Nathan casting agency
الذهاب إلى القناة على Telegram
The best place to get the best casting jobs Our services -casting models - for music clips - movies - series dramas - fashion shows - television shows Contact: 0920358051
إظهار المزيدEthiopia16 170الفئة غير محددة
408
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ይሄን ምስል ወገን ልብ ብለን እንመልከተው!!!!
ጌታችን ዘውድ ኣላረገም ይሄን ምስል ተጠቀሙ ምትለዉ እኮ እህተ ማርያም ምትባለዋ መናፍቅ ናት የማርያም ልጅ ዘውድ ማረግ የለበትም ትላለች eotc ብታዩ እኮ ስለሷ ብዙ ነገC ትሰሙ ነበር ባለማወቅ እንዳታረጉ ሌላ ካላችሁ እሱን አርጉ
አደራ አንሸወድ የምናየው ስእል አድኖ ላይ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘውድ አላረገም እና ምእመናን አንታለል። #Share እናድርግ ለሌሎች እናዳርስ!!!!!!!
እባካችሁ እናስተውል!!!!!!!
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 34(የመጨረሻው ክፍል)
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
.... ከተመረኩኝ በኃላ ብዙ ነገር አስብያለሁ ኢንሸ አላህ ይሳካል እኔ እና ሳሉ ከተመረቅን በኃላ ጀምአችንን የበለጠ ለማጠናከር አስበናል ወይኔ ለካ ትልቅ የረሳሁት ነገር አለ የሳሉ ወንድም ሊያገባኝ እንደሚ
ልግ ነግሮኛል ጥያቄው እኔንም በጣም አስደስቶኛል ግን ያው ለወጉ ያህል ወዲያው ፈቃደኝነቴን አልግረው አልፈለኩም ነገ እነግረዋለሁ ብዬ አስቢያለሁ ሳሉ ቀድማኝ ሁሉን ነገር ብታውቀም እንዲሁ ትወቀው ብዬ ነግሬያታለሁ በጣም ደስተኛ እንደሆነች ከፊቷ ላይ ማንበብ ችያለሁ ሙአዝ እና ሳሉም ካሰብኩት በላይ ሆነዋል እሱም ለትዳር ጠይቋታል መስከረም ላይ ኒካህ ለማሰር አስበዋል በጣም ደስ ብሎኛል ከተመረቁ በኃላ ይጋባሉ አሁን ብዙ ነገር ተቀይሮዋል ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ ይዟል ፡፡ሳሉ ከዩንቨርሲቲ ተመልሳለች ነገ ከጁምአ በኃላ ዝግጅቱን ለማዘጋጀት ተስማምተናል ለአጓቴ አስቀድሜ ነግሬዋለሀለ ነገ ጁምአንም ከሳሉ ለመስገድ ተስማምተናል፡፡
፡
ዛሬ በጠዋት ነው የነቃሁት ግን የሆነ ነገር ከብዶኛል ዝግጅቱ ጋር መሄድ ደበረኝ ለምን እንደሆነ እንጃ
ሸወር ወስጃለሁ አጎቴ እቤትነው አሎጣም አብረን እንወጣለን ብሎኛል አሁን ልወጣ ነው.....
....ብሎ ዲያሪው አበቃ መጨረሻውን ማወቅ በጣም ፈልጊያለሁ ማንን ነው የምጠይቀው እማዬ እንድጠይቃት ባትፈቅድልኝም አሁን ግን የግድ መጠየቅ ስላለብኝ ልጠይቃት ነው ወደ ሳሎን ቤት ሄድኩ እማዬን ሳሎን ቤት አጣኃት በዚህ ማታ የት ሄደች ብዬ ወደ ውጪ ስወጣ በረንዳ ላይ አገኘኃት ብቻዋን በረንዳው ላይ ተቀምጣለች
.... እማ ምን ሆንሽ
.....ምንም ሰሚሬ ምንም አልሆንኩም
.....እና ብርድ ላይ ብቻሽን ምን ትሰሪያለሽ
..... ምንም እንዲሁ ነው ያለፈ ሂወቴን እያሰብኩ ነው አየሩም ደስ ይላል
....እሺ ወደ ውስጥ ግቢ በጣም ይበርዳል
..... እሺ ግባ እመጣለሁ
ብለኝ አቀረቀረች
..... አብረን እንግባ እጂ ተነሺ
...ትንሽ መቆየት እፈልጋለሁ አንተ ግባ
..... ካልገባሽ እኔም አልገባም
.... ሰሚሬ ተው እባክህን አታስቸግረኝ ዛሬ ከፍቶኛል
..... ምን ሆነሽ ነው ለምን ከፈሽ እማ
እማዬን ሲከፋት ማየት አያስችለኝም ከእሷ የበለጠ እኔን ነው የሚከፋኝ እማዬ ሳትመልስልኝ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ውስጥ ገባች ተከትያት ገብቼ በሩን ዘጋሁት አብሬያት ተቀመጥኩኝ ቤታችን እንዲህም እንዲህ ነው ጭራሽ እንዲህ ዝምታ ተውጦ እማዬ ምን አንደሆነች በድጋሚ መጠየቅ አልፈለኩም እራት ላቅርብ ብዬ ጠየኳት አንገቷን በመነቅነቅ አዎንታዋን ገለፀችልኝ እራት አቀራርቤ ድብርቷ እንዲጠፋ እየቀለድኩ አሳኳት ሳቀችልኝ ድብርቷን እንደመርሳት እያለች ነው አራት ከበላን በኃላ ትንሽ ተጨዋወትን እና ስለ ሙና ልጠይቃት ፈልጊያለሁ ዳር ዳር እያልኩ ነው እኔ የምልሽ እማ አስቲ ስለ ሙና ንገሪኝ አልኳት እንዳትቆጣኝ እየተሳቀቀኩ "አንተ ልጅ ዛሬ ከሙና ጋር ምንድን ነው ያ ያያዘህ እሲቲ ተወኝ" አለችኝ መልስ መስጠት አቃተኝ በድጋሚ ያ የሚጨንቅ ዝምታ ሰፈነ "ቆይ ግን ለምንድን ነው የጠየከኝ "አለችኝ ምን ልበላት ዝም አልኳት"ንገረኛ እንጂ " አለችኝ ልንገራት አልንገራት እያልኩ ነው በቃ ልንገራት የግድ መጨረሻውን ማወቅ አለብኝ ያነበብኩትን እንዳለ ነገርኳት እማዬ አንገቷን ደፍታ እያለቀሰች ነበር ምነው እማ አልኳት እያለቀሰች ይሄን ነገረችኝ
" የዛ ቀን ከአጎቷ ጋር ስቶጣ ያለመደባትን አንተን ስማህ እኔንም ደና ወይ ብላ እጇን ስተዘረጋልኝ የማይሆን መልስ ሰጥቻት ነበር እሷ ግን ፈገግ ብላ ከአጎቷ ጋር ወጡ እና የሄደችው የሆነ ዝግጅት አለን ብላ ነበር እዚህ ሰፈር አብሯት የሚሄድ ልጅ እና ሌላኛዋም ሴት ጓደኛቸው አብራቸው እንደነበረች አባትህ ነግሮኛል " ይሄን ተናግራ ዝም አለች እ..እ ከዛስ አልኳት እማዬ ሳግ እየተናነቃት ቀጠለችልኝ " እና አባትህ ታክሲ አሲዟቸው ሄደ ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ በማያውቀው ስልክ ተደውሎ ሙና ከባድ የመኪና አደጋ እንደ ደረሰባት እና ሆስፒታል እንዳስገቧት አረዱት አባትህ የነገሩት ሆስፒታል እስኪደረስ ሙና አልጠበቀችውም የደረሰባት የመኪና አደጋ በጣም ከፍተኛ ስለነበር እሱ እዛ ከመድረሱ በፊት ቤተሰቦቿን ተቀላቀለቻቸው ሁለቱ ጓደኞቿ ከ እሷ ቀድመው ነበር የሞቱት ብለኝ ተንሰቅስቃ አለቀሰች
..... እኔ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም በተቀመጥኩበት ደርቂያለሁ ሙና እንደ ሞተች አስቀድሜ ባውቅም የጓደኞቿ መሞት ግን አሁን ነው የሰማሁት፡፡
እማዬ ለመናገር እየሞከረች ነው ጆሮዬን ሰጥቿት በድጋሚ ማዳመጥ ጀመርኩ እና አባትህም እሷ ከሞተች በኃላ ሀዘኑን መቋቋም አቃተው ደም ግፊቱም ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት መጣ እሱም ከእሷ ሞቶ በኃላ ብዙም ሳይቆይ ሞተ፡፡ ስለ ሙና መናገር የማልፈልገው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ አለችኝ በዝምታ ተመለከትኳት አንድም ቀን በእኔ ተደስታ አታውቅም ሁሌም እንዳስከፉኀት ነበር እሷን ሳስብ ሁሌም ውስጤ ሰላም ያጣል ፡፡
አለችኝ
፡
፡
፡
፡
፡
፡
ተ ፈ ፀ መ
Join me👇
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 33
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
.... ውጤት ተቀብለናል ሁላችንም አልፈናል ሂዊም አልፋለች እነ ሪቾ ወድቀዋል ባይወድቁ ደስ ይለኝ ነበር ግን ምን ማድረግ አይቻልም ......
.
.
.
.
ከሁለት አመት በኃላ
.
ከአጎቴ ሚስት ጋር ተጣልተን አክስቴ ነበርኩ ለሁለት አመት ስወጣ ዲያሪዬን ትቼ ነበር የወጣሁት አሁንም አጎቴ ስለታመመ ነው የተመለሰኩት ብቻ ሁሉም ነገሮች መልካቸውን ቀይረዋል የሳሉ ወንድም ሳሎደው አልቀርም እሱ እንደዛው ይመስለኛል የአስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ወደ ዩንቨርሲቲ ልንሄድ ነው ከሳሉ ጋር ተለያይተናል እሷ ከ በህር ዳር ዩንቨርሲቲ ነው የተመደበችው እኔ ደግሞ አዲስ አበባ ሙአዝ ደግሞ መቀሌ ነው እኔ እዚሁ ስለሆንኩ ብዙም አልተጨነኩም ግን ከሳሉ ተለይቼ መቆየት አልችልም በጣም ከፍቶኛል ግን እሷን ላለ ማሳዘን ምንም እንዳልመሰለኝ እያስመሰልኩ ነው ፡፡
አጎቴ ደም ግፊት አለበት እና ከአጎቴ ሚስት ጋር ተጣልተው መሰለኝ የተነሳበት ቢድንልኝ ምኞቴ ነወሸ ኢንሸ አላህ ይድናል እያልኩ እራሴን ለማሳመን እየሞከርኩ ነው፡፡
ዛሬ ትምህርት ጀምሪያለሁ አጎቴ በሽታው ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት ነው በጣም እያሳሰበኝ ነው ከአጎቴ ሚስት ጋር ብንታረቅም ብዙም አንነጋገርም የተጣላንበት ነገር ለመርሳት እየሞከርኩ ነው አልቻልኩም የተጣላነው ከነ ቁርአን ቤት አርፍጄ ስለመጣሁ ነበር እንደ አጋጣሚ ከሳሉ ጋር የሆነ ወሬ ይዘን እየተጨዋወትን ሰአቱ ሄደ እና ወደ ቤት ስገባ እንደለመደችወሸ ሰደበችኝ ግን "አላህም አውቆ ነው ወላጆችሽን የወሰደብሽ በሂወት ቢኖሩማ አቃጥለሻቸው ነበር ለነገሩ ምን ታደርጊው የእናትሽ ቢጤ " እንዲህ ስትናገረኝ አልቻልኩም ነበር እኔም ተናገርኳት እኔን የፈለገችውን ትናገር እናቴ ግን ምን አደረገቻት ሳስበው በጣም ያናደኛል ፡፡
ከሳሉ ወንድም ጋር አልፎ አልፎ እንገናኛለን ብቻችንን መገናኘታችን ግን ብዙም ደስ አላለኝም
.
ጊዜው እየበረረ ነው እኔ የዚህን አመት ትምህርት ልጨርስ ነው በነገራችን ላይ ሳሉ የአመቱ ግማሽ ላይ መታ ነበር እንዴት እንደከሳች ጠወላልጋለች አየሩ አልተስማማትም መሰለኝ .... እና በቅርቡ ትመጣለች ብዬ ተስፉ አደርጋለሁ
እረስቼው አጎቴን ተሽሎታል ማለት ይቻላል አልሀምዱ ሊላህ በጣም ለውጥ አለው ስራ መውጣት ጀምሮዋል በጣም ደስ ብሎኛል ፡፡
ጀምአችን አሁንም አልተበተነም አንዱ ሲወጣ አንዱ ሲገባ እንደምንም እስከዛሬ አቆይተነዋል ሳሉ ከመጣች በኃላ አንድ አነስ ያለ ዝግጅት አዘጋጅተን ለመሰባሰብ አስበናል
፡
፡
የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል
join
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 32
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
.... የሁለተኛ ሴሜስተር ትምህርት ከጀመርን በጣም ቆይተናል ሞዴል ፈተና ልንፈተን ነው ከዛ ከአስራ አምስት ቀን በኃላ ማትሪክ እንወስዳለን ልንገላገለው ነው
ከነ ሪቾ ጋር መንገድ ላይም ብንገናኝ ተዘጋግተን ነው የምንተላለፈው እነሱም አያናግሩኝም እኔም አላናግራቸውም አምና ቀጥረውኝ ከጠፉ በኃላ ምንገጥሟቸው ነው የቀሩት ብዬ ልጠይቃቸው ሄጄ ነበር በእኔ ቤት ጥሩ መሆኔ ነበር ለካ እነሱ ሙድ እየያዙብኝ ነበር እና ሲያዩኝ ተሳስቀው ትተውኝ ሄዱ ከድሮ ጭራሽ ብሶባቸዋል እነሱን መውቀስ አልፈልግም ምክንያቱም እኔም ዛሬ እንደ እነሱ እሆን ነበር አላህ በሙአዝ ምክንያት እንዲህ እንድሆን ስለረዳኝ እንጂ በእርግጥ የሚመክራቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል ያ ሰው እኔ ብሆን ደስ ይለኝ ግን የሚሰሙኝ አይመስለኝም ትላንት ከእነሱ ጋር እንደዛ እንዳልነበርኩ ዛሬ ልምከራቹ ብዬ ብነሳ ማን ይሰማኛል ማንም ግን እሲት የምችለውን ያህል እሞክራለሁ፡፡
ኡፍፍፍፍፍ ተገላገልኩ ፈተና ተፈትነን ጨረስን አሁን ፈታ ልበል በነገራችን ላይ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ከፈተና በኃላ ጉዞ አዘጋጅተዋል ያዘጋጁትም ባቦጋያ (ደብረዘይት) እንጂ መሄድ ፈልጌ ነበር ግን ሀሳቤን ቀየርኩ ምክንያቱም የአልኮል መጠጥ ምናምን ብቻ ለተማሪ የማይሆን ነገሮችን አካተዋል በዋናኝነት አልኮሉ አንደኛ ነገር ሀራም (ወንጀል) መሆኑ ሁለተኛ ደግሞ መጠጡ ይዞት ሊመጣ የሚችለውን ነገር አሰብኩና ተውኩት ፡፡
እነ ሪቾ ይሄዳሉ እንዴት ላስቁማቸው በድፍኑ አትሂዱ ብለቸው ከ ሪቾ ምላስ ውጪ ምንም እንደማላገኝ አውቃለሁ ቢሆንም ዝም ብዬ አላየኃቸውም ሙአዝ የነገረኝን ነገር ነገርኳቸው ግን ከጠበኩት ውጪ ነበር ምላሻቸው ሪቾ ምንም ብትል አይደንቀኝም ከሀና መስማቴ ነው ያስገረመኝ ከእኛ ትሻላለች ብዬ የማስባት ልጅ እንዲህ መናገሯ... ሙአዝ የነገረኝን ከነገርኳቸው በኃላ እና አትሂዱ ልላቹ ነው አልኳቸው ሀና "አንቺ ዛሬ ከአንድ ፋራ ጋር ውለሽና እና ልትመክሪ ምናምን ትሞክሪያለሽ እንዴ ይሄን ምክርሽን ለግጣምሽ ንገሪው አለችኝ" ሁሉም ተሳሳቁብኝ እየገረመኝ ከአጠገባቸው ዘወር አልኩላቸው ማድረግ የምችለወሸ ይሄን ብቻ ነው ፡፡
እኛ እነ ሳሉ ቤት ሄደን እዛ አሳለፍነው ወንድሟም ነበር ሙአዝም እሱን ፈልጎ መቶ ስለነበር አብረን ፈታ ብለን ዋለን ሲመሻሽ እኔ ወደ ቤት ሄድኩ ፡፡
እረስቼው ቁርአን የመጀመሪያዬን ለኸትም (ልጨርስ) ነው ትንሽ ነው የሚቀረኝ ሳሉ በእዚህ እንደኮረችብኝ ነግራኛለች አንዴ ከ አኸተምኩ በኃላ የጀማሪ ኪታብ እንደምጀምርም ነግራኛለች ለዚህ ለሳሉን ለዚህ ውለታዋ ምን እንደምከፍላት እንጃ ሳሉ እህት ፣እናት፣ጓደኛ ፣ኡስታዝ፣ሁሉ ነገሬ ሆናልኛለች ምንም ማለት አልችልም አላህ ኸይር ጀዛዋን ይክፈላት .....
፡
፡
ይቀጥላል
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 31
✍ሂክማ ጀማል
፡
፡
....ዛሬ ትምህርት ቤት ለምዝገባ ሄደናል ሙአዝም መቶዋል ስላገኙሁት ደስ ብሎኛል ሳሉም መታለች መስከረም አምስት ትምህርት እንጀምራለን ፡፡
.
.... ትምህርት ከጀመርን ዛሬ ሁለት ቀን ሆኖናል እንደድሮዎ ከነ ሪቾ ጋር አይደለንም ተበታትነናል ደግነቱ እኔ እና ሂዊ አንድ ክፍል ነን ቢያንስ ብቻዬን አይደለሁም ዘንድሮ ማትሪክ ተፈታኝ ስለሆንን ማጥናት ከጀመርን ቆይተናል ትምህርት ብዙም አልተጀመረም ይሄን ክፍተት ተጠቅመን ጥናታችንን እያጧጧፍነው ነው ፡፡
የትምህርት ቤት ጀምአችን አሪፍ እየሆነ ነወ ከተማሪዎች ውጪ ሰራተኞችም ገብተውበታል በተለይ እርዳታው ላይ የሰበሰባቸው የሳሉ ወንድም ነው ከእኛ ጀምአ ውጪም ለየግላቸው እየሰሩ ነው ብቻ አሪፍ ነው ፡፡
...ይሄን ሰሞን ምንም ክፍት ሰአት እያገኘሁ አይደለም ትምህርት ከዛ ጥናት ቁርአን ቤት የቤት ውስጥ ስራ ተደራረበብኝ የምፅፍበት ሰአት እያገኘሁ አይደለም በነገራችን ላይ ትምህርት ከተጀመረ አራት ወር አልፎዋል ለፋይናል ፈተና እየተዘጋጀን ነው ከ አራት በኃላ ማትሪክ እኖስዳለን እስክንፈተን ድረስ ጨንቆኛል ፈታ የምልበት ቀን ናፈቀኝ ግን በጣም ደስ እያለኝ ነው የማጠናው ምክንያቱም ለማምጣት ያለምኩትን ውጤት እያሰብኩ ስለማጠና ደስ እያለኝ ነው የመጠናው ብቻ ከአሰብኩት ውጪ እንዳይሆን እንጂ.....
... ፈይናልን ተፈትነናል ሁላችንም ማለት ይቻላል አሪፍ ውጤት ነው ለነገሩ በደንብ ስለተዘጋጀንበት ብዙም አልከበደንም እንግዲ ውጤት ቀጣይ ሳምንት ተብለናል እየጠበቅን ነው የሰሞኑ አዲስ ነገር እኔ እና የሳሉ ወንድም በጣም ተቀራርበናል ቅርርባችን ጤነኛ አይመስልም ብዙ ግዜ ለማጥናት እነ ሳሉ ቤት ስለምሄድ ብዙ ግዜ እንገናኛለን ሳሉ ነገረ ስረችንን እያየች ከመሳቅ ውጪ ምንም አላለችም ፡፡
ከሙአዝ ጋር እንደሌላ ጊዜው ትምህርት ቤት አብራን እንሄዳለን አብረን እንመለሳለን እሱ አብዛኛውን ጊዜ የሚያጠናው ሰፈርቸው ያለው ቤተ-መፅሀፍት ውስጥ ነው እኛ ደግሞ እነ ሳሉ ቤት ነው የምናጠናው እንደበፊቱ ከእኛ ጋር አያጠናም ስለዚህ ብዙም አንገናኝም ፡፡ የፈተና ውጤት ከተቀበልን በኃላ አስራ አምስት ቀን እረፍት ተሰቶናል ፡፡
.....ከአስራ አምስት ቀን በኃላ ወደ ትምህርት ጀምረናል ውጤት የሚነገረን አርብ እንደሆነ ተነግናል
.... ውጤት ከጠበኩት በላይ አሪፍ ሆኖዋል እኔም አንደኛ ወጥቻለሁ በጣም ደስ ብሎኛል የተመኘሁትን አግንቻለሁ ለካ ለፍቶ የልፋትን ውጤት ማግኘት እንዲህ ደስ ይላል ደስታዬ ብዛት ጩሂ ጩሂ አስባለኝ ግን ሳሉ በቅድሚያ አልሀምዱሊላህ እንድል ነገረችኝ የደስታ እንባ አነባሁ ፌቴ በሀሴት ደመቀ እንደለመድኩት ውጤቴን ለአጎቴ ነገርኩት እሱም በጣም ደስ ብሎት አቀፈኝ "አኮራሽኝ ልጄ አለኝ "አኮራሽኝ ከሚለው ይልቅ ልጄ የሚለው ቃል ነበር ቀድሞ ወደ ጆሮዬ የደረሰው አቆለማምጦ ይጥራኝ እንጂ ልጄ ብሎኝ አያውቅም ነበር ይሄ ቃል በደስታ ላይ ደስታ ጨመረልኝ ዛሬ ግን የአጎቴም ሚስት ተደስታለች እሷም ደስ ብሏት ግንባሬን ሳመችኝ ገና ዛሬ የሚያኮራ ስራ ሰራሽ አለችኝ ያው ደስ ቢላትም ከምላሷ አላመለጥኩም ድንገት ነበር "ቆይ ቆይ ግን የራስሽ ውጤት ነው ስልሽ በራስሽ ሰርተሽ ነው ወይስ በኩረጃ ነው እ እስቲ ንገሪኝ" አለችኝ ቆይ እንዴት እንደዚህ አይነት ጥያቄ ይጠየቃል የቱንም ያህል ብኮርጅ እንዴት ነው እንደዚህ አይነት ውጤት ላመጣ የምችለው ደግሞ እኔ በእራሴ ሰርቼ እንደዚህ አይነት ውጤት ማምጣት አልችልም ማለት ነው ግን በጣም ነው ያዘንኩባት ቢሆንም እድሜ ለነ ሳሉ ለክፋም ለደጉ ፈገግ ማለትን አስተምረውኛል ፈገግ እያልኩ አው በኩረጃ አልኳት "እኮ እንዲህ በይኛ "አለችኝ አጎቴን "እሳን ተያትና ሙኒ ማሻአላህ አላህ ያበርታሽ የኔ ልጅ"አለኝ በድጋሚ ልጄ አሚን አባዬ ብለው ምንያህል ደስ ባለኝ ግን አይሆንማ አሚን አጎቴ ብዬው ከእቅፋወደ ውስጥ ገባሁ እሁድ የወላጆች ስብሰባ አላቸው አጎቴን እንዲሄድ ነግሬዋለሁ፡፡
..... ሳሉ የያዘችውን ውጤት አለቀቀችም እኔ እነደ አምናው ነው የመጣችው ለእሳ ብቻ ነው ለየት ያለ ሽልማት የተሸለመችው ሌሎቻችን አጋዥ መፅሀፍ ነው የተሸለምነው ሙአዝም አንደኛ ነው የወጣው ሁለታችን ደረጃችን እኩል ይሁን እንጂ ነጥባችን ግን ይለያያል በትንሽ ነጥብ ሙአዝ የበልጠኛል ሂዊን እረስቻት እሳም አሪፍ ውጤት ነው ያመጣችው አራተኛ ነው የወጣችው ብቻ ሁለችንም አሪፍ ውጤት ነው ያመጣነው ...
፡
፡
ይቀጥላል
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 30
✍በሂክም ጀማል
፡
፡
.... እነ ሙአዝ ከመጡ በኃላ ዝግጅቱን ጀመርን ቀኑን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍነው ሁሉም እቤት አርፍጄ ነበር የገባሁት ለአጎቴ ነግሬው ስለነበር ምንመ አላለኝም ሰኞ የፈተና ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት እንሄዳለን ፡፡
.
... ዛሬ የፈተና ውጤት ለመቀበል ሁላችንም ትምህርት ቤት መተናል ውጤታችን እንደጠበቅነው አሪፍ ነበር እኔ ባለው ከመጣሁት የተሻለ ውጤት ነው ያመጣሁት ሂዊም አሪፍ ውጤት ነው ያመጣችው በእዚህኛው ውጤቴ ከባለፈው የተሻለ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡
የዚህን አመት ትምህርት በዚህ ሁኔታ ጨረስን ዛሬ ውጤት ሰርተክፌት እንቀበላለን ሳሉ ያው እንደሚታወቀው አንደኛ እንደምትወጣ አያጠራጥርም ሙአዝ ደግሞ ከባለፈው በማሻሻል ሁለት ወይም አንድ የራሴን ግን አልገመትኩም ነበር እንደጠበኩትም ሳሉ አንደኛ ወጣች ሙአዝም አንደኛ ወጣ እኔ ደግሞ ባላሰብኩት መንገድ አስረኛ ወጣሁ በጣም ነው ደስ ያለኝ እንደዚህ አይነት ውጤት አልጠበኩም ነበር ለአጎቴ አስከማሳየው ድረስ በጣም ጨንቆኛል በዚህ አይነት አንደኛ ብወጣ ምን እንደምሆን እንጃ አነ ሳሉ በእኔ ውጤት በጣም ነው የተደሰቱት የዚህን አመት ትምህርት ጨርሰናል ፡፡
አጎቴ ውጤቴን ሳሳየው በጣም ነው ደስ ያለው ደስተኛ እንደሚሆን ባውቅም ይሄን ያህል ግን ደስተኛ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር ሰሚር የኔ ሚጢጢ እሱም አቅፎ ሳመኝ ምን አለበት ዛሬ የሳሉን ውጤት እኔ አምጥቼው በነበረ ነው ያልኩት ከቅናት የመጣ ሳይሆን በዚህ ውጤት አጎቴ እንዲህ ከተደሰተ አንደኛ ወጥቼ ቢሆን ኖሮ ምን እንደሚሆን እንጃ ....
ይሄን ሰሞን ምንም አዲስ ነገር የለም እቤት ውስጥ ስለምውል ነው መሰለኝ ትምህርት ከተዘጋ አስራ አምስት ቀን ሆኖዋል ትምህርት ለመጀመር አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ይቀረናል ቀኑን እየቆጠርኩ ነው ከሳሉ ጋር ቁርአን ቤት እንገናኛለን ሙአዝን ግን አላገኘውም በጣም ይናፍቀኛል በተለይ ሙኒ የምትለዋ ጥሪው በጣም ናፍቆኛል ግን ደግሞ ትምህርት ቤት ካልሆነ ማግኘት አልችልም እንግዲህ ትምህርት እስኪከፈት መጠበቅ አለብኝ ፡፡
... ቀኑ እየሮጠ ነው ይሀው ከፃፍኩኝ እራሱ አንድ ወር ሆነኝ እነደዚህ የቆየሁ አልመሰለኝም ነበር ለነገሩ የሚፃፍ ነገር ስላላጋጠመኝ ነው የተወሰነ ቀን የእናቴ አጎት ጋር ከአጎቴ ጋር ሄደን ነበር ከአጎቴ ጋር ነበር የሄድነው እሱ የዛኑ ቀን ተመለሰ እኔ ደግሞ አንድ አራት ቀን ቆይቼ ተመለስኩ አሪፍ ቀን ነበር ያሳለፍኩት፡፡ ምዝገባ ይሄን ሳምንት እንደሆነ ተነግሮናል ሙአዝም እንደሚሰማ ተስፋ አደርጋለሁ ....
፡
፡
ይቀጥላል
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 29
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
...አባዬ ብዬ አልጠራው ነገር አልጠራው ነገር ብጠራወሸ እራሱ የአጎቴ ሚስት አሽሙሯን አልችለውም እግሩ ላይ ተኝቼ ፀጉሬን እያሻሸ ሲያወራኝ የሚሰማኝን ስሜት ይሄ ነው ብዬ መግለፅ አልችልም አባት ያላቸው ልጆች ሁሉ እንዲህ እየተደረገላቸው የሚያድጉ ነው የሚመስለኝ ከዚህ በፊት ይሄ ነገር ያስቀናኝ ነበር አሁን ስለአገኘሁት በጣም ደስተኛ ነኝ ፡፡ አንዳንዴ ሳስበው እናትና አባቴ በሂወት ቢኖሩ ከእናቴ ይልቅ አባቴን የምወደው ይመስለኛል ብዙ ሰው ከአባቱ ይልቅ እናቱን ነወ የሚወደው እኔ ግን በተቃራኒው ነው ይመስለኛል አጎቴ ስለ አባቴ አካብዶ ስለ ነገረኝ ነው መሰል ስለ እናቴ ምንም አላውቅም ብቻ እኔ እናት ከማለት ይልቅ አባት ማለት በጣም እወዳለሁ ፡፡
... ለዝግጅቱ ወደ እነ ሳሉ ቤት ብቻዬን ሄድኩ ሙአዝ ከእኔ ቀድሞ ነበር የሄደው የሳሊሀ ቤተሰቦች ሁሉም ነገር አሪፍ አድርገው አዘጋጅተውታል ለወንድ ለብቻ ለሴት ለብቻ በተለያየ ክፍል ውስጥ አዘጋጅተዋል ምግብ በአይነቱ አዘጋጅተዋል የሚጠጣም እንደዛው እንግዶቹ የሚመጡት ለምሳ ነው የሳሉ ወንድም እና ሙአዝ እራሳቸውን ችለው መምጣት የማይችሉትን እነግዶች ለመምጣት መኪና ይዘው ወጡ እኛ እንዲሁ እቤት ውስጥ ሽር ጉድ እያልን የዝሁር አዛን ሰማን ኡዱእ አድርገን ከሰገድን በኃላ የጎደለ ነገር ካለ ማጣራት ጀመርን ከሰላት በኃላ ብዙም ሳይቆይ አንድ ሁለት ሰው መምጣት ጀመረ ቤት ውስጥ ከሳሉ አባት ውጪ ሌላ ወንድ አልነበረም እነሠ የመጡትም ወንዶች ነበሩ የሳሉ አባት ተቀበሏቸው እና ወደ ውስጥ ይዘዋቸው ገቡ ቀስ በቀስ ለወንዶቹ የተዘጋጀው ክፍል እንደመሙላት እያለ ነው ገና እነሙአዝ አልመጡም ለመጠባበቂያ እንዲሆን ሌላ ክፍል አዘጋጀን ሴቶቹም ጋር እየመጡ ነው ሴቶቹ ግን እንደወንዶቹ ብዙ አይደለም ያዘጋጀነው ክፍል ለሴቶች በቅቶዋል እነ ሙአዝ እየተጠበቁ ነው ግን አልመጡም ስንደውል ደርሰናል ያሉት ከ ሰላሳ ደቂቃ በፊት ነበር ታዲያ እስከ አሁን ለምን አልመጡም ትንሽ ጠብቀናቸው ካልመጡ ለመጀመር ተስማምተን መጠበቃችንን ቀጠልን ፡፡
በነገራችን ላይ የሳሉ ቤተሰቦችን በጣም አድንቂያቸዋለሁ ምክንያቱም በአሁኑ ሰአት ሁሉም ለየግሉ መኖር በጀመረበት ሰአት ተካፍሎ መብላት እየቀረ ባለበት ሰአት ይሄን ሁሉ ሚስኩኖችን ሰብስቦ መመገባቸው በጣም አስገርሞኛል አንዳንዴ ግን ስልጣኔ ባይመጣ እና እንደ ድሮዎቹ ብንሆን ያስብላል እንደድሮዎቹ መቻቻል እውነተኛ ፍቅር መተሳሰብ አብሮ መብላት ቢኖር አንተ ትብሽ አንቺ ትብስ እየተባባሉ መኖር ይሻል ነበር የአሁን ሰው ግን የምን መተሳሰብ የምን እውነተኛ ፍቅር የምን መረዳዳት ሁሉም ነገር የእውሸት መኖር ማስመሰል ሌላውን ከመርዳት ይልቅ ከ እሱ ላይ የቀረችውን ትንሽ ነገርም ብትሆን ለመውሰድ እና ባዶውን ለማስቀረት የሚሞክር ብቻ ነው ያለው ምን አልባት እንደ እነ ሳሉአ አይነት ቤተሰቦች ካሉ እንጂ ብቻ አላህ ይጨምርላቸው ምንዳቸውን እሱ ነው የሚከፍላቸው
ከረጅም ጥበቃ በኃላ እነ ሙአዝ መጡ .....
፡
፡
ይቀጥላል
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 28
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
ከቁርአን ቤት እንደተመለስኩ ቀጥታ ወደ ዲያሪው ነው የሄድኩት አልጋው ላይ ተቀምጬ ማንበቤን ቀጠልኩ
.... ዛሬ ፈተና እንጨርሳለን ዝግጅቱን ለማዘጋጀት ያሰብነው ቅዳሜ ቀን ነበር በነገራችን ላይ የሳሉ ወንድም ባመጣው ሀሳብ ተስማምተናል እና ለመምጣት የሚቸገሩትን እራሱ እንደሚያመጣቸው እና ሲመለሱም እራሱ እንደሚመልሳቸው ነግሮን ተስማምተናል ፡፡
.... እነ ሪቾ ዛሬ ከፈተና በኃላ እንደሚፈልጉኝ ነግረውኝ ነበር ከጨረስን በኃላ እንድንገናኝ የቀጠረኙ ቦታ ሄድኩኝ ረጅም ሰአት ጠበኳቸው ግን አልመጡም ሙድ እየያዙብኝ ነው እንዴ ወይስ ከፈተና አልወጡም ነው እኔ እንጃ የመጣሁትም ይቅርታ ሊጠይቁኝ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ደግሞ ሙአዝን እንዲጠብቀኝ ነግሬዋለሁ በዛ ላይ የጁምአ ሰላት እየደረሰ ነው ስድስት ሰአት አልፎዋል አምስት ደቂቃ ልጠብቃቸውና እሄዳለሁ ብዬ መጠበቀን ቀጠልኩ ግን አልመጡም ግን አልተናደድኩባቸውም ኡዝር(መልካም ምክንያት) ሰጠኃቸው የገጠማቸው ነገር ይኖራል እንጂ ቀጥረውኝ አይጠፋም ብዬ ወደ ሙአዝ ሄድኩ እሱም እጠብቅሻለሁ ያለኝ ቦታ ጥፋቱ የእራሴ ስለነበር እሱ ላይም አልተናደድኩም በጣም ቆይቻለሁ ሙአዝ ጁምአ ቀን አዛን ሳይተአዘን ነው ወደ መስጂድ መግባት የሚወደው አዛን እሰኪደረግ ድረስ መስጅድ ገብቼ በተረጋጋ መንፈስ ሀሳቤን ሰብስቤ ነው ኹጥባ መዳመጥ የምፈልገው ይላል እኔንም እሱ አስለምዶኝ በጊዜ ነበር የምገባው ዛሬ ግን ሳላረፍድ አይቀርም ብቻ አዛንም ተደርጎ ከደረስኩ ብዬ ወደ መስጅድ ሄድኩ ኹጥባው ሊያልቅ አካባቢ ነበር የደረስኩት መስጅዱ በሰጋጅ ተሞልቶ ስለነበር ቦታ አላገኘሁም ውጪ ላይ ሰግጄ ዳር ላይ ቆሜ ሳሉን ጠበኳት ቶሎ መጣች እንዳገኘኃት ስለ ሙአዝ ነበር የጠየኳት ብዙም እንዳልጠበቀኝ ነገረችኝ ስለዚህ አያኮርፎም ማለት ነው ለነገሩ እኔ እንጂ እሱ እንኳን ማኩረፍ ምናምን አያውቅም ስለ ሙአዝ እያሰብኩ ሳሉ እየጠበቀችኝ እንደነበር እርስት አድርጌው ነበር ምን አይነት ቀሽም ነኝ ሳሉ አንቺስ አልኳት" እኔ ምን ሙኒ" ብዙ ጠበቅሽኝ " አሁን ነው ያስታወስሽኝ" አለችኝ እንደ ማሾፍ እያለች እሷ እያሾፈች ትበል እንጂ እኔን ግን ስራዬ አሳፍሮኛል እኔም አንደማሾፍ እያልኩ "እና ከሙአዝ በፊት ስለ አንቺ ልጠይቅሽ ነበር " አልኳት እየሳቀች "አንቺ አዛ ዝም በይ " አለች አይ የምር ግን ሳሉ ብዙ ጠበቅሽኝ እንዴ ? "ብዙም አይደል አዛን መደረግ ሲጀምር ትቼሽ መጣሁ " አለችኝ ሙአዝ ከሄደ በኃላ ረጅም ሰአት ብቻዋን ነበረች ማለት ነው ሳሉ በአላህ ይቅርታ ብቻሽን አስጠበኩሽ ኸረ ሙኒ ምን እየሆንሽ ነው እኔ እንዲህ የምባል ሰው ነኝ ብላ ስታፈጥብኝ አይይይ አልኳት እየተቀላለድን ወደ ቤት ሄድን እንደተለመደው መለያያችን ቦታ ላይ ስንደርስ ተቃቅፈን ተሰነባበትን ፡፡
..ሙአዝና የሳሉ ወንድም ጥሩ ተግባብተዋል የልብ ጓደኛ ሳይሆኑ አይቀሩም ቅርርባቸው ከውጪ ለሚመለከታቸው የረጅም አመታት ጓደኛ እንጂ በቅርቡ የተዋወቁ አይመስሉም ብቻ ደስ ይላሉ ፡፡
ስለነገው ዝግጅት እያሰብኩ ነው እንዴት ይሆንልን ይሁን ካሰብነው በላይ አሪፍ እንዲሆን ምኞቴ ነው፡፡ ለአጎቴ ስለ ጀምአችን ነግሬው በጣም ደስ ብሎታል እና የምፈልገው ነገር ካለ እንድጠይቀው እና እንደሚያደርግልኝ ነግሮኛል ፡፡
አጎቴ በልጅነቴ ያጣሁትን ፍቅር እየሰጠኝ ነው አሁን የእውነት እንዳለው አጎት ሳይሆን አባቴ እመሰለኝ ነወሸ አጠራሬ ብቻ ነው ያልተቀየረው እንጂ ስለሱ የነበረኝን መጥፎ አመለካከት ፍራቻ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮዋል ቢሆንም መቼም አባዬ ብዬ አልጠራው....
፡
፡
ይቀጥላል
በ ህይወትክ ዉሥጥ የማትረሳቸው 18 ጓደኞች👨 እነማን ናቸው?ለነዚህ 18 ብቻ ይሄንን መልክት ላክ እኔ እንዳረኩት.ስንት ሰው መልሶ እንደሚልክልክ እናያለን!!በ ታማኝነት መላክ ጀምር !ለ 18ቱ ብቻ!ዛሬ የአለም የጓደኛሞች ቀን ነው.ይህንን መልክት ልዩ ለምትላቸው ላክ(ከፈለክ ለኔም ላንተ ልዩ ከምትላቸው ውስጥ ከሆንኩ!) ከ 1ሰው ብቻ 5 ከተመለሠልክ በዛ ሠው የምር ተወደካል ማለት ነው!!
😍😍❤️❤️❤️❤️😍😍😍😍😍💑💏💏💏👯♀️💕💖💜💗💛💚💋❤️💗💟💞💝
@fkrnahiwot
#ኢድ_ሙባረክ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሶቦቻችን እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ኢዱ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
@fkrnahiwot
ያልተፈታ ህልም
ክፍል 27
✍በሂክማ ጀማል
፡
፡
.... ከተመለስን በኃላ እኔ ወደ ቁርአን ቤት ሄድኩ ሳሉ በጣም አሪፍ እየቀራሁ እንደሆነ ነግራኛለች በሞራል ነው የምቀራው ፡፡
.
እንዲህ እንዲህ እያልን ወራቶች ቀናቶች ሳምንታትን እየፈጠሩ ሳምንታት ወራትን እየወለዱ ሶስት ወራቶች ተቆጠሩ እርዳታው ካሰብነው በላይ አሪፍ እየሆነልን ነው በነገራችን ላይ ሁልጊዜ እኔ ነገራቶችን ከረፈደ በኃላ ነው የማውቅው ብቻ ሊረዳን የመጣው የሳሉ ወንድም ነው እና እሱም የሚያውቃቸውን ሰዎችን አሰባስቦ የበለጠ አሪፍ አድርጎታል፡፡
የሁለተኛ ሴሜስተር ትምህርት ልንጨርስ ነው ፋይናል ብቻ ነው የቀረን በእዚህኛው አሪፍ ውጤት እንደማመጣ ተስፋ አደርጋለሁ ሂዊ እና እኔ ጥሩ እየሰራን ነው፡፡ ከነ ሳሉ ጋርም አሪፍ እየተዘጋጀን ነው የሚቀጥለው ሳምንት ፈተና እንጀምራለን ፡፡
ከፈተናው በኃላ እንደተለመደው የመለያያ ዝግጅት ለማድረግ ታስቦዋል ግን ከዚህ ቀደም እንደተደረገው ሳይሆን ለየት ባለ ሁኔታ ለማዘጋጀት ነው የታሰበው ዝግጅቱ እንዲሆን የታሰበው እስከዛሬ ስንረዳቸው ከነበሩ ሰዎች መካከል በጣም ደከም ያለው ሰው ጋር ሄደን አብረነው ለመዋል እና ሌሎች ከእነሱ ሻል የሚሉትን ደግሞ ከእኛ ጋር እንዲቀላቀሉን አድርገን ሁላችንም አንድ ላይ ለማሳለፍ አስበናል ግን ዝግጅቱ እንዲዘጋጅበት ያሰብነው ቦታ አምቺ አይደለም በጣም ጠባብ ነው እና የሳሉ ወንድም አንድ ሀሳብ ሰቶናል ዝግጅቱ እነሱ ቤት እንዲዘጋጅ ግን ደግሞ እንደዚህ ብናደርግ ሚስኪኖቹ ለቸገሩ ይችላል እነሱን የሚያመላልስ ሰው ያስፈልጋል ብቻ እስከ አሁን ምንም አይነት ውሳኔ አልተወሰነም ፡፡
ፈተና መፈተን ጀምረናል ዛሬ ሁለተኛ ቀናችን ነው ሁላችንም የቀለለን ይመስለኛል ከአጠናነው ውጪ አልመጣም አሪፍ እየሰራን ነው ፡፡
ሰሚር ....ሰሚር እያለ ከውጪ የሚጣራውን ድምፅ ስሰማ ዲያሪውን ዘግቼ ወደ ውጪ ወጣሁ አሊ ነበር ጓደኛዬ ነው ጎረቤትም ነን አስር እንደተሰገደ አልሰማሁም ነበር ወደ ቁርአን ቤት አብረን ለመሄድ ነበር የመጣው እኔ ገና አስር አልሰገድኩም ኡዱእ አድርጌ እዛው እሰግዳለሁ ብዬ አብረን ወጣሁ የተወሰነ መንገድ ከሄድኩ በኃላ ዲያሪውን አልጋው ላይ ትቼው እንደመጣሁ አስታወስኩ የያዝኩትን ኪታብ (መፅሀፍ) ለአሊ አስይዤው አምስት ደቂቃ ብቻ እቤት ደርሼ መጣሁ ብዬው ወደ ቤት ተመለስኩ አሊ ነገረ ስራዬ ግራ እንዳጋባው ገብቶኛል ማስረዳት አልችል አላስረዳው ነገር ብቻ ወደ ቤት ተመልሼ መኝታ ቤት ልገባ ስል እማዬ ሳሎኑ ቤት ተቀምጣ ነበር "አንተ ቀልበቢስ ምን እረስተህ ነው?" ምንም እዚህ..... ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ዲያረመው እንዳስቀመጥኩት ነው እማዬ አልነካችውም ማለት ብዬ አልጋው ላይ ያለውን ዲያሪ አልጋው ስር አስቀምጬ በድጋሚ ወደ አሉ ወደ ቁርአን ቤቱ አመራሁ ቁርአን ቤት ሆኜ ሀሳቤን መሰብሰብ አልቻልኩም ስለ ሙኒ ዲያሪ እያሰብኩ ነው በአካል ቁርአኔ ቤቱ ውስጥ ልሁን እንጂ ሀሳቤ ግን ቤት አልጋው ስር ያስቀመጥኩት ዲያሪ ላይ ነወሸ ፡፡
፡
፡
ይቀጥላል
