cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2) Ignorance of the law is no excuse. civil code article 2035(2) ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም [email protected] ይላኩልን።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 526
المشتركون
+424 ساعات
+287 أيام
+7730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ስለ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የምንዳስስ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ስለ ጋብቻ አይነቶች እና ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡ ቤተሰብ ትልቅ ተቋም በመሆኑ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከሚመሰረትባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ጋብቻ ነው፡፡ ጋብቻን እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራል ደረጃ የሚዳኙት ወይም የሚገዙት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት በሶስተ አይነት መልኩ ጋብቻ ሊፈፀም እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ እነዚህን የጋብቻ አይነቶች ከመመልከታችን በፊት ጋብቻ ለመፈጸመም ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡፡ አንድ ሰው ጋብቻ ለመፈፀም በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ቅድመ ሆኔታዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያ በተጋቢዎች መካከል ነጻ ፍቃድ መኖር ነው ፡፡ 2ኛው ተጋቢዎች 18 አመት እድሜ የሞላቸው መሆን ያለበት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን በፍትህ ሚንስትሩ ፍቃድ ሲሰጥ 16 አመት ለጋብቻ የተፈቀደ ጊዜ ይሆናል፡፡ 3ኛው ደግሞ በተጋቢዎች መካከል የስጋ እና የጋብቻ ዝምድና አለመኖር ነው፡፡ 4ኛው ተጋቢዎቹ በሌላ ጋብቻ ውስጥ አለመሆናቸው ወይም በጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ያለመፈጸም ነው፡፡ 5ኛው ተጋቢዎች በፍርድ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው 6ኛው እና የመጨረሻው ቅድመ ሁኔታ ለሴት ልጅ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ቀሪ ከሆነ በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለ180 ቀን ወይም ለ 6 ወር ያህል ሌላ ጋብቻ እንዳትፈፅም የተደነገገ ክልከላ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደገለፅኩላችሁ ሶስት የጋብቻ አይነቶች አሉ፡፡ 1ኛ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ወሳኝ ኩነት በመሄድ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ 2ኛው. በሃይማኖት ስርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደሞ በቤተክርስቲያን ስርአት፤ በሼርያ ህግ እና በሌሎችም የሃይማኖት ስርአቶች ሊፈጸም የሚችል የጋብቻ አይነት ነው፡፡ 3ኛው እና የመጨረሻው የጋብቻ አይነት ደግሙ በባህላዊ ሰርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህም በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ ባህላዊ ስርአቶች የሚፈፀም የጋብቻ አይነት ነው፡፡ በቀጣይ ክፍል ደግሞ ስለጋብቻ ውጤቶች የማቀርብላችሁ ይሆናል፡፡ የነጺ ሎው via Alternative legal enlightenment/ALE* አማራጭ የሕግ እውቀት🔴 #አለሕግ #Alehig @NegereHig https://t.me/NegereHig
إظهار الكل...
ነገረሕግ NegereHig

About laws Ethiopia.......ስለ ኢትዮጵያ ህግጋት.... ስለህጎችና ህግ ጉዳዮች ብቻ.......የህግ ነገሮችን It is All About Laws....Only Law Matters...... It is about law. ስለህጎች....... ጠበቃና የህግ አማካሪ ቢሮ አዲስ አበባ @AboutLaws_bot

Team Bahir Dar University comprising, Endrays Getachew Mekuria (coach), Mekashaw Chane, Tigist Derib, and Essubalew Mola has qualified for the oral round of the #2024_Nuremberg_Moot_Court_Competition, organized by the International International Nuremberg Principles Academy and the #International_Criminal_Law_Research_Unit at the #Friedrich_Alexander #University_Erlangen_Nuremberg. The Nuremberg Moot Court is an international competition, held in English in Nuremberg, Germany. University teams from all over the world are invited to argue a fictitious case before the "International Criminal Court" during the competition. A moot court is a simulated court proceeding that invites law students to compete based on their oral and written legal argumentation and presentation, from both the prosecution and defense positions.
إظهار الكل...
ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፣ ጎንደር እና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል
ከኢትዮጵያ ስድስት ዩንቨርሲቲዎች ከዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ባህርዳር እ ሐሮማያ ዩንቨርሲቲዎች ተካተዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ከአፍሪካ በ841ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ በ1701ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቀሌ ዩንቨርሲቲ ደግሞ በ1748ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ማዕከሉ የዩንቨርሲቲዎቹን ደረጃ ያወጣው ዩንቨርሲቲዎች በሚያካሂዷቸው ጥናት እና ምርምሮች፣ ትምህርት አሰጣጥ ጥራት፣ የፋኩልቲ አወቃቀሮች እና የሰው ሀይል ጥራት ዋነኛ መስፈርቶች ናቸው፡፡ @LawSchoolStudents https://t.me/LawSchoolStudents
إظهار الكل...
Law Students የሕግ ተማሪዎች

የሕግ ተማሪዎች Access legal info center Law school students legal info [email protected]

Photo unavailableShow in Telegram
#ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡  ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ? - የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት። - የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው። - የሃይማኖት ተቋም በራሱ #የገቢ_ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት። - ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦ ° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣ ° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣ ° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት። - ማንኛውም  የሃይማኖት ተቋም  የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል። - የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል። #ሪፖርተርጋዜጣ #tikvahethiopia
إظهار الكل...
#AddisAbaba አዲሱን " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " የተያያዘውን ፋይል ከፍተው በዝርዝር ያንብቡ። #አዲስ_አበባ_ንግድ_ቢሮ #tikvahethiopia አማራጭ የሕግ እውቀት 👉Telegram👈 https://t.me/lawsocieties 👉Facebook Page 👈 https://www.facebook.com/lawsocieties/ 👉 LinkedIn 👈 https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/ 👉YouTube 👈 https://youtube.com/@Ale_Hig
إظهار الكل...
በመቃወሚያ ላይ በተሰጠ ብይን ቅሬታ ያለው ወገን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር/ይግባኝ አቤቱታ በሚያቀርብበት ጊዜ መጀመሪያ ጉዳዩን አይቶ ብይን የሰጠው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን እና ብይኑ የጸናበትን ውሳኔ ከሰበር አቤቱታቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ቅሬታ የሚቀርበው በአፈጻጸም ላይ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ሲሆን አፈጻጸሙ የተጠየቀበት ፍርድ፣ የአፈጻጸም ማመልከቻ እና በማመልከቻው መሰረት በአፈጻጸም ጉዳይ የተሰጠ ትዕዛዝ/ዞች ከአመልካች አቤቱታ ጋር ተያይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ወደ ሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮች የክርክር አመራር ሥርዓትን በተመለከተ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ ከዚህ በታች የተያያዘውን የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አያይዘናል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
إظهار الكل...
#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን #መሠረቱ 👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው። 👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል። #ቅጣት የሚገደበው 1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤ 2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤ 3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል። 4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል። #ቅጣት የማይገደበው 1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤ 2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤ 3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤ 4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ። ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል። 👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም። ይግባኝ መብት ነው!!! ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ #laws2016 https://t.me/NegereFej #ነገረ_ፈጅ
إظهار الكل...
ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2) Ignorance of the law is no excuse. civil code article 2035(2) ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም [email protected] ይላኩልን።

Photo unavailableShow in Telegram
የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል። አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል። በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ #TikvahethMagazine
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል። አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል። በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ @TikvahethMagazine
إظهار الكل...
በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች በ፡ ካሴ መልካም በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን የሕግ ጉዳዮች ያገኛሉ፡ 1ኛ. የውርስ ይርጋ ማቋረጫ ምክንያቶች እና የውርስን የይርጋ ጊዜ የሚያቋርጡ ምክንያቶች 2ኛ. በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች 1. የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ 2. ከሕገ-ወጥ ተግባር ጋር የተገናኘ የኑዛዜ ሁኔታ 3. የውርስ ሐብቱን ስመ-ሐብት በጋራ ያስመዘገበ ወራሽ 4. የወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ ክስ የይርጋ ጊዜ 5. በጋራ የውርስ ሃብቱን ይዞ መጠቀም 6. ሟች ሳይሞት ንብረቱን በያዘ ሰው ላይ የሚቀረብ ክስ የይርጋ ጊዜ 7. የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በሕጉ የጊዜ ገደብ ያረጋገጠ ከሳሽ 8. በሀሰት የተሰጠን የወራሽነት የምስክር ወረቅ ማሰረዝ 3ኛ. የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄ የይርጋ ጊዜ 1. ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች 2. ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ወራሾች 3. በመንፈስ ጫና የተደረገ ኑዛዜ እንዲፈርስ/እንዲቀነስ የመጠየቂያ የይርጋ ጊዜ 4. በሃይል የተደረገ ኑዛዜን የማፍረሻ የይርጋ ጊዜ 5. ከውርስ የተነቀለ ሰው የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ 6. የሟች የኑዛዜ ወራሽ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ ጸሐፊው የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሠረታዊ ሀሳቦች በሚል መጽሐፍ አሳትሞ ለአንባቢ ያበቃ ሲሆን በሕግ የመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋና ዳኝነት ከሰባት ዓመት በላይ በማገልገል ይገኛል። መልካም ንባብ https://www.abyssinialaw.com/blog/inheritance-matters-not-restricted-by-a-period-of-limitation
إظهار الكل...
በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች

እንደ መግቢያ   ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ9ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ምዕራፍ 9 ተብሎ የነበረውን በአዲስ መልክ የውርስ ጉዳይ ይርጋዎችን በማዋቀር በመፅሐፉ ተሰንዷል፡፡ በምዕራፍ ...