼልሲ የመጣው በቅርቡ ቢሆንም ለመላመድ ግዜ አልፈጀበትም፣ በዚህ የውድድር ዘመን ለክለባችን ድንቅ ስራ እየሰራልን ነው። ከሼፍልድ ጋር በነበረን ጨዋታ በሁለቱም ጎሎች ላይ ተሳትፏል። አንድ ድንቅ ግብ አስቆጥሯል፣ ለሌላኛዋ ጎል መቆጠርም ምክንያት ሆኗል። በዚሁ ብቃቱ እንደሚቀጥል አምናለሁ፣ እሱ ከእኛ ጋር በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን። ኮል ለሁላችንም በጣም ጥሩ የቡድን ጓደኛም ነው" ኮኖር ጋላገር
إظهار الكل...
19
ለቼልሲ ውጤት ማጣት ዋነኛው ተጠያቂ ማነው? 1- የክለቡ ባለቤቶች - 63.3% 2 - አሰልጣኙ - 1.7% 3 - የስፖርቲንግ ዳይሬክተሮቹ - 18.3% 4 - ተጨዋቾቹ - 10.5% 5 - ሮማን አብራሞቪች - 6.5% ሰሞኑን ታዋቂው The Athletic በሰራው ለቼልሲ ደጋፊዎች ባዘጋጀው መጠይቅ 63.3% የሚሆኑት ደጋፊዎች ለቼልሲ ውጤት ማጣት የክለቡን ባለቤቶች ዋነኛ ተጠያቂ አድርገዋል። ለምን? ሮማን አብራሞቪች በቼልሲ የስልጣን ቆይታው መጀመሪያ ላይ ያደረጋቸው እና ውጤታማ ያደረጉት 3 መሰረታዊ ነገሮች ነበሩ። ሮማን አብራሞቪችን ውጤታማ እንዲሆን ያደረጉትን እነዚህን 3 መሰረታዊ ነገሮች አዲሶቹ የቼልሲ ባለቤቶች እነቶድ ቦሊ አላደረጓቸውም። እነዚህ ልዩነት የሚፈጥሩ 3 መሰረታዊ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። 1 - አሰልጣኝን በተመለከተ አብራሞቪች አሰልጣኝን በተመለከተ ያለው ሽግግር በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከናወን በመወሰኑ በወቅቱ የነበረውን አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒየሪን ለተጨማሪ አንድ የውድድር ዘመን አቆይቶ በ2004 የአውሮፓ ሻምፒዮን የሆነውን ጆሴ ሞሪንሆን አምጥቷል። ጆሴም በመጣበት አመት ቼልሲን ከ50 አመት በኋላ የሊጉ ሻምፒዮን አድርጎታል። የእነ ቦሊ አስተዳደር ግን በተቃራኒው ክለቡን ከተረከቡ በኋላ የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊውን ቶማስ ቱኩልን አሰናበቱ። 2 - አንጋፋ (መሪ) ተጨዋቾችን በተመለከተ ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን እንደተረከበ የክለቡን ነባር እና መሪ ተጨዋቾች ማለትም ኩዲቺኒ፣ ቴሪ፣ ጋላስ፣ ላምፓርድ፣ ሃሰልባይንክ፣ ጉድጆንሰን ወዘተ... አቆይቶ አዲስ ፈራሚዎችን በጥንቃቄ ሲመለምሉ ቆይተው ጆሴ ሞሪንሆ ሲመጣ በጋራ ሆነው ትልልቅ ተጨዋቾችን ማስፈረም ጀመሩ። የእነ ቦሊ አስተዳደር ግን በተቃራኒው ክለቡን ከተረከቡ በኋላ የቡድኑን አንጋፋ ተጨዋቾች በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ አሰናብተው ከ1 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ በማውጣት ልምድ የሌላቸውን እና እድሜያቸው ከ25 በታች የሆኑ ታዳጊና ወጣት ተጨዋቾችን አስፈርመዋል። ከነዚህ ሁሉ ዝውውሮች መካከል ኮል ፓልመር ብቻ ነው ለወጣበት ዋጋ ተመጣጣኝ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የሚመስለው። ኤንዞ እና ካይሴዶ እጅግ በውድ ዋጋ ቢመጡም ወጣት በመሆናቸው ለወደፊቱ ይጠቅሙ ይሆናል እንጂ እስካሁን የሰጡት አገልግሎት ከዋጋቸው በታች ነው። 3- የስፖርቲንግ ዳይሬክተርን በተመለከተ ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን እንደተረከበ ለረጅም አመታት የማንችስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር የነበረውን ፒተር ኬንዮንን የቼልሲ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር አድርጎ ቀጥሯል። ለምን? ምክንያቱም እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ እና 2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ማንችስተር ዩናይትዶች ፕሪሚየር ሊጉን ተቆጣጥረው ነበር። ለዚህም ስኬታቸው ፒተር ኬንዮን ቁልፍ ሚና ነበረው። እናም የሮማን ውሳኔና እርምጃ ሙሉ ለሙሉ ትርጉም ያለው ነበር። በተቃራኒው የእነ ቶድ ቦሊ አስተዳደር በስልጣን ላይ በነበረበት የመጀመሪያ ወር የአሸናፊነት ልምድ ያላቸውን የቦርድ አመራር አባላት የነበሩትን ብሩስ ባክን እና ማሪና ግራኖቭስካያን ጨምሮ አሰናበተ። የሚገርመው በዋናነት የሁለቱንም ቦታዎች ወስዶ የቦርድ ሊቀመንበር እና ጊዜያዊ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር አድርጎ ራሱን ሾመ። ቶማስ ቱኩል ከተባረረ በኋላ ቦሊ የተጨዋች ምልመላና ቅጥር የሚያከናውኑ ባለሙያዎችን ሳውዝሃምፕተን፣ ሞናኮ እና ብራይተንን ከመሳሰሉ አነስተኛና መካከለኛ ክለቦች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎችን ቀጠረ። ከዚያ በኋላ የሰማያዊዎቹ የውጤት ጉዞ በግልፅ እና በፍጥነት ማሽቆልቆል ጀመረ፣ ሮማን ልምዳቸው የተረጋገጠ ምርጥ ባለሙያዎችን እና ተጨዋቾችን ሰብስቦ ከታች በመነሳት በአጭር ግዜ የገነባው አስፈሪው የቼልሲ ማንነት በፍጥነት መፈራረስ ጀመረ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት "የጀመርነው የረጅም ግዜ ፕሮጀክት ነው ስለሆነ እንዲህ ያለ ነገር ያጋጥማል" የሚል ነው። እናንተስ ምን ትላላችሁ? በእናንተ አስተያየት ለቼልሲ የወቅቱ የውጤት ቀውስ ዋነኛው ተጠያቂ ማነው? ለምን?
إظهار الكل...
👍 5👎 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.