cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Dn Henok Haile

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመር እጅግ ጥልቅ ናት! #henokhaile #eotc #mahibere_kidus #tewahdomedio #orthodoxmezmur #ኦርቶዶክስ #Janderebaw_media #የአዕላፋት_ዝማሬ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
651
المشتركون
+224 ساعات
+77 أيام
+5130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

+++ "ስንሞት ያመናል እንዴ?" +++ ሕፃናት መጠየቅ ይወዳሉ። አንዴ መጠየቅ ከጀመሩ በኋላ ደግሞ ከእነርሱ የሚወጣው "ለምን ሆነ?" የሚለው የጥያቄ ዝናብ እንዲህ በቀላሉ ቶሎ የሚያባራ አይደለም። እኛም በእነዚህ ጥያቄዎቻቸው ቶሎ ተሰላችተን ወይም ተበሳጭተን ይሆናል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ ግን የሕፃናቱ አዲስ አእምሮ ራሱን የሚያሳድግበትና የነገ ማንነታቸውን የሚቀርጽበት ወሳኝ ሂደት ነው። የነገ ወጣቶችን ማንነት የሚቀርጹት ዛሬ "ለምን?" እያሉ ለሚጠይቁ ሕፃናት የምንመልሳቸው መልሶች ናቸው። ስለዚህ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። በጠና የታመመ ሕፃን ልጅ ያላት አንዲት እናት ነበረች። ይህች እናት በምትችለው ሁሉ ልጇን አሳክማና ተንከባክባ ለማዳን ብትጥርም፣ ይህ ልፋቷ ግን ሊሳካላት አልቻለም። ልጇን የያዘው በሽታ መድኃኒት ስላልነበረው ወደ ሞት አፋፍ አቅርቦታል። ታዲያ አንድ ቀን ሕፃኑ ልጅ እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት :- "እናቴ፣ መሞት ምን ይመስላል? ስንሞት ያመናል እንዴ?" በእናትየው ዓይኖች እንባዎች ሞሉ። ፊቷም በኃዘን ደፈረሰ። የረሳችው ነገር ያለ ይመስል "ቆይ መጣኹ" ብላ ሮጣ ከክፍሉ ወጣች። ብቻዋን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ልጇ የጠየቃትን ጥያቄ መመለስ እንዳለባት ብታውቅም ለዚህ ለጋ አእምሮ እንዴት አድርጋ መልስ እንደምትሰጥ ግራ ገብቷታል። እንደ ምንም ራሷን አረጋግታና ጥበቡን እንዲሰጣት ወደ ፈጣሪዋ ተማጽና ተመልሳ ወደ ልጇ ክፍል ገባች። ሕፃኑ መልሱን በጉጉት ይጠብቃል። እናትየውም የውስጧን ኃዘን ለመሰወር ለይምሰል ፈገግ ብላ እንዲህ አለችው "ልጄ፣ ታስታውሳለህ አንድ ጊዜ ጎረቤት ያለ ጓደኛህ ቤት ሄደህ ስትጫወት አምሽተህ ስለደከመህ በዚያው እንቅልፍ ወስዶህ ነበር። ከዚያም በማግስቱ ግን ስትነቃ ራስህ ያገኘኸው በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ስለሆነ 'እንዴት እዚህ መጣኹ?' እያልክ ስትጠይቀኝ ነበር። እኔም አባት ወደዚያ መጥቶ በጥንካራ ክንዶቹ ተሸክሞህ የአንተ ወደ ሆነው ቤትህ እንዳመጣህ ነግሬሃለኹ። አስታወስክ?" ልጅየው :- "አዎን እናቴ" እናትየው ቀጠለች :- "የኔ ልጅ፣ ሞትም እንደዚሁ ነው። እኛ መኖሪያችን ባልሆነች በዚህ ዓለም ሆነን እናንቀላፋለን። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ደግሞ ብርቱ በሆኑ እጆቹ አቅፎ ወደ ሰማይ ይወስደናል። ከዚያም ነግቶ እንደ ገና ስንነቃ ራሳችንን በገዛ አባታችን ቤት ውስጥ እናገኘዋለን" አለችው። እውነት ነው! ሞት ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚኖረው ትርጉም ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ተልከን ወደዚህ ዓለም እንደ መጣን ወደ እርሱ መመለሳችን ደግሞ የማይቀር ነው። ሞት ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ድንኳን" ብሎ ከገለጸው ከጊዜያዊው መቆያችን ወደ እውነተኛው መኖሪያ አገራችን መሸጋገር ነው። በ2ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ግሪካዊው ፈላስፋ አርስጣደስ በጊዜው አዲስ ሃይማኖት ስለሆነበት ስለ ክርስትና እና ይህ የክርስትና እምነት በሞት ላይ ስላለው እሳቤ ለአንድ ወዳጁ በጻፈለት ደብዳቤ ላይ እንዲህ የሚል ንግግር አስፍሮ ነበር። "ከክርስቲያኖቹ ውስጥ አንድ ጻድቅ የሆነ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ምእመናኑ ደስ ይሰኛሉ። ለፈጣሪያቸውም ምስጋናን ያቀርባሉ። ያም ሰው ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ቅርብ ሥፍራ የተሸጋገረ ይመስል ሰውነቱን በመዝሙራትና በምስጋና አጅበው ይሸኙታል" ይላል። ክርስትና እንዲህ ነዋ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ክርስቲያኖች በሞት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ እይታ ሲናገር "ከእኛ መካከል አንድ ሰው በሞተ ጊዜ፣ የማያምነው ሬሳ ሲያይ ክርስቲያኑ ግን ያንቀላፋ ሰውነት ይመለከታል። ያላመነው "የሞተው ሰው ሄደ" ይላል። በርግጥ በዚህ እኛም እንስማማለን። ነገር ግን ወደ የት እንደሚሄድም እናውቃለን። የሚሄደው ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ እንዲሁም ሌሎች የቅዱሳን ማኅበር ወደ አሉበት ነው። በኋላም ተስፋ መቁረጥ ባለበት እንባ ሳይሆን፣ በክብርና በማንጸባረቅ እንደሚነሣ እናስባለን!" +++ "ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ" +++ join
إظهار الكل...
7👍 2
እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ  ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ልብ አድርጉ :- ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል::  ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ  ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው:: ይህንንም እናስታውስ ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :- "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"
إظهار الكل...
7🙏 3
እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ልብ አድርጉ :- ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው:: ይህንንም እናስታውስ ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :- "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" #join
إظهار الكل...
ሳሙኤል ተመስገን

ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ልብ አድርጉ :- ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው:: ይህንንም እናስታውስ ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :- "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ #join
إظهار الكل...
ሳሙኤል ተመስገን

ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +   እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡     ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡     በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ ‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6 ‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10 ‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’  መዝ. 90፡7 እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡ ‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12 ‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5 ‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31   የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን  መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’  ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡  /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24   አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]   ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ  ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18   ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡   የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡ ’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’  1ዮሐ 1፡9 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ #join
إظهار الكل...
👍 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? + ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት:: "ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39 ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ:: "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ:: ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20) እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም? ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3 ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር:: የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23) ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን? ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ:: "ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም:: ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13) ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ:: ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ:: አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር:: የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ተጻፈ "ማርያም ገጸኪ እፈቱ ርእየ ድንግል ድንግል ንዒ ኀቤየ እስመ ኪያኪ ጸምአት ነፍስየ" ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም
إظهار الكل...
🙏 3👍 2
+• እንደ ፈቃድህ ይሁን •+ ብዙ ጊዜ "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች፥ እንዲሁም በምድር ትሁን" እያልን እንጸልያለን። ይህንን የምንለው ግን እየጎረበጠን ነው። ደግነቱ ጸሎቱ የአባታችን ሆይ ክፍል ስለሆነ አይዘለልም። ጸሎት ከእምነት ይመነጫል፥ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ማለትም እምነትን ይጠይቃል። እምነታችን ግን ደካማ ስለሆነ ይህንን ጸሎት በሙሉ ልብ ለማለት ይተናነቀናል። በእኛ አስተሳሰብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ ማለት ያሰብነውን ሁሉ እንዲከለክለን ማመቻቸት እንደሆነ እናስባለን። "ፈቃድህ ይሁን" ብለን ስንጸልይ ቸር አባትነቱን እንረሳና፥ ሁሉን ከልካይ እንጀራ አባት አድርገነው "ይከለክለኝ ይሆን? ያስቀርብኝ ይሆን?" እያልን በሰቀቀን ውስጣችን ይናወጣል። እግዚአብሔር ግን ለልጆቹ መልካም የሆነውን ሁሉ የሚለግስ አባት ነው። ድሮ በጨዋታ መሃል ሰዎች "እስቲ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" ሲሉኝ እናደድ እንደነበር አስታውሳለሁ። ቃል ገብተው ቃላቸውን ሊያጥፉ፥ ከቀጠሩኝ ቦታም ሊቀሩ እያንገራገሩ ይመስለኝ ነበር። በወቅቱ ለእኔ "እንደ ፈቃዱ ይሁን" ማለት ያለመወሰናቸው ምልክት ነበር። ለካ ጉዳዩ ሌላ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ።  ይልቁንም፣ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል።" (ያዕቆብ 4:14-15) ይለናል። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቆ ለመቀበል ከመዘጋጀት፥ የእኛን ፈቃድ ፈርሞ እንዲያጸድቅልን መጠየቅ እንመርጣለን። በዚህ መንገድ የሄድነው አካሄድ ግን ጉዳቱ ብዙ እንደሆነ ለማወቅ ሕይወታችንን መለስ ብሎ ማሰቡ ብቻ በቂ ነው። በራሳችን መንገድ ሄደን ያዋጣናል ያልነው ሲከስር፥ እረፍት ይሰጠናል ያልነው ሲበጠብጥ፥ ያስደስተናል ያልነው ሲያሳዝን፥ ያሳርፈናል ያልነው ሲያቅበዘብዝ አይተናል። በራስ መንገድ የተጓዙት እንደማይበጅ በብዙ ማሳያዎች አረጋግጠናል። ወገን፥ አይበቃም ወይ? እግዚአብሔርን አምኖ እና እጁን ይዞ "እንደ ፈቀድከው ይሁን" ብሎ መከተል አይሻልም ወይ? #join
إظهار الكل...
11🙏 4
+• ለትልቅ ሰው እንናገር •+ በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን አንድ ሹም ጥፋት አጠፉና ታሰሩ። እርሳቸው ታስረው እያለ ግን ሚስታቸው ከአሽከራቸው ጋር ግንኙነት ጀመረች። ይህ ወሬ ቀስ ብሎ ከንጉሡ ጆሮ ደረሰ። ንጉሡ “ይህን ሹም አሳስሬ አስደፈርኩት” ብለው በጣም አዘኑ። የታሰሩትንም ሹም አስጠርተው “ሚስትህ ያደረገችውን ነገር ሰምቼ አዝኛለሁ። ፈቃድህ ከሆነ፥ እርሷንም አሽከርህንም ደህና አድርጌ እቀጣልሃለሁ” አሉት። ሹሙ ግን ዝም አሉ። ንጉሡም “ይህንን ጉዳይ ሰምተህ ግን እንዴት አልነገርከኝም?” ብለው ሹሙን ጠየቋቸው። ሹሙም “ለትልቅ ሰው ነግሬያለሁ፥ ንጉሥ ሆይ” አሉ። ንጉሡም ተበሳጭተው “አንተ ትዕቢተኛ፥ ደግሞ ከእኔ ወዲያ ትልቅ ሰው የት አለ?” ሲሉ፥ ሹሙም “ለትልቅ ሰው ለመድኃኔዓለም ነግሬያለሁ፥ ንጉሥ ሆይ” ብለው መለሱ። ዐፄ ቴዎድሮስም “ትልቅ ሰው አልከው?” ብለው ተገረሙ።  ይህ በሆነ በሦስተኛው ቀን የሹሙ ሚስት እና አሽከር እየተዝናኑ እያለ በጠራራ ፀሐይ የወደቀ መብረቅ ሁለቱንም ገደላቸው። ይህንን የሰሙት ንጉሡም ሹሙን አስጠርተው “በል ወዳጄ፥ ለትልቅ ሰው ነግረህ እኔንም እንዳታስጨርሰኝ ውጣልኝ” ብለው እንዳሰናበቷቸው ይነገራል።  እኛስ ጉዳያችንን ለማን እንነግር ይሆን? ዕንባችንን በማን ፊት እናፈስ ይሆን? አቤቱታችንን ለማን እናቀርብ ይሆን? ለሰው ከተነገረ ቃል ይልቅ በእግዚአብሔር ፊት የቀረበ ዝምታ፥ በወዳጅ ፊት ከሚቀርብ እልፍ ምሬት ይልቅ በእግዚአብሔር ፊት የፈሰሰ ዘለላ እንባ፥ ለሹማምንት ከሚገባ የአቤቱታ ደብዳቤ ይልቅ ለመድኃኔዓለም የተነገረ አንድ የእውነት ቃል በእጅጉን ይበልጣል። እናቶቻችን ሲጸልዩ “የሚነግሩህን የማትረሳ መድኃኔዓለም” ይላሉ። እውነት አላቸው። ሰው ፈጥኖ ይዘነጋል፥ መድኃኔዓለም ግን የነገሩትን ፈጽሞ አይረሳም። "አቡነ ዘበሰማያት ሲመታ እንጂ ሲወረወር አይታይም" የሚባለው ሰው የነገሩትን ለሰው መልሶ ሲነግር፥ መድኃኔዓለም ግን ምስጢሩን ጠብቆ ምላሹን ብቻ ስለሚሰጥ ነው። ከሰዎች መፍትሔ በመጠበቅ የባዘንንበት ዘመን ይበቃናል። ዝም ብለን ‘ለትልቅ ሰው’ ብንናገር ይሻለናል። #join
إظهار الكل...
5
Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ኤፍሬም የአገልጋዩን ልብ መለሰ!! እጅግ ደስ የሚል ዜና ነው:: ዶ/ር ሰባስቲያን ብሮክ የሲሪያክ ጥናት ፕሮፌሰር ሲሆን ሶርያዊውን ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምን ለምዕራቡ ዓለም በማስተዋወቅና ለእኛም ብዙ የቅዱስ ኤፍሬም ድርሰቶችን ለማንበብ እንድንችል ትልቅ ዕድል የከፈተ በዚህ ክፍለ ዘመን ወደር ካልተገኘላቸው የClassic studies ሊቃውንት አንዱ ነበር:: የሶርያ ቤተ ክርስቲያን ላደረገው አስተዋጽኦ ከዚህ በፊት የክብር ሜዳይ ብትሸልመውም በሃይማኖቱ ግን ፕሮቴስታንት ነበረ:: ያገለገለው አምላክ የቅዱስ ኤፍሬምን ጸሎት ሰምቶ ሰባስቲያን ብሮክ አሁን በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀተ ክርስትናና ምሥጢረ ሜሮን ተፈጽሞለታል:: የእኛን አባቶች ጥንታዊ መጻሕፍት ሲተረጉሙ ሳይድኑ የቀሩ ብዙዎች ናቸውና በሰባስቲያም ብሮክ መመለስ ከመላእክት ጋር ደስ ይለናል::
إظهار الكل...
👍 8 7