cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢትዮ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር 🇪🇹

🇪🇹Ethiopian Muslim Students Union 🇪🇹 "አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ♥ ይህ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። "ባረከላሁ ፊኩም ተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!👇 Telegram👇 https://t.me/EthiopianMuslimStudentsUnion

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
988
المشتركون
-124 ساعات
-47 أيام
-2230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailable
ትዝብት‼ ======== ሐይስኩልና ዩኒቨርስቲ ላይ ኒቃብና ጂልባብ ኢስላማዊ አለባበስ ነው ብለው እህቶቻችንን ከፈተና እና ከትምህርት የሚያግዱ ሙስሊም ጠሎች፤ እንዲህ አይነቱን ግልፅ ኃይማኖታዊ አለባበስ ግን ፈቅደዋል። ይህ ፎቶ የ12ኛ ክፍል ለመፈተን ወደ ካምፓስ የሚገቡ ሰው ፎቶ ነው። እንኳን ሊከለክሏቸው ጭራሽ ተሳልመው ነው የሚያስገቧቸው¡ Double Standard at its tip! ©MuradTadesse
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailable
እድሜያችሁ ከ35 አመት በታች ለሆናችሁ የቁርኣን ሐፊዞች በሳዑዲ ኤምባሲ አዘጋጅነት በየአመቱ የሚካሄደውን የቁርኣን ሃገር አቀፍ ውድድር እንድትካፈሉ በሳዑዲ ኤምባሲ ጥሪ ቀርቦላችኋል።
إظهار الكل...
ኡስታዙ ከመድረሳ የተቀጠረ አዲስ ኡስታዝ ነው:: ለመጀመሪያ እንዲያስተምር ሶስት ልጆች ተሰጥቶታል:: በትምህርቱ መሐል እውቀታቸውን ለመፈተሽ "አቡ ጀህልን ማን ነው የገደለው?" ይላቸዋል:: መጀመሪያ የተጠየቀው "እኔ መችም አልገደልኩትም!" በማለት ይመልሳል:: ኡስታዙ በመገረም ሁለተኛውን ልጅ ሲጠይቀው "ኡስታዝ! እኔ ማታ ከቤቴ አልወጣሁም! እኔም አልገደልኩትም!" በማለት ይመልሳል:: ኡስታዙ የገባበት ጉድ እየደነቀው እሺ አንተስ ሲል ሶስተኛውን ሲጠይቀው "እኔ ሲጀመር እንዴት እንደሚገደል አላውቅም!" ይላል:: ግራ የተጋባው ኡስታዝ የመድረሳውን አስተዳደር በመጥራት የተፈጠረውን ነገር ያስረዳዋል:: አስተዳደሩም ወደ ተማሪዎቹ በመሄድ የተጠየቁትን ጥያቄ ጠየቃቸው:: ተማሪዎቹም መጀመሪያ ላይ የመለሱትን መልስ ደግመው መለሱለት:: በስተመጨረሻም አስተዳደሩ ኡስታዙን ከቢሮ እንግባና ለብቻችን እንወያይ ይላቸዋል:: ከቢሮ እንደገቡ አስተዳደሩ "ግን ኡስታዝ! አቡ ጀህልን የገደለው ሰው ከሶስቱ ተማሪዎች መካከል ነው?" ብሎ ይጠይቃቸዋል:: የባሰ አለ አገርህን አትልቀቅ ይሉ ይህን ነው¡
إظهار الكل...
Photo unavailable
የቢላል ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። ቢላል የሀይማኖት መምህር የመጅሊሱም አመራር ነው። የታሰረው ግለሰብ አይደለም። እንዲህ አይነት ቀይ መስመር ሲታለፍ፤ የሀማኖት መምህር ክብሩ ተጥሶ ያለ አግባብ ሲታሰር፤ ታስሮም ፍትህ ሲነፈግ የሚመለከታችሁ የመንግስትም ሆነ የመጅሊስ አመራሮች አንድ ቀን ባደረ ቁጥር ብዙዎችን በእናንተ ላይ ያለውን እምነት እየሸረሸራችሁት ነው። ፍቱት ብቻ ሳይሆን አላግባብ ያሰሩት ሰዎች በህግ ይጠየቁ።
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailable
እውነተኛ ታሪክ ነው አንብቡት" ይሄ ፎቶ የተነሳው ሀርባን ፕሮቪኒካል ሆስፒታል ውስጥ ነው..አንድ የካንሰር ታካሚ ነበር ከዛም ቦርሳ ሙሉ ገንዘብ ይዞ ዶክተሩን ጠየቀው .... እባክክ ዶክተር ህይወቴን አድንልኝ እና ከበቂ በላይ ገንዘብ እንደሚከፍለው ወይም እንደሚሰጠው ነገረው.ግን ዶክተሩም በምንም አይነት መንገድ እንደማይድን እና ካንሰሩም መጨረሻ ደረጃ እንደደረሰ ነገረው.ከዛም ታካሚው ቁጣ በተሞላበት እና ተስፋ በመቁረጥ በሆስፒታሉ መንገድ ላይ በምታዩት መንገድ ገንዘቡን በተነው ከዛም "ጮክ ብሎ"''የገንዘብ ጥቅም ምንድነው" ምንድነው የገንዘብ ጥቅም አለ."ገንዘብ ጤና መሆን አይችልም,ገንዘብ ጊዜ አይሆንም,ገንዘብ ህይወት መሆን አይችልም በማለት አምርሮ ተናገረ."ይሄ ታሪክ የሚያስረዳው ጤናማ መሆን ከገንዘብ እንደሚበልጥ ነው። አላህዬ ጤናችሁን ይስጣችሁ🙏 አሚን በሉ ደሞ😊 መልካም ቀን🫶
إظهار الكل...
🥰 1👏 1
01:00
Video unavailable
ስለዚህ ነገር ምን ትላላቹ😊😊        
إظهار الكل...
5.00 MB
👍 1
#ለኢንትራንስ ፈተና ወደ ግቢ ለምትገቡ እህቶች የተላለፈ የጥንቃቄ መልእክት። 1⃣ዶርም ስትይዢ በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እህቶች ጋር ያዢ። 2⃣ጋጠወጥ ከሆኑና እይታን ከሚሹ መጥፎ ጓደኞች ራስሽን አርቂ። 3⃣በማንኛውም ሰኣት ግቢ ላይ ለብቻሽ አትንቀሳቀሺ። 4⃣ዶርም ውስጥ ለብቻሽ አትሁኚ/አትተኚ/አታንብቢ። 5⃣ሂጃብሽን ጠብቂ፤ስርአት ያለውን አለባበስ ብቻ ልበሺ። 6⃣የሴቶች ተብሎ በሚከለለው የዶርም አከባቢም ቢሆን ብቻሽን አትሁኚ። 7⃣ከመሸ በኋላ በተቻለ አቅም ከዶርምሽ አትውጪ። 8⃣ሰላትሽንም ቢሆን ዶርምሽ ውስጥ ስገጂ። 9⃣"አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቅ" የሚውን አዝካር አዘውትሪ። 🔟አላህ ከክፉዎች ተንኮል እንዲጠብቅሽ ዱዐ አድርጊ። 💥እነዚህን ቅድመ ጥንቃቄዎች በመተግበር ራስሽን ከፆታዊ ጥቃት ከአላህ ጋር ጠብቂ!! #Share #ሼር
إظهار الكل...
☘🤍☘🤍የአመቱ የመጨረሻ ጁመዐ🤍☘🤍🍀 🎍{خير الناس من طال عمره، وحسن عمله.} ☘ከሰዎች ሁሉ መልካማቸው እድሜው ረዝሞ ስራው ያማረለት ሰው ነው። (رسول الله  ﷺ) 🎍ሁሌም ቢሆን ባለቤት በሆንበት ጊዜ "አሁን" ላይ ተውበት ማድረግና ኸይር ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ☘ስለትላንት ወንጀሎቻችን ተውበት በማድረግ ይቅርታውን በመጠየቅ… 🎍አሁን ደግሞ ስራችንን በማሳመር ላይ በመበርታት… ☘በኃላ በአላህ እጅ ነው መድረሳችን አይታወቅም… 🎍ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ወደአላህ መመለስ ላይ መዘውተር አለብን።👍 ☘ባሪያዎችህን በጥበብህ ወደራስህ የምትመልስ ጌታ🥹 🎍የዩኑስን (ዐ.ሰ) ህዝቦች በጥበብህ ወደራስህ ያማረ መመለስን እንደመለስካቸው… ☘ያ ሀኪም.....             እኛንም በጥበብህ ወዳንተ ያማረ መመለስን መልሰን🥺🤲 🎍አንተ ጥበበኛ የሆንከው ጌታ "በጥበብህ"… በማለት እንበርታ👍 ☘በአመቱ ጁመዐዎች ያደረግናቸውን ዱዐዎች ሁሉ አላህ ይቀበለን፤ 🎍በአመቱ ውስጥ በተሰጡን መልካም እድሎች ከተጠቀሙበት፤ ☘ኢባዳቸውንም ከተቀበላቸው መልካም ነገራቸው ከባለፈው አመት ከጨመረላቸው፤ መጥፎ ነገራቸውም ከቀነሰላቸው፤ 🎍ሁሌም ወደሱ ተመላሾች ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን!!🥺🤲              ☘🤍☘መልካም ጁመዐ☘🤍☘
إظهار الكل...
👍 2
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ t.me/asdajlahh በሚቀጥለው ወር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ምን አይነት ዝግጅት እና ምን አይነት ግዜ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን አምና ተፈታኝ ሆኘ ካሳለፍኩትኝ ሁኔታ አንጻር የተወሰኑ ጥቆማዎችን ለተፈታኞ አደርስ ዘነድ የሞነጫጨርኳት… ፈጅር እንደተሰገደ እንድትሰባሰቡ ወደታዘዛችሁበት ትምህርትቤት በመሄድ በተዘጋጀው የየትምህርትቤታችሁ ባስ ላይ ከመጀመርያ ዙር ቀለል ያለ ፍተሻ በኋላ ገብታችሁ ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ መፈተኛ ግቢ እንደደረሳችሁ የያዛችሁት እቃ እንደ እቃችሁ ብዛት ጠንከር ላለ ፍተሻ ይበተናል፡፡(በዚህ ፍተሻ ሰዐት ቤታችሁ ጥንቅቅ አድርጋ እናታችሁ ያስተካከላችው ልብስ ከፍተሻ በኋላ እንዳልነበረ ሆኖ ሻንጣችሁ ሊጠባችሁ ስለሚችል እቃ አለማብዛቱ ይመከራል)፡፡ ግቢ ከገባችሁ በኋላ በመጀመርያ ወደተመደባችሁበት ብሎክ በመሄድ ከብሎካችሁ ስር ከሚገኛው ዶርሚተሪ ዶርም ውስጥ በሚገኘው አልጋ ልክ እየመደበ ለአንዳችሁ የዶርም ቁልፍ ይሰጣል፡፡(በአንዳንድ ግቢዎች ላይ እንደተፈታኙ ፍላጎት የዶርም ምደባ ስለሚደረግ ለማንኛውም ግዜያችሁን በአግባቡ ሊያስጠቅም የሚችል ጓደኛ ጋር ቀድማችሁ በመነጋገር ቀደም ብላችሁ በመገኘት ከዶርሚተሪ ቁልፍ በመቀበል የራሳችሁን ዶርም ለመያዝ ብትሞክሩ የተሻለ ነው፡፡) ከፈተናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በምትፈተኑበት አዳራሽ በሱፐር ቫይዘሮች ቀለል ያለ ኦረንቴሽን ይሰጣል፡፡ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ በየእለቱ ሁለት ፈተና (ጠዋት አንደ ከከሰዐት አንድ) ይሰጣል፡፡ ከፈተና በፊት በሚደረገው ሁሉም ፍተሻ የሴት እና የወንድ ፍተሻ የተለየ ስለሆነ ኒቃብ የምታደርጉ ተማሪዎች ሳትደናገጡ ዩኒፎርማችሁን እንደለበሳችሁ ከነኒቃባችሁ በመቅረብ ፈተና መፈተን የምትችሉ ሲሆን ( ሆነ ብለው ከፈተና እንዳርቋችሁ በመጀመርያ ግቢ ላይ በሚኖራችሁ ፍተሸ ስትማሩ እንደነበራችሁት በማስክ እና በሂጃባችሁ ብትሸፈኑ እላለሁ) የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ እስከነጅልባባችሁ ያስፈትኗችኋል፡፡ ከፈተና 30 ደቂቃ በፊት መገኘት እና ፈተና ከተጀመረ ኋላ እስከ 45 ደቂቃ ድረስ መቀመጥ ግዴታ ስለሆነ በግዜ መገኘት ትእግስት አድርጋችሁ መቆያታችሁን አትዘንጉ፡፡ ወደ መፈተኛ ክፍል ስትገቡ ADMISSION CARD ፣ ማንነጽን የሚገልጽ መታወቂያ ፣ እስራስ ፣ ላጲስ እና መቅረጫ ውጭ (የእጅ ሰዐትም ቢሆን) ይዛችሁ አለመግባታችሁን አረጋግጡ፡፡ * ምግብ ከዩኒቨርሲቲው የምትመገቡ ምሳ ከ5፡30 እስከ 7፡00 ፣ እራት ከምሽቱ 12፡30 እስከ 2፡00 እንዲሁም ቁርስ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 2፡00 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በሰዐታችሁ ተገኝታችሁ መመገባችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ምግቡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ሊሆን ቢችልም የሚታማ አይነት ምግብ ስላልሆነ ብትመገቡት አትጎዱም ይልቅ ወስፋታችሁ ይከፈት ዘንድ ከታች የዘረዘርኩላችሁን ደረቅ ምግቦች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው፡፡ ካፌ ከፍላችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑ ከሆነ ደግሞ ምግብ ሊያልቅ ስለሚችል ከሁሉም በፊት ቀደም ብላችሁ በመገኘት ምግብ ማዘዝ ይኖርባችኋል፡፡ * ከሁሉም በላይ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር የሰላት ወቅት ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ መሳጂዶች ላይኖሩ ስለሚችል ዲስኮ(ደቂቃ ብቻ የሚቆጥር መዘነጫ ያልሆነ የእጅ ሰዐት) መያዝ እና የሰላት አውቃቶችን እና የቂብላ አቅጣጫን ግቢ ከመግባታችሁ በፊት ማረጋገጥ ተመራጭ ነው፡፡ ለፈጅር ሰላት ለመነሳት ብቸኛው መፍትሄ በግዜ መተኛት ስለሆነ ከአልባሌ መዝናኛ ቦታዎች ራስን ማራቁ ይመረጣል፡፡ የተፈታኙ ብዛት ከፍተኛ በሆነበት ዩኒቨርሲቲ ብዛት ያለው ጀማዐ ሊከለከል ስለሚችል ለደህንነታችሁ ሲባል እናንተ ብሎክ ጋር ካሉ ተማሪዎች ጋር ብቻ ባዶ በሆኑ ዶርሞች ወይም ከዶርም አጠገብ በሚኖረው ግሪን ኤሪያ ላይ ብትሰግዱ የተሻለ ነው፡፡ * ዶርም ውስጥ ሁሉም ተማሪ የየግሉ ሎከር ስለሚኖረው ተመሳሳይ መክፈቻ በመይገኝለት የጋን ቁልፍ መቆለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡ * ተማሪዎች ሰብሰብ ብለው ከሚያመሹባቸው ቦታዎች ራስን ማራቁ ከደህንነት በተጨማሪ በአቻ ግፊት ምክንያት ከሚመጡ ፈሳዶች ይከላከላል፡፡ በተረፈ በሚኖራችሁ ትርፍ ግዜ መጽሀፍ ማንበብ ከድብርት ሙድ ውስጥ ያወጣችኋል፡፡ * በፈተና የመጭሻ ቀን በየቦታው የቡድን ጸቦች ስለሚኖሩ ከዶርም አካባቢ ራቅ በማለት ራሳችሁን የምትጠብቁበት ቦታ ብትሆኑ እና በየትኛውም አይነት ጸብ እጃችሁን ከማስገባት መቆጠብ ይኖርባችኋል፡፡ * ካልተመደባችሁበት ብሎክ እና ወንዶች ወደሴቶች ዶርም ሴቶች ወደወንዶች ዶርም መሄድ ካለማወቅ ከሚፈጠሩ ምናልባትም ቅጣታቸው ከፍ ያለ ሊሆን ከሚችሉ ስህተቶች ውስጥ ነው፡፡ * ለማንኛውም ፈታኝ ፣ ጥበቃ ፣ የስራ ሀላፊ በተለይ ለማንኛውም ከጸጥታ አካላት ለሚመጣ ትእዛዝ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይኖርባችኋል፡፡ * ዳቦ ፣ ነጠላ ጫማ እና ፈሳሽ ምግቦች ሱቅ ላይ ስለሚገኙ ባትሸከሙ… * ልትይዟቸው የሚገቡ … 1 ታጣፊ የኪስ መስገጃ እና በመጠኑ አነስ ያለ ቁርዐን(ብዙ ተፈታኝ የሚዘነጋቸው) 2 በትርፍ ግዜ ሊነበቡ የሚችሉ አጠር አጠር ያሉ አዝና እና አስተማሪ መጽሀፍት(ሁለት መጽሀፍ በቂ ነው) 3 የ ATM ማሽን ያሉባቸው ቦታዎች በጸጥታ እና በንብረት ጥበቃ ጉዳይ ዝግ ሊሆኑ ስለሚችሉ ለዝርፊያ የሜጋልጣችሁን ቢበዛ እስከ 1000 ብር ካሽ 4 የምትመገቡት ምግብ መላመዱ ሊከብዳችሁ እና እንደ ቤት ላይሆን ስለሚችል ከቤት የተዘጋጁ ደረቅ ምግቦችን እና የታሸጉ ምግቦችን(ለውዝ ቅቤ ፣ ማርቤላ) መያዝ 5 ፍተሸ ሰአት እንዳትቸገሩ ከዪኒፎርም ውጭ ሁለት ተቀያሪ ልብስ ብቻ መያዝ 6 ማንነትን ሊገልጽ የሚችል መታወቂያ (የትምህርት ቤት ፣ የቀበሌ ፣ ብሄራዊ መታወቂያ) 7 የሻንጣ ጋን ቁልፍ(ትንሿን ብቻ) 8 ለፍተሸ ምቹ የሆነ ንብረታችሁን በሙሉ በትክክል ሊይዝ የሚገባ ሻንጣ ወይም ቦርሳ 9 የሰላት እና ሌሎች ግዜያችሁን አብቃቅታችሁ ለመጠቀም ዲስኮ ሰዐት መያዝ 10 ለሴቶች የወር አበባ መቆጣጠሪያ(ሞዴስ) 11 የታዘዘላችሁ መድሀኒት ካለ እስከነማዘዣ ወረቀቱ ይዛችሁ መገኘት ባትይዟቸው የሚመረጡ እና እንዳትይዟቸው የሚከለከሉ 1 በጠንካራ ማይካ ወይም ፕላስቲክ ፣ በጠርሙስ እና በብረት የታሸጉ ማንኛውም አይነት ነገሮች 2 እንደ በሶያሉ ዱቄት ይዘት ያላቸው ምግብ ነክ ነገሮች ጋር አደገኛ እጾች ስለሚገቡ የጸጥታአካላት ሊያስጥሏችሁ ይችላሉ 3 ጥቅል ሶፍት(ግቢ ውስጥ ባሉ ሱቆች ውስጥ ስለሚገኝ ባትይዙ) 4 ከስክስ ሰፍቲ የወንድም የሴትም ጫማ አላህ ከናንተ ጋር ይሁን፡፡ ጽሁፉን በከፊልም ሙሉውንም ሀሳባችሁንም አድርጋችሁ ለተማሪዎች ማጋራት ትችላላችሁ፡፡ ወንድማችሁ ASD @EthiopianMuslimStudentsUnion @EthiopianMuslimStudentsUnion
إظهار الكل...
ASD AJ LAH

ካነበብኩት…

👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.