ar
Feedback
የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

الذهاب إلى القناة على Telegram

*ጥቃቅን ለውጦች- አስደናቂ ውጤት!!! ** የእለት ከእለት ልማዶችን በመጠቀም የላቀ ሕይወት መምራት *** ራስን የመቆጣጠር ምስጥር **** የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ኃይል ***** ዘላቂ ውጤቶችን የማምጣት ምስጢር

إظهار المزيد
945
المشتركون
+124 ساعات
+47 أيام
+430 أيام
أرشيف المشاركات
ሀላፊነቱን ውሰድ! ለውጥ መጀመር የሚፈልግ ሁሉ ስለ ራሱ ህይወት ሀላፊነት ይውሰድ! ከተለወጥኩ በራሴ ጥንካሬ ነው፤ ቆሜ ከቀረውም በራሴ ጥፋት ነው በልና መቀየር የምትችላቸው ነገሮች ላይ ትኩረትህንና ጉልበትህን አሳርፍ። ወዳጄ አንተ ብቻ ቆርጠህ ወደ ተግባር ግባ እንጂ የማይቀየር ነገር የለም! የለውጥ ህይወት ተመኘውላችሁ🙏

እውነታችንን እንጋፈጠው ! ለጥፋቶቻችን ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ እናቁም ቤተሰብ እንደዚህ ባያሳድገኝ ኖሮ እኮ ሀገሬ እንደዚህ ባትሆን ኖሮ ሰዎች እኮ ቢተባበሩኝ መንግስት የስራ እድል ቢያመቻችልኝ እያልን ሰበብ መደርደር ግዜያዊ እፎይታ ይሰጠን ይሆናል ራሳችንን ተጠያቂ ከማድረግ ጥፋተኛ ከመሆን የሚያድነን ይመስለናል ነገር ግን ላለንበት ሁኔታ መፍትሄ አይሰጠንም ገንዘብ የለንም አይደል እና እነዚህን ሰበቦች መደርደር ገንዘብ ያስገኘናል? እድገት ማግኘት አልቻልንም አይደል ታድያ ሰበብ በመደርደር እናድጋለን? ህይወታችን ይስተካከላል? ስለዚህ ለነገሮች ሁሉ ተጠያቂም ሆነ መፍትሄ ሰጪ እኛው ራሳችን ብቻ መሆናችንን እንወቀው ስለዚህ ሰበባችንን ከኋላ ጥለን እንደ አዲስ መነሳት እንጀምር ! እውነታችንን እንጋፈጠው ! መልካም 🌆 ምሽት ተመኘው 🙏

ደስተኛ መሆን! ደስተኛ መሆን ያለብህ አሁን ነው፤ የሆነ ነገር ሳገኝ እደሰታለው ብለህ ቅድመ ሁኔታ አታስቀምጥ፤ የዚህ አለም አስገራሚው ነገር አሁን ባለህ ስትደሰት ነው ጥያቄህ ራሱ የሚመለሰው። ህይወትህ ላይ አስገራሚ ለውጦች ያየኸው ባለህ ነገር ተደስተህ ባመሰገንክባቸው ወቅቶች ነው፤ ሳገኝ እደሰታለው አትበል! መጀመሪያ ተደስቼ የምፈልገውን አገኛለው በል! ደስታ የሞላው ህይወት ተመኘውላችሁ😍

ውድድር ጀምር ! ህይወት ያለውድድር ወደፊት እንድትሄት አታደርግህም ! ውድድር ከሌለባት ወደኋላ ነው የምትሄደው ፤ ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር የምትወዳደረው ከማን ጋር መሆኑን መለየት ነው! ከሰዎች ጋር ወይስ ከራስህ ጋር ? እኔ የምመክርህ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ውድድርህን ከራስህ ጋር አድርገው ከትላንት ማንነትህ ጋር ተወዳደር ፤ የሰዎችን እማ ያለፉበትን ነገር ምን ታውቃለህ ምን እንደገጠማቸው ምን እንደሚያስቡ ምን እንደሚፈልጉ በምን ታውቃለህ ከምናቸው ጋር ነው የምትወዳደረው ? በዚህች ምድር ላይ እኮ ጠንቅቀህ የምታውቀው አንተን ራስህን ብቻ ነው ስለዚህ ትላንትህን ታሪክህን እምነትህን ድልህን አስበው  ዛሬ ላይ ደግሞ ምን እንዳለህ እየው ከዛም ከትላንቱ የበለጠ ለማሸነፍ ታጥቀህ ተነሳ ራስን እነደማሸነፍ ትልቅ ድል የለም !

አትጓጓ! ለነገሮች በጣም የምትጓጓ ከሆነ ያ ነገር እንዳይሳካ መንገድ እየከፈትክ ነው፤ ቢሳካ ራሱ እንደጠበከው አትደሰትም። በጓጓህ ቁጥር አይምሮህ ውስጥ የዛ ነገር  ምስል አለመጠን ይገዝፍና የተግባር ሰው መሆን ይከብድሀል። ለህይወት ጣዕም እንድታጣ ያደረገህ መጓጓት ነው፤ አሁንም እየጓጓህ የሀሳብ ሰማይ ላይ መንሳፈፍ ካላቆምክ ብዙ ነገር ታጣለህ! ወዳጄ አጥብቀህ ፈልግ ግን አትጓጓ አለዚያ ስህተትህ በዝቶ ከመንገድ ትቀራለህ! የተባረከ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ወስን! ወይ ወስነህ ትቀየራለህ፤ ወይ ቆመህ ትቀራለህ እስከመቼ ትፈራለህ? እስከመቼ ታመነታለህ? እስከመቼ በሌሎች ሰዎች ለውጥ ትቀናለህ? የፍርሀትና ራስን የመጠራጠር ዘመን ማብቃት አለበት! መቼም ደግመህ የማታገኘው አንድ ህይወት ነው ያለህ! ለመኖር የቀረህ ጊዜ በጣም አጭር ቢሆን ምን ታደርግ ነበር? ምን ትወስን ነበር? ምን ትጀምር ወይ ምን ታቆም ነበር? ይሄንን አስብና ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ቁረጥ! ወደ ተግባር ግባ! እኔ አንተን ብሆን ይሄን ነው ማደርገው! የሚገርም ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

አሁን ሞክር! ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው ይቆጩሀል፣ 'ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ' ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ። የሚገርም ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ማደግና መስጠት! የሰውን ልጅ ደስታ ሙሉ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። የመጀመሪያው ማደግ ነው፤ ከትላንት የተሻለ ማንነት፣ ዕውቀትና ልምድ እየጨመርክ እያደክ መሄድ ለአይምሮህ ሰላም ይሰጥሀል። ሁለተኛው ደግሞ መስጠት ነው፤ ካለህ ላይ ጊዜህን፣ ገንዘብህን፣ ዕውቀትህን ወይ ሀሳብህን ስትሰጥ የመንፈስ እርካታ ይኖርሀል። ወዳጄ በየቀኑ ማደግና መስጠት ፀባይህ መሆን አለበት! ድንቅ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ታሪክ የሚቀይር ፈጣሪ ነው! እስከመቼ ትጨነቃለህ? ልብህ ንፁህ ከሆነ ከባድ የመሰሉህን ነገሮች በቅርቡ ታልፋቸዋለህ፤ አንተ ብቻ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ እምነትህን ካጠነከርክ አጎንብሰህ አትቀርም! ወዳጄ ታሪክ የሚቀይር ፈጣሪ ነው፤ አንተ ተመልካች ነህ! ልዩ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ሁለቱ ሸክሞች የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ! ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወዳጄ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው። ዳይ ወደ ስራ! ግሩም ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ሙሉ ደስታ ለሰዎች ብለህ ማስመሰሉ እኮ ነው ደስታህን የነሳህ! "ደስታ ማለት የምታስበው ከምትናገረውና ከምታደርገው ጋር አንድ ላይ ሲዋሀዱ ነው" ይለናል ማህተመ ጋንዲብቻህን ደስተኛ ካሎንክ ይመስልሀል እንጂ በሰዎች ብትከበብም ሙሉ ደስታ አይኖርህም፤ ሁልጊዜም ውስጥህ የሚነግርህን ህሊናህ የሚያዝህን አድርግ! ጣፋጭ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ትላንት አልፏል! ፈጣሪ ጊዜን ከፈጠረበት አንዱ ምክንያት 'ድሮ' የሚባል ላጠፋሀቸው ጥፋቶች ሁሉ መቀበሪያ ጉድጓድ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ እዛ የመቃብር ስፍራ ምን ታረጋለህ ወዳጄ? ለምን ስለትላንት እያሰብክ ራስህን ታስጨንቃለህ?! ወዳጄ አሁንን መኖር ጀምር! አጠገብህ ያለውን በረከት እይና ተመስገን በል፤ ተደሰት! ውብ ምሽት ይሁንላችሁ🙏

መስጠት! አንዳንዴ የምትወደውን ነገር ስትሰራ ይበልጥ ማተኮር ያለብህ አንተ የምትሰጠው ላይ ነው፤ የምትወደውንም ሰው ስትንከባከብ የምትቀበለውን ሳይሆን የምትሰጠው ፍቅር ላይ አተኩር፤ የፈጣሪ ቀመር ደስ የሚለው አንተ ቀንሰህ ስታካፍል እሱ በተቃራኒ ደምሮ እያባዛ መስጠቱ ነው። የመስጠት ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ፅናት ያስፈልግሀል! አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤ በህይወት የሚያሸንፈው ብርቱ የሆነ ወይ አስተዋይ (Smart) የሆነው አይደለም፤ ውስጡ ላመነበት ነገር እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ነው። ወዳጄ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ላመንክበት ጉዳይ መኖር ጀምር ከዛ በአላማህ ፅና! አስገራሚ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏 @yikdem

የግል ሐኪምዎ #Ethiopia | በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል!!! 👉ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል! በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡ ♦1. ለአእምሮ እድገት ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ♦2. ለስትሮክ በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡ ♦3. ለደም ግፊት ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ♦4. ለጨጓራ ህመም አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡ ♦5. ለድብርት ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡ ♦6. ለሆድ ድርቀት በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ♦7. ለስኳር ህመም ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡ ♦8. ሙዝና ደም ማነስ በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ♦9. ሙዝ ለስካር ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ♦10. ለሞቃታማ አየር በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡ ♦11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡ 👉 ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል። 👉 ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡ 👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡ በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡ ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡ ------መረጃ ሐይል ነው! 👉 በሽርፍራፊ ሰከንድ የተሰራች ስህተት የሰውን ህይወት እንደምታጠፋ ሁሉ፡ በሰከንዶች ቅፅበት የደረሰች መረጃ ህይዎትን ለማትረፍ ሰበብ ትሆናለችና እባከዎት የሚለቀቁ ጤናነክ መረጃዎችን ለሌሎች ወገኖች ለማድረስ ሼር ቢያደርጉላቸው መልካምነት ነው ጤና መረጃ

#በህይወታችን ልንማርባቸው የሚገቡ ጠቃሚ #አባባሎች 1️⃣ ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! 2️⃣) ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎ
#በህይወታችን ልንማርባቸው የሚገቡ ጠቃሚ #አባባሎች 1️⃣ ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! 2️⃣) ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ! 3️⃣) ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ! 4️⃣) ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ! 5️⃣) ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ! 6️⃣) ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ 7️⃣) ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ! 8️⃣) ወሬኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ! 9️⃣) ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ! 🔟) ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ! 1️⃣1️⃣)አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!        

አስገራሚው የጉንዳኖች ባህሪ 👉ጉንዳን የክብደቱ 50 እጥፍ መሸከም እና 30 እጥፍ መጎተት ይችላል:: 👉አንድ ጉንዳን 250,000 የአንጎል ህዋሳት አሉት:: 👉ከአካላቸው ክብደት አንፃር ትልቅ አ
አስገራሚው የጉንዳኖች ባህሪ 👉ጉንዳን የክብደቱ 50 እጥፍ መሸከም እና 30 እጥፍ መጎተት ይችላል:: 👉አንድ ጉንዳን 250,000 የአንጎል ህዋሳት አሉት:: 👉ከአካላቸው ክብደት አንፃር ትልቅ አንጎል ያላቸው ፍጥረታት ጉንዳኖች ናቸው:: 👉ጉንዳኖች በምድር ጥልቀት ውስጥ ያለን ውሀ በማሽተት ለይተው ያውቃሉ:: 👉ንግስቲቱ ጉንዳን እስከ 15 አመት እድሜ ትቆያለች:: 👉ጉንዳኖች ውሀ ውስጥ እንደሰመጡ አየር ሳያገኙ ለሁለት ቀናት መቆየት ይችላሉ:: 👉 ጉንዳን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚሞትበት ሰአት ድረስ በፍፁም አያንቀላፋም:: 👉በ 1 የጉንዳን መንጋ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ:: 👉 ብታምኑም ባታምኑም በምድር ላይ  ያሉ ጉንዳኖች በሙሉ ተሰብስበው ክብደታቸው ቢለካ ከአለም ህዝብ አጠቃላይ ክብደት ይበልጣል:: ምንጭ:- 👌National Geographic wild

በህይወት ስትኖር ማወቅ ያሉብህ 3 ነገሮች 1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው ስለዚህ በሙሉ አቅም መጣር አለብህ 2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ ላንተም የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ 3⃣ ስትፈልገዉ ያጣከውን ነገር ትንሽ ከታገስክ በተራው ሲፈልግህ ታገኘዋለህ        የተባረከ ምሽት ተመኘው🙏