cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ትምህርተ ቅዱሳን

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።" ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ "እስመ፡ኢየኀፍር፡ምህሮ፡ወንጌሉ፤በወንጌል አላፍርም።" ኀበ ሰብአ ሮሜ ፩፥፲፮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 🔆ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ አስተምህሮዎች የሚለቀቁበት፣ ታሪካዊ ገዳማትን የምንጎበኝበት ቻናል ነው። ይህን ቻናል በማጋራት ድርሻዎን ይወጡ። https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
334
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
🎁Safaricom ethiopia ሽልማት🎁 በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል። 🎁ለእርስዎ እና ለ2 ጓደኛዎ የ 3000 ብር ስጦታ 🎁smart phone( s21 ultra) 🎁Asus personal computer ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ ። ብቻ ነው https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0811707078
إظهار الكل...
የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ‹ቅድስት› ‹ቅድስት› ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፤ የተቀደሰች፤ የከበረች፤ ልዩ፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም፡- ትዕቢት፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡ ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ ድንግል፤ ወለመስቀሉ ክቡር!!
إظهار الكل...
? #ሶሎዳ_በሃገረ_አድዋ 🔶በንጉሡ ትዕዛዝ እና አዋጅ መሠረት <<ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበት የሌለህ ለሃገርህ ፣ ለሃይማኖትህ፣ ለልጅህና ለሚስትህ ስትል በጸሎትህ እርዳኝ፤ ወስልተህ የቀረህ ግን ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም ትጣላኛለህ>>የሚለውን በመስማት ነጻነታችንን ፍለጋ አልገዛም ባይነታችንን ይዘን በጥቅምት እኩሌታ አድዋ ወረኢሉ🌄 ከትመን ተገኘን ፤ በሃገሬው ዘንድ #አንድመቶ_ሺህ አርበኛ #ከአንድ_መቶ አምሳ አዝማሪ ጋር አሰልፈው ከሶሎዳ ሲደርሱ የወንድሞቻችን ጦር #ኻያ_ሺህ ሰራዊት #ከአምሳ_ስድስት መድፈኞች ጋር አሰልፈው አስከተሉ። 🔶ለቱ ጊዮርጊስ ነው የካቲት #፳፫ ፲፰፻፹፰ ዓ.ም ከመውጫ ሌሊቱ ፲፩ ሰዓት እስከ መግቢያ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት ድረስ ውጊያው ቀጠለ።ዋናው ውጊያ ግን ለ #አምስት ሰዓታት ብቻ ነው የፈጀው።በአምስት ሰዓት የዘለዓለም ነጻነት። 🔶የምሽት መግቢያ ሲደርስ በሃገሬው ዘንድ ድል ኾነ፣ ለመላው አፍሪቃ የብርሃን ወገግታን ፈጠረ።ነጭ የበላይነቱ ጥቁር የበታችነቱ ተለውጦ ጥቁር ከበረ ነጩም በተራው አፈረ። 🔶እነሆም ለዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ከምቀር ልሞክር በማለት እንዲህ አልኩ ስልጣኔ መጥቶ፣ አሻራን ያኖሩ፤ በዲፕሎማሲው፣ በርትተው የሰሩ፤ አድዋ ላይ ከብረው፣ ጠላት ያባረሩ፤ ታላቅ መሪ ናቸው፣ ለሃገር የኖሩ። ዛሬም ለጠላት ወንድሞቻችን(#ምንም_ቢሆኑ_ኢትዮጵያዊነት_ትርጉም_ነውና)እንዲህ እያል ጠላት መመለሻ መጥፎ ሃሳብ መደምሰሻ ይሆነን ዘንድ ይቺን ሞነጫጨርኳት ዘራፍ እናቴ ዘራፍ ዘራፍ ሃገሬ ዘራፍ ጀግና የወለደችኝ፣ እንድሆን መከታ፤ ከቶም እኔ አልረሳም፣ የሃገሬን ውለታ። በመቅደላ አምባ ላይ፣ በአድዋ ጦርነት፤ ተምሬያለሁ በጣም፣ ለሃገር ስለመሞት። ወደፊት ነው እንጂ፣ የለም ወደኋላ፤ ኢትዮጵያን አይደፍርም ፣የማንም ቅሪላ። በዘር ሀረጋችን፣ ከዓለም የቀደምን፤ በስልጣኔያችን ፣ሁሉን ያስደመምን፤ በታሪክ ዘመናት፣ በቀኝ ያልተገዛን፤ ጠላቶቻችንን ፣በድል ያሸነፍን፤ ከቶ ማን ሊደፍረን ፣ይኸው ነቅተን አለን። ከየትም ያለኸው፣ ፍጠንና ተነስ፤ ፍቅር አንድነት ነው ፣ጠላት የሚመልስ። 🔶በድላችንም አንቀጽ ፲፯ትን እንዲሁም አንቀጽ ፫ትን ገረሰስን። በጀግኖቻችንም ተከበርን የአድዋን ሥላሴ ጠላት አረከሰው፤ ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው። 🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠 እንኳን ለ፩፻፳፮ ኛው የነጻነት ድል የአድዋ በዓል አደረሳችሁ። 🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠🎠 #ክብር እና ዘለዓለማዊ ዕረፍት ኢትዮጵያን በስስ ብሌናቸው ለጠበቁልን አባቶች እና እናቶች #ስለ ሃገራችን ለተሟገቱ ዜግነታቸውን ንቀው ነጻነትንና ሕይወትን ለመረጡ በቅርብ ዓመታት በሥጋ ሞት ለተለዩን #ሪቻርድ_ፓንክረስ ከእናቱ #ሲልቪያ_ፓንክረስ ክብር ይሁን። ✍ዳግማዊ ሲሳይ በቀለ የካቲት ፳፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም አዲስአበባ ኢትዮጵያ
إظهار الكل...
#ትምህርተ_ቅዱሳን ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ ዕውቀት ከሃይማኖት ታማኝነት ከኃላፊነት ጥበብ ከሱባኤ ጀግንነት ከትጋት ሹመት ከችሎታ እውነት ከርእዮት ጋር ይዘን እንጓዝ። https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN
إظهار الكل...
ትምህርተ ቅዱሳን

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።" ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ "እስመ፡ኢየኀፍር፡ምህሮ፡ወንጌሉ፤በወንጌል አላፍርም።" ኀበ ሰብአ ሮሜ ፩፥፲፮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 🔆ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ አስተምህሮዎች የሚለቀቁበት፣ ታሪካዊ ገዳማትን የምንጎበኝበት ቻናል ነው። ይህን ቻናል በማጋራት ድርሻዎን ይወጡ።

https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN

Photo unavailableShow in Telegram
https://t.me/finoteabew ያገኙታል
إظهار الكل...
"የብርሃን እናት"
إظهار الكل...
ጥቂት ቀናት "የብርሃን እናት" ከቀናት በፊት አንድ የአዲስ መጽሐፍ ረቂቅ እጄ ገባ፡፡ መጽሐፉ ‹‹የብርሃን እናት›› ! በእርግጥ ደራሲው ከዚህ በፊት በጻፋቸው ድንቅ መጻሕፍቱ የምናውቀው ቢሆንም ይህኛው ግን ከእስከ ዛሬው የተለየ ለመሆኑ እኔ ምስክር ነኝ፡፡ ከሕማማት ወዲህ ምን ሊጽፍ ነው? ያሰኘን ወንድማችን በዚህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን እንደማያልቅባት አስመስክሮአል:: ከአቀራረቡ ጀምሮ ከወትሮው በተለየ ‹‹የብርሃን እናት›› ላይ የየሚደንቅ የሥነ ጽሑፍ መራቀቅ ጨምሮ ብቅ ብሏል፡፡ ጥልቅ ሐሳቦቹን የሚያሳፍርባቸው የቃላት ሠረገላዎቹ እጅግ ጌጠኞች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የመጽሐፉ ምዕራፎች የዕውቀት ጥም ለመቁረጥ ኩልል ብለው የሚፈሱ "አያልፉሽ ምንጭ"ን ይመስላሉ። የይዘቱ ነገር ግን ለመግለፅ ይጨንቃል፡፡ ይህንን መጽሐፍ ማንበብ ሕመም አለው፡፡ በየገጹ የሚንበለበለው የምሥጢር እሳት ስለሚያቃጥልህ በአንድ እጅህ መጽሐፉን በአንድ እጅህ ደግሞ ልብህን ደግፈህ ካልሆነ አትዘልቀውም፡፡ "የብርሃን እናት" ባለማወቅ አመድ ውስጣችን የተዳፈነውን የፍቅሯን ፍሕም የሚገላልጥና "እፍ እፍ" እያለ እንደ አዲስ የሚያቀጣጥል ነው። ይህን ጊዜ እርሷን የማወቅ ደስታ በደምህ ይራወጣል። አንዴ ፈገግ የሚያስብል ቆይቶ ደግሞ የሚያስለቅስ በልብ የሚፈላ የፍቅሯን ማዕበል ይቀሰቅስብሃል። እንዲህ ያለው ድርሰት የወላዲተ አምላክ የፍቅሯ ኃይል ካላረፈብህ እንዴት ሊከናወንልህ ይችላል? በእርግጥም ‹‹የብርሃን እናት›› እመቤታችንን ለሚወዱም ብቻ ሳይሆን ለማያውቋትም ሳይቀር የተሠጠ ትልቅ ገጸ በረከት ነው፡፡   ደራሲው በዚህ መጽሐፍ ቀደም ሲል ከነገረ ድኅነት ጋር ተያይዘው ሲነሡ ዐውቃቸው የነበሩትን ታሪኮች በተለየ መንገድ በማቅረብ ለታሪኮቹ መልሶ እንግዳ አድርጎኛል፡፡ በዚህም ትንሽ መቆጨቴን እና ‹እንዲህ ጉድ ታደርገኝ!› እያልኩ መብሰልሰሌን አልደብቅም፡፡ ነገር ግን ይህ ቁጭት የእኔ ብቻ ሳይሆን መጽሐፉን የሚያነብ ሁሉ የሚጋራው ስሜት ይመስለኛል፡፡ ዲያቆን ሄኖክ በተባ ብዕሩ ታግዞ በመንፈስ ቅዱስ ስለትነት እያንዳንዱን የታሪክ ክፍል በብልሃት እየሰነጣጠቀ በውስጡ የተሰወሩትን መንፈሳዊ ምሥጢራት አንድ በአንድ እየገለጠ ያሳየበት መንገድ ብቻውንማ ሊጽፈው አይችልም አሰኝቶኛል፡፡ ደግሞ ለሚያነሣቸው ሐሳቦች እንደ ማስረጃ ከየቦታቸው እየጠራ የሚያመጣቸው እና እነርሱም መጥተው ስክት የሚሉት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያለዚያ ቀን አይቼ የማላውቃቸው ናቸው፡፡ ምናልባትም ይህን መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ ከምንረዳቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስን አለማንበባችንን ሊሆን ይችላል፡፡ መጽሐፉ እንዲሁ ዝም ብለህ የምታነበው እና መረጃ የምትሰበስብበት ዓይነት አይደለም፡፡ በውስጡ በቀጥታ ከራስህ ጋር ልታያይዛቸው የምትችላቸው የሰሉ ተግሣጻት እና ጸሎቶችን ቋጥሮ ይዟል፡፡ እንደውም መጽሐፉን ይዘህ ከተቀመጥህ ከጥቂት የንባብ አፍታ በኋላ አንተ መጽሐፉን መግለጥ ታቆምና መጽሐፉ አንተን መግለጥ ይጀምራል፤ አንተ ወደ መጽሐፉ በመግባት ፈንታ መጽሐፉ ወደ አንተ ይገባል፡፡ ነፍስና መንፈስህን ጅማትና ቅልጥምህን እስኪለይ ድረስ ይወጋሃል፡፡ የልብህንም ስሜትና ጥልቅ ሐሳብ ይመረምራል፡፡ የክብርን እመቤት ለመቀበል ሰውነትህን እንድታሰናዳ ያደርግሃል፡፡ እኔን የገጠመኝ ይህ ነበር፡፡ በጉባኤ ኤፌሶን ልክ ባለ 431 ገጹ የብርሃን እናት መጽሐፍ አራት ምዕራፎችና ባለ 30 ንዑሳን አርእስቱ የያዘ ሲሆን ለአንባቢያን ብዙ በረከት የሚያስከትል መጽሐፍ እንደሚሆን እምነቴ ነው:: አንዳንድ ጊዜ ወደ ዓለም ሄደህ ሰውን ሁሉ በንባብ እስክታጠምቅበት ድረስ እረፍት የማይሰጥህ መጽሐፍ አለ፡፡ ‹‹የብርሃን እናት›› እንደዚህ ያለው ነው!!! መጽሐፉ ከጥቂት ቀናት በኋላ (ዐቢይ ጾም ላይ) በእጅዎ ይገባል
إظهار الكل...
#ትምህርተ_ቅዱሳን ተከታታይ የሆነ በተመሳሳይ መጠሪያ የሚጠሩ የቅዱሳን ታሪኮችን ለማቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። 🔶መነሻችን የሚሆነው ደግሞ በ<<ማርያም>> ስም የሚጠሩ ቅዱሳንን ይሆናል። አብራችሁን ተማሩ 🔶🔶 ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN
إظهار الكل...
ትምህርተ ቅዱሳን

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።" ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ "እስመ፡ኢየኀፍር፡ምህሮ፡ወንጌሉ፤በወንጌል አላፍርም።" ኀበ ሰብአ ሮሜ ፩፥፲፮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 🔆ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ አስተምህሮዎች የሚለቀቁበት፣ ታሪካዊ ገዳማትን የምንጎበኝበት ቻናል ነው። ይህን ቻናል በማጋራት ድርሻዎን ይወጡ።

https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN

#ትምህርተ_ቅዱሳን የቅዱሳን ትምህርት የሚነገርበት የሚተላለፍበት የቴሌግራም መርሃ ግብር እነኾ፤ በዚህ መርሃ ግብር ከትምህርት ባሻገር ምክር አዘል ምክሮችን ያገኙበታል።በመንፈሳዊ ቅኝት መርሃ ግብሮቻችን የተለያዩ ገዳማትን ባለንበት እንዳስሳለን፤ ደብረ ሊባኖስ ዝቋላ ደብረ ቢዘን ሬማ እና ራማ ምሁር ኢየሱስ ሐይቅ እስጢፋኖስ ዳጋ ለበረከት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተድባበ ማርያም መርጡለማርያም አክሱም ጽዮን አራዳ ጊዮርጊስ ኹሉንም በአንድነት ይዘን ቀርበናል። ⚜ከሰሞኑ ሊንካችን የተቀየረ በመሆኑ ይህን ከታች ያለውን አዲሱን ሊንክ ይጠቀሙ። https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN
إظهار الكل...
ትምህርተ ቅዱሳን

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።" ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ "እስመ፡ኢየኀፍር፡ምህሮ፡ወንጌሉ፤በወንጌል አላፍርም።" ኀበ ሰብአ ሮሜ ፩፥፲፮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 🔆ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ አስተምህሮዎች የሚለቀቁበት፣ ታሪካዊ ገዳማትን የምንጎበኝበት ቻናል ነው። ይህን ቻናል በማጋራት ድርሻዎን ይወጡ።

https://telegram.me//TMHRTEKIDUSAN