cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

DIRE DAWA UNIVERSITY INSTITUTE OF TECHNOLOGY 🇪🇹

Welcome to the official Telegram Channel of Dire Dawa University Institute of technology

إظهار المزيد
Ethiopia7 161Amharic6 839الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
659
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
-330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
Need Assessment for training

Dire Dawa University Research and Technology Transfer Vice President Office would like to collect training needs for 2016 academic year. Here under are list of potential training areas in the aras of research, publication, technology transfer, Indigenous knowledge, and etc. Accordingly, you all are invited to fill this need assessment questionnaire. We appreciate you for taking your time.

የቴክስታይል፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት ሁለተኛዉን ሃገር አቀፍ ኮንፈረንስ አካሄደ፡፡ 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቴክስታይል፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት “Conventional and Advanced Technology in Textile and Fashion Design’’ በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ ኮንፈረንስ ለሁለተኛ  ጊዜ አካሄዷል። በዚሁ ኮንፈረንስ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቴክስታይል፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት ዲን የሆኑት አቶ አማረ ወርቁ  ሲሆኑ በንግግራቸውም ይህ የሃገር አቀፍ አውደ ጥናት   ዋና ዓላማ  ተቋማት ከተቋማት ትስስር ለማጠንከር፣  አብሮ ለመሰራት እና የመተጋገዝ ባህልን ለማሳደግ እንዲሁም በጋራ የሚሰሩ  ምርምሮችም አብሮ ለማስራት መንገድ የሚከፍት  ነው ሲሉ  ገልጸዋል፡፡ አቶ አማረ ወርቁ  ለተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ ካሳሰቡ በኋላ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደረጉ የኢንስቲትዩቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌቱ ግርማን በመጋበዝ ንግግራቸው ዘግተዋል፡፡ አቶ ጌቱ ግርማ በመክፈቻ ንግግራቸው  የቴክስታይል፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት  በኢንስቲትዩቱ ስር ከሚገኙ  ት/ቤቶች አንዱ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ቴክስታይል ምህንድስና እንዲሁም ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ክፍሎችን በመክፈት በመጀመሪያ ድግሪ በማስተማር ላይ ይገኛል ካሉ በኋላ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖጂ ኢንስቲትዩትም ለዚህ ት/ቤት ልዩ ትኩረት በመስጠት የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችን በማሟላት ላይ ይገኛል ሲሉ ገልጻዋል። አቶ ጌቱ ግርማ በተጨማሪ እንደሀገርም ቢሆን መንግስት ቅድሚያ ትኩረት ተሰቷቸው እየተሰሩ ካሉ ኢንዱስትሪዎች መካከል አንዱ የቴክስታይል ዘርፍ በመሆኑ እና ድሬዳዋ የኢንዱስትሪ ከተማ በመሆኗ የቴክስታይ ፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት ከኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር ፈጥሮ ለመስራት ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው ት/ቤቱ በምርምር ፤በማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር  በንቃት እየሰራ በማውሳት ይህን ስራውን በተሻለ ደረጃ ያሳድግለት ዘንድ በዛሬው ዕለት የሚካሄድው የመጀመርያው ዓመታዊ  ሃገር አቀፍ ዓውደ-ጥናት ማካሄዱ  ወሳኝ መሆኑ በመግለጽ ንግግራቸው ቋጭተዋል። በኮንፈረንሱ መርሃ ግብር ተገኝተው የመጀመርያው ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የቀድሞው የEiTEX ሳ/ዳይሬክተር, (ባ/ህ/ዩ)  እና በተለያዩ የስራ ተሳትፎ የሚታወቁትን በአንጋፋነት የሚታወቁትን  ተ/ፕ ዶ/ር አበራ ከጪ ሲሆኑ በንግግራቸው ፕሮግራሙን ለማዘጋጀት ድጋፍ ላደርጉ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ ለዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ኮንፈረንሱን  ላዘጋጀው ት/ቤት   ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል። ተ/ፕ ዶ/ር አበራ ከጪ በዘርፉ በማምረት አቅም ያሉበት ደረጃ፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና ለወደፊቱ ዉጤታማ ለማድረግ ምን መሰራት እንዳለበት በቁልፍ መልዕክታቸው ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ተ/ፕ ዶ/ር አበራ ከጪ በተለያዩ የአለም ሀገራት ያሉ የቴክስታይል ዘርፎችን ዳሰዋል፡፡ የመጀመርያው ዘመናዊ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በድሬዳዋ እንደተከፈተ በማውሳት የእለቱን ቁልፍ መልእክት “ኢትዮጵያ ታምርት” የሚለውን መሪ ቃል በማንሳት እንዴት ታምርት፣ ለማን ታምርት፣እና የራሳችን ሃብት ተጠቅመን  ከማምረት አንጻር የሚደረገውን ርብርብ ከጨርቃጨርቅ ዘርፉ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተለይም ፖሊሲንና ኢንዳስትሪዎችን ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰሩ እንደሆነ ለኮንፈረንሱ ታዳሚዎች ሰፋ ያለ ማብራርያ  ሰጥተዋል። በኮንፈርንሱ አምስት የምርምር ስራዎች ቀርበው ከታዳሚዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስታያየት የተነሱ ሲሆን ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎቹም ሰፋ ያለ ምላሽ እና ማብራርያ ሰጥተዋል። ከዚህ በመቀጠል እንደ አጠቃላይ የቴክስታይል ዘርፉን በተመለከተ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን የማጠቃለያ ሃሳብ ተሰጥቶበታል። በመጨረሻም በአፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች ዲዛይነርነት፣ በዩኒቨርሲቲው በተለያየ ዲፓርትመንት በተዉጣጡ ሞዴሎች፣ እና በት/ክፍሉ መምህራን የፋሽን ሾው ታካሂዷል፡፡ ለፋሽን ሾው ዝግጅትም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ንጉስ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ስፖንሰር አድርገዋል፡፡ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር አዘጋጆችን እና ተሳታፊዎችን አመስግነው ት/ቤቱ ተስፋ የተጣለበት በመሆኑ የሚያስፈልገውን ግባት ለማሟላት ቁርጥኛ መሆናቸውን እና በዝግጅቱ እጅግ ደስተኛ እንደሆኑ  ገልጸዋል። የኮንፈረንሱን የመዝጊያ ንግግር  ያደረጉት የቴክስታይል፣ አፓረል እና ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት ዲ/ን የሆኑት አቶ አማረ ወርቁ በንግግራቸው ለኮንፈረንሱ የምርመር ስራ አቅራቢዎች፣ተጋባዥ እንግዶች፣ ተሳታፊዎች እንዲሁም ዝግጅቱ ያማረ እና የተሳካ እንዲሆን ብርቱ ጥረት ላደረጉ ሁሉም የኮሚቴ አባላት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። በመጨረሻም በዝግጅቱ ለተሳተፉ፣ ከተለያዩ ኢንደስትሪ ለተሳተፉ ፣ በት/ቤታቸው ለሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች እነዲሁም ለፋሽን ሾው ዝግጅት ስፖንሰር ላደረጉት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ንጉስ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ከፍ ያለ ምስጋና በማቅረብ ኮንፈረንሱን ቋጭተዋል፡፡
إظهار الكل...
ማስታወቂያ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የ2015 አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በያላችሁበት ቀድማችሁ የተመደባችሁበትን ዶርሚተሪ ሙሉ መረጃ የሚያሳይ እንዲሁም የተማሪዎቻችንን መጉላላት ለማስቀረት ይረዳ ዘንድ ለዲጂታል መታወቂያ የሚሆን ፎቶ Upload በማድረግ የምትልኩበት ፕላትፎርም/ሲስተም ላይ ለባለ አንድ ካርድ (One Card ID) መታወቂያ አግልግሎት የሚውል ሶፍት ኮፒ ጉርድ ፎቶ መጠኑ 4x3 የሆነ የምትልኩበት ሲስተም ተዘጋጅቷል። በመሆኑም በመጀመርያ ሲስተሙን ለመጠቀም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት ሲስተሙን በመጠቀም የተመደባችሁበትን አስፈላጊውን የዶርሚተሪ መረጃ ማወቅ እንዲሁም ለዲጂታል መታወቂያ ፎቶ በመላክ የመጉላላትን ጊዜ መቀነስ የሚያስችል በመሆኑ ለአጠቃቀም እንዲያመች እንደሚከተለው ይጠቀሙ የዩኒቨርሲቲውን ድህረ-ገጽ https://www.ddu.edu.et/ ላይ መግባት 2. Important Links ስር Dormitory Placement አማራጭ መጫን 3.Sign Upን መጫን 4.በመቀጠል አስፈላጊውን መረጃ እና ጉርድ ፎቶ upload በማድረግ Sign Up ማድረግ 5. Sign Up ስትጫኑ ሲስተሙ ቀጥታ የመገልገያ ስም እና የማለፊያ ሚስጥራዊ ቁልፍ (Username and Password) ይሰጣችዋል 6. በቀጣይ Login በመጫን ሲስተሙ የሰጣችሁን Username and Password በመስጠት Login መጫን 7. ከላይ ያሉትን ሂደቶች ሲጨርሱ your ID has been printed የሚለው በትክክል መምጣቱን ማረጋገጥ 8.ID Card እስኪዘጋጅ Barcode Generate በማድረግ ይጠቀሙ። መጨረሻም My dorm በመጫን የተመደባችሁበትን ዶርሚተሪ ሙሉ መረጃ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩታችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like በማድረግ ይከታተላሉ። Telegram channel: https://t.me/+Wj3iMcceGu1mODc1 Facebook page: https://www.facebook.com/DDUIOT
إظهار الكل...
Dire Dawa | University

Dire Dawa University

أرشيف المشاركات
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.