cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopian Electric Utility

EEU Official Telegram Channel Web: www.eeu.gov.et

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
24 729
المشتركون
+1124 ساعات
+1427 أيام
+49630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ባሉበት ሆነው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን በቀላሉ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ ወይም በአዋሽ ብር ፕሮ አማካኝነት ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይፈፅሙ፡፡ በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣብዎ ተጨማሪ የአገልግሎት ቅጣትና ወጪም ይዳኑ! #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
Invitation of #bids #ethiopianelectricutility
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ በአዋሽ ብር ፕሮ ቀሏል ካሉበት ሆነው ክፍያዎን ይፈፅሙ!
إظهار الكل...
በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ኃይል የተቋረጠባቸው ከተሞችና መንደሮች አገልግሎቱ ወደ ቦታው ተመልሶለቿዋል፡፡ በወለጋ ዞኖች በኤሌክትሪክ በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ጉዳትና ውድመት የተቋረጠው አገልግሎት በተሰራው የመልሶ ግንባታ ስራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ከተሞችና መንደሮች ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡ በዚሁ መሰረት በሆሮ ጉዱሩ ዞን ሀሮ ብጅጋ፣ጌምቦ ስላሴ ቴሌኮም፣ቁብሳ ቅዳሜና ቆርኬ ተብለው የሚጠሩ ከተሞችና መንደሮች አገልግሎቱን መልሶ እንዲያገኙ ተደረጓል፡፡ በምስራቅ ወለጋ ዞን ደንቢ ጎዴ ተብሎ የሚጠራ መንደር ዳግም አገልግሎቱን ያገኘ ሲሆን በዚሁ ዞን ከጊዳ ተነስቶ ወደ ጎቡ ከተማ የሜሄድ 12 ኪሎሜትር የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ ጎቡ ከተማ አገልግሎቱን ዳግም ማግኘት ችሏል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊ ኬሌ የውሃ ፕሮጀክትና ጫላ ዳቡሰ ተብለው የሚጠሩ ቦታዎች አገልግሎቱን ዳግም ያገኙ ሲሆን በዚሁ ዞን በመንዲ ከተማ ልዩ ቦታው አምበራስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ከሁለት ዓመታት የጊዜ ቆይታ በኋላ ዳግም አገልግቱን ማግኘት ችሏል፡፡ በተቀሩት ቦታዎችም የተጎዱ መስመሮችን መልሶ የመገንባት፣የወደሙ ትራንስፎርመሮችን የመተካት፣በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ያሉ ዛፎችን የማፅዳት እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን በመስራት የተቋረጠውን አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ በሁሉም የወለጋ ዞን አቅጣጫዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 11 7
በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ኃይል የተቋረጠባቸው ከተሞችና መንደሮች አገልግሎቱ ወደ ቦታው ተመልሶለቿዋል፡፡ በወለጋ ዞኖች በኤሌክትሪክ በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ጉዳትና ውድመት የተቋረጠው አገልግሎት በተሰራው የመልሶ ግንባታ ስራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ከተሞችና መንደሮች ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡ በዚሁ መሰረት በሆሮ ጉዱሩ ዞን ሀሮ ብጅጋ፣ጌምቦ ስላሴ ቴሌኮም፣ቁብሳ ቅዳሜና ቆርኬ ተብለው የሚጠሩ ከተሞችና መንደሮች አገልግሎቱን መልሶ እንዲያገኙ ተደረጓል፡፡ በምስራቅ ወለጋ ዞን ደንቢ ጎዴ ተብሎ የሚጠራ መንደር ዳግም አገልግሎቱን ያገኘ ሲሆን በዚሁ ዞን ከጊዳ ተነስቶ ወደ ጎቡ ከተማ የሜሄድ 12 ኪሎሜትር የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ ጎቡ ከተማ አገልግሎቱን ዳግም ማግኘት ችሏል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊ ኬሌ የውሃ ፕሮጀክትና ጫላ ዳቡሰ ተብለው የሚጠሩ ቦታዎች አገልግሎቱን ዳግም ያገኙ ሲሆን በዚሁ ዞን በመንዲ ከተማ ልዩ ቦታው አምበራስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ከሁለት ዓመታት የጊዜ ቆይታ በኋላ ዳግም አገልግቱን ማግኘት ችሏል፡፡ በተቀሩት ቦታዎችም የተጎዱ መስመሮችን መልሶ የመገንባት፣የወደሙ ትራንስፎርመሮችን የመተካት፣በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ያሉ ዛፎችን የማፅዳት እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን በመስራት የተቋረጠውን አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ በሁሉም የወለጋ ዞን አቅጣጫዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
የቆጣሪ ውል ለማደስ ምንም አይነት ክፍያ አያስከፍልም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያሉትን ደንበኞች አውቆ ለሚጠይቋቸው የትኛውም አይነት የመብት ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት እንዲችል ውል ከፈፀሙ5 አመት እና ከዚያ በላይ የሞላቸው ደንበኞች የቆጣሪ ውል ዕድሳት እንዲፈፅሙ እያደረገ ይገኛል፡፡ ደንበኛች ውል ለማደስ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃ ፍቃድ፣ አንድ ወቅታዊ 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣ የኪራይ ቤት ከሆነ ቤቶቹን ለማስተዳደር ስልጣን ከተሰጠው አካል ወይም የባለቤትነት ኃላፊነት በመውሰድ የተፃፈ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ያልተከፈለ እዳ ካለ ከአከራይ የተፈረመ የውል ግዴታ ሰነድ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ሰነድ በመያዝ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ማዕከል በመሄድ ውል መፈፀም ይኖርባችዋል፡፡ ይሁን እንጂ ደንበኛች የቆጣሪ ውል ለማደስ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሲሄዱ ገንዘብ ክፈሉና የሚሉ ደላሎች እንዳሉ መረዳት ችለናል፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን የቆጣሪ ውል ለማደስ ምንም አይነት ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እናሳውቃለን። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 18 5
Photo unavailableShow in Telegram
የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የሃይል አቅርቦት ሰኔ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በላምበረት፣ ጉርድ ሾላ ሜታ፣ መገናኛ ሾላ ገበያ እና አካባቢዎቻቸው የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 20🏆 3 2
ሃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የተወሰኑ የወለጋ ዞን ከተሞች ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኑ በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወለጋ ዞኖች በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በደረሰ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ውድመት ሃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የገጠር ከተሞች በተሰራ የጥገና ስራ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት በተሰራው የጥገና ስራ በዞኑ ስር የሚገኙት የዶንጎሮ ጌቦ፣ ዶንጎሮ ዲስ፣ ሆታሎ ቴሌኮም ሳይት እና የካለይ የውሃ አቅርቦት ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ስር የሚገኙት የሃሮ ፎላ ቴሌኮም፣ መንደር 8፣ ኤፈሬም፣ ጉቤ እና መንደር 15 አገልግሎቱን ዳግም ማግኝት የቻሉ ሲሆን በሆሮ ጉዱሩ ዞን ስር የሚገኙት የገንቦ ስላሴ ቴሌኮም እና ኡታልቾ የህዝብ ማዕከል ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት ዳግም ተመልሶላቸዋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የአካባቢው ማህበረሰብ ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ በአካባቢው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት አምስት ቴክኒካል ቡድኖች ተዋቅረው ወደስራ መግባታቸውን መግለጻችን የሚታወስ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 7 4👏 1🏆 1
በነፃ የስራ ዘመቻው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲከናወኑ ውለዋል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲያካሂድ በዋለው አገር አቀፍ ነፃ የስራ ዘመቻ መረሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲከናወኑ ውለዋል፡፡ ለዘጠነኛ ጊዜ በተካሄደው ነፃ የስራ ዘመቻ የመልሶ ግንባታ ስራዎች፣ የቅድመ መከላከልና አስቸኳይ ጥገና ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ መደበኛ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በተቋሙ የድሬ ድዋ ሪጅን የመስመር ፍተሻና የኃይል ጭነት ለሚበዛባቸው ትራንስፎርመሮች አጋዥ ትራንስፎርመር የማስቀመጥ ስራ ያከናወነ ሲሆን ሌሎች ሪጅኖችም የቆጣሪ ውል እድሳት፣አዲስ ቆጣሪ የመግጠምና ሌሎች መደበኛ ስራዎችን አከናውነዋል፡፡ በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን በሚል መሪ ቃል አዲስ ኃይል ጠያቂ ደንበኞችን በአንድ ቀን ለማስተናገድ ከዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 15 ቀናት ሚቆይ ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የመጨረሻውና አስረኛው ዙር ነፃ የስራ ዘመቻ በሚቀጥለው ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
5👍 4👏 1
የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶች መልሶ በመጠገን ዜጎች መልሰው አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተከናወነ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር ገለፀ፡፡ በወለጋ ዞኖች በተፈጠሩ የሠላምና የፀጥታ ችግር ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች መልሶ በመጠገን አገልግሎቱን ወደነበረበት ለመመለስ በስፍራዎቹ ያቀኑ የስራ መሪዎችና ባለሙያዎች ተቀናጅተው በተለያዩ ቦታዎች ተሰማርተው ስራውን በመከወን ላይ ናቸው፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር በበኩሉ ተቋሙ አገልግሎቱ የተቋረጣባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን ዳግም እንዲያገኙ እየተከናወነ ያለው ስራ አበረታች በመሆኑ ከተቋሙ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡ የመልሶ ጥገና ስራው ከፍተኛ ጫና ያለበትና እልህ አስጨራሽ ስራ የሚጠይቅ ቢሆንም በስፍራዎቹ የተሰማሩ የተቋሙ ባለሙያዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከቦታ ቦታ ማጓጓዝን ጨምሮ የተጎዱ የኤሌክትሪክ መስመሮችን መልሶ የመዘርጋት፣የተጎዱና የወደቁ ምሰሶዎችን የማቆም፣ ትራንስፎርመሮችን የመተካት እንዲሁም ሌሎች መሰል ስራዎችን በመስራት አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው ዜጎች አገልግሎቱን መልሰው እንዲያገኙ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስራው እየተከናወነ የሚገኘው በአራቱም የወለጋ ዞኖች ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት፣ከነቀምቴ ዲስተረሪክትና በስሩ ካሉ ማዕከላት ባለሙያዎችና ከሌሎች አቻ ሪጅኖች በተውጣጡ የስራ መሪዎችና ባለሙያዎች የጋራ ቅንጅት ሲሆን በስፍራዎቹ በየደራጀው ያሉ የመንግሰት አደረጃጀት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣የሰላምና የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ትብብር እያደረጉ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
إظهار الكل...
👍 22 4👏 1