ar
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

الذهاب إلى القناة على Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

إظهار المزيد
1 878
المشتركون
-124 ساعات
-157 أيام
-5630 أيام
أرشيف المشاركات
​♦️ አመጋገብና ውሃ፦ በፈተናው ጥዋት ቀለል ያለ ቁርስ መመገብን አትርሱ። አእምሯችሁ ንቁ እንዲሆን በቂ ውሃ ጠጡ። ​♦️ የሰዓት እና የፈተና አያያዝ ስልት፦ ፈተናው ሲጀምር መጀመሪያ የምታውቋቸውን ጥያቄዎች በፍጥነት በመስራት በራስ መተማመናችሁን አሳድጉ። በአንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ላይ ከሁለት ደቂቃ በላይ በማባከን ሰዓታችሁን አትጨርሱ። የከበዳችሁን ጥያቄ ምልክት አድርጋችሁ አልፉት፤ ሁሉንም ከሰራችሁ በኋላ ወደ እሱ ትመለሳላችሁ። ​♦️ በሰዓቱ መገኘት፦ ጥዋት ሳይደናገጡና ሳይጣደፉ በሰዓቱ (ከተቻለ 30 ደቂቃ ቀድሞ) በመፈተኛ ጣቢያ መገኘት አእምሮ ሰላም እንዲሆን ያደርጋል። ​🏅 ክፍል ➓፦ መዝጊያ፦ ወደ ድል አደባባይ ሂዱ! ​ውድ አበቦቻችን! ይህ ምናልባትም ከፈተናው በፊት የምንለዋወጠው የመጨረሻው ትልቅ መልዕክታችን ሊሆን ይችላል። እኛ በበኩላችን ሙሉ እምነት ጥለንባችኋል። እናንተ የታሪካችን አዲስ ምዕራፎች ናችሁ። ​ሰኔ 8 (ለ6ኛ ክፍል) እና ሰኔ 11 (ለ8ኛ ክፍል) ወደ ፈተና ክፍሉ ስትገቡ፣ ትከሻችሁን ቀና አድርጋችሁ፣ ፈገግ ብላችሁ፣ በፈጣሪ ስም ተማምናችሁ ግቡ። ይህንን ያህል የለፋችሁለት ስኬት በእጃችሁ ላይ ይወድቃል። ​የስኬት ቃል ኪዳን፦ "ያለፈውን ጊዜ በሚገባ ተጠቅሜያለሁ፤ አሁንም ያለኝን ጊዜ እጠቀማለሁ። ፈጣሪዬን አምኜ የላቀ ውጤት አመጣለሁ!"መልካም የፈተና እና የድል ቀናት ይሁኑላችሁ! እናንተ የነገዎቹ አሸናፊዎች ናችሁ! 🏆 ያ አላህ ተፈታኝ ተማሪዎቻችንን በድል አጅባቸው! አሚን። 🤲 ​ያ አላህ! ያ ረብ! 🤲 ​እነዚህ የነገው ንጋት ብሩህ ፀሐዮች የሆኑት ውድ ተማሪዎቻችን ላለፉት ዓመታት የለፉበትን ድካም ከንቱ አታድርግባቸው። በፍርሃት ፈንታ ፍጹም መረጋጋትን በልባቸው ውስጥ አስፍር። ​ያ አላህ! በፈተናው ዕለት አእምሯቸውን አብራው፤ ማህደረ-ትውስታቸውን ክፈትላቸው። ያጠኑትን ነገር ሁሉ በፈተናው ወረቀት ላይ በትክክለኛው ሰዓት እንዲያስታውሱት ቀናውን መንገድ ምራቸው። ብዕሮቻቸውን ወደ ትክክለኛው መልስ አቅናላቸው። ​ፈጣሪ ሆይ! ከፈተናው አዳራሽ በታላቅ ድልና በፈገግታ እንዲወጡ አድርጋቸው። የወላጆቻቸውን ልብ በደስታ አርስ፤ የትምህርት ቤታቸውን እና የአስተማሪዎቻቸውን ድካም በላቀ ውጤት አጅበው። የወደፊት ጉዟቸውን የከፍታና የብርሃን ማማ አድርገው! ​አሚን! ያ ረበል ዓለሚን! 🤲 ══════════════ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

​🎯 የክብር ዘመቻው የመጨረሻው 10 ሜትር፦ ከጭንቀት ወደ ንግስና!ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨ ​🔶 ክፍል ❶፦ መግቢያ፦ ለውድድር ሳይሆን ለታሪክ የተፈጠራችሁ የነገው አበቦች! ​ይህ ታላቅ ዕለት የውድድር መድረክ ሳይሆን፣ እናንተ ለታሪክ የተፈጠራችሁ ድንቅ ትውልድ መሆናችሁን ለዓለም የምታበስሩበት የክብር መጀመሪያ ነው! ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ል ላይ ቆመን ወደፊት ስንመለከት፣ ወደዚያ ታላቅ የድል አደባባይ ለመድረስ የቀሩን ቀናት ከ10 አይበልጡም። የ6ኛ ክፍል ሰኔ 8፣ 9 እና 10፤ የ8ኛ ክፍል ደግሞ ሰኔ 11 እና 12 የውሳኔ ቀናቶቻችሁ ናቸው። ይህ የሚኒስትሪ ፈተና እናንተን ለመመዘን ወይም ለማስፈራራት የሚመጣ ጠላት ሳይሆን፣ ለአመታት በክፍል ውስጥ ያፈሰሳችሁትን የትጋት ላብ፣ ያደራችሁበትን የሌሊት ጥረት እና የወላጆቻችሁን ተስፋ በታላቅ ውጤት የምታክሱበት፣ የታላቁ ስኬታችሁ ባለቤት የምትሆኑበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ​ከፊት ለፊታችሁ የሚጠብቃችሁ ፈተና ፍርሃትን ሳይሆን ስኬትን የሰነቀ፣ የትላንት ጥረታችሁ ዛሬ አብቦ ነገ ፍሬ የሚያፈራበት የከፍታ ማማ ነው። እናንተ የምድር ጨው፣ የሀገር ኩራት እና የነገዋ ማራኪ ማለዳ ናችሁ! ይህ መመሪያ ለእናንተ የተዘጋጀ የመጨረሻው ስልታዊ የድል ጎዳና ነው፤ እንደ ሰይፍ የሳለ፣ በአላህ ፍቃድ እንደ ሚሳኤል ያለ ስህተት ግቡን የሚመታ። ይህንን የመጨረሻ 10 ሜትር በልበ-ሙሉነት፣ በፈገግታ እና በድል አድራጊነት እንዴት እንደምትሻገሩት እነሆ በተግባር የተፈተኑ መመሪያዎች። ​📚 ክፍል ❷፦ የቀሩትን 10 ቀናት "መጨቅለቅ" (The Ultimate Crunch Time) ​ጊዜው የሰከንድ ሳንቲሞች የሚቆጠሩበት ወርቃማ ወቅት ነው። አሁን አዲስ መጽሐፍ የምታገላብጡበት ሳይሆን፣ የነበራችሁን እውቀት የምታጠቁሩበት ጊዜ ነው። ​◆ የጊዜ አጠቃቀም (Time Compression): የቀሩትን ቀናት በሰዓታት ከፋፍሏቸው። በእያንዳንዱ ሰዓት ላይ ምን እንደምታነቡ ግልጽ እቅድ ይኑራችሁ። ​◆ የአንበሳው ድርሻ ለዋናው ርዕስ: ከፍተኛ ማርክ ሊያስገኙ የሚችሉ ዋና ዋና አርዕስቶችን ለይታችሁ አጥኑ። ​◆ ትኩረትን ሰብሰብ ማድረግ: ማህበራዊ ሚዲያ እና ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮችን ለነዚህ 10 ቀናት በቁልፍ አስቀምጧቸው። ታላቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን እንደተናገረው፦ ​"በጣም ብልህ ስለሆንኩ ሳይሆን፣ ከችግሮች ጋር ረዘም ላለ ጊዜ አብሬ ስለማቆይ ነው!" አሁን ካጠኑት ርዕስ ጋር ብቻ አብሮ የመቆያ ጊዜ ነው። ​🔄 ክፍል ❸፦ የክለሳ ጥበብ እና የሞዴል ፈተናዎች ስልታዊ ውጊያ ​ማንበብ ብቻውን አይበቃም፤ ያነበቡትን ማስታወስና ለፈተናው ማዋቀር የድል ቁልፍ ነው። ​✅ በማጠቃለያ መክለስ (Active Recall): የያዛችኋቸውን አጫጭር ማስታወሻዎች (Summary Notes) ብቻ በዓይን እያነበቡ በፍጥነት መሮጥ። ​✅ የሞዴል ጥያቄዎች ጋጋታ: ላለፉት ጥቂት ወራት የተሰጡ የሞዴል ፈተናዎችን እና ያለፉት ዓመታት የሚኒስትሪ ጥያቄዎችን ሰዓት እያዩ መስራት። ይህ ፈተናው ላይ የሚመጣውን ድባብ በጭንቅላታችሁ ውስጥ አስቀድሞ ይቀርጻል። ​✅ ስህተትን ማረሚያ ደብተር: በሞዴል ጥያቄዎች ላይ የተሳሳታችሁትን ነጥብ ደግማችሁ እዩት። ስህተት አሁን ሲታረም ለፈተናው ዕለት ትልቅ ስጦታ ይሆናል። ​🧠 ክፍል ❹፦ በራስ መተማመን እና በአላህ መመካት (Effort + Trust) ​በራስ መተማመን የሚመጣው ካለምክንያት አይደለም። ለአመታት ካፈሰሳችሁት ላብ፣ ካደራችሁበት ሌሊት እና ካደረጋችሁት ከፍተኛ ጥረት የሚቀዳ ነው። ​🔶 ከትጋት በኋላ መመካት፦ ሙሉ አቅማችሁን አውጥታችሁ ካጠናችሁ፣ ከለፋችሁና ከደከማችሁ በኋላ፣ በራሳችሁ ጥረት ላይ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ። ​🔶 ቀሪውን ለባለቤቱ መስጠት፦ ሰበቡን (ምክንያቱን) በሚገባ ካደረሳችሁ በኋላ፣ ቀሪውን ነገር ሙሉ በሙሉ በአላህ ላይ ጣሉት (ተወኩል አድርጉ)። ጥረታችሁን አምኖ ፈጣሪ ላይ የተደገፈ ተማሪ መቼም አይወድቅም። ያኔ ፍርሃት ቦታውን ለውስጥ ሰላም ይለቃል። ​🛡️ ክፍል ❺፦ የጭንቀትና የውጥረት ሚሳኤል መከላከያ (Psychological Armor) ​ፈተናው ሲቃረብ የልብ ትርታ መጨመርና "ሁሉንም ነገር የረሳሁት መሰለኝ" የሚል ስሜት መፈጠሩ ተፈጥሯዊ ነው። ይህ የውሸት ስሜት ነው። ጭንቅላታችሁ መረጃዎችን እያደራጀ መሆኑን ማሳያ እንጂ የመርሳት ምልክት አይደለም። ​♦️ አዎንታዊ ንግግር (Positive Self-Talk): "እችላለሁ! ተዘጋጅቻለሁ! የለፋሁበትን ውጤት አገኛለሁ!" እያላችሁ ለራሳችሁ ንገሩ። ​♦️ የኢማሙ አሕመድ ድንቅ ምክር: ታላቁ ሊቅ ኢማሙ አሕመድ የተረጋጋ አእምሮ ስላለው ስኬት ሲናገሩ፦ ​❝በጎ ነገርን አስብ፤ ሁልጊዜም በበጎ ነገር ላይ ትሆናለህ።❞ ጭንቀትን በአዎንታዊ አስተሳሰብ አሸንፉት። ​♦️ ከአሉታዊ ሰዎች መራቅ: "ፈተናው ይከብዳል" የሚሉ፣ ፍርሃትን የሚዘሩ ጓደኞችን ለነዚህ ቀናት በሩቁ በሏቸው። አሁን የሚጠቅማችሁ ብርታትና ተስፋ ብቻ ነው። ​🕋 ክፍል ❻፦ የሰበብ ማድረስ ትርጉም (የአላህ ቃል ማጠናከሪያ) ​ሙስሊም ተማሪዎችም ሆናችሁ የሌላ እምነት ተከታዮች፣ የሰው ልጅ ግዴታ መጣርና መጣር ብቻ ነው። ውጤቱን የሚወስነው ግን ፈጣሪ ነው። አላህ በቁርዓኑ እንዲህ ይላል፦ ❝​...በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፤ አላህ ትዕዛዙን አድራሽ ነው...❞ (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ፡ 3) ​እናንተ ሰበቡን አድርሱ፤ ቀሪውን ለፈጣሪ ተዉት፣ ፍጹም ሰላምና መረጋጋት ያቅፋችኋል። ​🤲 ክፍል ❼፦ የዒባዳ፣ የዱዓ እና የወላጆች ምርቃን ኃይል ​እውቀት የፈጣሪ ስጦታ ነው፤ ያንን ስጦታ ደግሞ በዱዓ እና በጸሎት እንለምነዋለን። የወላጆቻችሁ ምርቃን ደግሞ የተዘጋውን በር ሁሉ የመክፈት ምስጢራዊ ኃይል አለው። ​◆ በዒባዳ መበርታት: ፈርደ ሰላቶቻችሁን በወቅቱ ስገዱ፤ በሱጁድ ላይ እውቀትንና መረጋጋትን ለምኑ። ​◆ የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰልም) መመሪያ: የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ ​❝ለአንተ የሚጠቅምህን ነገር ላይ ጉጉ ሁን (ትጋ)፤ በአላህም ታገዝ፤ አትስነፍም!❞ (ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2664) ​◆ የወላጆች ዱዓ: ዛሬውኑ ወደ ውድ ወላጆቻችሁ ሂዱና ዱዓና ምርቃታቸውን ለምኑ። የወላጆች ዱዓ በቀጥታ ተቀባይነት አለው፤ መንገድን ያቀናል፣ አእምሮን ይከፍታል። ​💤 ክፍል ❽፦ በቂ እረፍት እና የእንቅልፍ ወሳኝነት (The Brain Recharge) ​ብዙ ተማሪዎች የሚሳሳቱበት ትልቁ ስህተት ሌሊቱን ሙሉ ባለመተኛት አእምሯቸውን ማድከማቸው ነው። የተዳከመ አእምሮ ፈተና ላይ መረጃዎችን ማውጣት አይችልም። ​✅ ከ6-8 ሰዓት እንቅልፍ: በእነዚህ 10 ቀናት ውስጥ በተለይም በፈተናው ዋዜማ በቂ እንቅልፍ መተኛት ግዴታ ነው። ​✅ የአንጎል ሳይንስ: እንቅልፍ ስትተኙ ያጠናችሁት ነገር ከአጭር ጊዜ ማህደረ-ትውስታ ወደ ረጅም ጊዜ ማህደረ-ትውስታ ይሸጋገራል። ​✅ የኢብኑ ተይሚያህ ድንቅ ጥቅስ: ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ ስለ ነፍስና አካል እረፍት ሲናገሩ፦ ​"ነፍስ እረፍት ስታገኝ ትበረታለች፤ ስትደክም ግን ትጠፋለች።" አካላችሁንና አእምሯችሁን በቂ እረፍት በመስጠት አድሱት። ​📝 ክፍል ➒፦ የፈተና ዕለት ተግባራዊ ስነ-ስርዓት (Exam Day Readiness) ​♦️ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፦ የእርሳስ፣ የላጲስ፣ የመቅረጫ እና የመግቢያ ካርዳችሁን (Admission Card) በዋዜማው ምሽት አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ።

ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER & Creator ✅ Document Scanner ✅ Group PDF files together ✅ Table of contents ✅ Merge
ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER & Creator ✅ Document Scanner ✅ Group PDF files together ✅ Table of contents ✅ Merge multiple PDFs ✅  Split PDF ✅  Add watermark ✅  Images to PDF ✅  PDF to Image ✅  Lock PDF ✅  Unlock PDF ✅  Create Bookmarks ✅  Search  PDFs ✅  Dark and light mode ለጥናት መዝገበ ቃላት( Dictionary ) ሲያስፈልጎት የትም ሳይሄዱ እዛው Flex PDF Reader app ላይ ማግኝት ይችላሉ።    ✅ አማርኛ to English    ✅ English to አማርኛ    ✅ English to English  Dictionary

Hello world በProgramming አለም ውስጥ "Hello, World!" ማለት ብዙ ሰው አዲስ የprograming language መማር ሲጀመር ለመጀመሪያ ጊዜ ስክሪን ላይ እንዲታይ የሚደረግ ቀላል ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮግራም በጣም ትንሽ እና ቀላል ቢሆንም በፕሮግራሚንግ ውስጥ ብዙ ጥቅም አለው። ⚫ ቋንቋውን ለመፈተሽ (Syntax Check): አንድን አዲስ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ስንማር የቋንቋው አጻጻፍ ስልት (Syntax) እንዴት እንደሚሰራ ለማየት ይረዳል። ⚫ Environment Setup ኮድ የምንጽፍበትና የምናስነሳበት ሶፍትዌር (IDE/Compiler) በትክክል መጫኑንና መስራቱን ማረጋገጫ ነው። ⚫ ለጀማሪዎች በራስ መተማመንን ለመስጠት አንድ ጀማሪ ፕሮግራመር ኮድ ጽፎ ስክሪን ላይ ውጤት ሲያይ የሚሰማው ደስታ ለቀጣዩ ትምህርት ተነሳሽነት ይፈጥርለታል። የቃሉ መነሻ Brian Kernigan እ.ኤ.አ. በ1972 የመጀመርያውን የC ፕሮግራሚንግ መፅሃፍ ሲፅፍ ለምሳሌነት መጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ይህም coding ስትጀምሩ ቀላል እንዲሆንላችሁ hello world መፃፍ ትለማመዳላችሁ ከዛ ቀስ እያላችሁ በroad map ትላልቅ ስራዎችን መስራት ትችላላችሁ። የhello world አፃፃፍ እንደየ programming language አይነት ይለያያል። ለምሳሌ ✔️ በC++  std::cout << "Hello World!"; ✔️ በJava  System.out.println("Hello, World!") ✔️ በC  printf("Hello World!"); ✔️ በPython  print("Hello World") ✔️ በJavaScript. console.log("Hello, World!"); ✔️ በPHP  echo "Hello World!"; ✔️ በC#, Console.WriteLine("Hello World!"); ✔️ በFortran  print *, "Hello, World" ✔️ በRuby  puts "Hello World" ✔️ በAda  Put_Line("Hello World!"); Ok ✔️ በPhp  <? php echo '<p>Hello World</p>'; ?> ነገር ግን hello worldን በተለምዶ እንጠቀመዋለን እንጂ ቃሉ ቢቀየርም ችግር የለውም። ✍️ Comment ላይ በተመቻቸው language code ፅፋችሁ ምን እንደሚያወጣ (Output) ሌሎች ይገምቱ። ©️

Hello world በProgramming አለም ውስጥ "Hello, World!" ማለት ብዙ ሰው አዲስ የprograming language መማር ሲጀመር ለመጀመሪያ ጊዜ ስክሪን ላይ እንዲታይ የሚደረግ ቀላ
Hello world በProgramming አለም ውስጥ "Hello, World!" ማለት ብዙ ሰው አዲስ የprograming language መማር ሲጀመር ለመጀመሪያ ጊዜ ስክሪን ላይ እንዲታይ የሚደረግ ቀላል ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮግራም በጣም ትንሽ እና ቀላል ቢሆንም በፕሮግራሚንግ ውስጥ ብዙ ጥቅም አለው። ⚫ቋንቋውን ለመፈተሽ (Syntax Check): አንድን አዲስ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ስንማር የቋንቋው አጻጻፍ ስልት (Syntax) እንዴት እንደሚሰራ ለማየት ይረዳል። ⚫Environment Setup ኮድ የምንጽፍበትና የምናስነሳበት ሶፍትዌር (IDE/Compiler) በትክክል መጫኑንና መስራቱን ማረጋገጫ ነው። ⚫ለጀማሪዎች በራስ መተማመንን ለመስጠት አንድ ጀማሪ ፕሮግራመር ኮድ ጽፎ ስክሪን ላይ ውጤት ሲያይ የሚሰማው ደስታ ለቀጣዩ ትምህርት ተነሳሽነት ይፈጥርለታል። የቃሉ መነሻ Brian Kernigan እ.ኤ.አ. በ1972 የመጀመርያውን የC ፕሮግራሚንግ መፅሃፍ ሲፅፍ ለምሳሌነት መጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ይህም coding ስትጀምሩ ቀላል እንዲሆንላችሁ hello world መፃፍ ትለማመዳላችሁ ከዛ ቀስ እያላችሁ በroad map ትላልቅ ስራዎችን መስራት ትችላላችሁ። የhello world አፃፃፍ እንደየ programming language አይነት ይለያያል። ለምሳሌ ✔️በC++  std::cout << "Hello World!"; ✔️በJava  System.out.println("Hello, World!") ✔️በC  printf("Hello World!"); ✔️በPython  print("Hello World") ✔️በJavaScript. console.log("Hello, World!"); ✔️በPHP  echo "Hello World!"; ✔️በC#, Console.WriteLine("Hello World!"); ✔️በFortran  print *, "Hello, World" ✔️በRuby  puts "Hello World" ✔️በAda  Put_Line("Hello World!"); Ok ✔️በPhp  <? php echo '<p>Hello World</p>'; ?> ነገር ግን hello worldን በተለምዶ እንጠቀመዋለን እንጂ ቃሉ ቢቀየርም ችግር የለውም። ✍ Comment ላይ በተመቻቸው language code ፅፋችሁ ምን እንደሚያወጣ (Output) ሌሎች ይገምቱ። @bighabesha_softwares

ጠፍተሃል የሚል እንጂ የዳታ ጥቅል (ፓኬጅ) የሚልክ የለምስ‼️ 😂

Google Drive ብቻ ስልካችሁ ላይ በመጫን ⚫Google slides ⚫Google sheets ⚫Google docs እንዲሁም ማንኛውንም hardcopy document scan ማድረግ እንደምትችሉ ታውቃ
Google Drive ብቻ ስልካችሁ ላይ በመጫን ⚫Google slides ⚫Google sheets ⚫Google docs እንዲሁም ማንኛውንም hardcopy document scan ማድረግ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ? @bighabesha_softwares

ChatGPT PowerPoint ላይ ተካቷል። PowerPoint ላይ slide ለመስራት ChatGPTን መጠቀም ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ PowerPoint ከከፈታችሁ በኋላ Insert ላይ ትገባላችሁ።
ChatGPT PowerPoint ላይ ተካቷል። PowerPoint ላይ slide ለመስራት ChatGPTን መጠቀም ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ PowerPoint ከከፈታችሁ በኋላ Insert ላይ ትገባላችሁ። ከዛ Get Add-ins የሚለውን ትመርጣላችሁ። Search bar ላይ ChatGPT ብላችሁ search ታደርጉና add ታደርጉታላችሁ። Add ካደረጋችሁት በኋላ Home ላይ ስትገቡ ከላይ በቀኝ በኩል ChatGPTን ታገኙታላችሁ። እሱን በመክፈት Login አድርጋችሁ በቀላሉ prompt በመፃፍ slide እንዲሰራላችሁ ማድረግ ትችላላልችሁ። @bighabesha_softwares

ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨ ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ
+1
ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨ ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበትን ጊዜ በይፋ አሳውቋል። ​ትምህርት የማህበረሰባችን የውበት እና የእድገት መሰረት ነው። ውድ ተማሪዎቻችን ያካበቱትን እውቀት የሚያሳዩበት እና ወደ ላቀ የህይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት የፈተና ቀናት እንደሚከተለው ተወስነዋል፦ ​📌 የፈተና ቀናት፦ 📚 ​የ6ኛ ክፍል ፈተና፦ ሰኔ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ል የሚሰጥ ሲሆን 📚 ​የ8ኛ ክፍል ፈተና፦ ሰኔ 11 እና 12 ቀን 2018 ዓ.ል ይሰጣል! ​📊 የዘንድሮው ዝግጅት በቁጥር፦6ኛ ክፍል፦ 84,882 ተማሪዎች በ199 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። ​8ኛ ክፍል፦ 86,808 ተማሪዎች በ201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። ​💡 ለወላጆች እና ለተማሪዎች፦ለተማሪዎች፦ እውቀት መፈለግ እና መትጋት ትልቅ ክብር አለው። አላህን በመፍራት፣ በዱዓ፣ በራስ መተማመን እና በጽናት ተዘጋጁ። ድል የናንተ ነው! 📚🤲 ​ለወላጆችና፦ ልጆቻችን የነገ ተስፋዎቻችን ናቸው። በዚህ የፈተና ወቅት ተገቢውን የሞራል እና የሀሳብ ድጋፍ በማድረግ፣ አእምሯቸው በሰላም እንዲፈተን የበኩላችንን እንወጣ። ፈጣሪ ጥረታቸውን ይባርክ! 🤝❤️ ​ለሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎቻችን መልካምና የተሳካ የፈተና ወቅት ይሁንላችሁ!═══════════════ ◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች!

የባንክ አካውንታችሁን ከFayda መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የእያንዳንዱን ባንክ link ማስታወስ አይጠበቅባችሁም። ይህን link በመጠቀም የሁሉም ባንኮችን link ማግኘት ትችላላችሁ። https://
የባንክ አካውንታችሁን ከFayda መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የእያንዳንዱን ባንክ link ማስታወስ አይጠበቅባችሁም። ይህን link በመጠቀም የሁሉም ባንኮችን link ማግኘት ትችላላችሁ። https://id.et/connect ጊዜና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ ለወላጅ ዘመዶቻችሁ share አድርጉላቸው። @bighabesha_softwares

📚 የዕለት ተዕለት ስራችንን፣ ትምህርታችንን እና የፈጠራ ጉዟችንን ይበልጥ ለማሳለጥ፤ ልክ ጥምን እንደሚቆርጥ ቀዝቃዛ ውሃ ልብን የሚያረካ አንድ አዲስ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ (Update) ላካፍላችሁ። 📚 ​Google አዲሱን የGemini 3.5 ስሪት ይፋ አድርጓል፤ ይህ ማሻሻያ ዝም ብሎ የቴክኖሎጂ ለውጥ ሳይሆን፣ ጊዜያችንን ቆጥበን የተሻለ ውጤት እንድናመጣ የሚያግዝ ምርጥ አቅም ነው። ሁልጊዜም እንደምናወራው፣ ስኬት የሚገኘው በትክክለኛ እቅድ፣ በዲስፕሊን እና ዘመኑ በሚሰጣቸው መሣሪያዎች አግባባዊ አጠቃቀም ላይ ነው። ​ይህ አዲሱ ማሻሻያ በዝርዝር ምን አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል? ​1. Gemini 3.5 Flash — መብረቃዊ ፍጥነት ​ይህ አዲሱ ስሪት ከመቼውም ጊዜ በ4 እጥፍ የፈጠነ ነው። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ለምሳሌ ረጅም ፅሁፎችን እና ማስታወሻዎችን ለማንበብ፣ ውስብስብ የሆኑ የኮዲንግ (Coding) ስራዎችን ለመስራት ወይም ትላልቅ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ተንትኖ ለማውጣት ስንፈልግ፣ በሰከንዶች ውስጥ ጥራት ያለው ምላሽ በመስጠት ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ​2. Agentic Power — ከንግግር አልፎ ወደ ተግባር ​እስካሁን የነበረው የAI አጠቃቀም በመጠየቅ እና መረጃ በማግኘት ላይ የተመሰረተ ነበር። አሁን ግን Gemini ትዕዛዞችን በተግባር መፈጸም ወደሚችልበት ደረጃ አድጓል። መመሪያውንና ዋና ግቡን ብቻ ከሰጠነው፣ ራሱ አስቦ፣ አቅዶ እና ቅደም ተከተል አውጥቶ ብዙ ደረጃ ያላቸውን ተግባራት (Multi-step tasks) ያከናውንልናል። ይህ ለጥናት እቅድ ዝግጅትም ሆነ ለተደራራቢ ስራዎች ትልቅ እፎይታ ነው። ​3. Gemini Spark — የ24/7 የሥራ አጋራችን ​ይህ የሥራ አካባቢያችንን በራስ-ሰር የሚያቀናጅ (Automate የሚያደርግ) አዲስ ባህሪ ነው። ሳይሰለችና ሳይደክም በቀን 24 ሰዓት ሙሉ የእኛን መርሃ-ግብሮች፣ የይዘት እቅዶች እና ዲጂታል ስራዎች በስርዓት የሚያደራጅ ታማኝ ዲጂታል አጋር ሆኖ ያገለግለናል። ​4. Efficiency — ከፍተኛ አፈጻጸም በትንሽ ጊዜና ወጪ ​ቴክኖሎጂን ስንጠቀም ዋነኛው አላማችን ውጤታማ መሆን ነው። ይህ ማሻሻያ አላስፈላጊ ልፋትን፣ ወጪንና ጊዜን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጠብ፤ ከመቼውም ጊዜ የተሻለና የተሳለጠ አፈጻጸም (High performance) እንድናገኝ ያስችለናል። ​በአጠቃላይ፦ ይህ ቴክኖሎጂ ጥረታችንን ለማገዝ እና ስራዎቻችንን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተፈጠረ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ስለ ማሻሻያው ማውራት ብቻ ሳይሆን ራሳችሁ ገብታችሁ እንድትሞክሩትና በስራችሁ ላይ ያለውን ለውጥ እንድታዩት እጋብዛችኋለሁ። ​ሞክሩት 👉 https://gemini.google.com ​ቴክኖሎጂን በአግባቡ ተጠቅመን፣ በትጋትና በስነ-ስርዓት ስራችንን ወደ ላቀ ደረጃ እናሸጋግር!

አዲስ ለሆናችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ! 👋 ​እኔ Abuki እባላለሁ! የ Full-Stack Web Developer እና የ Abuki Tech CEO ነኝ። በኦንላይን አለም ትምህርት በመስጠትና ጥራት ያላቸውን ላፕቶፖች በአስተማማኝነት በማቅረብ ላይ እገኛለሁ። ​🚀 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦1. የቴክኖሎጂ እና የትምህርት ቻናል በየቀኑ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን፣ ነፃ ኮርሶችን፣ ስኮላርሺፖችን እና ቢዝነስ ነክ ፅሁፎችን አጋራለሁ። ቢቀላቀሉ በእጅጉ ያተርፋሉ! ​2. ጥራት ያላቸው የላፕቶፕ ሽያጭ ከዱባይ በቀጥታ የሚመጡ ላፕቶፖችን በታማኝነት እንሸጣለን። ለራስዎ፣ ለልጆችዎ፣ ለጓደኛዎ ወይም ለድርጅትዎ የሚሆኑ ላፕቶፖችን ሲፈልጉ ማዘዝ ብቻ ነው የሚጠበቅብዎት። ​✨ ከእኛ ሲገዙ የሚያገኙት ልዩ ጥቅሞች፦ነፃ ማድረሻ (Delivery): አዲስ አበባ ውስጥ ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን! ​አስተማማኝ ዋስትና: የ1 ዓመት የሶፍትዌር ዋስትና እና የ3 ሳምንት የመሞከሪያ ጊዜ! ​📍 አድራሻችን፦ መገናኛ፣ ቤተልሄም ፕላዛ 📞 ስልክ፦ 0920808168 💬 በቴሌግራም ለማዘዝ፦ @abukii_tech ​ስራችንን በተግባር መፈተሽ ይችላሉ፤ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን! 🤝 ​👇 ቻናሎቻችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! 📚 የመማሪያ ቻናል፦ @abukiweb 💻 የመሸጫ ቻናል፦ @Abuki_Computer

አዲስ ለሆናችሁ ~ Abuki እባላለሁ።በሞያዬ FullStack Web Developer ነኝ።የተለያዩ የዌብሳይት ስራዎችን እሰራለሁ።የAbuki Tech CEO በመሆን በonline ላይ የ Frontend Webdevelopmnet ትምህርት ለሁለት አመት ገደማ አስተምሬያለሁ።አሁንም እያስተማርኩ ነዉ። ቻናሌም ከሌላችሁ ልጋብዛችሁ የተለያዩ ወቅታዊ የሆኑ፣ ቢዝነስ ነክ፣እና የቴክኖሎጂ ፅሁፎች እለቃለሁ።ነፃ ኮርሶችን፣ስኮላርሺፖችን አጋራለሁ።ብትቀላቀሉ  ታተርፋላችሁ ቢኢዝኒላህ 👉 @abukiweb ~ Abuki  Computer ላይ ላፕቶፖቾ መሸጥ  አንዱ የስራ ዘርፌ ነው። እስካሁን ለበርካታ ወራት በጥራትና በታማኝነት ላፕቶፖችን ከዱባይ ከሚያስገቡ ነጋዴዎች ተረክቤ እሸጣለሁ። አዲስአበባ ያላችሁበት ቦታ ድረስ የዴሊቨሪ/የማድረስ  ስራ አለኝ። ማንኛዉም ላፕቶፕ ከኔ ስትገዙ የአንድ አመት የሶፍት ዌር ዋስትናና ሶስት ሳምንት የመሞከሪያ ግዜ አስተማማኝ ዋስትና እሰጣለሁ። አልሀምዱሊላ ምንም የእምነትም የጥራትም ችግር የለብንም። እዚዉ ቻናል ላይ በየቀኑ የተለያዩ ላፕቶፖች የማጋራችሁ ይሆናል።ለራሳችሁ፣ለልጆች፣ለጓደኛ፣ለድርጅት፣ ለማንኛዉ አይነት አገልግሎት ስትፈልጉ ማዘዝ ብቻ ነዉ። አድራሻዬ በአካል መገናኛ ቤተልሄም ፕላዛ። እንዲዉም በOnline ማዘዝ ከፈለጋችሁ @abukii_tech ወይ ደዉላችሁ መረጃ ለመጠየቅ 0920808168 መጠቀም ትችላላችሁ። በተረፈዉ ስራዬ በተግባር መፈተሽ ትችላላችሁ🤝 ስለመጣችሁ በድጋሚ አመሰግናለሁ። ==== የመማሪያ ቻናል 👉 @abukiweb ==== የመሸጫ ቻናል👉 @Abuki_Computer

1.4K (1400+) ተከታይ ያለውን የBasic Computer Skills የTikTok አካውንታችንን Follow ያድርጉ!! ✅ ተከታዮቹ በርከት ሲሉ በርከት ባሉ የBasic Computer Skills ትምህርቶች በቪድዮ የምንለቅ ይሆናል። ኢንሻአላህ!! 📚 tiktok.com/@basiccomputerskills

​ወደ ስኬት ማማ የሚወስደው ወርቃማው ድልድይ! ​(የሞዴል ፈተና ሚስጥር) ​════════════════ ​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ! ​📚 ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች፣ የነገ ሀገር ተስፋዎችና የዚህ ዘመን የለውጥ ፀሐዮች! ​ይህ መልዕክት ለዛሬ ወይም ለነገ ብቻ ሳይሆን፣ አላህ በሰጠን የዕውቀት ጎዳና ላይ እስካለን ድረስ ዘወትር የሚሰራ እውነተኛ የህይወት ስንቅ ነው። ልባችሁን ሰፋ አድርጋችሁ፣ በአላህ ፈቃድ ሕይወትን የሚያናውጸውን ይህንን ውብ ሀሳብ አጣጥሙት፤ አላህም ማስተዋሉንና ማስተርጎሙን ይክፈትላችሁ። 🤲 ​1. ራስን የመመልከቻው "እውነተኛው መስታወት" ብዙዎቻችን የምንሰናከለው ባለማወቃችን ሳይሆን፣ "አውቃለሁ" በሚል ስሜት ውስጥ ስለሚዘናጋን ነው። ሞዴል ፈተና ማለት የውሸት ካባችንን አውልቆ፣ ትክክለኛውን የእውቀት ደረጃችንን የሚያሳይ ጥርት ያለ መስታወት ነው። ​የድክመት ካርታ፦ ሞዴል ፈተና የትኛው የእውቀት ክምችትህ ላይ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ጠቋሚ መሳሪያ (Compass) ነው። ክፍተቱ ሳይንስ ላይ ነው? ወይስ ቋንቋ ላይ? ዋናው ፈተና መጥቶ ሳይነግርህ በፊት በሞዴል ፈተና እራስን መገምገም ትልቁ ጥበብ ነው። ​2. የስነ-ልቦናው "ሰላምና እርጋታ" (Peace of Mind) ፈተና ማለት እውቀት ብቻ አይደለም፤ የስነ-ልቦና ዝግጅትም ጭምር ነው። ብዙ ተማሪዎች ጎበዝ ቢሆኑም፣ የፈተና ክፍል ሲገቡ ግን ይርበተበታሉ። ​ድንጋጤን ማራቅ፦ ሞዴል ፈተናን በተደጋጋሚ መውሰድ አዕምሮን ከ"አዲስ ነገር" ድንጋጤ ያላቅቀዋል። ልክ ዋናተኛ ውሃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን እንደሚያላምደው፣ እናንተም የፈተና ወረቀት ሲሰጣችሁ ልባችሁ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ እንዲመታ ያደርጋል። ​3. ጊዜን የመግራት ብልሃት ሰዓቱ ሲሮጥ ማየት ያስጨንቃል። ሞዴል ፈተና ግን ከሰዓቱ ጋር አብሮ መጓዝን ያስተምረናል። አንድን ጥያቄ ለመመለስ ስንት ደቂቃ እንደሚያስፈልግህ በደመ-ነፍስ እንድታውቅ ያደርግሃል። ​ጊዜ እንደ ወርቅ ነው፦ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ይባክናል። ጊዜን መግደል አንችልም፤ በአግባቡ ካልያዝነው ግን እሱው ጥሎን ይበርራል። ሞዴል ፈተና ይህንን ውድ ጊዜ እንዴት በብልሃት እንደምትጠቀሙበት መንገዱን ያሳያችኋል። ​4. አዕምሮን ማጎልበትና ማነቃቃት አንድ ስፖርተኛ ለውድድር ከመቅረቡ በፊት ሰውነቱን ያሟሙቃል። ለምን? ብቁ ለመሆን! የኛም አዕምሮ ዝግጅት ያስፈልገዋል። ​የማስታወስ አቅም፦ ሞዴል ፈተና ስትሰሩ፣ አዕምሮአችሁ በመጋዘኑ ውስጥ ያስቀመጠውን መረጃ በፍጥነት ፈልጎ የማውጣት ልምምድ ያደርጋል። መጽሐፍን ዝም ብሎ ደጋግሞ ከማንበብ ይልቅ፣ እራስን መፈተን የማስታወስ ችሎታንና የመረዳት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። ​5. ከስህተት የመማር "ወርቃማው ሚስጥር" ፈተናውን መውሰድ ብቻውን ሙሉ አይሆንም፤ ትልቁ ትምህርት የሚገኘው ከፈተናው በኋላ ነው። ​ስህተትን ማረም፦ በሞዴል ፈተና ላይ መሳሳት ወንጀል አይደለም፤ ስህተትን አለማረም ግን ዋናው ፈተና ላይ ዋጋ ያስከፍላል። ፈተናውን ከጨረሳችሁ በኋላ የተሳሳታችሁትን ጥያቄዎች ለምን እንደተሳሳታችሁ መለስ ብሎ መመርመርና መምህራንን መጠየቅ ለስኬት ዋነኛው ቁልፍ ነው። ​6. በራስ መተማመን እና የድል መንፈስ አንድን ተራራ ከመውጣትህ በፊት፣ የመንገዱን ካርታ የሚያውቅ ሰው ልበ-ሙሉነቱ ልዩ ነው። ​የአሸናፊነት ስሜት፦ በአላህ እገዛ በሞዴል ፈተና ጥሩ ውጤት ስታመጡ፣ ውስጣችሁ "እችለዋለሁ!" የሚል ኃይለኛ ተነሳሽነት ይገነባል። ይህ ስሜት በዋናው ፈተና ቀን እንደ ጋሻ ሆኖ ከጭንቀት ይጠብቃችኋል። ​መረጋጋት (ሰኪና)፦ በደንብ የተዘጋጀ ተማሪ አይጣደፍም። እርጋታው እራሱ ለሌሎች ተማሪዎች ያስቀናል። ይህ እርጋታ የሚመጣው ከቅድመ-ዝግጅት ነው። ​🔥 የልብ መልዕክት ​ሞዴል ፈተናን እንደ "ሸክም" አትዩት። እንደ "ወርቃማ እድል" ቁጠሩት። ዛሬ ላይ ተሳሳቱ፣ ዛሬ ላይ ተደናገጡ፣ ዛሬ ላይ ጊዜ ይለቅባችሁ። ምክንያቱም ዛሬ በአላህ ፈቃድ ማረም ይቻላል! በዋናው ፈተና ቀን ግን ስህተትን ማረም አይቻልም፤ የሚቻለው ውጤትን መቀበል ብቻ ነው። ​ይህንን እድል ተጠቅማችሁ፣ እራሳችሁን አብቅታችሁ፣ ድክመታችሁን አርማችሁ ለድል ብቁ እንድትሆኑ አደራ። ትምህርት የኢባዳ (የአምልኮ) አካል ነው፤ ጠንክሮ መማር ደግሞ "ኢህሳን" (ምርጥ ስራ) ነው። ስኬታችንም ሆነ ጥረታችን ሙሉ የሚሆነው በአላህ እገዛና ቸርነት ብቻ መሆኑን አንዘንጋ። ​🤲 ዱዓ ​ያ የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ሆይ! ይህንን ለወገኖቻቸው፣ ለሀገራቸውና ለራሳቸው ብለው ሌት ተቀን የሚደክሙ ተማሪዎችን ልፋት አንተ ባርክላቸው። ​ጌታዬ ሆይ! በፈተና ሰዓት የመረጋጋትን መንፈስ አውርድላቸው። የረሱትን አስታውሳቸው፣ የከበዳቸውን አቅልላቸው። እውቀታቸው በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን በህይወታቸውም ላይ ብርሃን ሆኖ እንዲፈነጥቅ አድርግላቸው። ​ለወላጆቻቸው የዓይን ማረፊያ፣ ለሀገራቸው የጀርባ አጥንት፣ ለዲናቸውም ጋሻና መከታ አድርገህ ያማረ ውጤትን ወፍቃቸው። አሚን! 🤲 ​📖 ማጠቃለያ (መለኮታዊ ቃል) ​ንግግሬን የምዘጋው ሁሉን በሚያውቀውና ስኬትን ሁሉ በእጁ በያዘው ጌታችን በአላህ ቃል ነው። የሰው ልጅ የሚለፋው ለራሱ ነው፤ ውጤቱንም የሚያገኘው በአላህ ፍቃድ እንደ ልፋቱ ልክ ነው። ​"ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም። ሥራውም ወደ ፊት (በቂያማ ቀን) በእርግጥ ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ዋጋ ይመነዳል።" (ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-41) ​በልበ ሙሉነትና በአላህ ተስፋ ተዘጋጁ! የስኬት ማማ በጌታችን እገዛ እጃችሁ ላይ ነው! ✨━━━━━━━━━━━━✨ 🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Be teachable…… you’re not always right and you don’t know everything!! ✍️ Reshad Ibnu Muzemil
Be teachable…… you’re not always right and you don’t know everything!! ✍️ Reshad Ibnu Muzemil

ለ2018 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ልምምድ ያድርጉ! የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ተፈታኞች ፈተና የሚለማ
ለ2018 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ልምምድ ያድርጉ! የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ አድርጓል። ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ያለውን ሊንክ በመጠቀም፣ User Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Password በሚለው ላይ 1234 በማስገባት በዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት፣ በስልክ እና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሳሪያዎች ማንኛውንም አይነት የኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከነገ ግንቦት 07/2018 ዓ.ል ጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉ ተገልጿል።