cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

House of Peoples' Representatives of FDRE

የህዝብ ተወካይ የህዝብ አገልጋይ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 937
المشتركون
+3824 ساعات
+987 أيام
+69530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት የምክር ቤቱ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል ------------------------- (ዜና ፓርላማ) ስኔ 26 ፣ 2016 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል። ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የሚቀርበውን የበጀት ረቂቅ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል። በተጨማሪም ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጡ ነው የሚሆነው። በዚሁ መደበኛ ስብሰባ ላይም በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 4 4
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ስልክ ፡ 011 113 49 70 ሞባይል፡ +251 911 01 06 06 / +251 912 35 63 92 ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ፕሬስ ሪሊዝ ምክር ቤቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፤ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሚገኙበት 36ኛ መደበኛ ስብሰባውን ይካሂዳል፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 55 (17) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 (3) እና አንቀፅ 92 መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በመደበኛ ስብሰባው በመገኘት በፌዴራል መንግስቱ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (11) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 76 መሰረትም ምክር ቤቱ የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በምክር ቤቱ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

3
ምክር ቤቱ የበጀት ዓመቱን የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ ------------------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 26፣ 2016 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተባባሪ እና አማካሪ ኮሚቴዎች የምክር ቤቱን ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግመዋል፡፡ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ምስራቅ መኮንን ለምክር ቤቱ አስተባባሪ እና የአማካሪ ኮሚቴዎች አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በበጀት ዓመቱ ምክር ቤቱና በስሩ የሚገኙት ቋሚ ኮሚቴዎችም ሆኑ በተለያዩ አደረጃጀቶች በህግ አወጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር፣ የውክልና ስራዎች እንዲሁም የፓርላማ ዲፕሎማሲ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ዶ/ር ምስራቅ ባቀረቡት ሪፖርት ተመላክቷል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በ2016 በጀት ዓመት በምክር ቤቱ ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች ከተመሩ 59 ረቂቅ አዋጆች መካከል 38 ሂደታቸውን ጠብቀው እንዲፀድቁ ስለመደረጉ ጠቁመዋል፡፡ አንዳንድ አዋጆች በጥንቃቄና በዝርዝር መታየት ስለሚኖርባቸው፤ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በስፋት በማሳተፍ ለመመርመር ስላስፈለገ ወደ ቀጣዩ በጀት ዓመት ስለመሸጋገራቸው ነው አፈ ጉባኤው ያስረዱት፡፡ በቀጣይም ምክር ቤቱ የሚያወጣቸው ህጎች በአግባቡ ተፈጻሚ እንዲሆኑና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግሉ ለማስቻል በጥንቃቄ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡ እቅድና ሪፖርት ለምክር ቤቱ በወቅቱ አለመላክ እንዲሁም በቋሚ ኮሚቴ የሚሰጠውን ግብረ መልስ ወስዶ ተግባራዊ ያለማድረግ ችግር ባለባቸው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ላይ በቀጣይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግም አሳስበዋል፡፡ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው በዘንድሮ አመት ምክር ቤቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን፤ በቀጣይም የነበሩትን ክፍተቶች በመሙላት መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል። የ2016 በጀት ዓመት የምክር ቤቱ አጠቃላይ ሪፖርት በነገው እለት ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ የሚጸድቅ ስለመሆኑ የተከበሩ አቶ ታገሰ ተናግረዋል፡፡ (በአበባው ዮሴፍ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 1 1
ምክር ቤቱ 3 ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ ------------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 25 ቀን ፣ 2016 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 35ተኛ መደበኛ ስብሰባው ሁለት ኢሚግሬሽንን የሚመለከቱ ረቂቅ አዋጆች እና በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት በኢትዮጵና በኩዌት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎችም መስኮች ጠንካራ ትስስር ተፈጥሮ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁለቱ ሀገራት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ አላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል በስራ ስምሪት መስክ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና ህጋዊ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት እንዲሁም በኩዌት የሚገኙ ዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ወደ ሁለተኛ ንባብ ተሸጋግሮ አዋጅ ቁጥር 1337/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡ በተመሳሳይ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁም ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1338/2016 ሆኖ በ4 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡ የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ጠንካራ የቅድመ ጉዞ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለውን የተዋጣለት የመረጃ ልውውጥ በማሳለጥ ወንጀለኞችና ህገ ወጦች በሀገርና ህዝብ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ የሚያግዝ ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑንና ሌሎችንም በሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡ የተካተቱ ጉዳዮች ገልጸዋል፡፡ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁም ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1339/2016 ሆኖ በ2 ተቃውሞ በ4 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

8👍 5🏆 4
ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሰት በጀት በጥንቃቄ እንዲመራ አሳሰበ ------------------ (ዜና ፓርላማ)፣ ሰኔ 25 ፣ 2016 ዓ.ም ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት አመት የፌደራል መንግሰት በጀት ለታለመለት ዓላማ ስለመዋሉ እና የህዝብ ተጠቃሚነትን ስለማረጋገጡ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ አሳስቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባው በፌደራል መንግስት የ2017 በጀት አመዳደብና አስተዳደር ዙሪያ ከገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ በዚሁም ወቅት የወጪ ንግድን ከማሳደግ፣ የእዳ ጫናን ከመቀነስ፣ የፕሮጀክቶች አስተዳደርን ከማሻሻል፣ የዋጋ ንረትን ከማረጋጋት፣ የሃብት ብክነትን ከመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ፣ በጀትን በእውቀትና በፋይናንስ አሰራር ከመምራት አኳያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምን ያህል ዝግጁ ነው የሚሉ ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የወጪ ንግድን ከማሳደግ አንጻር በአምራች ኢዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት ይደረጋል ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ የአገሪቱን እዳ ጫና ከመቀነስ አኳያ ባለፉት አምስት አመታት እዳን ከማሰረዝ ጀምሮ በርካታ ክፍያዎችን በመፈጸም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በመሆኑ የውጭ እዳ ጫና እንዲቀንስ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ነው ያስገነዘቡት፡፡ ከፕሮጀክት አስተዳደር አኳያ ችግሮች እንደነበሩና ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ተከታትለው እንደሚያስፈጽሙ እና ሁሉም ተቋማት የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ አገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንደሚያደረግም ተናግረዋል፡፡ በጀቱ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞችን ታሳቢ ስለማድረጉና የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል ስለመታቀዱ ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ፤አጠቃላይ የደመወዝ ማስተካከያ የሚደረገው አገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ መሆኑን እና የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡ የሀብት ብክነትን ከመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ አኳያ ከፌደራል ዋና ኦዲተር ጋር በቅርበት እንዲሚሰሩ የገለጹት አቶ አህመድ ሽዴ፤ በቀጣይም አጠናክረው በመቀጠል ችግር ያለባቸውን ተጠያቂ የማድረግና መልካም አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት ደግሞ እውቅና የመስጠት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ በጀቱ ካለው አጠቃላይ የመልማት ፍላጎት አኳያ ሲታይ በቂ ባይሆንም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሪ እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በየደረጃው ያለው አካል የተመደበውን በቁጠበና በውጤታማነት የመጠቀም ሃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 6 5
Ethiopia and Azerbaijan discussed working together on climate change ------------------- (Parliament News) July 2,2024; Ethiopia and Azerbaijan discussed working together to prevent disasters caused by climate change. The Speaker of the House of Representatives of Ethiopia Honorable Mr. Tagese Chafo discussed with the delegation of Azerbaijan on the issues that can be worked closely to prevent damages caused by climate change. Speaker Tagese explained that Ethiopia is working to prevent climate change as a priority agenda.  He pointed out that many activities have been done in the field of green development and concrete results have been seen. The Minister of Planning and Development of Ethiopia, Dr. Fitsum Asefa, said that many changes have not been seen as Ethiopia is working in the green economy sector to prevent climate change. She said that it is important to strengthen the cooperation between Ethiopia and Azerbaijan in order to achieve sustainable results. Mukhtar Babayev, Minister of Ecology and Natural Resources of Azerbaijan, said that; his country is willing to work in cooperation with Ethiopia on climate change. The minister added that Azerbaijan can share with Ethiopia its extensive experience in the prevention of climate change-related disasters such as droughts, floods and related disasters. Finally, Honorable Speaker Mr. Tagese and the delegation of Azerbaijan together planted saplings in the premises of the Council. For more news follow us on:- Facebook http://www.facebook.com/hoprparliament YouTube https://www.youtube.com/@FDREHOPR Telegram    https://t.me/ParlamaNews twitter   http://twitter.com/fdrehopr Website.  www.hopr.gov.et
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

5
ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ ------------------ (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 25 ፣ 2016 ዓ.ም፤ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በአየር ንበረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን  ለመከላከል በትብብር  እንደሚሰሩ ተወያይተዋል። የሕዝብ  ተወካዮች  ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የአዘርባጃንን ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚህ ወቅት ሁለቱ  ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ተቀራርበው መሰራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የተከበሩ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ  ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ቀዳሚ አጀንዳ አድርጋ እየሰራች እንደሆነ ገለጸው፤ ለዚህ ማሳያም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ በርካታ ተግባራት ተከናውኖ ተጨባጭ ውጤት መታየቱን አስገንዝበዋል። በአየር  ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን በመከላከል የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ኢትዮጵያ  ከአዘርባጃን ጋር በትብብር  ለመስራት እንደምትፈልግም አፈ-ጉባዔው ገልጸዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች በመሆኑ በርካታ ለውጦች አየታዩ መሆኑን ገልጸው፤ ቀጣይነት ያለው ውጤት ለማስመዝገብም የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ትብብር መጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። በአዘርባጃን የኢኮሎጂ እና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ሙክህታር ባባየቭ  በበኩላቸው  አገራቸው በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር  ለመስራት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጸዋል። አዘርባጃን በአየር ንብረት ለውጥ በሚከሰቱ እንደ ድርቅ፣ጎርፍ እና ተያያዥ አደጋዎችን በቅድመ መከላከል ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ለኢትዮጵያ ማካፈል እንደምትችልም ሚንስትሩ አክለዋል። በመጨረሻም የተከበሩ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የአዘርባጃን ልዑካን ቡድን በጋራ በመሆን በምክር ቤቱ ግቢ ውስጥ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አስቀምጠዋል። (በተስፋሁን ዋልተንጉስ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

6🏆 1
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 35ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄዳል --------------------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 24፣ 2016 ዓ.ም፤ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ35ኛ መደበኛ ስብሰባው ነገ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል። ምክር ቤቱ ቀዳሚ ባደረገው አጀንዳው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ይወያያል። በመቀጠል በኩዌት እና በኢትዮጵያ መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ የሚያፀድቅ ነው የሚሆነው። በተጨማሪም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን  እንዲሁም የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 9 2
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 35ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል --------------------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 24 ፣ 2016 ዓ.ም፤ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ35ኛ መደበኛ ስብሰባው ነገ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል። ምክር ቤቱ ቀዳሚ ባደረገው አጀንዳው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ይወያያል። በመቀጠል በኩዌት እና በኢትዮጵያ መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ የሚያፀድቅ ነው የሚሆነው። በተጨማሪም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል። በመጨረሻም የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 3🏆 1
"ከተረጂነት ተላቀን የኢኮኖሚ ነጻነታችንን ልናረጋግጥ ይገባል" ------ የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) -------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 24፣ 2016 ዓ.ም፤ ኢትዮጵያ ከተረጂነት ተላቃ የኢኮኖሚ ነጻነቷን እንድታረጋግጥ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስቴር የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡ የህብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር ፣ ነጻነት እና ሉአላዊነት" በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡ በርእሰ ጉዳዩ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የምክር ቤቱ አባል የተከበሩ ስንታየሁ ኃይለሚካኤል(ዶ/ር) ሲሆኑ፤ እንደ ሀገር በ2030 ዓ.ም ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚያስችል እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የፖሊሲ እቅዱ በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀ መሆኑንና ክልሎችም እንደየአከባቢያቸው ነባራዊ ሁኔታ እቅዱን ተግባራዊ እንደሚያደርጉትም ገልጸዋል፡፡ የተከበሩ ተስፋዬ (ዶ/ር) በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ተረጂነት የሀገራችንን ሉአላዊነት እየተፈታተነ በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ዜጋ በአመለካከትም ሆነ በተግባር ከተረጂነት የሚላቀቅበት ስራ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ "የቀደሙት ጀግኖች አባቶቻችን ያስረከቡንን ነጻ ሀገር የኢኮኖሚ ነጻነታችንን በማረጋገጥ ማስቀጠል ይገባል" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሳቢያ በርካታ ዜጎች ለተረጂነት እንደሚጋለጡ የተከበሩ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጠቁመው፤ እነዚህን አደጋዎች ለመቋቋም የሚያስችል ውስጣዊ አቅም ማጎልበትና ስርዓት ማበጀት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም በሀገሪቱ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ አምራች ሀይል እንዲሁም ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየውን የተሳካ አፈጻጸም በመጠቀም በሀገሪቱ ስር እየሰደደ የሄደውን የተረጂነት እሳቤ መለወጥ እንደሚገባ ነው የመንግስት ተጠሪው ያሳሰቡት፡፡ ኢትዮጵያን ለተረጂነት ከዳረጋት ጉዳይ ዋነኛው የጸጥታ ችግር በመሆኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ እያንዳንዱ የምክር ቤት አባል በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ተረጋግጦ ከተረጂነት ለመውጣት የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው በሰብኣዊ ድጋፍ ስም ለጋሽ ሀገራት ለአፍሪካም ሆነ ለሀገራችን የሚያቀርቡት ድጋፍ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝንና በቀጣይ ከተረጂነትና ከልመና ለመውጣት በቁጭት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ ላለፉት አራት ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲደረግ የነበረው የህብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የምክክር መድረክ በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡ (በ አበባው ዮሴፍ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 4🏆 2 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.