cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

" የብዕር ምርኮኛ "✍

«ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? {ፋሲለት:33}🍁🍁 የእውቀት መዓድ ይቀላቀሉ 👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFkQxaW5cGELvPrwRQ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
937
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-1930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🌾🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾 فتاوى زاد المعاد ቁ/128 ማክሰኞ 3/3/1442 ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የዳውን ሊንኩን ይጫኑ 🔹🔸🔹🔸🔹🔸 🔎https://bit.ly/2Hogn8N 🔹🔸🔹🔸🔹🔸 ▪️1/የህፃን ልጅ ሽንት ከስንት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚነጅሰው?ልብስ ከነካስ እንዴት ነው ማድረግ ያለብን የነካውን ብቻ ነው ማጠብ ያለብን ወይስ ከነገላችን ሙሉ ነው መታጠብ ያለብን? ▪️2/ ሀገር እያለሁ ያመኝ ነበር እና ቤተሰብ ፀበል ወሰዱኝ ቦታውም ቤተክርስትያን ነው አሁን ላይ ሺርክና ኩፍር መሆኑን አወቅኩ ከእስልምና ወጥቻለሁ? ፣ እንዲሁም አይንናስ አስወጥቼ ነበር ይህስ እንዴት ይታያል?ቢያብረሩልኝ ▪️3/ቁርአንን ከፍቶ ስራ መስራት እና ያ ሰው ከፍቶ እያዳመጠ ሌሎች ቢያወሩ እሱ ወንጀለኛ ይሆናል ወይ? ▪️4/የመቶ ሰባ ስድስት ሺ 372 ብርየሁለት ዓመት ዘካ ስንት ነው የሚወጣለት ለአህባሽ ወገኖቻችንስ መስጠት ይቻላል እንድሁም ሶላት ለማይሰግዱትስ ▪️5/አፍንጫ መበሳት እንዴት ይታያል?የተወላገደ ጥርስንስ እንዲስተካከል ማሳሰር እንዴት ይታያል ▪️6/እኔ ያደጉት ከእናቴ አክስት ልጅ ጋር ነው በልጅነቴ ነው እናቴ የሞተችብኝ ያሳደገችኝ ሴትዮ ህፃን ሆኜ አጥብታኛለች እስከ 2 አመት 6 ወር ድረስ አሁን እኔ ያለሁት ስደት ነው የሷልጆች ለኔ አጅ ነብይ ይሆኑብኛል ?ባሏስ ለኔ አጅ ነብይ ነው እነሱ እኔን ማየት ይችላሉ ወይስ አይችሉም ቢያብራሩልኝ ጀዛ ከላሁ ኸይረን ▪️7/አዳበ ነውም አድርጌ ከተኛሁ በኋላ እንደገና ከእንቅልፍ ብነሳ እንደገና ስተኛ ደግሜ አዳበ ነውም ማድረግ አለብኝ? ወይስ የመጀመሪያው ይበቃል? ▪️8/ባለቤቴ ሁሌም ፎቶ ላኪ እያለ ያስቸግረኛል ይሄ ደግሞ ሀራም እንደሆነ እየተማርኩ ነው እና አልክም አልኩት ይህን ባልኩበት ተጠያቂ ነኝ ? ሀቄን አልተወጣሽም እያለ ይዝትብኛል በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜም እንጣላለን ምን ማድረግ አለብኝ ምክር ይስጡኝ ▪️9/አባቴ ሌላ ሚስት አግብቷል እናም እኛን አይጠይቀንም እኛም ስናናግረው በግድ ነው መልስ የሚሰጠን እቤቱም በተደጋጋሚ ስንሄድ አያናግረን ደስተኛ አይደለም እኔ ቤቱ ሄጄ አድሬ ሳናግረው ደስተኛ አልነበረም እንዲሁም ለትዳር ሲጠየቅ ያለምክኒያት አያገባኝም ይላል እኔ በድርጊቱ በጣም እየተሰማኝ ስለሆነ ግንኙነቴን ለማቋረጥ እያሰብኩ ነው ምን ይመክሩኛል?እንዲሁም ወንድሜ ወኪል ሆኖስ መዳር ይችላል?አባታችን አያገባኝም ስለሚል ያብራሩልኝ 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/~~~~~~~~~~~~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
إظهار الكل...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

ስኬት #ከልፋት ጋር  ✅:ስኬት በርግጥም #ልፋትን ይጠይቃል፡፡ 🐜:#ጉንዳን ካሰበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች ፤ ትነሳለች • 🐝:#ንብ ጣፋጩን ማር🍯 ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሣለች •   🕊:#ወፍ መኖርያ ጎጆዋን ለመሥራት ማልዳ ወጥታ አምሽታ ትገባለች፡፡           •-•-•-•⚘•-•-•-• ☄:አዎን - ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል… ያለ #ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደርሰም፡፡ ልብ በሉ፡- 🐺:#ተኩላ ያለመውን ለማደን ቦታና አቅጣጫ ቀያይሮ ያደባል ৲   🐈:#ድመት የተመኘችውን ለማግኘት በትእግስት ትጠባበቃለች ৲ 🦁:#አንበሳ ያቀደውን ለመያዝ በአንክሮ ይከታተላል ৲         ════  •• ════ ✅:ስኬትና ውጤት ያለ እንቅስቃሴ አይገኝም፡፡ አስተዉሉ ፦ 🐆:ነብር ካልተወረወረ አይዝም ⨳ 🏹:ቀስት ካልተስፈነጠረ አያድንም ⨳ 🗡:ሰይፍ ካልተሠነዘረ አይገድልም ⨳ 💡ተንቀሣቀስ አትተኛ • • •   🎯:ለረጅም ጊዜ የተኛ ውሃ ይሸታል √   🎯:በአንድ ቦታ ላይ ለዘመናት የቆየ ድንጋይ አንድ ቀን ይፈለጣል √ ✅:እንቅስቃሴ በረከት አለው ✅:በሥራ ዉስጥ ለውጥ አለ ✅:ሥራ ፈት ዋጋ የለዉም #ዜሮ ቁጥር ነው ✅:ሽቶ ጫን ጫን ሲሉት ጥሩ ሸተተ ৲ ✅:ሰንደል ሲያቃጥሉት አከባቢውን አወደ ✅¹:የሰው ልጅም #በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም #ወዳጆቼ ! መከራ፣ ፈተና ችግርን አትጥሉ፡፡ 🌀:ዱኒያን የታገላት ነው የሚጥላት ☇ 🌀:ዓለምን እልህ የተጋባ ነው የሚያሸንፋት ☇ 🌀:ጀነትን በመንገዷን የፀና ነው የሚያሳካት ☇ 🌿: ህይወት በየቀኑ ሩጫ ናት፡፡    🌿: የስኬት ገበያ ሁሉ ከባድ ውድድር አለው፡፡  🌿:መጀመሪያ የጨሠ ነው ኋላ ብርሃን የሚወጣው፡፡  ዛሬ የደከመ ነው ነገ የሚያርፈው፡፡ @islamic_picture_wallpaper @islamic_picture_wallpaper
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሶፊያን አስውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይሉ ነበር፦ ﴿إذا عرفتَ نفسَك لم يضرَّكَ ما قيلَ لَكَ،﴾ “አንተ ስለራስህ የምታውቅ ከሆነ፤ ስላንተ የሚባለው የሰዎች ንግግር አይጎዳህም።” [«አልሙኽለሲያት» ሊአቢ ጣኺር አልሙኽለስ (1626)] @Islamic_picture_wallpaper @Islamic_picture_wallpaper
إظهار الكل...
ተፈሲር ሱረቱ ኒሳዕ part 5 ሰዎች በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እንዳይጋጩ የእያንዳንዱ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ዲነል ኢስላም አስቀምጧል ፣ ከላይ የምእራፏ መጀመሪያ ላይ ስለ የቲሞች ይናገር ነበር .. ስለ መህርም ተናግሯል ፣ ውርሻ ላይ ወንድም ሴትም ባለድርሻ እንደሆኑ ተናግሯል ፣ ቀጥሎ ድርሻውን ወደ መመጠን ይገባል .. يُوصِيكُمُ اللّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الاُنثَيَيْنِ የአንቀፁን መጀመሪያ በጥልቀት ተመልከቱ «ዩሲኩሙሏሁ ፊአውላዲኩም» ይላል «አሏህ በልጆቻችሁ ጉዳይ አደራ ይላችኋል»። እንግዲህ ከወላጆች የበለጠ አሏህ አዛኝ ስለሆነ ወላጆች አደራ አስፈለጋቸው! “የልጆችን ነገር አደራ” ብሎ አርሀሙራሂሚን ጉዳዩን ወደሱ መለሰው። አንድ ሰው ማግኜት ያለበት ከሚመለከተው ሸክምና ሀላፊነት አንፃር ነው ። በወጭ በኩል ሴቶች እንዳይጨነቁ ነው ያደረገው ሸርዑ ሙሉለሙሉ! ለዚህም አንዳንድ ኡለሞች “ማሉል መርአቲ ናሚን” ይላሉ (የሴት ገንዘብ በባህሪው መልማት ብቻ ነው) ካላባከነችው በስተቀር ፥ የራሷንም ወጭ ባሏ ነው መሸፈን ያለበት ። ስጦታም ብታገኝ ፣ ውርስም ብታገኝ ፣ በምንም መልኩ ብታገኝ የሷን ገንዘብ እሷ በፍቃዷ ካላወጣች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ የወጭን ሀላፊነት ወንድ አንዲሸከም ነው አሏህ ያደረገው ። አባት ከዛ ባል ከሌሉም ወንድም እንዲወጣ ነው ያደረገው ። እሷ መከራ ማየት የለባትም .. አንተ አገልጋይ ነህ ኸድም ነው በአጭሩ ። ወንዱ ሲያገባ ግን ከፍሎ ነው ፡ ተከፍሎት አይደለም ። በትዳር ሲኖር ሁሉን ወጭ የሚሸፍነው እሱ ነው ፣ የሚሸፍንለት የለም ። ኢንፋቅ የሚባል ነገር እሱን ነው የሚመለከተው ። ይሄ ጠቅለል ያለ መንዙመተል ኢስላም ነው ። አንድ ሰው ወራሽ መሆን የሚችለው ከሶስቱ አንዱ ውስጥ ከሆነ ነው ። አንደኛው መወለድ ነው ( ወላጅ ወይም ልጅ መሆን) ፣ ሌላኛው ጋብቻ ነው ፣ ሌላኛው ደግሞ ወላእ ነው ( ከባርነት ነፃ የወጣ ማለት ነው) ። የጀመረው ከልጅ ነው ፥ ብዙ ጊዜ ወላጆች ቀድመው ነው የሚሄዱትና አልፎ አልፎ ተቃራኒም አለ ግን ኖርማል ከሆነው ነገር ጀመረ ። የዚህ አያ ሰበበ ኑዙል እንዲህ ነው ፦ ሰእድ ኢብኑ ረቢዕ የተባለ ሶሃቢይ ኡሁድ ላይ ሸሂድ ሆነ ፣ ሚስቱ ወደ ረሱል ﷺ መጥታ እነዚህ የሰዕድ 2 ሴት ልጆች ናቸው ፣ አጎታቸው መጥቶ ያለውን ገንዘብ ጥርግርግ አድርጎ ወሰደባቸው (ተመልከቱ የጃሂሊያን ሁኔታ እነዚህን የቲሞች መርዳት ሲገባው የወንድሜ ገንዘብ ነው ብሎ ለሚስቲቱም ሳያስቀር ወሰደ ) እንዴት ይደረግ ብላ ጠየቀች ። ረሱልም በዚህ ጉዳይ የሚፈርደው አሏህ ነው አሉ ፣ ይህ አያ ወረደ .. ፣ የአሏህ መልክተኛ ወደ ልጆቹ አጎት ለሰዕድ ልጆች 2/3ኛውን ስጥ ብለው ላኩበት ። እንግዲህ ወራሾች ወንድና ሴት ልጆች ብቻ ከሆኑ 2/3 ኛው ለወንዱ 1/3ኛው ለሴት ስጡ ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሴት ካለ ደግሞ 2/3 ኛው ለሴቶቹ ይሰጣቸዋል ፣ አንድ ሴት ብቻ ከሆነች ደግሞ ግማሽ ይሰጣታል አለና የልጆችን በዚህ ጨረሰ ። ወላጆችና የጋብቻውን በቀጣይ እናየዋለን..! https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
إظهار الكل...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

📘 ተጅዊድ ቁርአን የጥበቦች ሁሉ መፍለቂያ ድንቅ እና ታላቅ መለኮታዊ መጽሐፍ ሲሆን ዘላለማዊ ተአምር የሆነ ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው። ይህን መለኮታዊ መጽሐፍ እያስተነተን ተረድተነው ለማንበብ ደግሞ ከቁርአን ጋር በሚኖረን ትስስር ልንላበሳቸው የሚገቡ ደንቦችና በስርአት ለማንበብ የሚያስችሉን ህጎች አሉ። ይህም የተጅዊድ ህግ ተብሎ ይጠራል። ለዚህም ነው አሏሁ አዘወጀል "وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا" ያለን። እነዚህን ህግጋቶች ለመረዳት እንሆ በተከታዩ መፅሀፍ በአማርኛ ተዘጋጅቶልናል  ዳውንሎድ በማድረግ እንማማር ! @Islamic_picture_wallpaper @Islamic_picture_wallpaper
إظهار الكل...
ተፍሲር ሱረቱ ኒሳዕ ፥ part 4 ከአንቀፅ 7-10 የሱረቱ ኒሳዕ 7ኛው አያ መውረድ ብዙ ነገርን ቀይሯል ፣ በጃሂሊያው ማህበረሰብ ሴት ምንም አይነት ድርሻ አልነበራትም .. ምክንያቱም መውረስ የሚገባው ጠላት የሚመክት እንጂ ፈረስ ያልጋለበ ፣ በሰይፍ ያልመታ ፣ ቀስት ያልወረወረ ሰው እንዴት ብሎ ይወርሳል ይሉ ነበር ። እንደውም ሴቶችን እንደ እቃ በመቁጠርም እነሱም ይወረሱ ነበር - በጃሂሊያ ። ይህ በአረቦች ብቻ ሳይሆን በሩሞችም ፣ በፋርሶችም ዘንድ የነበረ ልማድ ነበር። ከዚህ አያ መውረድ በኋላ ግን መጠኑ ይለያይ እንጂ ሴትም ድርሻ አላት ትወርሳለች አለን ። ባለ ደርሻዎች ሲከፋፈሉ ዙሪያውን የሚታዘቡ ሰዎች ይኖራሉ ። የነሱንም ነገር በ8ኛው አያ ተናገረ ። የሀብታምን ገንዘብ ልጆቹ ፣ እህት ወንድሞቹ ወይም ወላጆቹ ቁጭ ብለው ዳጎስ ያለ ድርሻ ሲያገኙ ጎረቤት ያለ የቲም ቁጭ ብሏል ፣ ሚስኪኖች አይናቸው እየቃበዘ እኛም ቢደርሰን ብለው ይጓጓሉ ። እነዛ ሰዎች እንዳይረሱ ምንም እንኳ መጠኑ ይህን ያህል ነው ባይባልም የተወሰነ ነገር ቀነስ አድርጋችሁ ስጡ «ተገቢ ንግግርም ተናገሯቸውም» አለን ፣ ሁሌም ከአንድ ስራ በኋላ መልካም ንግግርን ጎን ለጎን ነው የሚያስቀምጠው ቁርዐን ልብ በሉ ! ንግግር ተፅኖው ከባድ ነው ፣ ጦር ካቆሰለው ንግግር ያቆሰለው ያስቸግራል አይሽርም ። እንደገና ብዙ ችግሮችን በንግግር መፍታት ይቻላል ። 9ነኛው አያ ደግሞ ውርስ የሚያከፋፍሉ ሰዎች በሆነ ሰበብ ወደ አንድ አካል እንዳያደሉ "ነግ በኔ" ይበሉ አለ። ለልጆቹ ፊውቸር የሚሰጋ ሰው በሌላ ሰው ልጅ ላይ ግፍ መስራት የለበትም። እንዲሁ ወሲያ ላይ ሟች ያልሆነ ኑዛዜ ሲናገር የሰማ እንደሆነ መከልክልም አለበት ፣ አንዳንዴ ወራሾችን መጉዳት የሚፈልግ ሰው ይኖራል ። ለፍቼ ለፍቼ ይሄ መናጢ ልጅ ሊወርሰው ነው አንዴ ገንዘቤን :) "ሰደቃ ነው የማደርገው" ሊል ይችላል፣ ለዛም ነው 1/3 ድረስ እንጂ ከዛ በላይ ሰደቃ መስጠት አይቻልም ። "አሱሉሱ ወሱሉሱ ከሲር" ብለዋል ሀቢባችን ፣ በሌላ ሀዲሳቸው ድግሞ “ወራሾችህን ራሳቸውን የቻሉ አድርገህ ጥለህ መሄድ ድሆች አድርገህ እጃቸውን ወደ ሰው የሚዘረጉ አድርጎ ከመሄድ የተሻለ ነው” ብለዋል ። 10ኛው አያ የየቲም ገንዘብ መብላት እሳት መብላት እንደሆነ ይነግረናል ። ረሱልም “የሁለት ደካማ ሰዎችን (የቲሞች እና ሴቶች) ብር ከመብላት እንድትጠነቀቁ አደራ እላችኋለሁ” ብለዋውናል። https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
إظهار الكل...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

የሴቶች ምዕራፍ ትንታኔ ክፍል ሶስት፥ አንቀፅ ቁጥር ⑥ ትናንት ለሰፊሆች ብር መስጠት ተገቢነት እንደሌለውና እኛ ልንጠብቅላቸው እንደሚገባ ተነጋግረናል ። ታዲያ እስከመቼ ነው የሰፊኾችን ገንዘብ እኛ እየጠበቅን ፣ እኛ እያለማን ፣ እኛ እየተንከባከብን እኛ ወጭ እየሰጠናቸው የምንኖረው? ቢባል ፤ ነፍሳቸውን አውቀው ገንዘባቸውን ማስተዳደር የሚችሉበት አቅም ላይ እስከሚደርሱ ነው ። ለዚህ ብሎ ምን አለ ፦ «ወብተሉል የታማ/የቲሞችን ፈትኗቸው» ማለት ብቃታቸውን ከዚህ በኋላ ብሩ ቢሰጠው ማስተዳደር ይችላል ወይስ አይችሉም? የሚለውን ማለት ነው። "ሀታ ኢዛ በለጙ ኒካህ" ጋብቻ እስከሚደርሱ ድረስ» በሸርዕ ደረጃ የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ ፣ እነዛ ሲሟሉ ህፃን ከሚለው ወጥቷል ። ነገር ግን አንዳንዴ አካለ መጠን ደርሰውም የአእምሮ ብስለቱ ገና የሆነ ይኖራል ። ስለዚህ ምን አለ፦ "ፈኢን አነስቱም ሚንሁነ ሩሽደን/ ከፈተናው በኋላ ነፍስ ማወቅን ከታዘባችሁ ፣ ከተገነዘባችሁ «ፈድፈዑ ኢለይሂም አምዋለሁም/ገንዘቦቻቸውን ወደነሱ አስጠጉ»። "ሩሽድ" የሚለው በዲናቸው ላይ ጥሩ መሆናቸውንና በገንዘብ ጥበቃም ላይ ጥንቁቅ መሆናቸውን ስታውቁ ለማለት ነው ። አንዳንዴ ጎረምሳ ሆኖ ገንዘብ ሲሰጠው ወዳልሆነ አቅጣጫ የሚሄድ አለ .. ይሄ ሰው አይሰጠውም። ምክንያቱም አካሉ በስሏል አምሮው አልበሰለም። ቀደም ብሎ ባለው አያ ላይ  “አምዋለኩም/ገንዘባችሁ” እያለ ነበር አሁን ደግሞ “አምዋለሁም/ገንዘባቸው” ይለናል ፣ ያኔ እንደዛ ያለው ከብክነት ለመታደግ ነው ፣ ዛሬ ደግሞ ሰዎቹ ራሳቸውን ስለቻሉ የነሱ ብር ተብሎ ወደ ባለቤቱ ይመለስ በሚል አገላለፅ ገለፀው - የቁርአን አገላለጽ ሁሌም ድንቅ ነው። ለካ አካለ መጠን ሲደርሱ ገንዘባቸው ወደነሱ ይመለሳል። ያ ቀን ሳይደርስ በፊት ለምን ዛሬ ቀንጨብ ፣ ቀንጨብ አላደርግም የሚል ዟሊም እንዳይኖር ደግሞ "ወላ ተዕኩሉሃ ኢስራፈን" አለ በማባከን መልኩ ገንዘባቸውን እንዳትበሉ። "ወቢዳረን አን የክበሩ" ነገ አድጎ ከእጄ ከመውጣቱ በፊት ዛሬ አትበሉ ። እናንተ ባለ አደራ እንጅ ባለ ገንዘብ አይደላችሁም ። እንበልና ገንዘቡን ስንረከብ ልጁ የአንድ አመት ቢሆን አስራ አምሰት አመት በእኔ እጅ ነው ይሄ ገንዘብ ያለው ፣ ብሩን ማልማት አለብኝ ። አሁን ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ፦ በሱ ገንዘብ ላይ ጉልበቴን ፣ ጊዜዬን ..ሳባክን የራሴን ኑሮ ትቼ እንዴት ነው የሚሆነው? የሚል ጥያቄ እንደሚመጣ ስለሚያውቅ ምን አለ « ወመን ካነ ጘኒየን ፈልየስተዕፊፍ» የየቲም ገንዘብ የሚንከባከብ ሰው ከዛ ከየቲሙ ገንዘብ ውጭ የራሱ የሆነ ገቢ ኖሮት የተብቃቃ የሆነ ሰው ለአሏህ ብሎ ይስራ .. ክፍያ ሳይጠይቅ ። ከዚህ ነገር ይጠንቀቅ ወይም ይራቅ ። ድሃ ከሆነሳ? የየቲሞችን ገንዘብ የሚያለማ ከሆነ የራሱ ስራ ሊቀር ነው ፣ የነሱን ትቶ ወደ ራሱ ስራ ከሄደ የዚህ የየቲም ገንዘብ ሊባክን ነው። እህ ምን ይሁን ታዲያ ? ... ደመወዝ ይመደብለት! «ወመን ካነ ፈቂረን ፈልየእኩል ቢልመዕሩፍ» የሚፈልገውን ያህል ሳይሆን የሚገባውን ያህል ደመወዝ ይመደብለት! ማነው የሚመድብለት? ከተባለ ያው ቤተዘመድ አለ ፣ ፍርድ ቤት ይኖራል ይህን በማስተዳደርህ ይሄ ይገባሀል ብሎ ይመድብለታል ። በዛ መልኩ መጠቀም ይችላል ። አሁንም ሌላ ጥያቄ ፦ ደሃ የሆነ የየቲም አሳዳጊ ይህን የየቲም ብር በደመወዝ መልኩ ከበላ በኋላ ሲያገኝ ይመልሳል ወይስ አይመልስም? በዚህ ላይ ፉቀሃወች ሁለት ቀውል አላቸው። የመጀመሪያው .. አነስ ያለ መጠን የችግሩን ያህል ይመገብ መመለስ አይጠበቅበትም። የላቡ ስለሆነ ሌላ ቦታ ቢሰራ ሊያገኝ የሚችለውን ነው ያገኘው ችግር የለውም የሚሉ አሉ (ሻፊኢያዎች) ምክንያታቸው ደግሞ አያው «ፈልየእኩል ቢልመዕሩፍ» ሲል "ይመልስ" አላለምና ይላሉ ። ሁለተኛው ቀውል ደግሞ የየቲም ገንዘብ በመሰረቱ ክልክል ነውና ለችግር ቢፈቀድለትም ሲያገኝ የመመለስ ግዴታ አለበት ያሉ ኡለሞችም አሉ ። ገንዘባቸውን አስረክቡ ካለ በኋላ አሁን ደግሞ ሲያስረክቡ ሞግዚቶች እንዳይበደሉ መስፈርት አስቀመጠ።ምን አለ «ፈኢዛ ደፈዕቱም ኢለይሂም አምዋለሁም» እናንተ አሳዳጊዎች የቲሞቹ አካለ መጠን ደርሰው ገንዘባቸውን ስታስረክቧቸው ዝም ብላችሁ ጠርታችሁ ና ውሰድ ሳይሆን «ፈአሽሂዱ አለይሂም/አስመስክሩባቸው » አለ ..ገንዘብ ያጨቃጭቃል ፣ የሚያናቁረውም የሚያፋቅረውም እሱ ነው ። ሙሲባ ነው ። ደግሞ ከሱ መብቃቃትም አይቻልም ። ስለዚህ የየቲሞቹን ዘመዶች አስቀምጦ ፦ የተረከብኩት ይሄ ይሄ ነበር ፣ ይህን ያህል ወጭ በማሳደግ ሂደት አውጥቻለሁ ፣ ይሄን ያህል ልማት ለምቷል ፣ በጥቅሉ ዛሬ የቀረለት ደግሞ ይሄ ነው ብሎ በምስክር ፊት ያስረክብ ይላል ። 🛑 ምስክር ከሌለ በኋላ የቲሙ ሊከዳ ይችላል ..ገንዘቤን ሲበላ ኖሮ መጨረሻ ላይ የቀረችውን እንኳ ሳያስረክበኝ ቀረ ሊል ይችላል ። አልያም አሳዳጊው ትንሽ ነገር ወርወር አድርጎ ሌላውን ለራሱ ሊያስቀር ይችላል። ሲረከብም ምስክር መኖር እንዳለበት ሁሉ ወጭዎችም በትክክል መመዝገብ አለባቸው ፣ ሲያስረክብም በምስክር ፊት ቆጥሮ ማስረከብ ይጠበቅበታል።ይሄ ህግ ነው ።በዚህ ህግ የሚኖር ማህበረሰብ ሚጨቃጨቅበት ምንም ሰበብ የለም!! ተቋጥሯል፣ ተደንግጎለታል ። አስመስክረናል ብሎ ደግሞ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ደብቆ ፣ አታሎ የሚሰራ ካለ ደግሞ አብሽር ፣ የሰው ምስክር ባይኖርህ እኔ አለሁ እያለ ነው (ወከፋ ቢሏሂ ሀሲባ /ሂሳብ አድራጊ በአሏህ ይብቃ) ማንኛውንም ነገር አሏህ በመዝገቡ ላይ አስቀምጦታል ስለዚህ ዛሬ አማና ያልተወጣ ሰው ነገ ረቡል አለሚን ይተሳሰበዋል። ከምስክር ሁሉ በላይ ነው አሏህ .. ይሄ ስሜት ልቡ ውስጥ ያለ ሰው ለማጭበርበር ፣ አኼራን ለመሸጥ አይጋለጥም .. ለህጉ ያህል ነገ ላለመጠየቅ ምስክሮችን ያስቀምጣል ፣ ረቡል አለሚን ፊት ደግሞ ላለመጠየቅ የራሱን ጥንቃቄ ያደርጋል ። ተቅዋ ካለ ፣ ህግ ካለ በደል የለም ። በመሰረቱ የየቲም ገንዘብን ወደማስተዳደር ሰፍ ብሎ መግባት አደጋ ነው ፣ እንደውም አፊያ የፈለገ ሰው ከመጀመሪያው ይሄ ነገር ይቅርብኝ ቢል ይሻላል ። እሱ ካልገባ ይጠፋባቸዋል ብሎ ካልሰጋ በስተቀር ..ረሱል ﷺ ለአቡዘር «ኢኒ አራከ ዶዒፋ/ አቡዘር ሆይ እንደው ሳይህ ደከም ያልክ ሰው ነህ (ገራገር ነበሩ) ፣ እኔ ደግሞ ላንተ ለራሴ የምወደውን እወድልሃለሁ (ለራሴ የምመክረውን እመክርሃለሁ እንደማለት ነው) ፦ በሁለት ሰው መካከል አሚር እንዳትሆን (ስልጣንን ሽሻት ማለት ነው) የየቲም ገንዘብ ላይም እንዳትሾም» ብለውታል ፤ መወጣቱ ከባድ ስለሆነ ማለት ነው ። https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
إظهار الكل...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0