cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🌴አንደበቴ🌴

moonlight

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
882
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-57 أيام
-4030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ቃል ከረከሰበት ቅጥፈት ከበዛበት ከኔና ካንተ አለም የማለልን እንጂ የኖረልን የለም አላፊ እኔና አንተ ምን ብንዋደድም ዘላለም በሚል ቃል አንሸዋወድም ስሞ ያሞካሸኝ ዘላለም ላይረባኝ እስካሉ መውደድ ነው በጊዜ የገባኝ::
إظهار الكل...
"ወዴት ነሽ?" ኃይሉ ከትናንት ተርፎ ዛሬን ወደሚሰርቀው ትዝታ! መጥፎ ሲሰሩበት ሊረሱት ግድ ወደሚያደርጉት ትዝታ! ሲከብሩበት ወደሚደሰኩሩት ትዝታ! የራስን ክፉነትና መልካምነት ወደሚያንፀባርቁበት አለም... ወደ ኋላ!
إظهار الكل...
ሴትን ልጅ ወደህና ፈቅደህ ወደሂወትህ ካመጣሀት በሆአላ እንደአባት መካሪ እንደወንድም ተቆርቋሪ እንደእናት እንስፍስፍ ሁንላት እንጂ ፈፅሞ ፈፅሞ የእንባዋ መፍሰስ ምክንያት እንዳትሆን ነገ ለልጆችክ የምትነግራቸው ልዩና ዘመን የማይሽረው ፍቅር ና ክብር ይኑርህ::
إظهار الكل...
<< በለሆሳስ የሚጮኹ እዬዬዎች አሉ። በፈገግታ የሚግሉ መከፋቶች አሉ። ትኩረት፣ እይታን በመፈለግ ውስጥ፣ በጥልቅ ላለመድከም የታይታ በራስ መተማመን በማሳየት ውስጥ የተሸሸጉ ግራ የሚያጋቡ ሰቃዥ ስሜቶች አሉ። ብዙ ነገሮች እንደምናያቸው አይደሉም። የአንዳንድ ሰዎች ሁኔታ እንዲህ ነው። ስል የሆነ ቢላዋ ላይ ቆሞ እንደ መደነስ፣ በስል ቢላዋ ላይ ሸርተቴ እንደ መጫወት፣ ደም እያንቆረቆሩ ላቤ ምነው ቀላ እንደማለት፣ በጥፍር ዳገትን እንደ መውጣት። >>
إظهار الكل...
የወደድክ ግዜ  ጥሎህ የማይሄደውን ውደድ....ፍጥረታትን ስታፈቅር  ውዴታህን ከአይንህ አሳልፈህ ለልብህ ስጥ....የአይን ወዳጅህ  ከእይታህ ሲርቅ  በናፍቆት ይገድልሃል...የልብ ወዳጅ ግን ዝንተዐለም  ካንተ ጋር ይኖራል...! 🔗
إظهار الكل...
የጊዜ ጉዳይ እንጂ በዳይ በዚህ ምድር ላይ የእጁን ያገኛል፡፡ ዛሬ ቢፈነድቅ ቢደሠት ለጊዜው ነው፡፡ ዛሬን ሳይቀጣ ቢያልፍ እንኳ ነገ ሌላ ኬላ አለበት፡፡ በትንሳኤ ቀን የሚጠብቀው መዓት ከባድ ነው፡፡ በቂያማ ቀን ለምርመራ ዋናው መርማሪ ፊት ይቆማል፡፡ መልካም ምንዳዉን ሁሉ ዐይኑ እያየ ይነጠቃል፡፡ የበደላቸዉን  ሰዎች እንዲክስ ይደረጋል፡፡ የሚክሰዉም ዱንያ ላይ ከሠራው የመልካም ሥራ ምንዳው እየተወሰደ ነው፡፡ ዐይን እያየ የራስን መልካም ሥራ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ህመም አለ!!፡፡  በዚህ መልኩ  የበደለዉን ሁሉ ይክሳል፤ የሰረቀዉን ሁሉ ሳይወድ በግዱ ይመልሳል፡፡ መልካም ሥራ ከሌለው ወይም ለተበዳዮች ተሠጥቶ ካለ ከተበዳይ መጥፎ ሥራ ተቀንሶ ዕዳ እንዲሸከም ይደረጋል፡፡ በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማ ነው፡፡ በዳይ ሰው ኪሳራው ብዙ ነው፡፡ ማረፊያዉም ጨለማ ነው፡፡ ለበዳይ ሰው እዘንለት እንጂ ተበደልኩ ብለህ አትማረር፡፡ የተበዳይ ዱዓ ምላሽ አለው፡፡ የተበዳይን ጉዳይ አላህ አይረሳም፡፡ አንድ ቀን ይመልስለታል፡፡ እንባዉን በማረ ሁኔታ ያብስለታል፡፡  በደል ጉዳት ቢመስልም ትርፍ አለው፡፡ እናም ምን አሳሰበህ … @ከአላህ ጋር መጽሐፍ
إظهار الكل...
አካሉ ከአካሌ ቢርቅም ...አብሮኝ እንደሚውል ከሀሳቤ የማይጠፋ ...እንደ ቅርቤ ሁሉ ምቱን የማደምጠው ፥ አለ ሚናፍቀኝ🧡
إظهار الكل...
Repost from N/a
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳቹ አደረሰን መልካም የኢባዳ ጊዜ ይሁንልን🌺
إظهار الكل...
ሐራም ነገርን በሩቁ መጠየፍን የመሰለ ነገር የለም። ከተጠጉት ግን በሂደት ሳይታሰብ ይዞ ይሄዳል። እንደ ከባድ ወንጀል ሲታይ የነበረው ለዐይን ይቀላል። ከዚያ መሥራቱ ይገራል። ከዚያ መደጋገሙ ይለመዳል። ከዚያ ከሐላል ጋር ተመሳስሎ መለየቱ ይከብዳል። ከዚያ ኖርማልና ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ እንደ ሐላል ይወሰዳል። ቀልብ ይበልጥ እየደረቀ ሲሄድ ደግሞ ሐላልና ሐራምን መለየት ይሳነዋል። ይመር የነበረው ይጣፍጣል ፣ ያዝናናል። ከዚያ ሱስ ይሆናል። ከዚያ ማግኘቱ ያጓጋል። ቀልብ እንዲህ እስክትሆን መጠበቅ የሞት ሞት ነው። ሙእሚን በወንጀል ሊወድቅ ይችላል፣ ቢወድቅም ወድቆ አይቀርም አፈር ልሶ ይነሳል። ቢሸነፍና ድንገት ስህተት ቢሠራ ጥቂት ቆይቶ ይነቃል። የሚወቅሰው ህሊና፤ የምትቆጣው ነፍስ አለዉና ሽንፈቱን መቀበል ይከብደዋል። አላህም ተፀፃች ባርያውን ያግዛል።
إظهار الكل...
ሳላይህ አመንኩብህ፣ ሳላይህ ሰገድኩልህ፣ ሳላይህ ለመንኩህ፣ ሳላይህ ተመካሁብህ፣ ያየኸኝ እና ያየሁህ ቀን እዘንልኝ፣ ካንተ መገናኘቴን አሳምርልኝ።😢 ያ ረብ። ሽይኽ ሸዕራዊ።
إظهار الكل...