cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🏷 قناة السلف الصالح 🔍

🔍የተለያዩ ዳእዋዎች ትምህርቶች እንዲሁም ለዑማው ጠቃሚ ነገሮች በሱና ኡስታዞች የሚተላለፍበት ቻናል ነው:: 🔘ቁርአንና ሐዲስን በቀደምቶች በሰሃቦች አረዳት ለዑማው ማድረስ.. ከሽርክ እና ቢዳአ ማስጠንቀቅ❗️ 👉ሀቅ ለሚፈልግ ሰው አንድ ደሊል ይበቃዋል ለስሜት ባልተቤቶች ምንም ቦታ የለንም :

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
275
المشتركون
+124 ساعات
-27 أيام
-130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ የቱርክ ኤምፓየር ሱዑዲያ የምትባለውን ሀገር ማጥፋትና መካና መዲናን ማስመለስ ጊዜ የማይሰጠው ዋናው ስራ አደረገው ። ግዙፍ ጦር አዘጋጅቶ ወደ ዐረቢያ ግዛት ላከ ። ጦሩ ወደ መዲና ለመድረስ በሚያደርገው ግስጋሴ ያገኘውን ሁሉ ከምድር በታች እያደረገ ጉዞ ቀጠለ ። መዲና ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዶ ህፃን አዋቂ ፣ ሽማግሌ አሮጊት ሳይል እየረሸነ መዲናን ተቆጣጠረ ። መዲና የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶችን ወደ ኢስታንቡል ጫነ ። እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች አሁንም በቱርክ ዋና ከተማ ሙዘየም ላይ ይገኛሉ ። አላማው የመምለካን መሪዮች የሱዑዲ ዋና ከተማ የነበረችው ዲርዒያን ወሮ መሪዮቹን ማርኮ መቀጣጫ ማድረግና የተውሒድዋን ሀገር ማፈራረስ ነበርና መገስገስ ጀመረ ። ጉዞውን ወደ መካ ያደረገው ይህ ጦር ማውደሙንና መረሸኑን በመቀጠል መካ ደረሰ ። መካ ላይም የተለመደውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማድረግ በቁጥጥሩ ስር አደረጋት ። ሒጃዝን ( መካና ነዲናን) በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ጉዞውን ወደ ነጅድ አደረገ ። የዚህን ትልቅ ሀላፊነት መወጣት ለሚስር ( ግብፅ ) መሪዮች አስረከበ ። በወቅቱ የነበረው ሙሐመድ ዐሊ ባሻ ጦሩን እየመራ ወደ ዲርዒያ አቀና ። ከመጀመሪያ የባሰ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተለያዩ ከተሞች እያደረሰ ቢሄድም ዲርዒያን መቆጣጠር አልቻለም ። መሪነቱን ለልጁ ኢብራሂም ባሻ አስረክበ ። ኢብራሂም ባሻ በአዲስ መልኩ ጦሩን አደራጅቶ ሳር ቅጠሉን እያነደደ የህፃንና አዋቂን የአረጋዊያንን ጀናዛ ለአሞራ እየተወ ወደ ዲርዒያ ገሰገሰ ። ዲርዒያን ለሰባት ወር አካባቢ ከበባት ። ምንም ነገር እናዳይገባና እንዳይወጣ ከለከለ ። ረሀቡና ጥሙ ህፃናትና አረጋዊያንን ማርገፍ ሲጀምር የሳውዲ ( የሱዑዲ ) መሪ የነበረውን ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ከበባው እንዲያበቃና ዋስትና ከሰጠው እጁን እንደሚሰጥ መልእክት ላከ ። ኢብራሂም ባሻ ጥያቄውን የተቀበለው መሆኑና ምንም ጉዳት እንደማያደርስ መልስ ሰጠ ። ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ከነመማክርቱና ጠባቂዮቹ እጅ ሰጠ ። አሳፋሪው ኢብራሂም ባሻ ግን ቃሉን አፍርሶ ዲርዒያን አነደዳት ። ‼ በህዝቡ ላይ የተለመደውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ አካሄ ። ሙርከኛቹን ወደ ግብፅ ላካቸው ። ከግብፅ ወደ ቱርክ ተላኩ ። ቱርክ ላይ ዐብዱላሂ ኢብኑ መሐመድ ተገሎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ የቱርክ ኤምፓየር መሪ ተላከ ። የተቀሩትም ተረሸኑ ። ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ለማፅዳት ዑለሞቹን ማደን ጀመረ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የሸይኽ ሙሐመድና የዳዕዋቸው ሁኔታና የተከታያቸው ብዛት ሲያይ ሶስት ነገር ቃል እንዲገቡለት ጠየቃቸው ። 1ኛ — የያዝከው ነገር አላህ ከፍ ሲያደርገው ጥለኸኝ ላትሄድ 2ኛ – በየአመቱ የምቀበለው ግብር አለ ላትከለክለኝ 3ኛ – የዲን ጉዳይ እሳቸው ሊመሩና የዱንያዊው ስልጣን ለሱ እንዲሆን ሸይኽ ሙሐመድ ጥሎ መሄድን በተመለከተ ደሜ ከደማችሁ ጋር ነው ጥዬህ አልሄድም ። የግብሩን በተመለከተ አላህ በምርኮ ይተካልሀል ። የዱንያው ስልጣን ያንተ ነው አሉት ። ከዚህ ስምምነት በኋላ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በስልጣን ዲኑን እየረዳ ሸይኽ ሙሐመድ ዲኑን እየመሩ ዳዕዋው ቀጠለ ። በጋራ ሆነው የሚመለኩ ቀብሮች ላይ የተሰሩ ዶሪሖችን መናድ ጀመሩ ። ሸሪዓ በስራ ላይ ዋለ ። ዝሙት የሰራ እየመጣ ሸሪዓዊ ቅጣት ልቀጣ ማለት ጀመረ ። ሽርክና ቢዳዓ አንገታቸውን ደፉ ። ወንጀል መክሰም ጀመረ ። የተውሒዱ ብርሀን አድማሱን እያሰፋ በአራቱም አቅጣጫ ይኖግድ ጀመር ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ስዑዲያ) የሚባለው ሀገር በሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ አባት ስም ተመሰረተ ። ሳውዲ ከመመስረቷ በፊት ነጅድና አል ጀዚራ አል ዐረቢያ የሚባሉ ግዛቶች በወቅቱ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር አያውቀውም ነበር ። እነዚህ አካባቢዮች በአብዛኛው በጎሳ መሪዮች የሚመሩ የነበሩ ስለሆኑና እንዳጠቃላይ በረሀማ ግመል አርቢ ዘላኖች የሚበዙበት ለስርኣቱ የሚያስገኘው ብዙ ጥቅም ስላልነበረ ከዑስማንዮች ትኩት ተነፍጓቸው የቆዩ ነበሩ ። በተወሰነ መልኩም ቢሆን ትኩረት የሚሰጠው ለመካና ለመዲና ነበር ። ይህም የዐለም ሙስሊሞች ልባቸው የሚንጠለጠልባቸውና ለሐጅና ዑምራ እንዲሁም ለነብዩ መስጂድ ዚያራ የሚፈለጉ ስለነሩ ነው ። በፍቅ የሻፍዕይ መዝሀብ በዐቂዳ ሱፍይ የነበረው የቱርክ ኢምፓየር ስርኣት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ ሳውዲን መመስረትና የተውሒድ ዳዕዋ ማወጅ የቀብር አምልኮ ማስወገድና ሸሪዓ በስራ ላይ ማዋል የራስ ምታቱ ሆነ ። መስራቾቹ ለትውልድ አስረክበው ሄደዋል ። ማግኘት አይቻልም ። የተመሰረተውን ሀገር ማፍረስና መሪዮቹን ማጥፋት የቱርክ ኤምፓየር ትልቅ የቤት ስራ ሆነ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 1
♻️ #እኔ_ሰለፍይ_ነኝ_ማለቱ ምን አስፈለገ #ሙስሊም_በሚለው ለምን #አንብቃቃም ? ➥ይሄ የመከፋፈል ጥሪ አይደለምን? የሸይኹ መልስ፡ ሙሐመድ ናስር አል-ዲን አል አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና ጥሩ ውይይት፣ ሰለፊይ የሚለውን ቃል ለማረጋገጥ ጥሩ ውይይት። በውስጡ መከፋፈልን በመፍራት እኔ ሰለፊይ ነኝ ማለትን ለሚቃወሙት ምላሽ ይዟል። ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁላህ ስለ ጉዳዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ወንድሞቻችንን የእውቀት ፈላጊወች ይህንን ውይይት እንዲያስታውሱት እጠይቃለሁ። ምክንያቱም ፍሬው በጣም አስፈላጊ ነውና። ➛ጥያቄው ፦ አንዳንድ ዱዓቶች እንዲህ ይላሉ፡- #እኔ_ሰለፍይ_ነኝ ማለትን #እቃወማለሁ (ምክንያቱም) #ሰዎች እንደ #ወገንተኛ #እንዳይመለከቱኝ_በመስጋት#ይህ አባባል #ትክክል ነው #ወይንስ #ሰለፊያን_ለሰዎች_ማስረዳት_አለብኝ? መልስ፡- በእኔ እና በቁርኣንና በሱና አብረውን ካሉት የእስልምና ጸሃፊዎች በአንዱ መካከል ውይይት ተደረገ። የእውቀት ፈላጊወች ይህንን ውይይት እንዲያስታውሱ እጠይቃለሁ; ምክንያቱም ፍሬው በጣም አስፈላጊ ነው። ➜ እኔም እንድህ አልኩት፦ #አንድ_ጠያቂ #መዝሃብህ_ምንድነው? #ብሎ_ቢጠይቅህ፡ መልስህ ምንድን ነው? ➛እርሱም እንድህ አለኝ፡- #ሙስሊም (ብየ እመልሳለሁ) ➜እኔም እንድህ አልኩት፦ #ይህ_መልስ_ስህተት ነው። ➛እርሱም፡- #ለምን? አለኝ ➜ እኔም ፦ #አንድ_ጠያቂ #ሃይማኖትህ_ምንድነው? ብሎ ቢጠይቅህስ አልኩት ➛እርሱም፡- #ሙስሊም (ብየ እመልሳለሁ) አለ ➜ እኔም እንድህ አልኩት፡- #በመጀመሪያ #ሃይማኖትህ_ምንድን ነው? ብየ አልጠየቅኩህም። #የጠየቅኩህ_መዝሃብህ ምንድነው? ብየ ነበር። ➤ እና ዛሬ #በእስልምና_ምድር ላይ #ብዙ እና #በጣም_ብዙ_መዝሃቦች እንዳሉ ታውቃለህ። ➥ #ጥቂቶቹ_በፍፁም_የእስልምና አካል #እንዳልሆኑ_በመወሰንም_ከእኛው_ጋር_ነህ። ➥ለምሳሌ እንደ ድሩዝ፣ ኢስማዒሊያ፣ ዓላውያ እና የመሳሰሉት። ⛔️እንድህ ከመሆኑም ጋር እነርሱ ግን፡- #እኛ_ሙስሊሞች_ነን ይላሉ። ➥እዚህ ላይ #በእርግጥ_ከእስልምና_ወጥተዋል_የማንላቸው_ሌሎች_አንጃዎችም አሉ። ● #በብዙ_ጉዳዮች_ከቁርኣንና_ከሱና #ያፈነገጡና_የተሳሳቱ_አንጃዎች_መካከል #መሆናቸው_ምንም_ጥርጥር_የለውም። እንደ ሙዕተዚላ፣ ኸዋሪጅ፣ ሙርጂዓ፣ ጀብሪያ እና የመሳሰሉት። እና ምን ይመስልሃል #ዛሬ #እነዚህ (አንጃወች) #አንተ_ጋር_አሉ_ወይ?(አሉ ብለህ ታምናለህ ወይ) ➛እርሱም፡- አዎ አለኝ ➜ እኔም እንድህ አልኩት፦ ከዚሁ ጋር #ከእነዚህ #ሰዎች_አንዱን #መዝሃብህ #ምንድነው? #ብለን_ብንጠይቀው ልክ እንዳንተ ንግግርህን በመጠበቅ #ሙስሊም_በማለት_ይናገራል ! ➤ #አንተም_ሙስሊም ነህ #እርሱም_ሙስሊም ነው። ➦አሁን #ከእስልምናህና_ከሃይማኖትህ_በኋላ #ስለ_መዝሃብህ_በመልስህ_ግልጽ_እንድታደርግ_እንፈልጋለን? ➛እርሱም፡- #ስለዚህ_መዝሃቤ_ቁርኣንና #ሱና_ነው አለ። ➜እኔም ፡- #በድጋሚ ይህ #መልስ_በቂ_አይደለም አልኩት። ➛እርሱም፡- #ለምን? አለኝ ➜እኔም ፡- 👉ምክንያቱም #የጠቀስናቸው_ሰዎች_ሙስሊም_መሆናቸውን_ስለራሳቸው_ይናገራሉ። ➤አንዳቸውም ቢሆኑ፡- #እኔ_ቁርኣንና_ሱናን_አልከተልም_አይሉም ። ⛔️ ለምሳሌ፡- #ሺዓዎች፡- #እኛ_ቁርኣንና_ሱናን_እንቃወማለን_ይላሉ? ይልቁንም፡- #እነሱ_በቁርኣንና_በሱና #ላይ ነን #ይላሉ። #እናንተም_ከቁርኣንና_ከሱና_አፈንግጣችኋልይላሉ። ኡስታዝ ሆይ፡- እኔ #በቁርአን_እና_በሱና ላይ #ሙስሊም_ነኝ_ማለቱ_በቂ_አይደለም። #ሌላ #ማቀፊያ_መኖር_አለበት። ➦ ምን ይመስልሃል፡ #ቁርኣን እና #ሱናን #በአዲስ_መንገድ_መረዳት_ይፈቀዳል? ወይንስ #ቁርኣን እና #ሱናን #በመረዳት_ረገድ #የሰለፉነ_ሷሊህ(የመልካም ቀደምቶቻችን) አረዳድን #መጠበቅ_ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው? ➛እሱም: #ይሄማ_ቅሮት_የሌለው_ጉዳይ ነው አለ። ➜እኔም፡- የሌላ መዝሃብ ተከታዮች - ከእስልምና ውጪ ያሉት ፤ #እስልምናን #የሚሞግቱት አሁንም #በእስልምና_ክበብ ውስጥ ያሉ ነገር ግን #አንዳንድ_ፍርዶቹን_የተው #ከአንተና_ከእኔ ጋር ፡ #እኛ_በኪታብና_በሱና ላይ #እንድሁም #በሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ ላይ ነን #ማለት #አለባቸው_ብለህ_ታምናለህን? አልኩት። ➛እሱም: #አይ_ከእኛ_ጋርማ_መጋራት #የለባቸውም። አለ ➜እኔም ፡- #ስለዚህ #እኔ_ኪታብና_ሱናን_እከተላለሁ ማለት #በቂ_አይደለም፡ #ሌላ—ማቀፊያ_ሊኖር ይገባል። አልኩት ➛እርሱም፡- አዎ። አለ ➜ እኔም፡- እንደዛ ከሆነ ፡ #እኔ_በቁርኣንና_በሱና እንዲሁም #በሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ ላይ ነኝ እንዲህ ማለት አለብህ። ➤ አሁን ወደ ዋናው ነጥብ እንደርሰናል #የፊደል_ሰውና እና #ጸሃፊ_ለሆነው እንዲህ አልኩት፡- #እነዚህን ሁሉ #ቃላቶች_የሚያጠቃልልን በአረብኛ ቋንቋ አንዲት ቃል አለች ወይ፦ #ሙስሊም_በቁርኣንና #በሱና ላይ እና #የሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ የሚሉትን የሚያጠቃልል #ለምሳሌ #እኔ_ሰለፍይ ነኝ? ማለትን ይመስል እርሱም፡- #አወ_እንደዚሁ ነው። (ትክክል ነው) አለ (እሱም) #ተፀፀተ_መልሱም_ይህ ነው። አለ ➤አንድ ሰው እንደዚህ (ስለሰለፊያ) ቢቃወምህ የጠቀስናቸውን ቃላት ንገረው፡ አንተስ? እሱም ፡ ሙስሊም ነኝ ይልሃል እና የቀረውን ከእሱ ጋር ውይይቱን ቀጥል። አላህ ሆይ ጥራት ይገባህ ምስጋና ይድረስህ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። መሃርታህንም እጠይቅሃለሁ ወደአንተም እመለሳለሁ። 📚 ምንጭ፡ ሲልሲለቱ አል'ሁዳ ወአል'ኑር -725። ሰለፍይ የሚለውን ቃል ለማረጋገጥ ጥሩ ውይይት https://t.me/selefochin_enketel
إظهار الكل...
«ሰለፎችን እንከተል» channel

قال الحافظ ابن حجر رحمه الله :  فالسعيد من تمسك بما كان عليه السلف واجتنب ما أحدثه الخلف" 📗{فتح الباري(13\143) 

👍 5
የጓደኝነት መስፈርቶች ——— አል ፈቂህ ኢብኑ ጁዚይ አል'ማሊኪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- የጓደኝነት መስፈርቶችማ ሰባት ናቸው 1ኛ, በእምነቱ ሱኒይ ሊሆን ግድ ነው። 2ኛ, በዲኑ ላይ አላህን የሚፈራ ሊሆን ነው። እርሱ የቢድዐህ ሰው ከሆነ አለያም ፋሲቅ አመፀኛ ሰው ከሆነ ባልደረባውን ወዳለበት አካሄድ ሊጎትተው ይችላል፣ አለያም ሰዎች በዚህ ይጠረጥሩታል፣ አንድ ሰው በጓደኛው ዲን ላይ ነውና። 3ኛ, የጥሩ አዕምሮ ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። የሞኛሞኝ ሰው ጓደኝነት በላእ ነው። 4ኛ, የጥሩ ስነ-ምግባር ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። መጥፎ ስነ-ምግባር ያለው ሰው ጠላትነቱ አይታመንም፣ ይህንም በምታስቆጣው ጊዜ ትፈትነዋለህ፣ ከተቆጣ ጓደኝነቱን ተወው። 5ኛ, ከሀሜት፣ ከምቀኝነት፣ ከሸር ፈላጊነትና ከሁለት ፊትነት ልቡ ንፁህ መሆን አለበት። 6ኛ, በቃሉ የሚፀና የማይዋልልና የማይቀያየር መሆን አለበት። 7ኛ, ለእርሱ ሐቅ እንደምትቆመው ለአንተም ሀቅ የሚቆምልህ መሆን አለበት። በአንተ ላይ ሀቅ እንዳለው እየተመለከትከለት ለአንተም ሀቅ አለህ ብሎ የማይመለከትልህ (ለሀቁ እንደምትቆምለት ለሀቅህ የማይቆምልህ) ጓደኛ ኸይር የለውም። [አል-ቀዋኒን አል-ፊቅሂየህ ገፅ 460] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) ➥ በዚህ ዘመን እነዚህን መስፈርቶች ያሟላ ጓደኛ ያለው ሰው ምንኛ ታድሏል!! ዋና ዋና መስፈርቶችንም ያሟላ ማግኘት ትልቅ ነገር ነው!! የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
إظهار الكل...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

🔷 ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – : " لا تحقرن من المعروف شيئا " رواه مسلم 🔹 " ከመልካም ነገር ምንን በትንሽ አይን አትይ " በዚህ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር ሲያመላክቱ የመልካም ነገር ትንሽ እንደሌለው በማመላከት ነው ። ገንዘብ የማይከፈልበት መልካም ነገር ሞልቷል ። ጉልበት የማይፈልግ መልካም ነገር ሞልቷል ። ብዙ ኪታብ መቅራት የማይጠይቅ መልካም ነገር ሞልቷል ። ለወነድም ፈገግ ማለት ፣ መልካም ንግግር ፣ ከመንገድ ላይ ቆሻሻ ማስወገድ ፣ ምላስን ዚክር ማስለመድና በማንኛውም ሁኔታ ዚክር ማድረግ ፣ ቤት ስትገባ ፈገግ ብለህ ማናገር ፣ ልጆችህን መሳም ፣ ምግብ ሲበላ ባለቤትህን ማጉረስና የመሳሰሉ የመሳሰሉ በቀላሉ የሚሰሩ መልካም ነገሮች እያሉ የመልካም ስራ ድሀ መሆን የለብንም ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
📢 ምዝገባ ጀምረናል 👉 እነሆ ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ክረምቱን ልዩ በሆነ መልኩ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:20 ሰኣት (ቀን ሙሉ) ከሐምሌ 1 እስከ ነሃሴ 30 ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!! የሚሰጡ የሸሪዓ ትምህርቶች 🔹ቁርኣን ከቃዒደቱ ኑራኒያ ጀምሮ 🔹ዐቂዳ (እምነት ነክ ስለ ተውሂድ…) 🔹ፊቅህ (ስለ ጡሃራ፣ ሶላት…) 🔹ሲራ   (የነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና የሶሃቦችን ታሪክ…) 🔹ነቢያዊ ሐዲሶች… 🔹አደብ (ኢስላማዊ ስርኣት…) ✅ በፍጥነት በማስመዝገብ ልጆች በጊዜያቸው እንዲጠቀሙ ያድርጉ!! 🕰 የምዝገባ ቀን:- ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 28 ሰኣት:- በሁሉም ቀናት ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ✅ ልብ ይበሉ! ሸሪዓን በጠበቀ መልኩ ሴቶችን በሴት ወንዶችን በወንድ ኡስታዞች እናስተምራለን 🏢 ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አድራሻ:- አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊትለፊት ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን 📞Tel:+251920908031 የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
إظهار الكل...
👍 7
አሻዒራዎች(አህባሾች) ዘንድ አብዛኛው ሙስሊም ካፊር ነው። እነሱ ጋር ሙስሊሞች የነሱ ዓሊም ተብዬዎችና ጥቂት ተከታዮቻቸው ብቻ ናቸው። ኢሄ የሆነበት ምክኒያት አሻዒራዎች ዘንድ ለአላህ ሚያሰብቱት ሰባት ባህሪዎችን ብቻ ነው።እነዚህን ሰባት ባህሪዎች እየለጠጡ ሀምሳ ያደርሷቸዋል። እናም እነዚህን የአላህ ባህሪያት እነሱ ዘንድ ማንኛውም ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው በአቅሉ አስተንትኖ መረጃቸውን አውቆ ሊያፀድቅ ግድ ነው፣ኢሄን ካላረግ ሙስሊም አይባልም። አብዛኛውን ሙስሊም ከወሰድነው ደሞ በነሱ አባባል ኢሄንን መስፈርት አያሟላም ስለዚህ ካፊር ነው ማለት ነው። እንደውም ቡዙ ተከታዮቻቸው ስለዚህ ጉዳይ አያቁም፣ ዝም ብለው ነው በጭፍን ሚነዱት። ድንገት ኣንድ ቀን ስለ ዐቂዳቸው ቢያጠኑ እራሳቸውን ካፊር አድርገው ነው ሚያገኙትt.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
إظهار الكل...
Ibn Awol

الحق يقال ولو كان مرا

👍 1
انتهت أيام  عشر ذي الحجة كالبرق   وتلتها أيام التشريق فمرت كلمح البصر كأنها دقائق معدودة وهكذا ستنتهي آجالنا ويأتينا الموت بغتة حتى ترى حياتك كلها بحلوها ومرها كأنها أضغاث أحلام ومرت كمر السحاب واللبيب من استغل الأوقات في القربات والطاعات وتذكر نعم الله عليه وشكر  الله عليها" وما بكم من نعمة فمن الله" وأعظم النعم نعمة التوحيد والسنة والثبات عليها حتى الممات وقد صح في البخاري من حديث ابن عباس رضي الله عنه يرفعه  " نعمتان مغبون فيهما كثير من الناس الصحة والفراغ"                                       قال الإمام أحمد : من مات على الإسلام والسنة مات على الخير كله. (السير).
إظهار الكل...
انتهت أيام  عشر ذي الحجة كالبرق   وتلتها أيام التشريق فمرت كلمح البصر كأنها دقائق معدودة وهكذا ستنتهي آجالنا ويأتينا الموت بغتة حتى ترى حياتك كلها بحلوها ومرها كأنها أضغاث أحلام ومرت كمر السحاب واللبيب من استغل الأوقات في القربات والطاعات وتذكر نعم الله عليه وشكر  الله عليها" وما بكم من نعمة فمن الله" وأعظم النعم نعمة التوحيد والسنة والثبات عليها حتى الممات وقد صح في البخاري من حديث ابن عباس رضي الله عنه يرفعه  " نعمتان مغبون فيهما كثير من الناس الصحة والفراغ"                                       قال الإمام أحمد : من مات على الإسلام والسنة مات على الخير كله. (السير).
إظهار الكل...
👍 1
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- 🔹“የዚል ሒጀህ ቀናቶች ልክ እንደ መብረቅ በፍጥነት አለፉ፣ አያሙ ተሽሪቅም ተከተለቻትና ልክ እንደ ዓይን እርግብግብታ የተቆጠሩ ደቂቃዎችን በሚመስሉ መልኩ ፈጥነው አለፉ። ልክ እንደዚሁ ነው እድሜያችን በፍጥነት የሚያበቃው፣ ሞት ድንገት ይመጣናል፣ ልክ ህይወትህ በፍጥነት ከማለፏ የተነሳ ጥፍጥናዋንና ፍጥነቷን ሁሉ እንደ ቅዠት እስክትመለከት ድረስ ይሁንብሃል፣ እንደ ዳመና በፍጥነት ታልፋለች። ብልህ የሆነ ሰው ጊዜውን አላህን በመታዘዝ፣ ወደ አላህ በሚያቃርቡ ነገሮች፣ የአላህን ፀጋ በማስታወስና እርሱንም በማመስገን የተጠቀመው ሰው ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏልና:- وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ «ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡» አን-ነህል 53 ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ የተውሒድና የሱንና ፀጋ ነው!! በዚህ ላይ እስከ እለተ ሞት ድረስ መፅናት ነው!! በእርግጥም በሶሂህ አል-ቡኻሪይ ከዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ - ረዲየላሁ ዐንሁ - መርፉዕ የሆነ እንዲህ የሚል ሀዲስ ተዘግቧል:- “በብዙ ሰዎች ላይ ስውር የሆኑባቸው አለያም ሰዎች የዘነጓቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: እነሱም ጤናማነትና ጊዜ ናቸው።” ኢማሙ አህመድ - ረሂመሁላህ - እንዲህ ብለዋል:- “በእስልምና እና በሱና ላይ የሞተ ሰው መልካም በተባለ ነገር ሁሉ ላይ ሆኖ ነው የሞተው።” [አስ-ሰይር] : የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
إظهار الكل...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.