cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 817
المشتركون
+124 ساعات
-87 أيام
-3530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

00:49
Video unavailableShow in Telegram
❤️#ሐምሌ_#ቅድስት_ሥላሴ❤️       🙏🙏🙏 https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
14.37 MB
1
00:40
Video unavailableShow in Telegram
#ለምን #ቅድስት_ስላሴ #በሴት_አንቀፅ_ተጠሩ??? https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
10.86 MB
🥰 1
😍 1
#ቅድስት_ሥላሴ (#ሐምሌ_7) ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! (ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ) https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

1
🙏🙏🙏
إظهار الكل...
👏 1😇 1
#ወደ_ገዳማት_መሄድ_ላሰባችሁ_መልዕክት ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ✤ ሰላምን ✤ መረጋጋትን ✤ ፍቅርን ✤ አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #EOTC https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

🥰 1
#ቅዱሳን_አባቶቻችን "ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው" ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፎአል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡ (አረጋዊ ታዴዎስ) https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

1
#በገዳማት_የምህላ_ፀሎት_ታውጇል ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ  በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን ‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ  ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ  በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ  የሆነው  ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ  አበክሮ ይነግረናል፡፡ በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት  ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡ ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና  ምእመናን  ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን  ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ›› ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፎቶ Eotc tv https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
1
#ሰው_ቢጠላችሁ#ሰው_ቢሸሻችሁ፣ ስታጡ ጋደኛም ቢከዳችሁ፣ ምንም ብትሆኑ፣ ማለዳም ተነስታችሁ ገንዘብ ብታጡ፣ ስራም ብታጡ ቢቸግራችሁ፣ ዳኛም ባይፈርድላችሁ፤ ዝም ብላችሁ አንድ ቃል በሉ "#እግዚአብሔር_ከእኔ_ጋር_ነው!" #ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
إظهار الكل...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

8👍 5
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.