cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔

مشاركات الإعلانات
697
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-1430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

07:24
Video unavailableShow in Telegram
🔴 አዲስ ዝማሬ " ኮከብ ብሩህ " በመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰንበት ትምህርት ቤት @-mahtot
إظهار الكل...
_አዲስ_ዝማሬ_ኮከብ_ብሩህ_በመካነ_ሕይወት_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ሰንበት_ትምህርት_scUN06182z8.mp430.28 MB
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ (ሐምሌ 5) ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው። #ቅዱስ_ጴጥሮስ ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19 ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ  ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/ ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበረና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ አካይያ ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት ከዚህ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን? አለ አንተ ብትፈራ እንጂ ነዋ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚህች ሐምሌ 5 ቀን ይታሰባል፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቶ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡ #ቅዱስ_ጳውሎስ ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (የተመረጠ ዕቃ) ማለት ነው፡፡ ሐዋ.9፥15 አንድም ብርሃን ማለት ነው፡፡ አንድም መድቅሕ ማለት ነው፡፡ ደንጊያ በመዶሻ ተጠርቦ ለሕንፃ ሥራ እንዲውል አሕዛብም በእርሱ ትምህርት ታንፀው ለገቢረ ጽድቅ ይበቃሉና የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ነው፤ ሳውልም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ማለት ነው፡፡ ፊል. 3፥5 አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ የተወለደው ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ነው፡፡ ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ ሐዋ. 22፥3 ለሕገ ኦሪት ቀናዒ ከመሆኑ የተነሣ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ እያለ ሐዋርያትን ይቃወም ምእመናንን ያሳድድ ነበር፡፡ በወንጌል ያመነው ጌታ በዐረገ በ8ኛ ዓመት ነው፡፡ ምዕመናንን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናት የሹመት ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሄድ መብረቅ ጣለበት፤ ደንግጦ ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ አንተ ማነህ አለ ምእመናንን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበት አላውል የምትልብኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፣ ሰይፍ ቢረግጡት የረገጠው ሰው እንጂ ሰይፉ ይጎዳልን፣ አንተስ እኔን ብትክድ ምእመናንን ብታሳድድ አንተ እንጂ እኔ እጎዳለሁን አለው፡፡ አሁን ምን ላድርግ አለው ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ የምታደርገውን ይነግሩሃል አለው፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩም ድምጹን ይሰማሉ መልኩን ግን አላዩም፤ ከወደቀበት ተነሥቶ ዓይኑ ጠፍቷልና ሰዎች እየመሩት ቤተ ይሁዳ አደረሱት እኅል ውኃ ሳይቀምስ 3 ቀን ውሎ አድሯል፡፡ ሐናንያ በደማስቆ ይኖር ነበርና ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎስን አጠመቀው፡፡ ሐዋ. 9፥1-19 በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ሲያስተምር ንጉሡ ኔሮን ቄሣር አሥሮት ነበርና አካይያ ዘምቶ ጠላት ድል ነሥቶ ሲመለስ ጥሩት አለ፤ መስቀሉን በእጁ ይዞ ቀረበ፤ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡት አለ፤ እንደ በግ እየነዱ ሲወስዱት የንጉሡ ልጅ አገኘቻቸው፤ አምና ነበርና መጎናጸፊያሽን ስጪኝ አላት ሰጠችው በዚያ ሸፋፍነው ሰይፈውታል፡፡ ደሙም ሰማየ ሰማያት ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል፡፡ እሱን ገድለው ሲመለሱ የንጉሥ ልጅ አገኘቻቸው ጳውሎስስ? አለቻቸው፡፡ በልብስሽ ሸፋፍነን በሰይፍ ገደልነው አሏት፡፡ ልብሴን መልሶልኝ ከጴጥሮስ ጋር አሁን በዚህ ሲያልፍ እያየሁት ገደልነው ትሉኛላችሁን አለቻቸው ልብሷን አይተው አምነዋል፡፡ ተቆርጦ የወደቀ ራሱንም ከአንገቱ ቢያጋጥሙት እንደ ቀድሞው ሆኖላቸው ቀብረውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚች ሐምሌ 5 ይታሰባል፡፡ የቅዱሳን አባቶች ጸሎታቸው በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደር፡፡ (ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ)
إظهار الكل...
🙌ሴቶች ሆይ መሰናከያ አትሁኑ #ዝሙትና አለባበስ #ለሴት እህቶቼ #ለሌሎች መሰናከያ አንሁን! "እኔ ግን እላችኋለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ ከእርሷ ጋር በልቡ አመንዝሮአል፡፡" (ማቴ 5፡28) በዚህ ዘመን እጅግ በከፋ ሁኔታ ትውልድን እያጠፉና ወደ ስኦል እያመሩ ያሉት የዝሙት መናፍስት ናቸው፡፡እነዚህ መናፍስት ሌሎች ክፉ መናፍስትን ጨምረው ህዝቡ ዳግመኛ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይሔዱ ከዚያም ይልቅ ወደ ዘፈን ኮንሰርቶች፣ወደ ምሽት ቤቶች፣እንዲሁም ወደ ፊልም ቤቶች እንዲሄዱ ያደርጓቸዋል፡፡የነዚህ መናፍስት ዋነኛ ተግባራቸው ደግሞ በአዳም ዘመን በሐጢአት ምክንያት ወደ ሰው ልጆች የመጣውን ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት ግዙ የሚለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተከትሎ አዳም ሔዋንን አወቃት ከተባለበት ቀን ጀምሮ የሰው ልጅ እርስ በእርስ የመራቢያ መንገድ ሆኖ እንዲያገለግል የሆነውን ወሲብ መልኩን በመለወጥ ሰይጣን እንደመዝናኛ አድርጎ የለወጠው በመሆኑ ነው፡፡እንደሚታወቀው ምንም እንኳን ወሲብ በብልቶች አማካይነት የሚፈጸም ቢሆንም ፤ነገር ግን የጭንቅላት አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር 👉“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” — ምሳሌ 4፥23 ስለዚህ ይህ የዝሙት ሐጥአት ልብን አጥብቆ ካለመጠበቅ የሚመጣ ነው ማለት ነው፡፡በነገራችን ላይ ለአድሱ በክርስቶስ ለተፈጠረ ማንነታችን ምንም እርባና የሌሌው ወሲብ አንዳንድ ሰዎችን ዋነኛ የህይወታቸው አካል አድርጎ የመግዛቱ ምሥጢር አስተሳሰባቸውን እንደ እግዚአብሔር ቃል ካለመጠበቃቸውም የሚቃወመውን ሐጥአት በጉያቸው ሸሽገው እኛ ዳግመኛ ተወልደናል ብለው ማመናቸው ነው፡፡ይህ ግን ጨርሶ ልክ አለመሆኑን ቤተክርስቲያን በግልጽ ልታስተምር ይገባታል፡፡ሰውነታችንን ህያውና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ቅዱስ መስዋዕት አድርገን ልናቀርብ እንደሚገባ እግዚአብሔር በቃሉ ይመክረናል፡፡ነገር ግን በተቃራኒው በዘመኑ ያለን ክርስቲያኖች የተቃራኒ ጾታን ደስ ለማሰኘት እራሳችንን አመቻችተን ስናቀርብ አይታወቀንም፡፡ እንደሚታወቀው ወንድ ልጅ 1ዐዐ% በሚባል ደረጃ በማዬት ነው ለወሲብ የሚነሳሳው፡፡ለዚህ ነው እህቶቻችን የገቢያቸውን 8ዐ% ለጌጣጌጦችና ራሳቸውን ለማስዋብ የሚያውሉት፡፡ይህ ጌጣጌጥ ደግሞ ከሌሎች ሴቶች ተመራጭ ማድረግ አለማድረጉን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ይቀጥላል፡፡እነዚህ ጌጦችና ራስን አለቅጥ ማስዋብ ደግሞ ወንዶችን ለዝሙት በማነሳሳቸው ልክ ይወደዳሉ፤ይለካሉ፡፡ እህቶቼ ለማነው አስቀድመን ሰውነታችንን የሸጥነው ? ተመልከቱ እንደዚህ ሆና የወጣች ወጣት ከከተማ ስትወጣ እንዲሁም ወደ ቤተክርስቲያን ስትሄድ ያያት ሁሉ በምኞትና በአድናቆት አብሯት ይሰስናል፣ያመነዝራል፡፡ ስለዚህ በለበሰችው በዚህ የዝሙት ቀስቃሽ ልብስ የተነሣ ምናልባት እጅግ ብዙ ወንዶች የነገሮች ምንጭ የሆነውን ልባቸውን ወስዳ የክፋት ምንጭ ታደርገዋለች፡፡በኋላም በተለያየ ምክንያት በየማይክሮ ሰከንዱ በሺ የምቆጠሩ ሰዎች ወደ ሲዖል ይነጉዳሉ፡፡ገላዋን አጋልጣና የጋለሞታ አለባበስን በመልበስ በተለያዩ የመገናኛ መረቦችና ማህበራዊ ሚድያዎች የለቀቀች ሴት እንዴት በአካል እንኳን የማያውቋትን ሰዎች ወደ ስዖል እንደምትነዳ ተመልከቱ፡፡እህቴ ሆይ አለባበስሽ የተስተካከለ ነው? ወይስ ለብዙ ወንዶች ወጥመድ ሆነሽ አሰናክለሻል ????? ምክንያቱም ዳሌ የሚያሳይ ፣ጡት በሚያሳይ እንዲሁም ማንኛውንም የሰውነት አካል ቅርጽሽን የሚያሳይና ወንዶችን በሚያማልል የትኛውም የዝሙት ቀስቃሽ በሆነ አለባበስሽ (ልብስሽ) ምክንያት ብዙ ወንድሞችን በማሰናከል ምክንያት ላይ ነሽ እህቴ ሆይ በዝሙት ሐጥአት ላለመውደቅና ለሌሎችም ማሰናከያ ከመሆን ጌታ ይጠብቅሽ ! ምክንያቱም አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ልጅ አይቶ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት እንደሚያደርግ (በምናብ ድርጊቱን ሲፈጽም) ከእርሷ ጋር በአካል ዝሙት እንዳደረገ ይቆጠራልና ተጠንቀቂ !!! ኤፌሶን 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ¹⁶ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ¹⁷ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። “ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ።” — ሶፎንያስ 1፥8 “በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።” — ማቴዎስ 18፥6 #Share እና #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
إظهار الكل...
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!! ከእለታት በአንዱ ቀን አንዲት ምስኪን ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ አንድ የቤት ስራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዮይቱም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሐ ገብቼ የተውኩት አንድ ኃጢአት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሐ ገብቼ የተውኩት ኃጢአት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እሱን ከነገረሽ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደቤቷ ሄደች። ተመልሳ እንደማትመጣ ግን ገምተው ነበር አባ፤ በበነጋው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴትዮዬቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህሳ ልጄ እግዚአብሔርን ንስሐ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢአት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ ... "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ... "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ... "እረስቸዋለሁ አለኝ" አለቻቸው .... እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደደረታቸው አስጠግተው አቀፏት! እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!! የሰው ልጅ ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሃለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ! ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔርን በእኛ መጠን መትረን ንስሐ በገባንበት ኃጢአት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ሂፆጱ ያጠበውን ኃጢአታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት እሾህ ራሳችንን የምንገርፍ? ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሃለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት እንዴት በቀለለ! በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳት ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነው'ኮ! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን ... እግዚአብሔር የይቅርታን ልብ ይስጠን!
إظهار الكل...
05:24
Video unavailableShow in Telegram
🔴 አዲስ ዝማሬ “ ምነው ዘነጋ “ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ​⁠@-mahtot @ማርያም
إظهار الكل...
_አዲስ_ዝማሬ_ምነው_ዘነጋ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_mahtot_ማርያም_KK6RDuEKt2g_135.mp43.14 MB
እችላለሁ ካልህ ትችላለህ!? ክርስቲያን "ሁሉን እችላለሁ" ይላል ወይ? አዎ ይላል:: ግን ከፊቱ የሚቀር ዐረፍተ ነገር አለ:: "ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" (ፊል. 4:13) በራስ መተማመንም እግዚአብሔርን ከለላ በማድረግ ብቻ ነው:: "በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ" ምሳ. 3:5 ስለዚህ በእግዚአብሔር መታመን በራስ ከመታመን በላይ ነው:: Confidence ከሚለው ይልቅ Godfidence የሚል አዲስ ቃል ሳይገልጸው አይቀርም:: የተፈጥሮ ጸጋህን እወቅ በሚል በጎ መነሻ የተጀመረው "ነኝ ካልኩ ነኝ" የሚለው መፈክር አሁን ላይ ምድርን እየበጠበጠ ይገኛል:: ሰዎች "ውብ ነኝ ጎበዝ ነኝ ፤ ደፋር ነኝ" ብለው ራሳቸውን በኃይል እንዲሞሉና አቅማቸውን እንዲረዱ ማድረጉ ባልከፋ ነበር:: መጽሐፍ ቅዱስ ላይም "ጥቁር ነኝ ግን ውብ ነኝ" "ድሆች ስንሆን ሌሎችን ባለጸጎች እናደርጋለን" "እንገፋለን እንጂ አንወድቅም" "እንጨነቃለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም" የሚሉ ሰው ከድካሙ ውስጥ ኃይሉን እንዲያይ የሚያደርጉ በጎ ቃላት አሉ:: "ውብ ነኝ ፤ ደፋር ነኝ ፤ጀግና ነኝ" የሚለው ግን ገደብ አልፎ ወንዱ "ሴት ነኝ" ሴትዋ "ወንድ ነኝ" እስከማለት ደረሰ:: I identify as a woman የሚሉ ጎረምሶች I identify as a man የሚሉ ልጃገረዶች ተነሡ:: አልፎ ተርፎ ትዳር ለምኔ ብለው የሰው ልጅ ሕልውናን የሚያስቀጥለውን የቤተሰብ ተቋም ገደል ሊከቱ መሮጥ ጀመሩ:: ሕፃናትን ስለዝሙት ጥበብ የሚያስተምሩ ጾታቸውን እያጠራጠሩ የሚያወዛግቡ ግፈኞችም በዙ:: ውስጥህን አታምቀው ነኝ ካልክ ነህ ተብለው ብዙዎች ነኝ ያሉትን ለመሆን በቀዶ ህክምና ፍዳቸውን እያዩ ነው:: Youtube ዕድሜ አይሠጠውም እንጂ በጉዳዩ ላይ የተሠሩ ዘጋቢ ፊልሞች እጅግ ልብ ይሠብራሉ:: አልበርት አንስታይን "ሰው የሚችለውን ነገር ከማወቅ በላይ የማይችለውን ማወቁ ይጠቅመዋል" ብሎ ነበር ፍጡር እንደመሆናችን አደርጋለሁ ያልነውን ሁሉ ላናደርግ እንችላለን:: "ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን፡ የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና። በዚህ ፈንታ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፡ ማለት ይገባችኋል" ያዕ. 4:13 ሰውዬው ወደ ሥራ ሲሔድ ከአንድ ወዳጁ ጋር ተገናኘ:: "ወዴት እየሔድክ ነው?" አለው:: "እግዚአብሔር ቢፈቅድ ገበያ ውዬ ልመጣ ነው" አለው:: ባለ ሥራው "ምን እግዚአብሔር ቢፈቅድ ትላለህ? ገበያ ልሔድ ነው አይበቃም?" ብሎ አሾፈበትና ተለያዩ:: ባለ ሥራው ወደ ሥራው ሲሔድ ሌቦች ጠብቀው ደብድበውት እጁ ተሠብሮ ሥራ በመግባት ፈንታ ሐኪም ቤት ዋለ:: ከሐኪም ቤት እጁን በፋሻ አንጠልጥሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ "እግዚአብሔር ቢፈቅድ ገበያ ውዬ ልመጣ ነው" ያለው ሰውዬ ጋር ተገናኙ:: "ውይ ወንድሜን ምነው ምን ነካህ" ብሎ የጉዳቱን ሁኔታ በዝርዝር ጠይቆ ከተረዳ በሁዋላ ታማሚውን "ታዲያ አሁን ወዴት እየሔድህ ነው?" ሲለው የጠዋቱ ትዕቢቱ ተንፍሶ እንዲህ አለ :- "እግዚአብሔር ከፈቀደ ወደ ቤቴ እየሔድሁ ነው" ሐዋርያው " ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፡ ማለት ይገባችኋል። አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው" ያለው ለዚህ ነው:: ያዕ.4::15-16 ፎቶ :- ቅዱስ ጳውሎስ ኃይልን በሠጠው በክርስቶስ ሁሉን የቻለበት የሰማዕትነቱ አደባባይ ምንጭ:-ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

Photo unavailableShow in Telegram
ወቅታዊ መልዕክት በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው እና በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ስም ተፈርሞ እንደወጣ በማስመሰል የተለቀቀው ከዚህ በታች የሚታየው ደብዳቤ ፍጹም የሐሰትና ሆን ተብሎ ተቀነባብሮ በፎርጅድ ተሰርቶ የተለጠፈ መሆኑን እንገልጻለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት። አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሰኔ ፲፬ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.