cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፈታ ብቻ

በዚህ ቻናል የተለያዩ አዝናኝ፣አስተናሪ፣እንዲሁም ቅይምነገር ተኮር ቀልዶች እየተመረጡ ይቀርባሉ እርሶም ሼር በማድረግ ይተባበሩን

إظهار المزيد
Ethiopia6 531Amharic6 376الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
822
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#አወይ_ጥርሷ ፡ ፡ ፡ ዓይኖቿ ጥለውኝ ገና ሳልነሳ፤ ከንፈሯ ደገመኝ አቤት የኔ አበሳ። ፡ ፡ እኔን ማለት ትታ፤ ጭራሽ በሱ ፈንታ፤ ከንፈሯን አሽሽታ፤ ሳቀችብኝ ልጅት መሬት ስወድቅ አይታ። ፡ ፡ እኔስ... ካ'ይኗ ከከንፈሯ እመሬት ከጣለኝ፤ የጥርሷ ድርድር ነው ይበልጥ ያቃጠለኝ። #ሄኖክ_ብርሃኑ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...
ሳቋ ከልብ ነው ፍልቅልቅነቷ ዘንድሮም እንዳምናው እንደ ልጅነቷ እያየናት አድገን እያየናት አድጋ ስንት ልጅ ፈዞባት ስንቱን ሞኝ አድርጋ አሳድገን በሰልፍ ሳታዝን ሳይከፋት እንዳሻት ስታምር ማንም ሳይጋፋት አካሄዷን አይቶ አንድ ሰው ሳይለክፋት አሳድገን እኛ ሱዚ እያዘለልን ሻሜታ እያንቃረርን ዝንብ እና አፍቃሪዋን አብረን እያባረርን አሳደግን እንጂ ገላዋ እንደጣይ በኛ ላይ ሲያፈካ ከማፍጣጥ በስቀር የቱ ደፍሮ ነካ? እያየን ስትዋብ እያየን ስታምር እያየን ስትቆነጅ እሷን ፀጋ ሲያድል ..እኛት ምኞት ሲፈጅ እያየናት ስታድግ አይናችን ሳነቅል ለጥ ያለው ደረቷ  ሎሚ ጡት ሲያበቅል እምቡጥ ከናፍሯ አብጠው ሲፈነዱ ጥቋቁር አይኖቿ ጥቁር ሳቅ ሲወልዱ የሚያምር ለዛዋ  ውበቷን ሲናገር ከጯፏ አልደረስንም ከመጎሞዠት በቀር ሀገር ሙሉ ኖሮ ሲያፈቅር ሲወዳት ዱብዳ ሆነበት ከየት መጣ ሳይባል  ባዳ ሰው ሲወስዳት እያየን ስትዋብ እያየን ስትቆነጅ እያየን ስትፈካ አለች ብሎ ማሰብ ዘበት ኖሯል ለካ መቼ አመንንና ያቺን መሳይ ጉብል ያቺን መሳይ ወጣት ከአፋችን ላይ ጠልፎ  ባዳ ሰው ሲውጣት በቅጡ ሳናዝን በቅጡ ሳንተክዝ የልባችን ቁስል ደምቶ ሳይመረቅዝ የእቃቃ ሚስት ሆናን ድግሷን ያደራን ሌላ ባል አግብታ ለሰርጓ ተጠራን እኛው አሳድገን እኛው ቆዳ ስበን .. ሽንጧን አነጥንጠን ተቃጠሉ ሲለን  ለባዳ ሠው ሰጠን ታዲያ የሰርጓ ለት  ..ትንሽ ስለጠጣን ሠርገኛው ሲመጣ "አናስገባም" ብለን  ክላሽ ይዘን ወጣን!   *-----------------* @mikiyas_feyisaከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...
መልበሴን ሳገኘው፣ እርቃኔን ስረታ የምብርክክ ጉዞዬ፣ በርምጃ ተረታ መራመድ ኃያሉ፣ መሮጥ ያስከጅላል ከመሮጥ በፊት ግን መንደርደር ይቀድማል!! ©ካሊድ አቅሉ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...
ጋዜጣ እያነበብሁ....📰 ካፍቴሪያው ሳይሞቅ ደንበኛ ሳይበዛ ባሬስታው ሳይነቃ ህይወት ሳይንዛዛ ከሁሉ ቀድሜ ወንበሬን ይዛለሁ ጋዜጣ እያነበብሁ አንቺን ጠብቃለሁ ⏳ ምክንያት?! ሁሌ ጠዋት ጠዋት ማኪያቶ ጠጥታ ፖፖቲን ማስቲካ ከኪሷ አውጥታ እሱን እያኘከች ትገባለች ስራ ይሄንን ለማየት አቤት ስጓጓለት:: እንደ ጠንቋይ ጓዳ እንደ ሀበሻ አረቄ ፊቴን በጋዜጣ ጠቅልዬ ደብቄ ስንት ግዜ ፉት አለች! ወዴት አማሰለች?! ይህንን ቆጥራለሁ... እፍፍፍ እያለች ጠጣች ወይስ ጨለጠችው ባልበረደ እንፋሎት ከንፈሯን ፈጀችው ብዬ እጨነቃለው!! ከ አምና ጀምሮ ተደብቄ ሳያት ከኔ እየቀደመ ብርጭቆ ይሳማት?! ብዬ እቆጫለው።😠 ጋዜጣ እያነበብሁ አንቺን ጠብቃለው በባዶ ሆዴ ለይ ማክያቶ አሸታለው ከ ፀበል ቀድሜ ጠረኗን ጠጣለው (NIVEA bodylotion) ማኪያቶ፣ጋዜጣ፣ማኪያቶ፣ጋዜጣ የኔ ገነት ሆኑ ነብሴ ሳትወጣ ፉት ባለችኝ😘:: ዳዊት ጌታቸው✍️✍️✍️© ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! https://t.me/kegetsoch
إظهار الكل...
ጥራኝ ድንገተኛው የሞት መላዕክ፣ መልዕክት ይዞ ላንተ ሲላክ፣ ስትነጠል ስጋህ ከነብስ፣ ያኔ ጥራኝ ቶሎ እንድደርስ፤ ሞት ጥላቢስ አንተን ይዞ፣ ሲነሳሳ ለሩቅ ጉዞ፣ ጉልበት ኑሮኝ ባላስጥልህ፣ ጥራኝ እና ልከተልህ፤ መላ እካልህ ሲሆን በድን፣ በሰመመን ስትቀር ሳትድን፣ ካለመኖር ስትጋፋ፣ ያኔ ጥራኝ ካንተው ጋራ ላንቀላፋ፤ ግን ምናልባት በሚያስፈራው ግርማ ሞገስ፣ ድንገት መቶ ቤቴ ድረስ፣ ቢደልለኝ ነብሴን ባጣ፣ ደጄ እዳትደርስ እዳትመጣ፤ ሞት ድንገቴ የመጣ እደሁ እኔን አልፎ፣ ሊወስድህ ሲል ከምድር አለም አንተን ጠልፎ፣ ለብቻዬ በትዝታህ ከምቆዝም፣ ሞት አርምሞን ጥራኝና እንበል ዝም። ✍❤️✍❤️✍❤️ ኤዶምገነት ፃፈችው ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን ....https://t.me/kegetsoch
إظهار الكل...
ሳቄን መልስልኝ ተግባር ላይ ያልታየ                     ቃልህን አምኜ          እንተን ብቻ እያሰብኩ               ሰማይ ምድር ሁኜ                  ፊደል አሳምረክ                   የሰጠከኝ ተስፋ                ድንገት ስትለይኝ                 ሳቄን ይዞት ጠፋ፡፡                    ሳቄን መልስልኝ                    ልቤን ትቸዋለሁ                  ልብ ማለት ቀርቶ              መስማት ጠልቻለሁ።   ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...
👱‍♀#ከቺኩ ጋር ተቀጣጥረው ጀለስ ገላውን ታጥቦ, ሽቶ ተቀብቶ, ፀጉሩን ተቆርጦ ሲጠብቃት ደውላ አልመጣም ስትለው 👨ጀለስ እኔ ምን🤷‍♂አገባኝ ንፅህና ለራስ ነው አላለም😃🤣😅😂
إظهار الكل...
እንደምነህ እግዜር ፣ ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ዳዊትስ ደህና ነው? ዛሬም ይዘምራል ? ዛሬም ይፎክራል? ሰላም ናት ጠጠሩ ፣ ሰላም ናት ወንጭፉ? እዛስ አቅል ገዛ ፣ ጎልያድ ተራራው ፣ ጎልያድ ግዙፉ? ።።። እልፍ አእላፍ ጎልያድ ፣ ከቦን ሲደነፋ ወንጭፉን ጠቅልሎ ፣ ምነው ዳዊት ጠፋ? ብለህ ጠይቅልን። ።።።። 👉 ከአሌክስ አብርሃም ግጥም ላይ የተቆነጠረ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...
----            ይኸውልሽ ስሚ ይወደኛል የሚል - ወሬሽን አቁሚ ወፍዘራሽ ስንደዶ የማንም ልቅምቅም የማንም ቅራሪ ማንአባሽ ስለሆንሽ ይወደኛል ብለሽ የምትናገሪ? በርግጥ አይሻለው ይህንን አልክድም አይን ያየውን ሁሉ ልብ ግን አይወድም አዎ አይቼሻለው ስትቆለጳጰሽ    ስትቆሚ ስተኚ ግን እንደሞኝ ሰው አይኔን እንዳታምኚ አንቺን የሚያስንቁ እቆጥራለው መቶ እንኳን አንቺን ጀዝባ ልለማመጥ ቀርቶ አስቤሽ አላውቅም - ትመስክር ጨረቃ ግን ግን ግን - አቦ ግን አበዛው ወድሻለው በቃ. *----------*   ❴ሚኪያስ ፈይሣ❵ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
إظهار الكل...
ራሴን ወግቼ ላንቺ የምወግን (በእውቀቱ ስዩም) አይደለሁም ጀግና ልቤን እና ክንዴን ፥እጠራጠራለሁ ግን ተኩሼ ባልጥል፥ አነጣጥራለሁ ቀማኛ ቢከብሽ፥ ፖሊስ እጠራለሁ:: ቅዱስ አይደለሁም፥ የጻድቃን ቤት ካለ፥ በውስጡ የለሁም:: መናኛው ራሴ፥ ቢበጠር፥ ቢላጭም ለሳር ባርኔጣ እንጂ፥ ላክሊል አይታጭም:: ምንድን ሆኘ ነው ግን? ራሴን ወግቼ ላንቺ የምወግን ምኔን አሞኝ ነው ግን ? እንችን የማሞግስ፥ ራሴን ወቅሼ ሳቄን የማካፍል፤ ለብቻየ አልቅሼ፤ እንደ ጋሻ ጃግሬሽ ፤ ከሁዋላሽ ስባክን ከፊትሽ ቀድሜ፥ እንቅፋት ሳመከን አይተሽ እንዳላየ ጀግኖች ምናረጉ ሰማታት ምን ሰሩ፤ ከዚህ የተለየ፥ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
إظهار الكل...