cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Gedeo Tube🇪🇹

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! @Gedeotube

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 406
المشتركون
-224 ساعات
+77 أيام
+1830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ህንድ ከአለም የማንጎ ምርት ግማሽ ያህሉን (45%) ታበቅላለች። ነገርግን ወደ ውጭ የምትልከው 1% ብቻ ነው። ማንጎው እዛው ሀገር ውስጥ ተበልቶ ያልቃል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ የተከሰተው የእሳት አደጋ በአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ሳይሆን በአቅራቢያው መሆኑን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ በአየር መንገዱ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ የለም፤ አካባቢው ላይ ተከስቶ የነበረው አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት አካባቢ ዛሬ ከቀኑ 9፡41 ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና አደጋው ከአየር መንገዱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ኮሚሽኑ አስታውቃል። አደጋው ከአየር መንገድ ግቢውም ሆነ ከተርሚናሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ያሉት አቶ ንጋቱ  በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እና ሚዲያዎች የእሳት አደጋው በአየር መንገዱ ውስጥ እንደተከሰተ አድርገው የሚያሰራጩት ዘገባ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል። አደጋው በአንድ የድንገተኛ እሳት አደጋ ባለሞያ ላይ ቀላል ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል። የእሳት አደጋው መነሻ ምክንያት እና ያስከተለው የጉዳት መጠን የማጣራት ስራው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
#Palestine ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ። " የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል። የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል። የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል። የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል። የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል። " ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል። " ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል። የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል። ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል። መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።
إظهار الكل...
እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ትኩሳት 😥 ራሱን ሰቅሎ የገደለዉ የአርሰናል ደጋፊ .. ክስተቱ ወደ ኬንያ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል የእግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ይበላል ተብሎ ሲጠቅ የነበረዉ አርሰናል ሳይሳካለት ቀርቷል.. በዚህ የተናደደው ቀንደኛ ታዳጊዉ ደጋፊ ደግሞ ለምን ይሆናል በሚል ይመስል ራሱን ሰቅሏል..
إظهار الكل...
😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማንችስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ ዲላ፣ግንቦት 11፣2016 (ዲዩ ኤፍኤም 89.0) ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር በታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ ነው ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው፡፡ በዚህም 91 ነጥቦችን በመሰብሰብ ፕሪሚየር ሊጉን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ለአራት ተከታታይ የውድድር ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማሳካትም ውኃ ሰማያዊዎቹ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡ በሌላ በኩል ሉተን ታዎን፣ በርንሌይ እና ሸፊልድ ዩናይትድ ወደ ሻምፒዮን ሽፕ ወርደዋል፡፡
إظهار الكل...
🇬🇧 #የእንግሊዝ_ፕሪሚየር_ሊግ  🇬🇧 23/24 ✅ 38ኛ ሳምንት | የመጨረሻው ሩጫ 📱 #ቀጥታ_ውጤት_መግለጫ      ⌚️ 90' አርሰናል 2⃣-1⃣ ኤቨርተን ⚽️ ቶሚያሱ 43' ⚽️ ኢድሪሳ ጋና ጉዬ 40' ⚽️ ሃቨርትዝ 89' 🏟 ኤምሬትስ ስታዲየም ማን ሲቲ 3⃣-1⃣ ዌስትሃም ⚽️ ፊል ፎደን 2' 18' ⚽️ ኩዱስ 42' ⚽️ ሮድሪ 59' 🏟 ኢትሃድ ስታዲየም
إظهار الكل...
ጎልልልልልልልልልልልልልልል ዩናይትድድድ ብራይተን 0-1 ዩናይትድ
إظهار الكل...