cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ድሬዳዋ መንበረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ገዳም

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ 👉 ትምህርቶች 👉 መረጃዎች 👉 ዝማሬዎች ያገኛሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው 🩸 ለአስተያየትዎ ፦ 👉https://t.me/menberebirhan7

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
255
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡  የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17) #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡            💎ጉልባን ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡           ፨አስራተ ገብርኤል፨ በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/menberebirhan7 የፌስቡክ ድህረ ገጽ ያግኙን ©2023. https://www.facebook.com/groups/370959364183228/permalink/851422332803593/?mibextid=dDOYB
إظهار الكل...
ድሬዳዋ መንበረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ገዳም

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ 👉 ትምህርቶች 👉 መረጃዎች 👉 ዝማሬዎች ያገኛሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው 🩸 ለአስተያየትዎ ፦ 👉

https://t.me/menberebirhan7

ረቡዕ  ||  ሰሞነ ሕማማት . ምክረ አይሁድ ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል። የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ ፪. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ፦ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ የሚል በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል። ፫. የእንባ ቀን ይባላል ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን! ኪራላይሶን አቤቱ ማረን ይቅር በለን ፨አስራተ ገብርኤል፨ በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/menberebirhan7 የፌስቡክ ድህረ ገጽ ያግኙን ©2023. https://www.facebook.com/groups/370959364183228/permalink/851422332803593/?mibextid=dDOYB
إظهار الكل...
ድሬዳዋ መንበረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ገዳም

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ 👉 ትምህርቶች 👉 መረጃዎች 👉 ዝማሬዎች ያገኛሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው 🩸 ለአስተያየትዎ ፦ 👉

https://t.me/menberebirhan7

#የሕማማት_ማክሰኞ_የጥያቄ_ቀን ♦ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ተአምራት ስለሚያደርግበት ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ ጌታችንም ጥያቄያቸውን በጥያቄ የመለሰበት ቀን ስለሆነ ጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ ♥ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. ፳፩፥፳፫- ፳፯ ፣ ማር. ፲፩፥፳፯-፴፫ ሉቃ. ፳፩፥ ፳፫-፳፯፣ ሉቃ. ፳.፩-፰/፤ ♥ እርሱም ሲመልስ፤ "እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ ♥ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ? ወይስ ከሰዉ(ከምድር) ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?" አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ ♥ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው" ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋተና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡ ♥ በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ሰጥቶበታልና ♥#የትምህርት_ቀን ይባላል። በማቴ. ፳፩፥፳፰፣ ምዕ. ፳፭፥፵፮፣ ፣ ሉቃ. ፳፥፱ ፤ ምዕ. ፳፩፥፴፰ የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ ♥ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡ ❗ "እንበለ ደዌ ወህማም እንበለ ፃማ ወድካም ያብፅሀነ ያብፅሀክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ፡ እግዚአብሔር በሰላም።❗   🔴#ለሌችም_እዲደርስ_በቅንነት🔴              🔴#ሼር_አድርጉ🔴 ፨አስራተ ገብርኤል፨ በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/menberebirhan7 የፌስቡክ ድህረ ገጽ ያግኙን ©2023. https://www.facebook.com/groups/370959364183228/permalink/851422332803593/?mibextid=dDOYB
إظهار الكل...
ድሬዳዋ መንበረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ገዳም

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ 👉 ትምህርቶች 👉 መረጃዎች 👉 ዝማሬዎች ያገኛሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው 🩸 ለአስተያየትዎ ፦ 👉

https://t.me/menberebirhan7

Photo unavailableShow in Telegram
👉 ሰኞ || ሰሞነ ሕማማት ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ 📌 መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ ” ( ማርቆስ 11፥11_14 ) በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። 📌 አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ” ማቴ 21፥13 በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። ኪራላይሶን አቤቱ ማረን ይቅር በለን አስራተ ገብርኤል፨ በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/menberebirhan7 የፌስቡክ ድህረ ገጽ ያግኙን ©2023. https://www.facebook.com/groups/370959364183228/permalink/851422332803593/?mibextid=dDOYBg
إظهار الكل...
#የካቲት_16 #ኪዳነ_ምሕረት (#የሰባቱ_ኪዳናት_ማሕተም) የካቲት ዐሥራ ስድስት በዚችም ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም አማላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓልን ያደርጋሉ። በዚች ዕለት መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጠራ ለድኆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀብላለችና። ይህችም የከበረች እመቤታችን ልጅዋ ንጹሕ ሥጋዋን ተዋሕዶ ከብቻዋ ኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ፈጽሞ ስለእኛ መዳን ወዶ ያደረገውን መከራ ተቀብሎ ሙቶ ተነሥቶ ከዐረገና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ እርሷን እናቱን ማርያምን በደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ዘንድ ትቷት ነበር እነሆ ልጅሽ እርሱንም እነሆዋት እናትህ ብሎ አደራ እንዳስጠበቀው። ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ማርያም ትጸልይ ዘንድ ያለ ማቋረጥ ወደ ልጅዋ መቃብር ሁል ጊዜ ስትሔድ ኖረች ይኸውም ጎልጎታ ነው። አይሁድም በአዩዋት ጊዜ ቍጣንና ቅናትን ተመልተው በድንጊያ ሊወግሩዋት ወደዱ እግዚአብሔርም ከዓይናቸው ሠወራት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መጥታ በዚያ እንዳትጸልይ ተማክረው ከመቃብሩ ዘንድ ጠባቂዎችን አኖሩ እርሷ ግን በየዕለቱ መሔድን አላቋረጠችም ጠባቆችም አያይዋትም የልጅዋ የጌትነቱ መጋረጃ ሠውርዋታልና መላእክትም መጥተው ያገለግሏታል ጌታችንም ዘወትር ይጐበኛታል የምትሻውንም ይፈጽምላት ነበር። ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ ሰማይ አሳረጓትና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳዩዋት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብም ወዳሉበት አደረሱዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያ ዕለት በአካለ ነፍስ ያሉ አባቶች ሁሉ አንቺን ከሥጋችን ሥጋን ከዐፅማችን ዐፅምን ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው በመሆኑ በአንቺ ድህነት አግኝተናል ከጥፋትም የሕይወት ወደብ ሆነሽልናልና እያሉ ሰገዱላት። ከዚያም ወደ ተወደደ ልጅዋ የእሳት መጋረጃ ወደተተከለበት ወደ ጌትነቱ ዙፉን አደረሷት ጌታችንም እጇን ይዞ ወደ ውስጠኛው መጋረጃ አስገብቶ ከጌትነቱ ዙፋን ላይ አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጣት ያዘጋጀላትንም ዐይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው በሰው ልቡና ያልታሰበ ተድላ ደስታን ሁሉ ነገራት። ከጌትነቱ ዙፋንም በታች የእስራኤል ንጉሥ አባቷ ዳዊትን የነቢያትና የመላእክት ማኀበር እንደ ግድግዳ ከበውት በመሰንቆ ሲያመሰግን አየችው እንዲህም ይላል ልጄ ስሚ በጆሮሽም አድምጪ ወገንሽን የአባትሽንም ወገን ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና እርሱም ጌታሽ ነውና። ዳግመኛም የሥቃይን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ መላእክት ከዚያ ውሰዷት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በእርሱ ጐዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደተዘጋጀ ወደጨለማው ዳርቻ አደረሷት እመቤታችን ማርያምም ወዮልኝ ወደዚያ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ማን በነገራቸው አለች መልአኩም አመቤቴ ቡርክት ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኖራልና ለአንቺም ከአንቺ በኋላም በቃል ኪዳንሽ ለሚታመኑ አትፍሪ አላት ከዚህም በኋላ ወደ ቦታዋ መለሷት። ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለ ኋጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች እንደ ዛሬይቱም የካቲት ዐሥራ ስድስ ቀን በጎልጎታ ቦታ ቁማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር አባትህ በክርስቶስ ስምህ ከአንተ ጋርም ህልው በሆነ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ አማፅንሃለሁ ዓለም ሁሉ ሊሸከምህ የማይችል ሲሆን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተሸከመችህ ማሕፀኔ አማፅንሃለሁ ልጄ ሆይ ያለ ሕማም ያለ ድካም ከእኔ በመውጣትህ በመወለድህ በአሳደጉህ ጡቶቼ በሳሙህ ከንፈሮቼ በአቀፋህ እጆቼ ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ አማፅንሃለሁ ። በውስጡ በተኛህበት በረት በተጠቀለልክበት ጨርቅ አማፅንሃለሁ የምወድህ ልጄ ሆይ በልቡናዬ ያለውን ሁሉ ትፈጽም ዘንድ የልመናዬን ቃል ሰምተህ ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ወዳንተ ፈጽሜ እማልድሃለሁ። የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ እነሆ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ከእርሱም ጋር አእላፍት መላእክት አሉ በዙሪያውም ሁነው ያመሰግኑታል እርሱም እናቴ ማርያም ሆይ ምን ላድርግልሽ አላት እመቤታችንም ለተወዳጅ ልጅዋ እንዲህ ብላ መለሰችለት ልጄ ወዳጄ ሆይጌታዬና ፈጣሪዬ አለኝታዬና መጠጊያዬ በእናቴ ማሕፀንም ሳለሁ ባንተ ጸናሁ አንተም ጠበቅኸኝ ሁልጊዜም ስም አጠራሬ አንተ ነህ። አሁንም ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ እኔም አገልጋይህ የምለምንህ ይህ ነው መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ወይም የተራቆተውን ለሚያለብሱ የተራበውን ለሚያጠግቡ የተጠማውንም ለሚያጠጡ የታመመውን ለሚጐበኙ ያዘነውን ለሚያረጋጉ የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ድንግል ማርያም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)
إظهار الكل...
#መሐረነ_አብ_ሙሉ_ፀሎቱ                      ✴️ ሼር በማድረግ ማታ ማታ ከአባቶች ጋር በጋራ እንጸልይ
إظهار الكل...
ከሰኞ ጀምሮ የምናከናውናቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዛት ። ፩. ጠዋት 12 ሰአት በቤተ ክርስትያን ኪዳንና ምኅላ ማድረስ ። ፪. ቢያንስ 41 ስግደት መስገድ ። ፫. ጠዋት 3 ሰአት ቀን 6 ሰአት እና 9 ሰአት በያለንበት ሰላም እለኪ እና አቡነ ዘበሰማያት መድገም {አላርም በመሙላት ማስታወስ} ። ፬. ቢያንስ እስከ 9 ሰአት ድረስ መጾም ፭. ሰርክ ከ11~12 ሰአት በቤተክርስትያን ተገኝቶ ምኅላ { ቢቻል ከስግደት ጋር } ፮. ማታ 3 ሰአት ላይ ከቤተሰብ ጋር በስዕለ ማርያም ፊት በሐዘን በእንባ ጸሎት ማድረስ ። ፯. ሌሊት 6 ሰአት ጸሎት ማድረግ ፰. ሶስቱንም ቀን ጥቁር ልብስ በመልበስ እንጾማለን እንጸልያለን ። ለፍጻሜው በክብር ያድርሰን ። ጾም ጸሎታችን ከእግዚአብሔር መልስ የምናገኝበት ይሁንልን ።               ፨አስራተ ገብርኤል፨ በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/menberebirhan7 የፌስቡክ ድህረ ገጽ ያግኙን ©2023. https://www.facebook.com/groups/370959364183228/permalink/851422332803593/?mibextid=dDOYBg
إظهار الكل...
ድሬዳዋ መንበረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ገዳም

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ 👉 ትምህርቶች 👉 መረጃዎች 👉 ዝማሬዎች ያገኛሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው 🩸 ለአስተያየትዎ ፦ 👉

https://t.me/menberebirhan7