ኑ እናዝግ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ኑ እናዝግ Official Telegram Page, Created June 30/2022 inbox me 👉 @AzegDotCom
إظهار المزيد4 741
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-247 أيام
-11730 أيام
أرشيف المشاركات
4 741
#ካነበብኩት
ካህሊል ጅብራን አንድ ወቅት እንደዚህ ብሎ ነበር ፦
"ከአንድ ሰው ጋር ለመጋጨት አንድ ደቂቃ በቂ ሊሆን ይችላል።”
" አንድን ሰው ለመውደድም አንድ ሰዓት አስተማማኝ ሊሆን ይችላል።"
" አንድን ሰው ለማፍቀርም አንድ ቀን ብቻዋን በቂ ልትሆን ትችላለች .…....ግን ግን አንድን ሰው ለመርሳት የእድሜ ልክ ጥረት ይጠይቃል"
ከወደዱት ❤️ ያድርጉ #Ethiopia
4 741
በትዳራቹሁ ላይ አደጋ አየፈጠራቹሁ መሆኑን የሚያመላክቱ 10 ነጥቦች።
1. ለባልሽ ሳታሳውቂ ከሌላ ወንድ ገንዘብ የምትቀበይ ከሆነ፤
2. ለሚስትህ ሳታሳውቅ ለሌላ ሴት ገንዘብ የምትሰጥ ከሆነ፤
3. ከትዳር አጋራችሁ ውጭ ወሬ የምታወሩ ከሆነ፤
4. የተላከላችሁን ሜሴጅ የትዳር አጋራችሁ እንዳያይባችሁ ብላችሁ የምታጠፉ ከሆነ፤
5. የትዳር አጋሮቻችሁ ሳይኖሩ እነሱ ባሉበት የማታወሯቸውን ተቃራኒ ፆታ ያላቸውን ሰዎች በለሊት በተለይ አልጋ ውስጥ ሆናችሁ ለረጅም ጊዜ የምታወሩ ከሆነ፤
6. በትዳር አጋራችሁ ፊት ሲደወልላችሁ ስልኩን ለማንሳትና ለማውራት ፈርታችሁ ተደብቃችሁ ወይም ራቅ ብላችሁ በሹክሹክታ የምታወሩ ከሆነ፤
7. ስልክ ቁጥር ሴቭ ስታደርጉ ስም ቀይራችሁ ሴቭ የምታደርጉ ከሆነ፤
8. ከተቃራኒ ፆታ ጋር ሻይ ቡና እያላችሁ እያለ የትዳር አጋሮቻችሁ ሲደውሉ ቦታ ቀይራችሁ ወይም ያላችሁበትን ዋሽታችሁ የምትናገሩ ከሆነ፤
9. ስልክ አውርታችሁ ስትጨርሱ የትዳር አጋሮቻችሁ ከማን ጋ ነው ያወራህ/ያወራሽ ብለው ሲጠይቋችሁ ማንነቱን/ማንነቷን ቀይራችሁ ወይም ዋሽታችሁ የምትመልሱ ከሆነ፤
10. በትዳር አጋራችሁ ላይ ቂም ይዛችሁ ምንም ያልተፈጠረ ለማስመሰል የምትሞክሩ ወይም አፈቅርሀለሁ/አፈቅርሻለሁ የምትሉ ከሆነ፤
እናንተ በትዳራችሁ ላይ አደጋ አየጣላቹሁ ነዎ
ራሳችሁን ስትፈትሹት እንዴት አገኛችሁት?
4 741
ፕሪምየር ሊግ ሊጀምር ነውና ለሚስቶች አንዳንድ ማሳሰቢያ፥-
1) ከነሀሴ እስከ ግንቦት ቴሌቪዥኑ የግሌ ነው በሪሞት ክርክር አልፈልግም፡፡
2) ኳስ እያየሁ በቴሌቪዥኑ ፊትለፊት ወዲያ ወዲህ መመላለስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
3) ሪፕሌይ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡አይቼውም ቢሆን ደግሜ ማየት አለብኝና ለምን ደግመህ ታያለህ እንዳትይኝ፡፡
4) ቲሜ ሲሸነፍ "አይዞህ ያጋጥማል ፥ ቀጣይ ያሸንፋሉ ፥ ኳስ ነው ተረጋጋ" ምናምን ፈጽሞ እንዳትይኝ፡፡
5) ማንኛውም የፍቅር ንክኪ የምፈቅድልሽ በእረፍት ሰአት ወይም ከጨዋታ መጨረሻ ብቻ ነው፡፡
6) እንድንነጋገርበት የምትፈልጊው ጉዳይ ካለ ከኳሱ ጋር በማይጋጭ ሰአት እና ሁኔታ ብቻ እንደማካሂድ እወቂው
7) ኦፍሳይድ ምንድን ነው ብለሽ እንዳትጠይቂኝ
ይገምቱ ይሸለሙ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል
ተጨማሪ መመሪያዎች በቀጣይ ይፋ ይደረጋሉ ፡፡
4 741
#Awesome_people
1. Take away : ምግብ ፡ ላይ ፡ ሚጥሚጣ ፡ አስረዉ ፡ ከጎን ፡ የሚያደረጉ ፡ ምግብ ፡ አብሳዮች።
2.የተቀደደ ፡ ብር ፡ የሚቀበሉ ፡ ወያላዎች።
3.ስታጎርሳቸዉ ፡ ከጉርሻዉጋ ፡ አፋቸዉን Ad just ፡ የሚያደርጉ ፡ ሴቶች፡፡
4.ምንም ፡ ወሬ ፡ ሳያወሩ ፡ ፀጉር ፡ አስተካክለዉ ፡ የሚሸኙ ፡ ፀጉር ፡ ቆራጮች::
5. ሰፈር ውስጥ ፡ በርካሽ ፡ ዋጋ ፡ የሚጣፍጥ ፡ ምግብ ፡ የሚሸጡ ፡ ሰዎች።
6.የማያለቅሱ ፡ ህፃናት።
7.ከማያዉቁት ፡ ሰዉ ፡ ጋር ፡ ጃንጥላ ፡ share ፡ የሚያደርጉ ሴቶች።
8.መንገድ ፡ ላይ ፡ የማይሸና ፡ሀበሻ ፡ወንድ ።
9.ሳያጠቡ ፡ ሳያሰፉ ፡ በልክ ፡ የሚሰፉ ፡ ልብስ ፡ ሰፊዎች።
1 0.ጥሩ ፡ ሽቶ ፡ ተቀብተዉ ፡ Taxi ፡ ውስጥ ፡ ከጎኔ ፡ ቁጭ የሚሉ ፡ ሴቶች።
4 741
#ጥያቄ
አንድ ቆንጆ ሴትን አራት ወንዶች ለትዳር ጠየቁ ። አንዱ ዘፋኝ ነው ፣ አንዱ ወታደር ፣ አንዱ ዓሳ አጥማጅ ፣ አንዱ ዶክተር ነው ።
አንድ ቀን ልጅቷ ወንዝ ዳር ልብስ እያጠበች በአጋጣሚ አዞ ሲመጣ በድንገጤ ወንዙ ወስጥ ወደቀች ። ከዛ ዘፋኙ ቶሎ ብሎ ምርጥ ሙዚቃ መዝፈን ጀመረ ። አዞዎቹ ልጅቷን ትተው ሙዚቃ ለማዳመጥ ከውሃ ወስጥ ወጡ ። ወታደር ተኩሶ ገደላቸው ። ዓሳ አጥማጁ ቶሎ ብሎ ልጅቷን ከወንዝ ውስጥ አወጣ ። ዶክተሩ በጣም ተጎድታ ስለነበረ አከማት ።
ጥያቄ ፦ ልጅቷን ማግባት ያለበት ማነው ?
4 741
#ማስታወቂያ
በእኔ ገጾች ላይ ማስታወቂያ እንዲሰራላቹ የምትልኩ ምእመናን ከክፍያ ይልቅ ጥራቱን አይቼና አረጋግጬ ካልሆነ አላስተዋውቅም:: በምርትና አገልግሎታችሁ የምትተማመኑ መምጣት ትችላላችሁ ::
inbox me @AzegDotCom
4 741
እነዚህ የ13 አመት እድሜ ልጆች ፍቅረኛ አላቸው አሉ . .ጭራሽ ኤክስም አላቸው. . እንደገናም የጎዳቸውም አለ . .ከዛ የጠገናቸውም አለ
ቆይ ምን እየተፈጠረ ነው ? . .
እኔና እናንተ የት ነው ያለነው ?
ፈጣሪየ ሆይ ቶሎ ና 🥹🙄
4 741
#ካነበብኩት
የወርነር ቡፌት ድንቅ አባባሎች...👌
1. ‹‹”ዋጋ” የምትከፍለው ነው፤ “እሴት” ደግሞ የምታገኘው ነው፡፡ ("Price is what you pay. Value is what you get.")
2. ‹‹የዘጠኝ ወር እርጉዝ በማግባት በአንድ ወር የራስህን ልጅ ልትወልድ አትችልም››
3. ‹‹ዛሬ ዛፍ ጥላ ስር የምንቀመጠው የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ ሰው ዛፉን ስለተከለው ነው፡፡››
4. ‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››
5. ‹‹ባልገባህ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት አታድርግ››
6. ‹‹ስጋት ወይም ፈተና የሚመጣው የምትሰራውን ባለማወቅ ነው፡፡››
7. ‹‹በአንድ ገቢ ብቻ ጥገኛ አትሁን፡፡ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ ፍጠር››
8. ‹‹በአሜሪካ ቢዝነስ ቁጭ ብሎ ማሰብ ያልተለመደ ነው፡፡ እኔ ግን ብዙ ጊዚዬን የማጠፋው ቁጭ ብዬ በማሰብ ነው፡፡
9. ‹‹በጣም አስፈላጊው ኢንቨስትመንት በራስህ ላይ የምታደርገው ነው፡፡››
10. ‹‹የማትፈልገውን የምትገዛ ከሆነ የምትፈልገውን ወዲያው ትሸጣለህ፡፡››
11. ‹‹ከመጥፎ ሰው ጋር ጥሩ ውል ማሰር አትችልም፡፡
12. ‹‹ደስተኛ ሰዎች የሚደሰቱት ምርጥ ነገር ስላላቸው አይደለም፡፡ እነሱ የሚደሰቱት ያላቸውን ነገር አክብረውና ወደው ስለያዙ ነው፡፡
13. ‹‹በመኝታህ ሰዓት ገንዘብ ለማግኘት አስበህ አዲስ መላ ካልፈጠርክ እስክትሞት ትሰራለህ፡፡
14. ‹‹አጥፍተህ የቀረህን አትቆጥብ፡፡ ከቁጠባ በኋላ የተረፈህን አጥፋ፡፡››
15. ‹‹ብዝሃነት ወይም ሁለገብ ዕውቀት ከመሐይምነት ይከላከላል፡፡ የሚሰሩትን ለሚያውቁ ትንሽም ቢሆን ስሜት ይሰጣል፡፡
16. ‹‹ታማኝነት በጣም ውዱ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ስጦታ ከርካሽ ሰዎች አትጠብቅ፡፡››
17. ‹‹ያልተለመደ ከሆነ ሰዎች ብዙ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ከመስራት ሊያስቆሙህ ይሞክራሉ፡፡
18. ‹‹በዓለም ላይ ሐይል ያለው ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ነው፡፡
19. ‹‹ሁልጊዜም ሐብት ማግኛ ምርጡ መንገድ ለራስህ ዋጋ መስጠት ነው፡፡
20. ‹‹አነባለሁ፣ አነባለሁ፣ አነባለሁ! በቀን ውስጥ ከአምስት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ አነባለሁ፡፡››
21. ‹‹እርካታ ትልቁን ቢዝነስ ይገድላል፡፡››
22. ‹‹ብዙ በተማርክ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ››
የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? comment አድርጉልን።
4 741
#ካነበብኩት
10 አይነት የሚስቶች ዓይነቶች አሉ
1. ቦክሰኛ ሚስቶች
ባሎቻቸውን ለማስቆጣት ሆን ብለው የሚጣሉ ሚስቶች ናቸው። እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሴቶች ትኩረት ለማግኘት በአብዛኛው በሕዝብ ቦታ ከባል ጋር ለመዋጋት ዝግጁ ናቸው።
2. አለቃ ሚስቶች
እነዚህ ሚስቶች በሙያቸውም ሆነ በንግድ ስራቸው ጥሩ ደሞዝ የሚከፈላቸው ነገር ግን በባሎቻቸው ላይ የገንዘብ አቅም ስላላቸው ብቻ ባለቤታቸውን ያቃልላሉ ።
3. ፖሊስ ሚስቶች
ይህ አይነት በጣም የተለመደ ነው። እነዚህ ሚስቶች ባሎቻቸውን በሄዱበት ሁሉ የሚቆጣጠሩና የሚፈትሹት ናቸው። ባልየው ወደ መጸዳጃ ቤት ሲሄድ እንኳን መልእክቶቹን በፍጥነት ለማየት ስልኩን ያነሳሉ። ባልየው የስልክ ጥሪ ካደረገ ደግሞ እያንዳንዱን ንግግር ለመስማት ከበሩ ጀርባ ይደበቃሉ ። ባልየው ከቤት ቢወጣ እንኳ የባልን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ ጓደኞች አሏቸው ።
4. መዝገበ ቃላት ሚስት ፡
እነዚህ ሚስቶች የባላቸውን ምክር የማይሰሙ ነገር ግን እናታቸውን ወይም እህታቸውን ወይም ጓደኛቸውን ማዳመጥን የሚወዱ ናቸው ።
ባሎቻቸው አንድ ነገር በተናገረ ቁጥር በፍጥነት ወደ እናት ወደ እህት ወይም ወደ ጓደኛ በመደወል ባሏ ምን ለማለት እንደፈለገ ትጠይቃለች ።
5. የግብዣ ሚስቶች
ምንም እንኳን ቤተሰቡ ለእንደዚህ አይነት ወጪ እና መዝናኛ የሚያስችል በቂ የገንዘብ አቅም ባይኖራቸውም ሁሉንም ፋሽን የሚባሉ የእጅ ቦርሳ እና ጫማዎችን መግዛት ይመርጣሉ። ... ልጆቻቸውን ፣ ባሎቻቸውን እና ቤታቸውን በቸልታ በመተው በሁሉም ግብዣ እና መጠጥ ቤት ይገኛሉ ።
6. ሞልቃቃ ሚስቶች
እነዚህ "የአባቷ ልጅ" በመባል ይታወቃሉ ... ባላቸው ጋር ያለውን ማንኛውም ትንሽ ንግግርም ሆነ ክርክር ደውለው ሁሉንም ነገር ለአባታቸው ያሳውቃሉ። በተለይ ባል በሀብታም የሚስት ቤተሰቦች ድርጅት ተቀጥሮ የሚሰራ ከሆነ።
7. የቆሻሻ ገንዳ ሚስቶች
ስሙ ከባድ ሊመስል ይችላል ነገር ግን አሉ ... እነዚህ ሚስቶች ቤት ሳያፀዱ እና ቆሻሻ ሳይጥሉ ከቤት ይወጣሉ። ቤቱን ለማፅዳት ሲሯሯጡ የምታያቸው በር ላይ እንግዳ ሲኖር እና ባላቸው ከስራ ወደ ቤት ሊመለስ ሲል ነው።
8. ፈጣሪን የሚፈሩ ሚስቶች
እነዚህ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ ናቸው። ለቤተሰብ ተጨማሪ ደስታን ይፈጥራሉ። ቤቱ በመንፈሳዊ ይመራል፣ በጣም ሀላፊነት ስለሚሰማቸው ባሏን እና ቤተሰቧን በአክብሮት ትንከባከባለች።
9. የፌስቡክ ሚስቶች
ሁል ጊዜ ኢንተርኔት ላይ ተጥዳ ሶሻል ሚዲያ ላይ የማይረቡ ፎቶዎችን እየለጠፉ እየተጫወቱ እየተወያዩ የቤታቸውን ግዴታ ይረሳሉ። ምክንያቱም ሶሻል ሚዲያ ላይ ምን እየተከናወነ እንዳለ ማወቅ ይፈልጋሉ ።
10. አድናቆት የተነፈጉ ሚስቶች
እነዚህ ሚስቶች ቤት ውስጥ የሚቀመጡ የቤት እመቤት ናቸው። ሁሉንም ነገር የሚቆጣጠሩ እና ሁሉንም ሰው የሚንከባከቡ ሆነው ነገር ግን ችላ ያልናቸው ናቸው ።
.
.
.. ሴቶችየ አንቺ የትኛዋ ነሽ? . . ወንዶችስ የትኛዋ ናት አሁን ያለህ ?...
#ethiopia
4 741
#ካነበብኩት
በስልካችን ላይ ሊኖሩ የማይገቡ አደገኛ መተግበሪያዎች
በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመምስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ
ቀጥለው የተዘረዘሩ መተግበሪያዎች በስልኮቻችን ላይ ካሉ ልናጠፋቸው ይገባል
በስማርት ስልካችን ላይ የምንጭናቸው መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽኖች) በርካታ ነገሮችን የሚያቀሉልን ቢሆኑንም አንዳንዶች ግን መረጃዎቻችን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ከመስጠት ጀምሮ ለሳይበር ጠላፊዎች እንድንጋለጥ ሊያደርጉን ይችላሉ።
በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመምስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ የሚለን ፎን አሬና ድረ ገጽ እንዚህን መተግበሪያዎች (አፕሊክሽኖች) ውለን ሳናድር ዛሬውኑ ከስልካችን ላይ እናጥፋቸው ሲልም ምክር ቢጤ አክሏል።
ቀጥለው የተዘረዘሩ አፕሊኬሽኖች በስልካችን ላይ ተጭነው ካሉ በፍጥነት ልናጠፋቸው ይገባል
*ዋለስ ላይት (Walls light - Wallpapers Pack
*ቢግ ኢሞጂ (Big Emoji – Keyboard)
*ግራድ ዋል ፔፐርስ (Grad Wallpapers - 3D Backdrops)
*ኢንጂን ዋል ፔፐርስ (Engine Wallpapers - Live & 3D)
*ኢፌክት ሚና (EffectMania - Photo Editor)
*አርት ፊልተር (Art Filter - Deep Photoeffect)
*ፋስት ኢሞጂ ኪቦርድ (Fast Emoji Keyboard)
*ከርኤት ስቲከር (Create Sticker for Whatsapp)
*ማትስ ሶልቨር (Math Solver - Camera Helper)
*ፎቶ ፊክስ ኢፌክት (Photopix Effects - Art Filter)
*ሊድ ቲም (Led Theme - Colorful Keyboard)
*ኪይ ቦርድ (Keyboard - Fun Emoji, Sticker)
*ስማር ዋይ ፋይ (Smart Wifi)
*ማይ ጂ.ፒ..ኤስ ሎኬሽን (My GPS Location)
*ኢሜጅ ወራፐ ካሜራ (Image Warp Camera)
*ስማርት ኪው.አር ክሬቶር (Smart QR Creator)
*ከለራይዝ ኦልድ ፎቶ (Colorize Old Photo)
*ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን ፋይነደር (GPS Location Finder)
*ስማርት ኪው.አር ስካነር (QR Scanner)
*ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን ማፕስ (GPS Location Maps)
*ቮልዩም ኮንትሮን (Volume Control)
*ሰክሪት ሆርስኮፕ (Secret Horoscope)
*ስማርት ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን (Smart GPS Location)
*አኒሜትድ ስቲከር ማስተር (Animated Sticker Master)
*ስሊፕ ሳውንድ (Sleep Sounds)
*አይ ሎቭ ፊልተር (I love Filter)
*ቤስት ካሜራ (Best camera)
*ቢዩቲፉል ካራ (Beautiful camera)
*ቻርሚንግ ካሜራ (Charming Camera)
*ታይድ ካሜራ (Tide Camera)
*ኬል ዴስክቶፕ (Cool Desktop)
*ዋይ ፋይ ቡስተር (Wifi Booster)
*ሲምፕል ካሜራ (Simple Camera
ናቸው
4 741
#ካነበብኩት
አይን አውጣው 😳
አንዱ አይን አውጣ የእጮኛው ቤት ይሄድና አባቷን አስጠርቶ "Hi ጋሼ ልጅዎን ለማግባት ነው የመጣሁት " ይላቸዋል።
አባት: - "ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ ማስቲካ ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም ? ክብረቢስ! " አሉት ብስጭት ብለው ከመቀመጫቸው ተነስተው ከዘራቸውን እየፈለጉ
ጎረምሳው: - "ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ እንዳይሸት ብዬ ነው "
አባት: - "ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ!?"
ጎረምሳው: - "አዎ ግን አልፎ አልፎ ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ ነው ምጠጣው "
አባት: - "ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ?!! " ሰውነታቸው በብስጭት እየጋለ መጣ
ጎረምሳው: - "ከእስር ቤት ስወጣ ነው መሄድ የጀመርኩት እንጂ በፊት አልሄድም ነበር "
አባት: - "የባሰ አታምጣ!!! አንተ ሌባ ልጄን ሰርቀህ ልታበላት ነው እንዴ? " እያሉ ከዘራቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘው ወደ ልጁ ቀረቡ
ጎረምሳው: - "ሌባ አይደለሁም ሰው ገድዬ ነው እስር ቤት የገባሁት "
አባት: - "ምን?!!!! ነብሰ ገዳይ ? "😡
ጎረምሳው: - "የታሰርኩበት ቀን በጣም ተናድጄ ስለነበር ነው። ሰውየው የኛ ጎረቤት ነበር ልጁን ለማግባት ጠይቄው ከለከለኝ ከዛ ገደልኩት:: "
አባት:- "ና እስቲ ልጄ ... ና እቀፈኝ ለልጄ እንዳንተ አይነት ጥሩ ባል ነበር ስፈልግላት የነበረው?! "🤗
ከወደዱት Share እና Like ያድርጉት
#Ethiopia #ኢትዮጵያ #ቀልድእናቁምነገር #
ተጨማሪ መዝናኛ. .👉 t.me/nuenazeg
4 741
#የአይን_ፈተና
በሥዕሉ ውስጥ ምን ቁጥር ተደብቋል?
ና ምን ያህል ጭንቀት እንዳለብህ ራስህን ፈትሽ
#ይሞክሩ #ፈታኝጥያቄ #የጭንቅላትጨዋታ
#Ethiopia #ኢትዮጵያ #ጠቅላላእውቀት
ተጨማሪ መዝናኛ. .👉 t.me/nuenazeg
4 741
#ድንቃድቅ
ይህ በሶሻል ሚዲያ መነጋገሪያ የሆነው ፎቶ በስፔን ሀገር ነው ይህ ደግ ሰው ከእሱ ቤት በላይ ያለ ጎረቤቱ በሆስፒታል ውስጥ ስለነበረ የጎረቤቱን ውሻ ብቻውን እንደቀረ አወቀ። ከዚያም ሰውየው ከሆስፒታል አስኪወጣ ድረስ ውሻውን ዘወትር ይመግበው ነበር ።
#ካነበብኩት #ኢትዮጵያ #Ethiopia
ተጨማሪ መዝናኛ. .👉 t.me/nuenazeg
#ሰብአዊነት
4 741
#ካነበብኩት
ወለዬዋ ፍልቅልቋ ከርታታዋ ዚነት ሙሃባ
👉 በስለት ተወልዳ በብዙ ስለት የአብራኳን ክፋይ ልጅ ለማየት ያልታደለችው
👉አልበሟ የበርካታ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራ ከገበያ ያባረረ
👉እሷ ዳግም አልበም ልታወጣ ከሆነ በሚል በርካታ የሙዚቃ ባለቤቶች ላይ ፍርሃት የሚያሳድር ሞገደኛ ድምፅ ባለቤት
👉 የሰራችበትን ለድሆች በመለገስ አንዳች ጥሪት ያላከበተች
👉እንስፍስፍ አልቃሻ ለሰው አዛኟ ክብርና ኩራትን የምትፀየፍ ወለየዋ ዚነት ሙሃባ
👉ለመጀመሪያ ጊዜ ከስቱዲዮ ውጭ በቆርቆሮ በተሰራ በወሎ ላሊበላ ኪነት አዳራሽ አልበም የተቀረፀው “እንደው ከምበል ደፋ” ባለቤት
👉3 አልበም ሰርታ አራተኛውን በመጨረስ ላይ በቂ ህክምና ተነፍጋ በባዶ ቤት ያረፈች
👉የወሎ ኪነት ቡድን አባላትም ሆኑ የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከነስራ ታሪኳ የቀበሯት ያቺ መልካም ፍልቅልቋ ዚነት ሙሃባ ናት
👉አደራ ስሞት ሙስሊም መቃብር ሰላተል ጀናዛ ሰግዳችሁ ቅበሩኝ ነበረ ኑዛዜዋ
የዛሬ ምርጫዬ ~~~~ "ምን ይሻላል "
via © Bilal M Guwale
👉 t.me/nuenazeg
4 741
#ካነበብኩት
አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል።
ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል።
በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው ቡኃላ አይነ ስውሩን አስፈቅዶ ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት
ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ዘንቢሉን ሞላው
የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል
"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት
ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው ።
ዛሬን ማየት እድለኛነት ነው !!❤️🙌🏼
ባለን እናመስግን !!
Via Zemelak Endrias #Ethiopia
ተጨማሪ መዝናኛ. .👉 t.me/nuenazeg
4 741
#ካነበብኩት
ባል ከሚስቱ ጋር ተጣልቶ ከቤት ውጪ ብሎ ሲያባርራት . .ወደ ቤተሰቧ ቤት ሄደች. . ከእዛ በጣም ስትናፍቀው ሊያያት ሄደ ። እየፈራ ሲያንኳኳ እሷ ነበረች በሩን የከፈተችለት. . እቅፍ አድርጋ ከሳመችው ቡኋላ ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በዝግታ ድምፅ "ለስራ ክፍለ ሀገር ሄዷል ነው ያልኳቸው ምንም ነገር አልነገርኳቸውም።" አለችው ...👌 🦋
ከምትወዱት ሰው ጋር ወይም ከባላችሁ ጋር ስትጣሉ ለቤተሰብም ሆነ ለጓደኛ አትናገሩ .. እናንተ እረስታችሁት ከእዛ ሰው ጋር ስትቀጥሉ እነሱ ግን በፍፁም አይረሱትም . ጓደኛሽ "እንደዚህ አርጎሽ እንደዚህ ብሎሽ ዛሬም ትወጅዋለሽ" ስትልሽ ቤተሰቦችሽ ደግሞ "ልጃችንን በድሏታል" ብለው ቂም ይይዙበታል ...
ከወደዱት ሼር ያድርጉት
#Ethiopia
ተጨማሪ መዝናኛ. .👉 t.me/nuenazeg
