cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መዝሙረ ማኅሌት

@zemariann & @zemarian የቀደመት ቻናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariian ይቀላቀሉን፡፡ ለአስተያየት .. @zemariiii_bot & @mzbot_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
15 114
المشتركون
+3824 ساعات
+3147 أيام
+1 13930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#ሐምሌ_7 #ቅድስት_ሥላሴ ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! https://t.me/zemariian
إظهار الكل...
መዝሙረ ማኅሌት

@zemariann & @zemarian የቀደመት ቻናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariian ይቀላቀሉን፡፡ ለአስተያየት .. @zemariiii_bot & @mzbot_bot

Photo unavailableShow in Telegram
+እንዘ ሰለስቱ አሃዱ + ግጥምና ዜማ :-ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በዘማሪ:-ሊቀዲያቆን ወንደሰን በላይ +እንዘ ሠለስቱ+ ዓለምን በጥበብ ለፈጠረ ጌታ ዘወትር እናቅርብ የክብር ሰላምታ መላእክት በፍርሃት ለሚያመሰግኑት ለሥላሴ እናቅርብ አኮቴት ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ በሃሳቡ ብቻ ዓለምን ለሠራ በአምላካዊ ቃሉ ብርሃንን ላበራ ሰውን በምሳሌው በአርኣያው ፈጥሮ ከአፈር አበጀው ከሁሉ አክብሮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ የሰው ልጅ ሲበድል አምላክ ልሁን ብሎ የሰይጣንን ምክር አምኖ ተቀብሎ አዳም አዳም ብሎ ፍለጋ ለወጣ ለይቅር ባይ ጌታ ምስጋናን እናምጣ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ ወደ ዓለም ልኮ አብ አንድ ልጁን ወልድም በፈቃዱ መጣ ሰው ሊሆን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተጸንሶ ተወልዶ አክሊል አቀዳጀን በመስቀል ተዋርዶ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ እንዴት ላመስግንህ የቅዱሳን አምላክ በልቤ ጉልበትም ለአንተ ልንበርከክ ዓይኔን ከእጄ ጋር ወደ ላይ አንሥቼ እዘምርልሃለሁ እንደ አባቶቼ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ ዝማሬ : ሊቀ ዲያቆናት ወንድወሰን በላይ ግጥምና ዜማ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
إظهار الكل...
እንዘ ሰለስቱ.mp36.74 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የስማቸው አጻጻፍና የፊደላቱ ትርጉም ( የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል።) ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል። ይህ “ሠ” ሠራተኛው ወይም ንጉሡ ሠ የሚባል ሲሆን፤ ይህ “ሰ” ደግሞ እሳቱ ሰ ይባላል። ➧ “ሥላሴ” ከስማቸው ፊደል ሠራተኛው "ሠ" ይገኛል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ ዓለምን መፍጠራቸውን ያመለክታል፤ በተጨማሪም ንጉሡ "ሠ" ይባላል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ የፈጠሩትን ፍጥረት የሚገዙ የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል። በአጠቃላይ በዚህ "ሠ" ስማቸው መጻፉ ቅድስት ሥላሴ ዓለምን ፈጥረው የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል። ➧ ከስማቸው ፊደል ላይም እሳቱ "ሰ" ይገኛል ይኸውም እሳት ባህር ገደል ካልከለከለው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል ቅድስት ሥላሴም ቸርነታቸው ካልገደባቸው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢሉ የሚቻላቸው መሆኑን ያስረዳል። - አንድም፦ እሳት ወርቅን ከእድፉ፣ ምግብንም ከተዋህስያን እንደሚያጠራ ቅድስት ሥላሴም ሰውን ከኃጢኣቱ በምህረታቸው የሚያነጹ ናቸው። 👉 በቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደል ላይ ሁለት በፊደል ቤት ቢለያዩም ተመሳሳይ ድምጸ ቀለም ያላቸው "ሥ" "ሳ" እና በፊደል ቤትም በድምጸ ቀለም ከሁለቱ የምትለይ "ላ" እናገኛለን። ይህም "ሥ" እና "ሴ" የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው በድምጽ ቀለም መመሳሰላቸውም አብና መንፈስቅዱስ ሰው አልሆኑም፥ "ላ" የወልድ ምሳሌ ናት "ላ" በድምጸ ቀለም ከሁለቱ እንደምትለይ ወልድም በተለየ አካሉ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይለያል።
إظهار الكل...
إظهار الكل...
#ለምኝ #ድንግል #ለምኝ #ሃጢአት #ለፈጀው #ዓለም

ዝማሬ ይገብር ምሕረተ .mp32.85 MB
መዝ ዎ በ፩ ይሰጠዎ-16 .mp31.64 MB
#መዝሙር_ዘሠንበት #ሃሌ_ሉያ ይሠጠዎ  ወይሰምዖ ጸሎቶ፤ ለኩሉ ዘሰአሎ፤ እግዚአ ለሰንበት አምላከ ምሕረት ፤ማ፦ ያርኁ ክረምት በበዓመት፤ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት አመላለስ፦ ያርኁ ክረምት በበዓመት/፪/ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት/፬/ @zemariian
إظهار الكل...
ይኸው የሐምሌ ገብርኤል 👍
إظهار الكل...
የእመብርሃን ወዳጅ ዘኆኅተ ብርሃን .mp34.88 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.