cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የናትዮጵያ ግጥሞች እና ፁሁፎች ስብስብ✍📜💚_💛_❤️

ስነ ፅሁፍ የነፍስን ስሜት መግለጫ ንፁህ የአምላክ በረከት ነው።✍️💚_💛_❤️

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
296
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የሰው ልጅ ጠባይና ባሕርይ እጅጉን ይገርማል። አንዳንዴ የምንፈልገው ነገር እውነትም የምንፈልገውን ነው? አንዳንዴ የምናሳድደው በእርግጥም መያዝ የምንሻውን ነው? ወይስ ከመያዝ ይልቅ በማሳደድ ውስጥ፣ ከማግኘት ይልቅም በመፈለግ ውስጥ ምሥጢር አለ? . . አንዲትን ሴት አጥብቆ የሚፈልግ ሰው ገጥሞኝ ያውቃል። ሁሌም ቀልቧን ለመማረክ ጥረት ያደርጋል። በአፍላ ትውውቃቸው ወቅት እሷን ካገኘ ከዓለም ምንም እንደማይፈልግ ይነግረኝ ነበር። ያቺ ሴት በዚያ ወቅት ፍጹም ናት። ንጽሕት ናት።  መንፈሱንና ልቡን ሁሉ ሞልታ ነበር። ብዙ ደጅ ጠንቶ የራሱ አደረጋት። የራሱ ከሆነች ቀን ጀምሮ ግን ዋጋዋ ቀንሶ ታየው። ቀድሞ ያልተገለጠ ነጭናጫነቷ የታየው መሰለው። ንጽሕናዋ ፍጽምናዋ ሁሉ ጠፋበት። ውበቷ ሀሰት ሀሰት ሆነበት። “ምን ሆኜ ነበር?” “ምን አስነክታኝ ነበር?” እያለ ለኃጢአቱ ምክንያት ሰጠ። . ለውጡ ግን የምንም ሳይሆን የቦታ ለውጥ ነበር። ድሮ ሲያሳድዳት ከፊቱ ነበረች። አኹን ከእጅ መዳፉ ላይ ነች። . አንዳንድ ነገሮች መፈለግ ላይ ብቻ መቆም አለባቸው ? አንዳንድ ነገሮችን አሳድደን ባንይዛቸው ይሻላል? ስኬት የጥረትን ያኽል ጣዕም የለውም? የለውም ወይ? . ይህ ሰው ምክንያት ፈልጎ ራቃት። ምክንያት ፈልጋ በተራዋ ፈለገችው። የማግኘት ስካር ሲያፋንነው የእልኋን ተከተለችው። ድሮ የተለመነችው በተራዋ ለመነች። አስለመነች። ምናልባት እሷም የተመኘችው ፈልጎ የማግኘትን ጣዕም መቅመስ፣ ሮጦ የመድረስን ሕልም ማሳካት እንጂ እሱን አልነበረም። ሁለቱም በውስጣቸው ያለውን ዕረፍት አልባ ተቅበዝባዥ ሰይጣን ለማገልገል ታተሩ እንጂ በውስጣቸው ፍቅር የለም —ቅንጣት እንኳ። . . ጠቢቡ ሶሎሞን የደረሰበት ይኽ ነው። “ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ” ለማለት ያበቃውን መሰልቸት ለመረዳት ሰሎሞን መኾንን ይጠይቃል። የመድረስ መከራ ኃያል ነውና ሰሎሞን በሎሌው ይቀና እንደኾነ ማን ያውቃል ? የሞላለት ከበርቴ ጌታ ለማኝ መኾን ይሻ እንደሆነ እንዴት ይታሰባል ? . . እንደዚህ በነፍስ ፈልጌያቸው ሳገኛቸው እንደ ጉም የሆኑብኝ … ልኾን ተመኝቻቸው ስሆን ደም እንባ ያስለቀሱኝ … እድሜዬን፣ ገንዘቤን ፣ ጥረቴን ሁሉ ሰጥቻቸው ሲሳካ “ተሳካ የልቤ ሞላ” ከማለት ይልቅ በዓይኔ እንኳ ለማየት ያስጠሉኝ፣ ያንገሸገሹኝ፣ የቀፈፉኝ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰዎች እንደ ዕድለኛ በሚቆጥሩኝ ነገር፣ “ታድለህ”በሚሉኝ ነገር፣ እኔን መኾን በተመኙባቸው አንዳንድ ነገሮች እኔ ግን አጥንቴ ድረስ ታምሜ ዐውቃለኹ። ሰው ከእኔ የተመኘውን ነገር እንደ ልብስ አውልቄ ብሰጠው ተመኝቻለኹ። . . የምፈልገውን ነገር እፈልገዋለኹ? መሄድ የምሻበት ሀገር መኖር እፈልጋለኹ ? ሰው የምኞቱ ባርያ የፍላጎቱም ሎሌ ነው። አንዳንዴ እርካታ ፍላጎትን፣ ማግኘትም ጣዕምን ያሳድዳሉ። መድረስ ዋጋውን የማይቀንሰው ደስታ ምንድነው ? ማግኘት የማያደበዝዘው መንገድ ምንድነው? በየቀኑ እንደ ዐዲስ በመገረም ሊሞላኝ የሚችል ነገር ምንድነው? ይህንን ደስታ ለራሴ እመኛለኹ። ይህንን እርካታ ለሰው ሁሉ እመኘዋለኹ። ካልኾነ ግን መንገዴን በእሾኽ ይጠረው፣ በጥርብ ድንጋይም ይዝጋው። አብረውኝ በማይከርሙ ደስታዎች ተሰላችቼያለኹ። ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17 ይነጋል💚💛❤
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
​​👉 ዘረኝነት፣ በሽታ፣ ጥላቻና ችግር ከምድራችን ጠፍቶ የምናይበት የፍቅር፣ የደስታና የሰላም ዓመት ይሁንልን!🙏 🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼 💚💛❤️💚💛❤️ ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17     
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ትንሽ ጉራ ለመቸርቸርና ለመንዛት ያህል ብቻ! አብሮ አደጎችህ፣ የትምህርት ቤት ጓደኞችሁ፣ የስራ ቦታ የምታውቃቸውን ሰዎች መሰረት በማድረግ ጥቂት ስለ ወንድ ልጅ መልካም ነገሮቹ እንመሰክራለን። እንዘክራለን። ወንድ ልጅ ❶ ሚስጥር ጠባቂ ነው። (የጋራ ታሪኮቻችሁ የጋራ ታሪኮቻችሁ እንደሆኑ ያልፋሉ! የሌላ ሰው ታሪክም ለአንተ መጥቶ አይዘረግፍም) ❷ ወዳጅነት ከቆመበትን ማስቀጠል ይቻላል። (ከረጅም ጊዜ በኃላ ዳግም ብትገናኙ ወሬውና ጫወታው ከቆመበት ይቀጥላል) ❸ ያበረታሃል ይደግፍሃል። (ድጋፍና ዕርዳታ ፈልገህ ብትጠይቀው ያለ ማመንታት ያደርጋል) ❹ ነገር አያወሳስብም ❺ ሀቀኛ ነው (ና ሻይ ልጋብዝህ ብትለው?..." ገንዘብ በደንብ ያዝ ርቦኛል በዛውም እበላለሁ" ይላል ❻ ፊት ለፊት የተሰማውን ይናገራል " ❼ ፖለቲካ፣ ሳይንስ፣ኳስ፣ ዜና....የጋራችሁ ነው ❽ ወንድ ልጅ በተለየ  ቤትህን፣ ቤተሰቦችህንና ያንን ሸፋፋ ጫማህን ያከብራል ❾ቢቀየምህም ቢናደድብህም ዞራችሁ ድጋሜ ትገናኛላችሁ ወንድ''ም''ነት👑🙏 ፍ.ሰ.ት ለኢትዮጵያ 💚💛❤ share ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ጨካኝ ነኝ ! ...እንድለማመጣት ነበር ያኮረፈችው... ...እንዳነጋግራት ነበር ዝም ያለችው... ...እንዳረጋጋት ነበር የተበሳጨችው... ...ይበልጥ ልትቀርበኝ ነበር "ዞር በል ልሂድበት" ብላ የጮኽችው... ጨካኝ ነኝ ! ...ስታኮርፍ እኔም አኮረፍኋት... ጨካኝ ነኝ ! ...ዝምታዋን በሚጨንቅ አርምሞ መለስኹላት... ጨካኝ ነኝ ! "ልሂድ ?" ስትለኝ "እስካኹን እዚህ ነሽ?" አልኋት። ጨካኝ ነኝ ! ጨ ካ ኝ ! ሄደች...ጭካኔዬን አይታ አልተመለሰችም። ©️ሶፊ ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤ ተቀላቀሉን👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በፊልማቸው በሙዚቃቸው በብዙ ነገራቸው ልባችን ወደ ውጪው አለም ቢያዘነብልም ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን የእምነት ባለቤቶች የህሊና እፍረት ባለቤቶች መሆናችንን በፍፁም መርሳት የለብንም እና Homosexuality❎ መቃወም ግድ ነው በእኛ በኢትዮጵያወዊያኖች ዘንድ ይህ አፀያፊ ድርጊት መቃወም አለብን ፨ ይህን ልጅ አስታወሳቹት አይደል በአንድ ወቅት ላይ በመስቀሉ ስለተቃወማቸው ብቻ ድብደባ እና እስራት እንደደረሰበት እኛም ኢትዮጵያዊያኖች ነገ ለማትረፍ ዛሬን ማወገዝ ግድ ይለናል ግብረሰዶም(Homosexuality) ❎❎❎❎ እኛ🇪🇹ዊያኖች ሃይማኖት ባህል ሀገር ብዙ የምናከብራቸው አዛዎት እናቶች አዛዎት አባቶች የምንፈራቸው የእድሜ ባለፀጎች ያሉን ህዝቦች ነን እነሱ በእኛ በልጆቻቸው ማፈር የለባቸውምና ግብረሰዶማዊነትን አጥብቀን እንቃወማለን ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤ share ተቀላቀሉን👉👉👉natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ውበት👑 ውበት ደም ግባት አንደለም    የሚጠፋ እንደ ጤዛ ኳሉኝ አደማምቁኝ ማለት    የሚፈልግ የሚያበዛ ውበት አለባበስም አይደል    አምሮ መሄድ ተሽቀርቅሮ ባማረበት ጫማና ልብስ    ያማረበት ራስን ፈጥሮ ውበት ማለት ውብ ማንነት    መልካምነት ያነገሰው ቀን ጠብቆም የማይረግፍ    ባርቴፊሻል የማይደምቀው🙌 ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤️ ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ስለምንወዳቸው ነግሰው በልባችን ስለተቀመጡ ሰዎች ሲያሻን ነግረናቸው ሲያሻን ምንም ሳንል ከፍ ዋንጫችንን🥂          ቶሎ ስለሚረዱን በቃላት ጋጋታ በጥያቄ ድርደራ ስለማያሰለቹን ሰዎች ከፍ🍷               ስለሚጥሩ ስለሰዎች ጥሩ በማሰብ ባህሪያቸውን ስለሚያላብሱን ከፍ🍷          ሁካታ ጫጫታ ስለሌለባቸው፣በራሳቸው በቤታቸው ትግል ስለተጠመዱ ሰዎች ከፍ🍷          ሰዎችን ስለሚያከብሩ ራሳቸውን ስለሚያስከብሩ ሰዎች ከፍ🍷                    ሁሉም ነገር ብርቅ ስለማይሆንባቸው ሰዎች ከፍ🥂                 ስለማጣት ስለማግኘት የገባቸው ቁስ ልብ ላልሆናቸው ሰዎች ከፍ🥂 ፍ.ሰ.ት ለኢትዮጵያ 💚💛❤ ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ አካባቢዎች 👇🏾 አንድ ሰው የሆነ ጥፋት ሲያጠፋ ለሁለት ቀናት ያህል አካባቢው ላይ ወደሚገኝ አንድ ቦታ ይወሰድና የጎሳው አባላት በህይወቱ የሰራውን መልካም ነገሮች እያነሱ ይነግሩታል ሁሉም ሰው በተፈጥሮ መልካም እንደሆነ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ጥፋት ሊገኝበት ወይም መንገድ ሊስት እንደሚችል ማሳያ አድርገው ይቆጥሩታል:: በዚህ ስርአት ላይ የጎሳው አባላት ከአጥፊው ጋር በህብረት በመቆም እና በማበርታት ከተፈጥሯዊ ማንነቱ ጋር እንዲገናኝ ያግዙታል:: እሳቤው እና አላማው 👇🏾 አንድነት እና አዎንታዊ እርማት ከማሳቀቅ እና ከቅጣት የበለጠ ባህርይን እና ክፉ ምግባርን የማረም ጉልበት እንዳላቸው ማሳያ ነው:: ይህ ስርአት "ኡቡንቱ" ይባላል ኡቡንቱ - ሰብኣዊነት ለሌሎች!! ❤️🙌🏼 ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤️ ተቀላቀሉን👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
"ፍቅሬ የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ይዘሃል?" እጇን በእጁ ያዘና "አሁን ይዣለሁኝ!" ❤️❤️🙌🏼 ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤️ ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አውቃለሁ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምትሆነው ፣ ምነው?!  ምን ሆነሻል ? ሲሏት  ትንሽ አሞኛል ነው የምትለው ! አውቃለሁ አሁንም አሁንም ስልኳን ታያለች ፣  በየወሬዎቿ ሁሉ  ስለቆራጥነት ነው የምታወራው ? ስለመርህ ነው የምታብራራው?  አውቃለሁ ስራ ያስጠላታል ፣ የምግብ ፍላጎቷ እንደ ቀድሞ አይሆንም ? እያስመሰለች ነው ፣ ገግማ ነው ፣ ማዳመጥ ስላልፈለገች ነው እንጂ ሁለ ነገሯ እኔን  ናፋቋል በእርግጥ የሚሰማት ሁሉ እየተሰማኝ ነው 😍 ፍ.ሰ.ተ ለኢትዮጵያ 💚💛❤️ ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.