cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Shega Media - ሸጋ ሚድያ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡ ማንኛውንም አዝናኝ ዜናዎች በአንድ ቦታ።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
45 414
المشتركون
-5724 ساعات
-4547 أيام
-1 69330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የጋሽ መሐሙድ አህመድ 83ኛ የውልደት ዓመት በድምቀት ተከበረ በትላንትናው እለት የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በመኖርያ ቤቱ በመገኘት ነው የልደት በአሉን ያከበሩት ። መልካም ልደት ጋሼ ! የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
إظهار الكل...
👍 4
በ1500 ብር ካፒታል ተነስቶ ሚሊየነር የሆነው ግለሰብ ስጋ ቤቱን ወደ ሆቴልነት አሳደገ።. አቶ አረጋ ወ/ሰንበት ከ1993 ብዙ የህይወት ውጣ ውረዶችን አልፏል ከልጅነት እስከ እውቀት በየሰው ቤት እየተቀጠረ አድጓል በአዲስ አበባ ታዋቂ በሆኑ ስጋ ቤቶች በስጋ ቆራጭነትም ተቀጥሮ ብዙ ጊዚያትን አሳልፏል እሱ በወቅቱ ስጋ በሚቆርጥበት ዘመን በ1993 ዓ.ም ኪሎ ስጋ ከ18 ብር እስከ 30 ብር እንደነበረም ይናገራል። ከተቀጣሪነት ወጥቶ በ1500 ብር ወረት የራሡን ስጋ ቤት ሲከፍት አሁን የደረሠበት ላይ እንደሚደርስ እና ከእሱም አልፎ ለሌሎችም የሥራ እድልን መፍጠር እንደሚችል በልበ ሙሉነት ይናገር ነበር። ይህ ሰው ስራና ስራ ወዳድ ከመሆኑ የተነሳ የራሡን ስጋ ቤት ከፍቶ ባተረፈው ብር ላዳ ታክሲ በ17 ሺ ብር ገዝቶ ጎን ለጎንም ሌሊት ላይ ታክሲ ሲሰራ አድሮ ወደ ስጋ ቤቱ ይመለስ ነብር ረጅም ሰአት መተኛት በእሱ ቤት አይታሠብም ነበር። ይህ ሰው ሀብት ለማግኘት እድል ወሳኝ ነው ለሚሉ ሰዎች በፍጹም ውሸት ነው ለሀብት ምንጩ ስራና ትጋት ብቻ ነው ያ ካልሆነ ፈጽሞ ሀብት ሊመጣ አይችልም ብሎ ይናገራል። አሁን ከበርካታ ሚሊዮኖች ተርታ ተሰልፎ ግሎባል ላንቻ አካባቢ የከፈተውን ትልቁን የፍየል ቁርጥ ቤት ወደ ሆቴልነት አሳድጎ ለበርካቶች የሥራ እድልን መፍጠር ችሏል። በዋካን ሆቴሉ ውስጥ ጥሩ የደለቡ በሬዎች እና ሰንጋዎች ቁርጥ፣ ክትፎ እና የመሣሠሉትን በጥራት በማቅረቡ እና ዋጋ ላይም ከሌሎቹ ለየት ባለ መልኩ በማቅረቡ ብዙዎቹ እንደሚመርጡት ይናገራል። ስጋ አቆራረጥ ላይና አመዛዘን ላይ እጁ የማይሰስት ሰው በልቶ የጠገበ የማይመሥለው ቅን ሰው መሆኑን ወዳጆቹና ደንበኞቹ ይመሠክሩለታል። አቶ አረጋ በአሁን ሰአት በስራው ላይ ትልቅ ተግዳሮት የሆነበት በበሬ ግዥ ወቅት በሬ የሚሸጠውና ደረሰኝ የሚሰጠው የተለያየ መሆኑንና የደረሰኙም ሕጋዊነት ችግር እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ በመጥቀስ ይህ የሚስተካከልበት መንገድ በመንግሥት በኩል እንዲመቻች ጠይቀዋል። አቶ አረጋ ወደፊት ባለኮከብ ትልቅ ሆቴል ለመገንባት ህልም እንዳላቸውና ግስጋሴያቸውም ወደዚያው መሆኑን ተናግረዋል።
إظهار الكل...
ድምፃዊ ተሙ የሽንብራው ጥርጥር :- አርሰናል ዋንጫ ከበላ በሬ አበላለው ዓመቱን ሙሉ ጉርሻ ፔጅ ስለ አርሰናል ሲዘግብ በኮሜንት ለአርስናል ሲደግፍ የነበረው እንዲሁም የአርሰናል ቀንደኛ ደጋፊ የሆነው ድምፃዊ ተሙ (የሽንብራው ጥርጥር) ከአሜሪካ🇺🇸 ቃል ገብቷል አርሰናል ዋንጫ ከበላ ይባላልም እሷ ና ጏደኞቹ ሙሉ በሬ አርደው እናበላለን ብሏል::
إظهار الكل...
👍 4🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ጊዜ የሙጋቤ ልጅ ቢሮው ሂዶ "አባዬ ለሴት ጓደኛዬ ዘመናዊ ፌራሬ መኪና ልገዛላት ስለምፈልግ ገንዘብ ስጠኝ!" ይለዋል። ሙጋቤም ቁጭ በል ይለውናው "ለመሆኑ ግንኙነት ጀምራችኃል?" ይለዋል። ልጁም "ግንኙነት እንኳን የለንም። ጡቶቿን አንድ ቀን ዳስሻቸው እንዴት ደስ ይላሉ መሰለህ አባዬ!" ይለዋል። ሙጋቤም ኮስተር ብሎ "እና አንድ ቀን ጡቷን ስላስዳበሰችህ ነው ፌራሬ መኪና ለመግዛት ገንዘብ የምትጠይቀኝ?" ሲለው ልጁም "አዎ! ግን ለምን ጠየቅከኝ አባዬ?" ይለዋል! ሙጋቤም ቀዝቀዝ ብሎ "አይ ልጀ! 3 ዓመት ሙሉ ጡቶቿን ላጠባችህ ሴት(እናትህ) አንድም ነገር እንድገዛላት ጠይቀኸኝ አታውቅም። ዛሬ ግን አንድቀን ብቻ ጡቶቿን ላስዳበሰችህ ሴት የብዙ ሚሊዮን ዶላር መኪና እንድገዛ ስትጠይቀኝ ገርሞኝ ነው!" .......... እና ምን ለማለት ነው ከምንም በፊት እናቶቻችን ለማስደሰት እንሞክር❤😍🙏 Via:- Fitness Ethiopia
إظهار الكل...
👍 6
ከታክሲ ረዳትነት የተነሳው ድምጻዊ 3.8 ሚሊየን ብር የፈጀውን አልበሙን ሊለቅ ነው መቼም ለሚወዱት ነገር የሚከፈለው ዋጋ እንዲሁ በቀላሉ የሚተመን አይደለም። ደሳለኝ መርሻም የገጠመው ይህ ነው። የመጀመርያ አልበሙ ያሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የታክሲ እረዳት እየሰራ ባለበት ወቅትነበር። ያኔ አንድ ሙዚቃ አልበም ለማሳተም የሚያስፈልገው ወጪ ይህ ነው አይባልም። ይህ ሁሉ ውጣውረድ 7ተኛውን የጉራጊኛ አልበም ማለትም ኑድኒያን አስመርቃለሁ ብሎም አስቦም አያውቅም . . . የደሳለኝ መርሻ ህይወት ጥሪውን ተከትሎም ከዚህ ቀደም ስድስት አልበሞችን ማለትም "ፍረህ ደነና በ1994 ዓ.ም፤ "መገናኘ 19961 ግነኖ 19981 “አያርሴ" 2001፣ "ሒታኒያ 20041 "ያሚያሚና 2009 ዓ.ም ለሙዚቃ ቤተሰቡ አድርሷል። ባለፉት 20 አመታትም ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን ሰጥቷል:: ያ ሁሉ ልፋቱ ከነ ጋሽ መሀሙድ አህመድ፣ ከ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ እና ከሌሎች አንጋፋ ድምፃውያን ተርታ እንዳሰለፈውም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፣ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ አኑሯል፡፡ ጉራግኛ መስማት የማይችሉ ሰዎች አንዱ የሚያጎድሉት ነገር ቢኖር በደሳለኝ የሙዚቃ ግጥሞቹ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ፣ የባህል፤ ማህበራዊ ጉዳዮች ውስጥ ያሉ አስገራሙ ፍልስፍናዎችና እይታዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በአሁኑ ሰአት አርቲስት ደሳለኝ መርሻ ቁጥር 7 የሙዚቃ አልበሙን ይለቃል፡፡ እጅግ ፈታኝ የሙዚቃ አለም ውስጥ እያለፈ ያለው ይህ አዲሱ አልበም፣ ደሳለኝ መርሻ ራሱ ከሰራቸው የቀደሙት ስድስት ሆኑ ሌሎች አቻ ስራዎች በተለየ መልኩ አዳዲስ የሙዚቃ ቴክኒኮችና የጉራግኛ ሙዚቃ ጠቅላላ መልክ የሚቀይር ስራችን በመስራት ላይ በመሆኑ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ይሆናል፡፡ አልበሙ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው፡፡ እልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ እራሱ ደሳለ” መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፤ ዘነበ መርሃባ፤ ሀብታሙ አብርሃም፥ አለማየሁ ወልዴ የተሳተፉ ሲሆን በቅርንብር አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፤ ሰማገኘው ሳሙኤል፤ ፋኑ ጊዳቦ፤ ቢኒእነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞ™ ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒአንዴ ተሳትፈዋል፡፡ ማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም የአሸነው ሲሆ በአርቲስቱ Desalegn Mersha ዩ-ቲዩብ ቻናልና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ ይገኛል፡፡ ሲዲውን ኪነ ኢንተርቴይመንት አሳትሞ ያከፋፍለዋል ተብሎ ይጠበቃል። ኑድኒያ ማለት የተወደደች እንቁ ሴት ማለት እንደሆነ ሰምተናል።
إظهار الكل...
👍 1
ጎሳዬና ቤተሰቡ - በዮርዳኖስ ወንዝ "በመልከአ ምሕረት አባ ስብሐት ገብሬ - በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ዋና ፀሐፊ አስጎብኝነት የአምላካችን የእግዚአብሔርን በረከት ተቀብለናል :: እድሜ ከጤና ይስጥልን እናመሰግናለን 🙏🏽 . ሌላው በግሌ እንደተዓምር ያስቆጠረኝ ነገር በዮርዳኖስ ወንዝ ሆነን ያጠለቅነው የመጠመቂያ ልብስ ነው:: በዚህ ጊዜ ማንም ጎብኚ ይመጣል ተብሎ ስለማይታሰብ የመጠመቂያ አልባሳት የሚሸጡባቸው ሱቆች በሙሉ ዝግ ናቸው :: ሆኖም ቅዱስ መፅሐፋችን "እግዚአብሔር ያዘጋጃል " እንዲል ፈጣሪ ከበረከቱ ጎድለን እንዳንመለስ በሚመስል እነኚህን በቁጥር 3 አልባሳት ብቻ ከልብስ መቀየሪያ ክፍል ውስጥ አገኘሁ ብዬ ስለእውነት ልመሰክር ወደድኩ !!! እንዲህ በፈጣሪ የታዘዘ በረከት በሁላችሁም ቤት ይግባ 🙏🏽🙏🏽🙏🏽 !!!" ጎሳዬ ተስፋዬ
إظهار الكل...
🥰 3
በቲክቶክ ለታማሚዋ የተሰበሰበውን ብር ይዞ የተሰወረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ። ምህረት ሀደራ የተባለች አህታችን ያልፍልኛል ቤተሰቤንም ካሉበት ችግር አግዛለው ብላ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሀገር ብትሄድም ነገሮች እዳሰበችው ሳይሆን በተቃራኒው ጭኗ ላይ ከፍተኛ እባጭ በመውጣቱና ወደ ካንሰር በመቀየሩ ችግር ውስጥ ትገባለች። ህጋዊ አለመሆኗ ደግሞ በዛ ሀገር መታከም አለመቻሏ ችግሩን ያበዛባታል። ይህን በሽታ ይዛ ለሁለት አመት ከቆየች በኋላ ካቅሟ በላይ ሲሆንባት ጉዳዩን ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘው በመምጣት በመላው አለም ያሉ ኢትዮጲያዊያን በማገዝ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት እሷም ወደ ሀገር ገብታ እድትታከም እሷን በኤርፖርት በመላክ የተሰበሰበውን ብር በአቶ ተስፋዬ ስዩም በሚባል ተጠርጣሪ በኩል እንዲደርሳት ቢላክም አቶ ተስፋዬ ስዩም ገንዘቡ አካውንቱ እደገባለት እራሱን ለመሰወር ቢሞክርም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ፖሊስ መምሪያ ከቅን ልቦች በደረሰው አቤቱታ እና ጥቆማ መሰረት ባደረገው የነቃ ክትትል በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋሉን ቅን ልቦች ለፋስት መረጃ ባደረሰው መልዕክት ያሳያል። ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባህልና እሴቶቻችንን የምናሳድግበት ለተቸገረ የምንረዳዳበት እንጂ ከነበርንበት የዃሊት የምንሸራተትበት መሆን የለበትም ሲሉ ቅን ልቦች መልዕክት አስተላልፏል ግለሰቡ በአሁን ሰአት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ፖሊስ መምሪያ ይገኛል። Source: FastMereja
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል! የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል። " በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት ተጠርጣሪው በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ በጩቤ_በመውጋት የተማሪዋ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል " ሲል ፖሊስ ገልጿል። ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል። የከተማው ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጭ እንደሆነ አመልክቷል። ተጠርጣሪው የግቢ ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈጸመ ገልጿል። በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች " ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው " በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው እየኖሩ የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል። Via - AssosaPolice የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
إظهار الكل...
👍 8
ላገባ ነዉ👫 ታዋቂዉ አለም አቀፍ ቲክቶከር ናፒ ኢትዮጵያዊዋን ጉብል በእጄ አስገብቻለሁ የሚቀጥለዉ ሣምንት በቤተክርስቲያን ስርአት አገባለሁ ሁላችሁንም ጋብዣለሁ ብሏል። 🌼🌼🌼 👉የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ: https://t.me/+mGvhgC8uMxRjZGZk
إظهار الكل...
ተወዳጇ ተዋናይት ቃልኪዳን ጥበቡ በእናቷ ወርቅ ተሸለመች። በበርካታ ፊልሞች ላይ በባለሙያዎች እና በተመልካቾች ተወዳጅ የሆነችው ተዋናይት ቃልኪዳን ጥበቡ በትወና ከፍ ብላ የተሳተፈችበት "ትዝታ" የተሰኘ ፊልም ትናንት ተመርቋል። ይህ ብርታቷን ጥንካሬዋን እንዲመለስ ከእግዚአብሔር በታች ከጎኗ ለነበራቹ በሙሉ እናቷ በመድረኩ አመስግነው የወርቅ ሃብል በተመልካች ፊት መድረክ ላይ ሸልመዋታል።
إظهار الكل...
👍 7