cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ET motivitional speaker

Any comment @st_hana

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
678
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from N/a
ለፕሮፋይል የሚሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች ለማግኘት 📸 https://t.me/kiya_pictures1
إظهار الكل...
ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም! ወዳጄ ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው። ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ 'አንተ ስትጨርስ እሱ ይጀምራል!' ከልፋት በኋላ ደስታ....ከፆምና ፀሎት በኋላ እርካታ እንዳለ የዛሬው ቀን ምስክር ነው። የሚገርም የኢድ በዓል ተመኘንላችሁ🙏 @ETmotivitionalspeaker
إظهار الكل...
ትችለዋለህ! ራስህን እየቀየርክ በአመለካከት ከፍ እያልክ በመጣህ ቁጥር የሚገጥሙህም ፈተናዎች ከፍ እያሉ ይመጣሉ፤ መቼም ለዩኒቨርስቲ ተማሪ የ 1 ክፍል ጥያቄ አይቀርብለትም አይደል? አየህ ፈጣሪ ላያስችል አይሰጥም የሚባለው በምክንያት ነው፤ ይሄን ችግር ለመቋቋም የሚችል ማንነት ስላለህ ነው አሁን ያሉት ነገሮች የገጠሙህ፤ ስለዚህ ወዳጄ ረጋ ብለህ ካሰብከው ይሄን ማለፍ ላንተ ቀላል ነው! ላያስችል አይሰጥም! ትችለዋለህ! ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @ETmotivitionalspeaker
إظهار الكل...
ቀን! ብዙዎች የራሳቸውን ድክመት አምነው ላለመቀበል በብዙ ነገር ያሳብባሉ ከማሳበብያቸው ደሞ አንዱ ቀን ነው። አሪፍ ነገር የሰሩ ሲመስላቸው ዛሬ እኮ ቀኑ ሲገርም አስደሳች ቀን ነበር ይላሉ። ምንም ነገር ሳይሰሩ ሲቀሩ ደሞ ዛሬ እኮ ቀኑ ሲከብድ ዶክኮ ነው ያዋለኝ እያሉ ራሳቸውን ያታላሉ። ወዳጄ አንተ ግን ራሳቸውን ከሚያታልሉት ሰዎች ጎራ መመደብህን አቁም ቀን አንተ በርትተህ እንድትሰራ ወይም እንዳትሰራ ሊያደርግህ አይችልም ቀን ያንተን ሁኔታ ሊወስን አይችልም። ቀንህን አስደሳች የምታደርገውም የሚዶክክ የምታደርገውም አንተው ነህ በአወንታዊ ነገሮች ራስህን አበርትተህ ራስህን አንቅተህ ቀንህን ከጀመርክ በቀኑ ውስጥ መስራት የሚጠበቅብህን ሁሉ በብቃት ከተወጣህ እንደዛ ቀን አስደሳች ቀን አላየውም እስክትል ድረስ አስደሳች ይሆንልሀል ነገር ግን ቀንህን በማማረር አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን በመስማት በማየት ወይም በመናገር ጀምረህ በቀኑ ውስጥ ማድረግ የሚገባህን ነገር የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠርክ ሳታደርግ ከቀራህ ደሞ እመነኝ እንደዛ ቀን ደበረኝ የምትለው ቀን አይኖርህም። "ቀን ያው ቀን ነው የጊዜ መለኪያ ብቻ ጥሩ ቀንም ሆነ መጥፎ ቀን የአንተ ምርጫ ነው ሁሉም የማስተዋል ጉዳይ ነው" ይለናል ደራሲው ዶናልድ ኤል. ሂክስ እናም እልሀለው ወዳጄ በቀኖች ማሳበብህን አቁም ምክንያቱም ላንተ ተብሎ በትዛዝ የሚዘጋጅ ቀን የለም ቀኖች ሁሉ አንድ ናቸው የቀኖችን ልዩነት የሚፈጥረው ያንተ ውሳኔ ነው አስተውለህ አሪፉን ውሳኔ ወስን። @isetmind @isetmind #share
إظهار الكل...
የቱን ትመርጣለህ ! ኢላማህን በሁለት መንገድ መምታት ትችላለህ ለረጅም ሰዓት የቱ ጋር መምታት እንዳለብህ በማሰብ ወይስ ዝም ብለህ ለኢላማህ ቅርብ የመሰለህ ቦታ ተኩሰህ እያስተካከልክ ኢላማህን መምታት። መልስህን ለህይወትም ተጠቀምበት ! መልካም እለተ ሰንበት ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
إظهار الكل...
የጀመርከውን እንዳታቆም! "መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ፤ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል፤ ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተኝፏቀቅ፤ ግን እንዳታቆም!" ይለናል ማርቲን ሉተር። ወዳጄ ያበቃልህ የተሳሳትክ ወይም የፈራኸው የደረሰ ጊዜ አይደለም፤ የሚያበቃልህ ተስፋ ቆርጠህ ያቆምክ እለት ነው! ስለዚህ የጀመርከውን በፍፁም እንዳታቆም፤ ወዳጄ አንተ የስኬትን ጥግ ለማየት እንጂ ለማቆም አልተፈጠርክም! ፅናት የሞላው ህይወት ተመኘንላችሁ🙏 @ETmotivitionalspeaker
إظهار الكل...
ራስህን ውደደው! ሰዎች ከሚወዱህ በላይ ራስህን ስትወደው እውነተኛ ደስታ ይሰማሀል፤ በዛ ላይ ያለ ምንም መስፈርት የሚወድህ ፈጣሪ አለ። ከነ ድክመትህ ሰዎች እንዲወዱህ ከፈለክ መጀመሪያ አንተ ራስህ ከነጉድለትህ ራስህን ውደደው! ራስን መቀበል ማለት ይሄ ነው። እስከዛሬ የህይወት ውሳኔዎችህ ሙሉ ለሙሉ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፤ ብዙ የሚቆጭህ ነገር ይኖራል፤ ሁሉም ወደ ኋላ ተመልሶ ማስተካከል የሚፈልገው ነገር አለው። ራስህን መውቀስ ሳይሆን ራስህን መቀበል ነው ያለብህ ምክንያቱም ስህተት የስኬት ተቃራኒ አይደለም እንደውም የስኬት አካል ነው! የእርካታ ምሽት ተመኝንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
إظهار الكل...
4_5996602238817012755.mp39.33 KB
አንተ ቅደም! አንተ ብትለወጥም ባትለወጥም ጊዜው እንደሆነ መሄዱ አይቀርም! ሊዮቶል ስቶይ የተባለ የራሺያ ድንቅ ደራሲ ደግሞ "ሁሉም ሰው አለምን ስለመቀየር ያስባል እንጂ ራሱን አይቀይርም" ይለናል። መንግስት እንዲህ ቢያደርግ ወይ እንትና እንዲህ ቢያደርግ እያልክ ጊዜህን የምታባክንበት ዘመን ማብቃት አለበት! መጀመሪያ ለራስህ እወቅበት! እኔ እንዲህ አድርጌ እቀየራለው በል፤ ራሱን የለወጠ ሰው ለቤተሰቡ ይተርፋል፤ ለአለም ይተርፋል። ለመለወጡ አንተ ቅደም ወዳጄ! ተዓምረኛ ቅዳሜ ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
إظهار الكل...
በአላማህ ፅና! "ካደኩ በኋላ የተማርኩት ትልቁ የህይወት ትምህርት ሁልጊዜም ለራሴ ቃል መታመን እንዳለብኝ እና ሰዎች ከአላማዬ ሊያቆሙኝ ሲሞክሩ መደንገጥ እንደሌለብኝ ነው" ትለናለች ሚሸል ኦባማ። ከምትፈልገው ነገር የሚያቆምህ አመለካከትህ ነው! ሰዎችና ሁኔታዎች ጠንካራ ከሆንክ ከጎንህ ይቆማሉ፤ በአላማህ የማትፀና ወይ ልፍስፍስ ከሆነክ ግን ሁሉም ይጠቀምብሀል፤ ለራሳቸው ፍላጎት መረማመጃ ያደርጉሀል። አላማህን አስቀድም ወዳጄ! ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @ETmotivitionalspeaker
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.