cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Nahom Records

nahom records

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
529
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
𝓲𝓽𝓼_𝓱𝓪𝓯𝓾

Нι gυуѕ ʝօɨռ tɦɨs ċɦaռռɛʟ ɨʄ ʏօʊ ɢɛt 👉𝑛𝑒𝑤 𝑚𝑢𝑠𝑖𝑐𝑠🎤🎧 👉𝑜𝑙𝑑 мυѕι¢ѕ📀💿 👉ɛռɢʟɨsɦ мυѕι¢ѕ🎤🎧 👉𝑓𝑢𝑛𝑛𝑦 𝑣𝑖𝑑𝑒𝑜📺💻 👉𝑡𝑖𝑘𝑡𝑜𝑘📷😁 👉ռɛա ʄaɖɦɨօռ👟👖👕 👉զʊօtɛs......📃📄 ʄօʀ aռʏ ċօʍʍɛռt & cross @Prince_hafu

እህቶቼ እናንተ ስትጨርሱ እርሱ ይጀምራል እግዚአብሔር በባህሪው በሰው እውቀትና ጥበብ ላይ ተደምሮ መስራት አይፈልግም እናንተ አለኝ የምትሉትን እስክትጨርሱ ድረስ ይጠብቃቿል፤ ያድነኛል ያላቹትን ሁሉ እስክትሞክሩ ይታገሳቿል፤ በስተ መጨረሻ ግን አይናቹን ከሰዎችና ከሁኔታዎች ላይ ስታነሱ እርሱ በእናንተ ህይወት ላይ መስራት ይጀምራል፤ ከ 12 ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ያልሞከረችው መድኃኒት፤ ያልደረሰችበት ባለ መድኃኒት ቤት አልነበረም፤ ነገር ግን በስተመጨረሻ ልቧን ወደ ፈጣሪዋ አዘነበለች፤ ከዛም ለብዙ ዘመናት ስትሰቃይበት የነበረው በሽታዋ በቅጽበት ትቷት ሄደ፤ ወዳጆቼ አይኖቻቹን አስር ጊዜ ባህሪውን ከሚቀያየረው ከዚህ አለም  ሁኔታ ላይ አንስታቹ ሁኔታዎች ወደ ማይለውጡት ወደ እግዚአብሔር ላይ አድርጉ፤ ያኔ  ህይወታቹ ጓዳችሁ ምንም ስጋት በሌለበት በአምላክ እጅ ላይ ይሆናል። ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
እህቴ 👸 እርሱ አልጨረሰም በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ አንድ የሚገርመኝ ታሪክ አለ ሉቃስ 8፡26 ላይ፤ እዚህ ሰው ላይ ተስፍ ያልቆረጠ አልነበረም፤ ቤተሰቡ፣ የጌርጌሴኖን ሀገር ሰዎች፣ በጤንነት ሳለ የሚያውቁት ጓደኞቹ ሁሉ እርሱ ላይ ያላቸውን ተስፍ ጨርሰዋል ፤ በዚህም የተነሳ ከሰው ተለይቶ በመቃብር ስፍራ ይህ ሰው ይኖር እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፤ እና በጣም የሚገርመው ሰውዬው ፈላጊ እንደሌለውና በማንም እንደማይፈለግ ህዝቡ ሁሉ ተረድተው ማንም በሌለበት የመቃብር ስፍራ ዋጋ እንደሌለው ሰው ጣሉት፤ነገር ግን ለዚህ ተስፍ ቢስ ሰው አንድ ወዳጅ ሊሆነው የፈለገ ሰው ነበር፤ ወዳጆቼ ይህ ሰው ለሰፈሩ ሰዎች ከአሳማ እንኳን ያነሰ ዋጋ ያለው ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው ምክንያቱም ተስፍ የሌለው ስለመሰላቸው፤ ፈጣሪ ግን ይህ ሰው ላይ የለውን አላማ አልጨረሰም፤ ፈፅሞም ተስፍ አልቆረጠበትም፤ እንደ ቤተሰቡም መቃብር ስፍራ እንዲኖር አልፈቀደለትም፤ ለዚህም ነው እርሱን ለመርዳት ሲል የውሀውን መአበሉ ፀጥ አድርጎ ወደ ነበረበት ስፍራ የመጣው። ውድ እህቶቼ 😍 እናንተ አበቃለት ብላቹ በጨረሳቹለት ጉዳይ ላይ ፈጣሪ ሲመጣ ከአዲስ ይጀምረዋል፤ ፈላጊ የሌላቹ የመሰላቹ እናንተ ናቹ  እርሱ ግን እናንተን ለመርዳት በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ይበራል በደመናትም ላይ ይራመዳል፤የእናቱ የእመብርሃን ምልጃም ዘወትር ይጠብቃችኋል እና ሁሉ ሳላችሁ አንዳች እንደሌላችሁ አትሁኑ እባካችሁ ልባሞች ናችሁና ልብ በሉ 🙏 ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
👩ልባሟ ሴት👩 #ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል። " (መጽሐፈ ምሳሌ 31:10)      👉ታውቂያለሽ እህት ዓለሜ  #ቀይ እንቁን ከ ሌሎች ማዕድናት ለየት የሚያደርገው ውበቱ ውስጣዊ ውበት ከመሆኑም ባሻገር  የውስጡ ውበት ዉጪውንም ማስዋቡ ነው        #አንቺም ልክ እንደዚሁ ነሽ ውስጣዊ ማንነትሽ የተዋበ አዲስ ማንነት ያለሽ የዋጋሽ ልኬቱ ከውድ ነገር የበለጠ      #አንድ ነገር ዋጋው የተገዛበትን ያህል ነው     #በፈጣሪሽ በአምላክሽ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተገዝተሻልና ዋጋሽ ያንን ነው የሚያክለው       #ዉድ ነገር የወጣበት ነገር በየቦታው እንዳማይገኝ      በተጠራሽበት ግብዣ ሁሉ አትገኚ    ተራ አይደለሽምና ተራ ከሆነ ከዚህ ዓለም ኮተት ራስሽን ሰውሪ       #በፍለጋ አትገኚ አድራሻሽ እንደ ማርያም በፈጣሪሽ እግር ከመስቀሉ ስር ይሁን     ልባም ሴት ነሽና ልብ በይ ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ምሽት ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
إظهار الكل...
𝓲𝓽𝓼_𝓱𝓪𝓯𝓾

Нι gυуѕ ʝօɨռ tɦɨs ċɦaռռɛʟ ɨʄ ʏօʊ ɢɛt 👉𝑛𝑒𝑤 𝑚𝑢𝑠𝑖𝑐𝑠🎤🎧 👉𝑜𝑙𝑑 мυѕι¢ѕ📀💿 👉ɛռɢʟɨsɦ мυѕι¢ѕ🎤🎧 👉𝑓𝑢𝑛𝑛𝑦 𝑣𝑖𝑑𝑒𝑜📺💻 👉𝑡𝑖𝑘𝑡𝑜𝑘📷😁 👉ռɛա ʄaɖɦɨօռ👟👖👕 👉զʊօtɛs......📃📄 ʄօʀ aռʏ ċօʍʍɛռt & cross @Hafu_na

እህቴ አንድ ብሂል አለ እርሱም ምን መሰለሽ ጨው ውሀ ሊቀዳ ሔዶ በዛው ቀረ 🤔 ምን ሆኖ ሲባል ? #ሟሙቶ 😳 እህት ዓለሜ ብዙ የሚያሟሟ ነገር በሞላበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው ። 👉 social media ያሟሟል 👉 የትምህርት ቤት ጓደኛ ያሟሟል 👉 የሰፈር ጓደኛ ያሟሟል 👉 የስራ ባልደረባ ያሟሟል 👉 የቲቪ ፕሮግራሞች ያሟሟሉ 👉 መጽሐፍት ያሟሟሉ ብዙ ብዙ 👉 ውሀ ሊቀዳ ሔዶ  እንደሟሟው ጨው እንዳንሟሟ  ራሳችንን ከውሀ ከሚያሟሟ ነገር እንጠብቅ 👉 "ቀዳሁ ብሎ #መቀዳት አለና።" አተረፍኩ ብሎ መክሰር አለ 👉 ክፉ ወደበዛበት ሀጢያት ወደ ነገሰበት ወደ ሚያሟሟው አንሂድ አንጠጋ አንቅረብ እንሽሸው 👉 ጨው አንዴ ከሟሟ በኋላ ጨዉን ለይቶ ማውጣት ከባድ ነው ብዙ ጊዜ እና አቅም energy ይፈልጋል:: 👉ጨው ውሀ ውስጥ ለመሟሟት ጥቂት ደቂቃ ይፈጅበታል  ከወሀው ለመለየት ግን በchemistry ቀመር boiling process ያስፈልጋል ። boiling processን እንደምታውቂው ደግሞ እሳት አለው መቃጠል አለው መንደድ አለው ። 👉በሀጢያት መንደር ከሟሟን እና ከተገኘን በኋላ ወደ ቀደመው መልካም ማንነታችን ለመመለስ ብዙ ጊዜ እና ብዙ እሳት እናልፋለን ። ለምን ካልሽኝ የዘራነውን ማጨድ ስላለብን 👉ከዚህ ሁሉ በፊት ግን አስቀድመን ራሳችንን ከሚውጡን ነገሮች እንጠብቅ መጽሐፍ እንዲህ ይላልና ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ 1ኛ ጴጥሮስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ሕይወትን #ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች #ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ¹¹ ከክፉ #ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ ¹² የጌታ ዓይኖች ወደ #ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም #ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው ። ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
እህቴ አንዳንዴ ዋጋቢስ እንደሆንሽ፣ የትም እንደማትደርሺ፣ መቼም ደስተኛ ለመሆን እንዳልታደልሽና እንደማትረቢ ሊሰማሽ ይችላል። ግን አንድ ነገር አድርጊ🤔 በየቀኑ ትናንሽ መስጠቶችን ተለማመጂ፤ ጊዜሽን ይሆናል፣ ገንዘብሽን ይሆናል፣ ጉልበትሽን ይሆናል ወይ ደግሞ ሀሳብሽን ይሆናል። ለተቸገረ ገንዘብ መርዳት ብቻ አይደለም መስጠት፤ የከፋው ሰው ካለ የሆዱን ሲነግርሽ ጊዜህን ሰጥተሽ ማድመጥ ብቻ ለዛ ሰው ሰላም ሲሰጠው ታይና ልዩ ስሜት ይሰማሻል። ጉልበት የከዳው አቅም ያነሰው የምታውቂው ሰው ካለ ጉልበትሽን ለደቂቃዎች አውሺው፤ ታላቅ ስጦታ እንደሰጠሽው አስቦ ሲያመሰግንሽ ይውላል። ይሄን ስታደርጊ እኔኮ የማልረባ ሰው ነኝ የሚለው ስሜትሽ ጠፍቶ ማንነትሽ በራስህ አይን ገዝፎ ይታይሽና "ለዚህ ክብር ያሰብከኝ ተመስገን አምላኬ!" ትያለሽ። ሰማሽኝ ልባሟ ሴት እንዳትጠራጠሪ ለክብር ነው የተፈጠርሽው! ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
👉 አንድ እናት ልጇን ጡት መጥባት አቁሞ ምግብ መብላት አንዲጀምር ብዙ በልመናም በቁጣም ትሞክራለች ታዲያ ግን አልሰማ ካለ አይ ይቅርበት ብላ አትተወውም ግራዋም ቢሆን ቀብታ  ተለምኖ እምቢ ያለውን ምግብ ለምኖም ቢሆን እንዲበላ ታረገዋለች።    ታዲያ ፈጣሪስ የሚመር ነገር እንዲያጋጥመን የሚፈቅደው አንድም አንለቅ ያልነውን ሊያስለቅቀን ሌላው ደግሞ ጣፋጩን እንድንመርጥ ቢሆንስ🤔?                        መልሱን ለእናንተ ተውኩት ! ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...
የኔ ውድ ሴት👸 የኔ ውድ ሴት የከበረች የቤተክርስቲያን ምሳሌ መሆንሽ እውነትም ውድ መሆንሽን ያሳያል። ታድያ ልክ እንደዚሁ ማንነትሽ በውድ ቦታና አነጋገር ውስጥ መኖር ይገባሻል። ያንቺ ህይወት ከሌሎች ምስክርነት ሊያገኝ ይገባል የአምላክ ጥበብ ያረፈብሽ ድንቅ ፍጡር ነሽ! ለማጋነን አይደለም ነገር ግን ይህን ማንነትሽን ከሚያረክሱ፣ከሚያቆሽሹ፣ዋጋ ከሚያሳጡ ነገሮች ጋር አታዛምጂ። እውነቴን ነው ምልሽ ተራ እቃን ተራ አላማና ተራ እቅድ ያላቸው ናቸው ሚፈልጉት አንቺ ደግሞ የሚገባሽን ጠንቅቀሽ የምታውቂ ልባም ሴት ነሽ ለሚፈልጉሽ፣ለተመኙሽ፣ለጠየቁሽ ሁሉ አትገኚ! ውድ መሆንሽን በምትውይው ስፍራ፣በምትናገሪው አነጋገር፣በምትሰሪው ስራ መግለጥ ይኖርብሻል።  ብዙ ሴቶች ውበትን ተገን በማድረግ ትዳር የሚያገኙ፣መልካም ህይወት የሚኖሩ፣እድሚ ልካቸውን የማይረግፍ ውበት ይዘው የሚቀጥሉ ይመስላቸዋል፦ በርግጥ ቆንጆ መሆን፣ መልካም የሰውነት አቋም መያዝ፣ አለባበስን ማሳመር በብዙ ሰዎች እንድንወደድ፣እንድንደነቅ፣እንድንፈቀር ሊያደርጉን ይችላሉ። አስተውይ ይህ ሁሉ ውበትሽ ሲጠፋ፣መልክሽ ሲረግፍ፣አቋምሽ ሲበላሽ እንደ ዶፍ ዝናብ በአንዴው ፀጥ ይላሉ!! እንዲህ አንዳታስቢ አሁን አንዳለሽ የሚቀጥል ነገር የለም። ጊዜ ሚዛን ይባል የለ በጊዜያት መካከል የማይደክምና የማይነጥፍ ፍቅር የሚሰጥሽን የራስሽን ሰው፣ ላንቺ የተፈጠረውን አካልሽን ፈልጊ። ልብሽ እያወቀ ውስጥሽ እየወቀሰሽ በእንቢተኝነት ስሜት አትቀጥይ የራስሽን ሰው እስክታገኚ ድረስ አትባክኚ ያንቺ ካልሆነ ሰው ጋር ጊዜሽን አታጥፊ እንቁሽን ለማንም አሳልፈሽ  አትስጪ ለሚገባው ብቻ አኑሪ....የእውነትም ውድ ነሽ ✍የአብስራ ተስፋዬ 📥 @Yeabm በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
إظهار الكل...