cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Exit Exam - Civil (🇪🇹)

We try to help any civil engineering students to succeed in exit exam

إظهار المزيد
Ethiopia5 873لم يتم تحديد اللغةالتعليم45 438
مشاركات الإعلانات
880
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሰላም የዚህ ግሩፕ አባሎቻችን ፤ መልካም የዕረፍት ጊዜ እያሳለፋችሁ እንዳላችሁ ተስፋ እናደርጋለን።እንደሚታወቀዉ መጀመሪያዉ ዙር ፈተና ያልተሳኣላቸዉ ተማሪዎች ለቀጣይ ዙር በቂ ዝግጅት ማድረግ ያለባቸዉ በመሆኑ ከወዲሁ እንቅስቃሴ ማድረግ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ። በመሆኑም የመጀመሪያዉ ዙር ፈተና ጥያቄ ያገኛችሁ ካላችሁ እንድትልኩልን እንዲሁም ተጨማሪ አስፈላጊ ናቸዉ ተጠቅመንበታል የምትሏቸዉን መረጃዎች እንድትልኩ በአክብሮት እንጠይቃለን። **በቀጣይ ለሙያዊ እድገት(Career development) የሚያግዙ መረጃዎችንም የምንለዋወጥ ይሆናል። ከምስጋና ጋር።
إظهار الكل...
👍 6👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርቃት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ። ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የሚያስመርቋቸው። ዘንድሮ ከተሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በምርቃት መርሃግብር ላይ ከመሳተፍ ጋር በተገናኘ በተመራቂዎች ዘንድ ጥያቄዎች የነበሩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ የተቋማቱ #የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ መሆኑን ገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት በተቋማት ሴኔት ውሳኔ ለምርቃት ብቁ የሆኑ / የምረቃ ፎርማሊቲ የሚያሟሉ ተማሪዎች የምርቃት ስነሥርዓት ላይ ይሳተፋሉ ፤ ነገር ግን ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃቸውን የሚወስዱት የመውጫ ፈተና ያለፉት ብቻ ናቸው። የተቋማት የምረቃ ቀን መቼ ነው ? ነገ ረቡዕ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ተቋማት መካከል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል። የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) ፤ ጊምቡ እና ሻምቡ በነጋታው። - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) ፤ በ15/2015 (ቡሬ ካምፓስ) - ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ) ፤ በነጋታው በሳውላ ካምፓስ - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ - ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰመራ ዩኒቨርሲቲ - ዲላ ዩኒቨርሲቲ - እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ - ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)  በነጋታው (ዱራሜ ካምፓስ) - መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ - ወራቤ ዩኒቨርሲቲ - መቱ ዩኒቨርሲቲ - አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ወልድያ ዩኒቨርሲቲ - አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ። ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ በኃላ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከሐምሌ 16 ጀምሮ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል። #tikvahethiopia @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👍 6
Repost from Tikvah-University
Photo unavailableShow in Telegram
የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦላን ላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል። ምንም እንኳን ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት መታየት የሚጀምረው ከማታ ጀምሮ መሆኑን ቢገልጽም ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተማሪዎችን የፈተናውን ውጤት እያዩ መሆኑን አረጋግጠናል። የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username እና Password በማስገባት ነው። ድረገፁ ተመራቂዎች ፈተናውን ማለፍ አለማለፋቸውን ካገኙት ውጤት ጋር Pass / fail እያለ ያሳውቃቸዋል። #TikvahEthiopia @tikvahethiopia
إظهار الكل...
1
Repost from N/a
" የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
إظهار الكل...
👍 3 2
ፈተናዉን እንዴት አገኛችሁ?
إظهار الكل...
👍 11
መልካም ፈተና እመኝላቿለሁ።
إظهار الكل...
26
Repost from Tikvah-University
#Update ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል። ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል። አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል። የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል። ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል። የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ላይ እንደሆነም ህብረቱ ጠቁሟል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
8👍 3
Exit EXAM 6.pdf1.40 KB
Explanation 6.pdf3.26 KB
👍 4
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ይነበብ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይጀምራል። በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ? [ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ] - ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል) - ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው። - ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው። - ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም። - ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው። - ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት። - በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም። - ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም። - ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። - ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ፈታኝ መምህራን እና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል። NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ ፈተና መፈተኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል። [ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ] - የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል። - ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። - ፈታኝ መምራህን የተፈታኝ ተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ። - በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው። - የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው። - በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከመተኛ ክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ። - ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው። - ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል። - ሲኮርጅ ወይም ሲያስኮርጅ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። - ፈተናው ከጀመረ ከ15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም። - የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው የሰበሰበው። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👍 4
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.