cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ayu ZeHabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

«በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣️‼️ትክክለኛው የአዩዘሀበሻ ቻናል ይሄ ብቻ ነው። https://t.me/Ayuzahabeshaofficial ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰዎች ሸር አድርጉ። #አመሰግናለሁ🙏 ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👇👇👇 @AyuZeHabesha_official_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 858
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-237 أيام
-15630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በምዕራብ ወለጋ 42 የጤና ተቋማት መዘረፋቸው ተገለጸ‼️ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ 42 የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን ተከትሎ አግልግሎት ማቆማቸው ተገልጿል። 100 ሺሕ የሚገመቱ ነዋሪዎች ባሉበት የቤጊ ወረዳ አብዛኛው የጤና ተቋማት በመዘረፋቸውና በመጎዳታቸው፤ አስቸኳይ ሕክምና የሚፈልጉ እንዲሁም ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና እክሎች ያጋጠማቸው ታካሚዎች አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጓል ሲል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል።  ለአብነትም በዚያው አካባቢ ከአምስት በላይ ወረዳዎችን ያስተናግዳል የተባለው የጉዱሩ የመጀምሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግድግዳው በጥይት መመታቱና የዉኃ ማጠራቀሚያ ገንዳው ጉዳት የደረሰበት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አልጋዎች፣ የቀዶ ሕክምና መሳሪያዎች፣ መድሃኒቶች እና አምቡላንሶችም መዘረፋቸው ተመላክቷል። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ኹሉም መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች መወሰዳቸውንና የድንገተኛ መድኃኒቶች እጥረት መኖሩን ጠቅሰው፤ ምንም ዓይነት የቀዶ ጥገና ክፍል አለመኖሩን እንዲሁም በውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳው ላይ በደረሰው ጉዳት የውሃ አቅርቦት እጥረት መኖሩን ተናግረዋል። በተመሳሳይ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ከተማ ሲገቡ የሕክምና ፈላጊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር ቢሆንም፤ አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት የማይችሉ መሆኑ ነው የተገለጸው። በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶች ላይ በተለይም የጤና እና የውሃ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱም ተነግሯል። ዓለም አቀፉ ቀይ የመስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ክፍል ሥራውን ቢቀጥልም ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ፈተናዎች እንዳሉበት ተመላክቷል። በአካባቢው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ በሚል በአሸባሪነት የተፈረጄው ታጣቂ ቡድን በሚሰነዝረው ጥቃት፤ እንደ ቡቡል፣ ቤጊ፣ ኮንዶሌ፣ ባሎ፣ ባሬዳ እና ኮምቦልቻ ያሉ አካባቢዎች ክፉኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እጥረት መኖሩም ተጠቁሟል።
إظهار الكل...
👍 106 28😢 13
Photo unavailableShow in Telegram
ሳዑዲ አረብያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአረፋ ኹጥባን(ሃይማኖታዊ ንግግርን)በ20 ቋንቋ ስትተረጉም የቢላልን ሀገር ቋንቋ በአማርኛም እንደሚተረጎም ይፋ ሆኗል። 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
👍 7
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ እገታ ግድያ ግፍና ሰቆቃ ገደቡን አልፏል‼️ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እለት ከእለት እየጨመረ የመጣው የንጹሐን ዜጎች መፈናቀል፣ እገታ፣ አፈና እና ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ያስጨንቀዋል፡፡ በተለይ እራሱን "የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት" እያለ የሚጠራው ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እና እንግልት ቀን በቀን እየተባባሰ መጥቷል፡፡ የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በሰላም በድርድር እና በውይይት ለመፍታት መሞከር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ላይ ግርታ ባይኖርም ለሰላም ነው እየተባለ ንጹሐን ዜጎች ላይ በጠራራ ጸሐይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ አፈና፣ ግድያ፣ ግፍና ሰቆቃ ሊታገሱት ይገባል ማለት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. የተፈረመውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ባወጣነው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች ላይም ለሰላም ውይይትና ድርድር በር አንዲከፈት አሳስበን የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልል የነበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ እንደፈቱ ተዘግቧል፡፡ መንግሥትም የሰላም በሩን ከፍቶ በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ኦነግ ሸኔ ከሚለው አሸባሪ ቡድን ጋር ታንዛኒያ ላይ ሰላማዊ ውይይት እንደጀመረ ሲያሳወቅ ተስፋ አድረገን የነበረ ቢሆንም ከድርድሩ በኃላ የሽብር ቡድኑ ጥፋት እየባሰበት ሲመጣ እንጂ ሲቀንስ ወይም ጨርሶ ሲጠፋ አላስተዋልንም፡፡ ይህም ንጹሐን ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ለአፈና እና ግድያ እየዳረጋቸው መደበኛ እለታዊ ሕይወታቸውን ተረጋግተው እንዳያከናውኑ እያደረጋቸው ነው፡፡ በመንግሥት በኩል የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ቡድኑን ጨርሶ ለማጥፋት እንዳልተቻለ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ፤ የሸኔ የሽብር ቡድንን አስቸጋሪ አወቃቀር በመጥቀስ እርምጃ ለመውሰድም ኾነ ለመደራደር የሚመሩት መንግሥት መቸገሩን ሲገልፁ ሰንብተዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሽብር ቡድኑ አባል ነን የሚሉ ታጣቂዎች በወለጋ ሁለት ዞኖች፣ በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ በሱሉልታ ወረዳ ቦቁ ጎልባ፤ ኤካ ጋጆና፤ ቦቁ ሁሩታ እና ሞዬ ጋጆ በሚባሉ ቀበሌዎች፤ በዝዋይ፣ መቂ፣ ሰዴን ሶዶ ወረዳ፣ የአዳ ባርጋ ወረዳ፣ ኩዩ ወረዳ፣ ገርበ ጉራቻ፣ ዋጫሌ ወረዳ፣ በአዳማ፣ በመተሀራ፣ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ በአርሲ ዞን፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ንጿሃን ዜጎችን እያገተ እና እየገደለ ፣ የትራንስፖርት እና እቃ ማጓጓዣ መኪና ሹፌሮችን እያፈነ እና በርካታ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ተግባራት እየፈጸመ እንዳሻው እየተንቀሳቀሰ የዜጎችን ህልውና እየተፈታተነ፣ ሀገራችንንም የምድር ሲኦል እያደረገ ነው፡፡ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ጭምር የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ፤ ኢሞራላዊ በኾነ መንገድ የሃይማኖት ሥፍራዎችን ሳይቀር እያዋረደ ነው። ይህንን የሚያክል የሀገር ህልውና ችግር በየእለቱ እንደተራ ዜና እየሰሙ ማለፍ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የሚመለከታችሁ የመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች ልብ ልትሉት ይገባል፡፡ በምንም መልኩ የዜጎች በሕይወት የመኖር ዋስትና በመንደር ሽፍቶች ሲገፈፍ በቸልታ ሊታለፍ አይችልም፡፡ መንግሥት የሚጠየቀውን መስዋዕትነት ኹሉ ከፍሎ የዜጎችን ደኅንነት ካላስጠበቀ፤ አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም ሥፍራ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ተንቀሳቅሶ መሥራት፣ ያለሰቀቀን መኖር እና የደኅንነቱ መጠበቅ እንደ ዳገት ሊከብደው አይገባም፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የመንግሥት በጣም ትንሽ የሚባለው ኃላፊነት የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህንን መሠረታዊ መንግሥታዊ ግዴታ አለመወጣት የአቅም ማጣት ወይም የግዴለሽነት ችግር ነው፡፡ መንግሥት ያለበትን ሁኔታ በግልጽ አሳውቆ፤ ሕዝብን በማስተባበር ዘመቻ በማካሄድ የሽብር ቡድኑን አደብ ማስገዛት ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን አለማድረግ ግን የቸልተኝነት ወይም የግድያው ተባባሪነትን ማሳያ ከመኾን ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ እዚህ ጋር መረሳት የሌለበት ዋና ጉዳይ ግን መሰል አይነት በደሎች የሚፈጥሩት ብሶት ዜጎች በራሳቸው ተደራጅተው ሰላምና እና ደህንነታቸውን ወደ ማስጠበቅ ይገቡና ወደ አላስፈላጊ ትርምስ ውስጥ ሊያስገባን እንደሚችል ነው፡፡ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ነገ ዛሬ ሳይሉ አፋጣኝና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚኖርበት መንግስትን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡ ምንም እኳን ላለፉት ጥቂት ዓመታት መንግሥት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሽብር ድርጅቶች እንዲሁም በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሴራ ተጨባጭ የሰላም እና ደኅንነት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ብንገነዘብም፤ ባለንበት ወቅት በራሱ አንደበትና በመገናኛ ብዙኀን እንደምንመለከተው መንግስት ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ማደራጀቱን እና የማያዳግም የሰላም ማስከበር ሥራ እያከናወነ መኾኑን እየገለጸ ስለኾነ፤ የሸኔ የሽብር ቡድን እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እንዳሻው መፈንጨት ምንም አይነት ምክንያት ሊቀርብበት የማይችል ሙሉ በሙሉ የመንግሥት የራሱ ድክመት መሆኑን ሊያምን ይገባል፡፡ በሕዝብ ይሁንታ የመንግስት መንበር ይዣለሁ ብሎ የሚያምን ኃይል ከመንግሥት ኃላፊነት ቀዳሚ የሆነውን መተላለፊያ ኮሪደሮች ማስከበር አለመቻል ሰበብ እንጂ ምክንያት ሊገኝለት አይችልም። እንዲህ አይነት አንገብጋቢ እና ቅድሚያ ሊሠጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ቢኖሩም አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ባልሆኑ ችግሮች ላይ ትኩረት መሥጠቱ ዜጎችን ለከፍተኛ ጥርጣሬ ዳርጓል። በመኾኑም፤ ይህንን ሀገራዊ የኅልውና አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን አስቸኳይ እና ዘላቂ እርምጃዎች እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡ 1ኛ/ የፌደራል መንግሥት በየጊዜው የጥፋት ተልዕኮውን እያሰፋና የራሱን ኃይል ለማግዘፍ የሚፍጨረጨረውን ኦነግ ሸኔን አደብ ለማስያዝና ዜጎችን ከሰቆቃ ለመታደግ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለህዝብ በይፋ እንዲያሳውቅ! 2ኛ/ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ እንደገለጽነው በራሱ ብልጽግና መንግሥት ውስጥ ተሰግስገው ለአሸባሪው ቡድን ሚስጥራዊ ድጋፍ በማድረግ የህዝብን ሰቆቃ የሚያባብሱና የቡድኑን እኩይ ተግባር በቸልታ የሚመለከቱ በተዋረድ ያሉ አካላትን ቁርጠኛ ሆኖ በመታገል ምንጩን እንዲያደርቅ! 3ኛ/ አሸባሪው ቡድን በዚህ ወቅት አፋፍሞ በየአቅጣጫው እየፈጸመ ያለውን መርህ አልባ እንቅስቃሴ ከወዲሁ እንዲሽመደመድ ካላደረገና ትጥቅ በፍጥነት ማስፈታት ካልቻለ የተጀመረውን ድርድር ማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንበት አጥብቀን መግለጽ እንሻለን። በመጨረሻም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በአሸባሪው ሸኔ ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙትም ኾነ ከዚህ በኋላ ለሚፈጸም ግድያ፣ መፈናቀል፣ እገታ፣ ውድመት እና ሰቆቃ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በህሊና፣ በሕግ፣ በሕዝብ እና በታሪክ ተጠያቂ እንደሚኾኑ ሊያውቁት ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
إظهار الكل...
👍 18
Photo unavailableShow in Telegram
ዋግነር ውጊያ ለማቆም መስማማቱን የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሴንኮ ተናገሩ‼️ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ከዋግነር መሪው ይቪግኒ ፕሪጎዥን ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፥ ቀኑን ሙሉ በተደረገው ምክክርም  ፕሪጎዥን በሩሲያ ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ ላለመግባትና የተጀመረውን ውጊያ ለማቆም መስማማቱን አስታውቋል። የቅጥረኛ ወታደር ቡድኑ መሪ ተዋጊዎቹ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡንም መግለጫው ማመላከቱን አርቲ አስነብቧል። ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋርም መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን፥ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የወጣው ዘገባ ውጥረቱን እንደሚያረግበው ይጠበቃል። በዩክሬኑ ጦርነት ባክሙትን በመቆጣጠር ለሩሲያ ወታደሮች አስረክቦ የወጣው ዋግነር ትናንት ምሽት በተዋጊዎቼ ላይ ጥቃት ደረሰ በሚል በሩሲያ መከላከያ ሃይል ላይ ውጊያ መጀመሩን ገልጾ ነበር። በደቡባዊ ሩሲያ የምትገኘውን ሮስቶቭ ከተማ በመቆጣጠርም ወደ ሞስኮ በመገስገስ ላይ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። #AlAin 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
👍 8
በደቡብ ወሎ ደላንታ ወረዳ ወገልጤና ከተማ መከላከያ ሰራዊት ትናንት ወደ ከተማዋ ገብቷል። በዚህም ከ2:00 በኋላ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ የለም። ሰሞኑን በአቅራቢያው የነበረው የተኩስ ልውውጥ ቆሞል።
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሃትን ወደ ህጋዊ ሰውነት እንዲመልስ የህወሓት አመራሮች ከመንግሥት ጋር ውይይት መጀመራቸውን አንድ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ለሪፖርተር ገልጸዋል። ምርጫ ቦርድ ህወሃትን እንደገና ላለመመዝገብ እና ህጋዊ ሰውነት ላለመስጠት ያሳለፈው ውሳኔ ትክክል ያልሆነ እና ፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አስታውቋል። ከምርጫ ቦርድ ጋር በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ የምንወያይበት ምክንያት የለም፣ጉዳዩ በቅርቡ በውይይት እንደሚፈታ እናምናለን ብለዋል(አዩዘሀበሻ)። 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ያለው የኮሌራ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ መስፋፋቱን ቀጥሏል‼️ እስካሁን በኮሌራ የተያዙ ሰዎች ብዛት 11,407 - ከነዚህም 22 በመቶው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ሲሆኑ - በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ክልል እና ሲዳማ ክልሎች 79 ወረዳዎች 156 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። OCHA እንዳስታወቀው የአሁኑ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ቁጥር ሲመዘገብ የመጀመሪያ ነው ብሏል። የተመዘገበው ሞት በአብዛኛው ከ0 እስከ 14 አመት እድሜ ያላቸው ናቸው (ከዚህ ውስጥ 26 በመቶው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው). ከጠቅላላው ተጎጂዎች ውስጥ፣ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ምንም አይነት የኮሌራ ክትባት (ኦ.ሲ.ቪ.) አልተቀበሉም። ትልቁ የሞት መጠን በጉጂ ዞን (21 በመቶ)፣ በመቀጠል ሊባን (16 በመቶ)፣ ምስራቅ ባሌ ዞኖች (9.6 በመቶ) እና ባሌ (9 በመቶ) ናቸው። የኦ.ሲ.ቪ መጠን ውስንነት እና በቂ የውሃ፣ የንፅህና እና የንፅህና አገልገሎት ባለመኖሩ በ79ኙ ወረዳዎች ውስጥ የሚኖሩት ከ7.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፍተኛ ስጋት ተጋልጠዋል(አዩዘሀበሻ)። 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
👍 6
በሰሜን ወሎ ግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ አቅራቢያ ምሽቱን የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። ተኩሱ የአሳምነው ፅጌን የመታሰቢያ ቀን አክብረው ሲመለሱ በነበሩ የፋኖ አባላት እና የመንግሥት የፀጥታ አካላት መካከል እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ወረዳ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ውሏል። 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
Ayu ZeHabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

«በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣️‼️ትክክለኛው የአዩዘሀበሻ ቻናል ይሄ ብቻ ነው።

https://t.me/Ayuzahabeshaofficial

ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰዎች ሸር አድርጉ። #አመሰግናለሁ🙏 ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👇👇👇 @AyuZeHabesha_official_bot

🥰 3👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4
በቦረና ድርቅ ምክንያት ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ለተጎጂዎች አልደረሰም ተባለ‼️ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመደገፍ እና መልሶ ለቋቋም በአገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበው ገንዘብ አልደረሰንም ሲሉ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች ለቪኦኤ ኦሮምኛ ተናግረዋል፡፡ "ድርቁ በተከሰተበት ወቅት ሲደረግ የነበረው ሰብአዊ ድጋፍ ጥሩ የነበረ ቢሆንም፤ ተሰበሰበ የተባለው ገንዘብ ወዴት እንደገባ አናውቅም።" ሲሉ ነው የድርቁ ተጎጂዎች ያስረዱት። በወቅቱ በርካታ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ በዘመቻ መልክ ብር ከተሰበሰቡ በኋላ ገንዘቡ ወዴት እንደገባ የሚታወቅ ነገር የለም ያሉት ተጎጂዎቹ፤ ለእነርሱ በእርዳታ የመጣ እህል ገበያ ላይ ሲሸጥ እንደነበርም ጠቁመዋል። የቦረና ዞን የቡሳ ጎኖፋ መምሪያ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት በሕዝቡ ሥም የሰበሰበውን ገንዘብ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ መጠየቁን እና መልስ እየጠበቀ መሆኑም ተመላክቷል። የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ የተሰበሰበው ገንዘብ በክልሉ መንግሥት አቅጣጫ ሰጪነት በቡሳ ጎኖፋ ቢሮው አካውንት በተለያዩ ባንኮች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ አመላክቷል። ቢሮው አክሎም፤ የተሰበሰበው ገንዘብ በትክክል ሥራ ላይ እንዲውል እና በድርቁ የተጎዱ ሰዎችን በሚገባ መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ እንደሚገባ በመገለጽ፤ ያንን ለማድረግ ግን ጊዜ ያስፈልጋል ብሏል። በሕዝብ ሥም ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩ እና ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ ሰዎችም በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው የተባለው። በእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ ከታዩ ክፍተቶች መካከል በትክክል መረዳት ያለባቸው ሰዎች ሳይረዱ በማታለልና በብልጠት መረዳት የሌለባቸው ሰዎች እርዳታ ሲወስዱ እንደነበር ጠቅሶ፤ ይህን የማጥራት ሥራም ጎን ለጎን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።   የክልሉ መንግሥት በተጎጂዎቹ ሥም የሚሰበሰበው ማንኛውም የእርዳታ ገንዘብ በቡሳ ጎኖፋ ቢሮ እውቅና ብቻ እንዲሰበሰብ እና ግለሰቦች በራሳቸው ሥም የሚሰበስቡት ገንዘብ እንዳይኖር መመሪያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። 👉ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ👇👇👇 https://t.me/Ayuzahabeshaofficial https://t.me/Ayuzahabeshaofficial
إظهار الكل...
Ayu ZeHabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

«በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣️‼️ትክክለኛው የአዩዘሀበሻ ቻናል ይሄ ብቻ ነው።

https://t.me/Ayuzahabeshaofficial

ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰዎች ሸር አድርጉ። #አመሰግናለሁ🙏 ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👇👇👇 @AyuZeHabesha_official_bot

👍 5 2