cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Bereka

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
179
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

♥️"ፍቅር እስከ ጀነት" #ክፍል_1 : ጅምር እንጂ ማብቂያ ከሌለው የዘላቂ ፍቅርን ልክ የሚያሳይ በሞት ግድግዳ የማይካለል የማይለያይ እውን ጥልቅ ፍቅርን በጥቂቱ እንዳስሳለን። : ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ለንባብ ካበቋቸው ስመጥር ስራዎቻቸው መካከል አንዱ ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘው ነው። ደራሲው የኖሩበትን የፊውዳሉን ዘመን ባህል፣ አስተሳሰብ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ በዘመኑ ያልተፈጠረን አንባቢን ጭምር በምናቡ ዘመኑን እየሳለ ያልኖረበትን ዘመን ጣእም እንዲያጣጥም ያስቻለበት የፍቅር መጽሐፍ ነው። ፍቅር በወረት በሚለካባት አለም ውስጥ በመወለዳቸው በድርሰታቸው የሳሉትን ምናባዊ ፍቅር በገሃዱ አለም ከነበሩ ድንክዬ ፍቅሮች አርዝመውና የአቅማቸውን ያህል ለጥጠውት እስከ ቀብር ድረስ አድርሰውታል፤ ይህንንም ለማንጸባረቅ ድርሰቱን “ፍቅር እስከ መቃብር” ሲሉ ሰይመውታል። በዚህች አጭር ጽሁᎊ ከመቃብር የዘለለ፣ ምናባዊ ሳይሆን ገሃዳዊ ፍቅር መኖሩን፣ ፍቅር የሚለው ቃል ራሱ ችሎ የማይገልጸው ከፍቅር በላይ የሆነ ፍቅር፣ ስሜትን ፈንቅሎ፣ አቅልን አስቶ በደስታ፣ በናፍቆትና በሀዘን መካከል ወዳለ የህመም አለም ይዞ የሚነጉድ ውዴታ መኖሩን በእፍታ እንመለከታለን። የማያውቁት አገር አይናፍቅም ይላል የአገሬ ሰው። ማወቅ ማለት ማየት ነው፣ እንጂማ የማይታወቅ አገር ኖሮ አይደለም። ፍቅርና ናፍቆት መግቢያቸው አይን ነው። ሳይታዩ የተፈቀሩ፣ ሳይገኙ የተናፈቁ ብቸኛው ስብእና ረሱሉላህ ሰ.አ.ወ ብቻ ናቸው። እልፍ አእላፍ ልቦናዎችን በፍቅር ማርከው ወረት የማይለካው፣ ሞት የማይበግረው፣ ግዜ የማይገድበው የፍቅር አዝመራ ዘርተዋል። አላሁመ ሶሌ የሚሉት አዝመራ ዝናብም አይፈልግ ጸሃይም አይፈራ : ነብዩን ሰዐወ በአካል ሳያገኟቸው ከነፍሶቻቸው በላይ የሚንገበገቡላቸው አያሌ ወዳጆች በየ ክፍለ አለሙ ተበትነው ሞታቸውን በፍቅር ይጠባበቃሉ። ልክ እንደ ሰይዲና ቢላል ጣእረ ሞታቸው ላይ ሆነው እንኳ “ነገ ነብዩ ጋር እንገናኛለን” እያሉ በደስታ ይፈካሉ። ስማቸው ሲወሳ ሳግ ይተናነቃቸዋል፣ ታሪካቸው ሲነገር የእንባ ግድባቸው ይፈርሳል፣ እርሳቸውን ማሰብ ብቻ ቀለብ ሆኗቸዋል። ቀን ከሌሊት ህልማቸው ነገ ነብዩ ጋር መገናኘት ብቻ ነው። አንድ አሊም ጀነት ምን አለ ተብለው ሲጠየቁ “ጀነትማ ነብዩ አሉ” ብለው ናፍቆታቸውን ገልጸዋል። የነብዩን ፍቅር ከሚገልጹ አንጸባራቂ ክስተቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ነብዩ ሰዐወ ከመሞታቸው አራት ቀናት ቀደም ብለው አቡ ሙወይሂባ ለተባለው ሶሃባቸው “ለበቂእ ሰዎች እስቲግፋር እንዳደርግ ታዝዣለው” አሉትና ይዘውት ሄዱ። ወደ በቂእ ከወረዱ በኋላ “አላህ ሁለት ምርጫዎችን እንዳቀረበልኝ እንደታውቅ እፈልጋለው፤ በዱንያ የተወሰነ ግዜ መቆየት፣ የዱንያን ቁልፎች መጨበጥና ግዜዬ ደርሶ የሞትኩ ግዜ ደግሞ ጀነት ገብቼ አላህ ጋር መገናኘት አንዱ ምርጫ ሲሆን ሌላኛው ምርጫ ደግሞ አሁኑኑ አላህን መገናኘት ነው” አሉት። አቡ ሙወይሂባ ቀልጠፍ ብሎ ፍቅርና ስስት በሞላው አንደበቱ “ያ ረሱለላህ እባኮትን እኛን ይምረጡ፣ አይሂዱብን” ሲል ለመናቸው። ነብዩም ሰዐወ ምርጥ ተፈቃሪ እንደሆኑት ሁሉ ወሰን የለሽ አፍቃሪ ነበሩና “አቡ መወይሂባ ሆይ ጌታዬን መርጫለው” ብለው “አል ረፊቂል አእላ አል ረፊቂል አእላ” እያሉ ጉብኝታቸውን ቀጠሉ። ነብዩ ሰዐወ ከሞቱ በኋላ እናታችን አኢሻ ነብዩ ለመጨረሻ ግዜ የቀሩት የቁርአን አንቀጽ ምንድን ነበር ተብለው ተጠየቁ። ለመጨረሻ ግዜ የቀሩት ሱራ ሱረቱል ሙርሰላት ነበር፣ ትኩሳታቸው ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ሲሄድ ግን “ ﻣﻊ ﺍﻟﺬﻳﻦ ” የሚለውን ደጋግመው ይቀሩት ነበር ብለዋል። ነብዩ ራሳቸው የሚናፍቋቸውና በአኼራ አብረዋቸው ሊሆኑ የሚመኙ አያሌ ስብእናዎች አሉ። ነብያቶች፣ ሷሊሆች፣ ሹሀዳዎች፣ ሲዲቆች፣ አባታቸው ኢብራሂም፣ ባለቤታቸው ኸዲጃ፣ አጎታቸው ሀምዛ፣ ሌሎችም። ከነብዩ ሞት በኋላ የርሷቸው ወዳጆች በሙሉ ምኞታቸው ነገ ሞተው እርሳቸው ጋር መገናኘት ሆነ። ኡስማን ኢብን አፋን በቤታቸው የቁም እስረኛ ሲደረጉ ጾምኛ ነበሩ። የሞቱበት እለት ነብዩን ሰዐወ በህልማቸው ያዩዋቸዋል። “ኡስማን ሆይ ውሃ እንኳ እንዳታገኝ ከለከሉህ አይደል” አሏቸው። “አዎ ያረሱለላህ” ሲሉ ይመልሳሉ። “ምግብ ከማግኘትስ ከለከሉህ አይደል” “አዎን ያ ረሱለላህ” “የኔ መስጂድ ገብተህ እንዳትሰግድስ አግደውሃል አይደል” “አዎን ያ ረስኡለላህ” “አብሽር ኡስማን ሆይ ዛሬ ጾምህን ከእኔ ከአቡበክርና ከኡመር ጋር ሆነህ ታፈጥራለህ” አሏቸው። ሰይዲና ኡስማን ጾመኛ እንደሆኑ የዛች እለት ተገደሉ። አቡበከር ረዐ ጣእረ ሞታቸው ላይ በነበሩ ግዜ እናታችን አኢሻን አስጠርተው “ቀኑ ምንድን ነው” ሲሉ ጠየቋቸው። እርሳቸውም “ዛሬ ቀኑ ሰኞ ነው” ሲሉ መለሱላቸው። ቀጥለውም አቡበከር “ነብዩ ምን ቀን ነበር የሞቱት” አሉ። “ሰኞ ቀን” የሚል ምላሽ አገኙ። “እንግዲያውስ” አሉ አቡበከር … “እንግዲያውስ ዛሬ የሞትኩ እንደሆነ እስኪነጋ እንዳትጠብቁኝ፣ ዛሬውኑ ቅበሩኝ። የኔ ምርጥ ቀን ከነብዩ ጋር ቅርበት ያለው ቀን ነው” አሉ። ትንሽ ቆየት ብለውም “ነብዩ ሲሞቱ እድሜያቸው ስንት ነበር” ሲሉ እናታችን አኢሻን ደግመው ጠየቁ። “63 ነበሩ” አሉ ኡሙል ᎀእሚኒን። “እኔስ ስንት አመቴ ነው ዘንድሮ” ብለው ጠየቁ። “63 ኖዎት አሚረል ሙእሚን” የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። እርካታ በተቀላቀለበት አነጋገር “አልሃምዱሊላህ” አሉ። ምን አይነት ፍቅር ነው እስቲ ነብዩ በሞቱበት እድሜ ልሞት ነው ብሎ መቋመጥ። ኣልላሁመሶሊ ኣላሰዪዲና ሙሃመድ ❤️❤️❤️❤️
إظهار الكل...
♥️«የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለምንድን ነው ዛሬ እጅግ ተደስተው ያደሩት፤ ፊትዎት የደስታ ብስራት ይታይበታል።» አሏቸው። ተፈቃሪያችን ﷺ እንዲህ አሉ: ‐ «መልአክ ከጌታዬ ዘንድ ወደ እኔ መጣና እንዲህ አለኝ: ‐ «ከኡመቶችህ አንድ ሰው በርሶ ላይ አንድ ሶለዋት ካደረገቦት አላህ ዐስር ሐሰናት ይፅፍለታል። ዐስር ኃጢኣት ይሰርዝለታል። በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል። በአምሳያውም የሶለዋት ምላሽ ያገኛል።» 📚ነሳኢ ዘግበውታል። : በረቢዑን‐ነቢ 9ኛው ቀን ላይ እንገኛለን። በርሳቸው ዉልደት ያገኘነውን ፀጋ ለማስታወስና አላህን ለማመስገን ከወሩ ጋር የተቆራኘ ምክንያት አለን! በዚያ ላይ ዛሬ ጁሙዐ ነው። ሶለዋታችንን በጆሯቸው ይሰሙታል። ስለዚህ ዉቡን ፊታቸውን እንደ ሙሉ ጨረቃ ደምቆ ማየት የሚሻ ሁሉ ሶለዋት ያብዛ! ጁሙዐህ ሙባረካ! https://t.me/joinchat/Thgs_FEJ8KISTVm9 💚اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد وعلى آله وصحبه.
إظهار الكل...
ከጠቢባን ምድር ツ

🖌 وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًۭا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّه وَعَمِلَ صَٰلِحًۭا وَقَالَ إِنَّنِى مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ 🖌ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው 🔰አባባሎች ከጠቢባን ምድር🔰 ✨ 🌴أقوال من دار الحكمآء🌴 ✨ 📨 ጥያቄ አስተያየት @Abdubot_bot

♥️«የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለምንድን ነው ዛሬ እጅግ ተደስተው ያደሩት፤ ፊትዎት የደስታ ብስራት ይታይበታል።» አሏቸው። ተፈቃሪያችን ﷺ እንዲህ አሉ: ‐ «መልአክ ከጌታዬ ዘንድ ወደ እኔ መጣና እንዲህ አለኝ: ‐ «ከኡመቶችህ አንድ ሰው በርሶ ላይ አንድ ሶለዋት ካደረገቦት አላህ ዐስር ሐሰናት ይፅፍለታል። ዐስር ኃጢኣት ይሰርዝለታል። በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል። በአምሳያውም የሶለዋት ምላሽ ያገኛል።» 📚ነሳኢ ዘግበውታል። : በረቢዑን‐ነቢ 9ኛው ቀን ላይ እንገኛለን። በርሳቸው ዉልደት ያገኘነውን ፀጋ ለማስታወስና አላህን ለማመስገን ከወሩ ጋር የተቆራኘ ምክንያት አለን! በዚያ ላይ ዛሬ ጁሙዐ ነው። ሶለዋታችንን በጆሯቸው ይሰሙታል። ስለዚህ ዉቡን ፊታቸውን እንደ ሙሉ ጨረቃ ደምቆ ማየት የሚሻ ሁሉ ሶለዋት ያብዛ! ጁሙዐህ ሙባረካ! https://t.me/joinchat/Thgs_FEJ8KISTVm9 💚اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد وعلى آله وصحبه.
إظهار الكل...
ከጠቢባን ምድር ツ

🖌 وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًۭا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّه وَعَمِلَ صَٰلِحًۭا وَقَالَ إِنَّنِى مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ 🖌ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው 🔰አባባሎች ከጠቢባን ምድር🔰 ✨ 🌴أقوال من دار الحكمآء🌴 ✨ 📨 ጥያቄ አስተያየት @Abdubot_bot

ኒዛሙ ጃሚኡድ የልብስ ስፌት ፋሽን ለሙስሊሙም ለክርስቲያኑም ለሴትም ለወንድም ለትንሽም ላዋቂም በፈለጉት ዲዛይን እና በተመጣጣኝ ዋጋ የፈለጉትን መርጠው የሚያሰሩበት ምርጥ የልብስ ፋሽን ይምጡ ይጎብኙን ደስ ብልሎዎት ይመለሳሉ ኣድራሻ ኣጣና ተራ እፎይታ የገበያ ኣዳራሽ ኣድሱ ህንጻ ኣንደኛ ፎቅ 78 ቁጥር ላይ ያገኙናል ጎራ ይበሉ የመረጡትን ያሰራሉ
إظهار الكل...
#ወንድሞቼ❤ #ነቃ_ብላችሁ_አንብቡት🎀 ወንድሜ!እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትክ መፈፀም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር " ➊☞_ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት። ➋☞ሴት ፍቅርህን እንድትገልፅላት ትሻለች #ባገኘኸው_አጋጣሚ ፍቅርህን ከመግለፅ ወደ ኃላ አትበል። ➌☞ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ።ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ።አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር። ➍☞ #_ሴቶችን_መልካም_ንግግር_ውብ_ገፅታ_ንፁህ_ልብሶችና _ጥሩ_መአዛ_ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖርህ ጥረት አድርግ። ➎☞ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው።ቤቷ ስትሆን ዙፏኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል።በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባት ነገር እንዳትፈጵም ።ከንግስና ዙፏኗ ላይ ልታወርዳት እንዳትሞክር።ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ። ➏☞ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።አንተን ከቤተሰቧ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ።ይህን ማድረግ ፋፃሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል። ➐☞ሴት ከጎንህ(ጠማማ አጥንት)መፈጠሯን አትዘንጋ።ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን አወቅ ።ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለው እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ።ስብራቷ ፍቺ ነው።ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት ።መካከለኛ ሰው ሁንላት ። ➑☞_ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል።ነገር ግን እንዲህ አደረገች ብቻ በማለት እንዳትጠላት።ይህን ባህሪዋን ባቶድላት ሌሎች ሚስቡህ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ። ➒☞ሴት አካላዊ ድካምና ስነ ልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። #የአንተን_ፍላጎት_ለማሟላት_የሚከለክላት_ነገር_አለ፡፡ በዚህ ወቅት ከፍጥረታት ሁሉ የተጥራራዉ ጌታችን አሏሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ የግዴታ አምልኮዎችን (ሶላትና ፆም)ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። #በዚህ_ጊዜ_እዘንላት_ትእዛዝ_አታብዛባት። ➓☞ #ሴት_አንተ_ዘንድ_ያለች_የፍቅር_ምርኮኛህ_መሆኗን_አትዘንጋ_ምርኮኛህን_በጥሩ_ሁኔታ_ያዛት_እዘንላት_በድክመቷ የምትፈፅመውን ስህተት እለፋት ።ምርጥ የህይወትህ አጋር ትሆንሀለች። ❣ትደር ላይ ላላችሁ በሙሉ ኑሯችሁ የጣፈጠ ይሁንላችሁ❣ #መልካም_ቀን❤️ ለምትወዱት ወንድማችሁ 🥇shar...share
إظهار الكل...
. ማፍቀር መፈቀር ስጦታ ነው 😍 ውለታን መመለስ ደግሞ መልካምነት ነው ተፈቃሪ ብቻ ሳይሆን አፍቃሪን ማፍቀርም ሀቅ ነው 😊 ያገባት በ15 አመት እንደምትበልጠው አውቆ ነው 🤔 ከእሱ በፊትም ሁለት ጊዜ አግብታ እንደተለያየችም አረጋግጧል😳 ያገባት ያለፈውን ታሪኳን በመመዘን ሳይሆን የአሁን ምንነቷን በመለካት ነው😍 እሷም ለእሱ እጅጉኑ ታማኝ ሚስት ሆነች 😇ስ ድስት ምርጥ ምርጥ ልጆችን አፈራችለት በችግሩና በከፋው የመከራ ዘመን በምክሬም በሀብቴም ከጎንህ ነኝ ብላ ከእሱው ጎን በእኩል ተሰለፈች 😌 ዘላለም አይኖርምና ይች ምርጥ ሚስት ሞተችበት 😞 ባልም በሞቷ ክፉኛ አዘነ እሷን ያጣበት አመት የሀዘን አመት ተባለ 😓 እሱም ታማኝ አፍቃሪ ነበርና በተለያዩ አጋጣሚዎች እሷን ከማወደስ ወደኋላ አይልም ፡፡ እሷኮ እንደዚህ ነበረች እንደዚህ ነበረች እያለ ያሞጋግሳታል 😎 ልጆችን ያፈራችልኝ በችግሬ ዘመን የረዳኝም እሷው ነች ፍቅሯን በሰፊው ተሰጥቻለሁ እያለ ለሌሎች ሚስቶቹም ጭምር ያወራል ☺️ ታማኙ አፍቃሪ የሚስቱን እህቶች አይነት ድምፅ ሲሰማ ሀውላ ትሆን እንዴ!! ብሎ የእንኳን መጣሽ መልእክት ያሰማል 😙 ስጋ አርዶ በሂወት ላሉት ሚስቶቹ ብቻ አያከፋፍልም ለሟች ሚስቱ እህቶችም ድርሻቸውን ይልካል ቀብሯን ይዘይራል በቅናት ምክንያት 🤩 "ለመሆኑ ለዚያች አሮጌ ሚስት ይሄን ያክል ማውራት ምን ይሉታል!!" የሚሉ ሚስቶችም ተፈጥረው ነበር። 😔 ከሞተኝም በኋላ በባሏ ልቦና በፅኑ የተፈቀረች ይች እድለኛ ሚስት ማን ነች ካላችሁ....... #ኸዲጃ_ቢንት_ኹወይሊድ መሆኗን እወቁ። አፍቃሪውስ ማነው ሙሀመድ ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም ❤️❤️❤️ 😘😘😘 #ፍቅር_ቀን❤️💚 ለኣብዱየ
إظهار الكل...
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካትሁ *ጀግናው አብዱሏ ብን ዙበይር ረድየሏሁ አንሁ* ጀግና እዎዳለሁ ተጋበዙልኝማ📍 ‍ *ወቅቱ 26ኛው አመተ ሂጅራ ነበር አብደሏህ ኢብኑ ዙበይር 20 ሽ የሙጃሂድን ስብስብ ይዞ 200 ሽ አባላትን ካቀፈው የሮማ ጦር ጋር ለመፋለም ገሰገሰ።* ሁለቱ ቡድኖች እሳት ጎርሰው ፊት ለፊት ተፋጠጡ። *የሮማው የጦር መሪ ጀርጅር እንድህ አለ፦ አዋጅ!!አዋጅ!!!አዋጅ!! አብደሏህ ኢብኑ ዙበይርን የገደለ ውብና ኮረዳዋን ልጀን እድረዋለሁ 100ሽ ድናርም ይሸለማል በማለት አወጀ* ሙስሊሞቹ ይህን ሲሰሙ መሪያችን ይገደልብናል ብለው ሰጉ። አብደሏህ ጀግናውም እንድህ አለ። አዋጅ!!ከሐድውን ጀርጅርን ለገደለ ጀግና የጀርጅርን ልጅ እንድረዋለን። 100ሽ ድናርም እንሸልመዋለን ጀርጅር የሚያስተዳድረውንም ግዛት እንሰጠዋለን የሚል አዋጅ አወጀ። *ጦርነቱ ተጀመረ እጅግ አሰቃቂ ነበር ሙስሊሞች ተፈትነው እንደወርቅ የነጠሩበት ጦርነት ነው።* ሀያ ሽ ለሁለት መቶ ሽ!!!! ግዙፍ ጀግንነት። *ሙስሊሞች በብዛተሰ ሳይሆን በጥራት የተገነቡ እንቁዎች ናቸው።* ጀርጅርን ጠባቂዎቹ ከፊት ለፊቱ ገጭ ብለው እሱን ይጠብቃሉ። ሁለት ሴቶች ከወፍ ላባ የተሰራ ዣንጥላ ይዘው ቁመውለታል። *አንድ ባለ ንስር አይን ጀርጅርን በእርቀት ተመለከተው* ወደ ጀርጅር አመራ ጀርጅር ጋ እንዳይደርስ ብዙ እንቅፋት ገጠመው እንቅፋቱን ሁሉ በሰይፉ ያስወግደው ጀመር መሪያቸውን ጥበቃ የተሰደሩትን ወታደሮች ሁሉ አንዱን በአንዱ ላይ በሰይፍ አደራረባቸው። አንገታቸውን እየሸለቀቀ መሬት ላይ አመረተው። *አሁንም ወደ ጀርጅር ይገሰግስ ይዟል ሊገታው የሞከረው ሁሉ የሰይፍ ሰለባ ይሆናል ይህንን ጀግና ማንም ወኔ ያለው አካል ጀርጅር ጋር ከመድረስ አላገደውም* ጀርጅር ጋር ደረሰ በሴትና በጠባቃ የታጀበው ጀርጅር ይህንን ጀግና ሲመለከት ገረመው።ከሰማይ ዱብ ያለ እንጅ ያንን ሁሉ ጠባቂ አመድ አድርጎ እሱ ጋ የደረሰ አልመሰለውም። ተፋለሙ!! *ከባድ ፍልሚያን ተለዋወጡ የኢስላም ወኔ ልቡን የደፈነው፣የኢማን ብርሐን ውስጡን ያጠነከረውን ጀግና ማን ይዘልቀዋልና* የጀርጅርን አንገት በጠሰው!!! በጠሰው ብቻ አይገልፀውም አንገቱን ከአካሉ ላይ ከረከመለት *የጀርጅርን ጭንቅላት በጦሩ ላይ በመሰካት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ይዞ ሁሉም እያየው ወደ ሙስሊሞች ካምፕ ተመለሰ* ጠላት ሐሞቱ ፈሰሰ ልባቸው ድቅቅ እምሽክ እንክት ብሎ ተፈጨ የሙስሊሞች ልብ ሻረ ይህ ጀግና እድሜው ከ21-23 ይገመታል በዛ ወቅት *ይህ ቆራጥ ጀግና የሙስለሙን ጦር የመራው አብደሏህ ኢብኑ ዙበይር ነበር።* አብደሏህን የገደለ ብሎ አዋጅ ሲያውጅ የነበረው ጀርጅር በአብደሏህ ሰይፍ ተቀነጠሰ አልሐምዱሊላህ!!!! ይህ ነበር የታሪካችን ገድል የሙስሊሞች ወኔ ይህ ነበርበጠላት ጨካኝ ነበርን እርስበርስ ደግሞ አዛኝ ነበርን!!
إظهار الكل...
ያኔ ኃያል ሳለን ቁ .1 ግብፅ ከኩፍር አመራርነት ተላቃ ወደ ሸሪዓዊ ጎዳና በተቀላቀለች ጊዜ ዓምር ኢብኑል ዓስን መሪ አድርጋ ሾመች። ዓምርም ግዙፍ መሰጂድ ለመስራት አሰበና ቦታ አዘጋጀ። መስጅዱ ሊሰራበት ከታሰበው ቦታ አጠገብ በዕድሜ የገፋች የሌላ እምነት ተከታይ ሴት ቤት ነበር። ቤትሽን እንግዛሽ ብለው ብዙ ገንዘብ አቀረቡላት። ሴትዮዋ ግን ፈቃደኛ ሳትሆን ቀረች። ብር ተጨመረላት አሻፈረኝ አለች። መሪው ሊያሳምናት ታገለ። ውይ ፍንክች። አቋሟን እንደማትቀይር ሲገባቸው ያለ ፈቃዷ ቤቷን ወደ መስጂድነት አጠቃለሉት። የመሪውን ውሳኔ በእጅጉ ተቃወመች። የሐገሩ ነዋሪ ቀሳውስቶች አቤቱታሽን ለበላይ አካል አሰሚ ብለው መከሯት። መዲና ሂጅና ጉዳዩን ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ አቅርቢ ስሞታሽን ንገሪ አሉ ቀሳውስቱ። ወደ መዲና ጉዞ ጀመረች። ከእልህ አስጨራሽ የድካም ጉዞ በኋላ መዲና ደረሰች። የሙስሊሞችን መሪ ቤተመንግሥት አሳዩኝ አሚሩን ፈልጌ ነው ረዥም ርቀት ተጉዤ የመጣሁት አለች ላገኘቻቸው የከተማዋ ነዋሪዎች። ከአንዲት ዛፍ ስር አሮጌ ጫማውን ተንተርሶ አስራ ሁለት ቦታ በብጣሽ ጨርቅ የተጣፈች ልብስ ለብሶ የተኛውን ሰው አመላከቷት። ዑመርን ነው እኮ የፈለኩት አለች። አዎ እሱ ነው ኡመር አሏት። የዓለምን ግማሽ ምድር የሚያስተዳድር ባለስልጣን እዚያ ዛፍ ስር ተኝቶ ስትመለከት "ድካሜ ውሃ በላው ይህ ነው ጉዳዬን የሚፈታልኝ?!" አለች ተስፋ በቆረጠ አንደበቷ። ቢሆንም ግን ስሞታዋን ለመናገር ወደ ዑመር ተጠጋችና በእግሯ ነካ አደረገችው። ገለጥ አድርጎ የተሸፈነበትን ጨርቅ ምን ልርዳሽ? አለ! አንተ ኡመር ነህ?? አለቻቸው አዎ አሏት። በግብፅ የተሾመው መሪ ያደረሰባትን ግፍ በሙሉ ተናገረች። ኡመር ፊታቸው ተለዋወጠ። በንዴት አይናቸው ቀላ። ከአጠገባቸው የወደቀ አጥንት ስባሪ አነሱና ደብዳቤ ፃፉ። «ከአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ለግብፁ መሪ ዓምር ኢብኑል አስ:- የአላህ ሰላም በአላህ ባሮች ላይ ሁሉ ይስፈን። አምር ሆይ! ፍትህን በማሰፈን የፐርሺያው ንጉስ ከእኛ የተሻለ ሊሆን አይችልም!!! ሰላም ባይተ ላይ ይስፈን!!» የሚል አጭር ፅሁፍ ፃፉና ይህንን ወስደሽ ለመሪያችሁ ስጪው በማለት አቀበሏት። በንዴት በገነች። በተስፋ መቁረጥ ተዋጠች። ወደ ሀገሯ ለመመለስ መንገድ ጀመረች። ከከተማው እንደወጣች ደብዳቤ የተፃፈበትን አጥንት ወርውራ ጣለች። ከኋላዋ ይከተላት የነበረ አገልጋይዋ የወደቀውን መልዕክት አንስቶ በያዘው የከረጢት ቦርሳ ውስጥ አስገባና ተከተላት። .... ግብፅ ደረሰች። የእሷ እምነት ተከታዮች የተባለችውን ለመስማት ጓጉተዋል። ምን ተባልሽ በማለት ጠየቋት። በሆነች አጥንት ስባሪ ደብዳቤ ፅፎ ሰጥቶኝ ነበር ምን ሊፈይድ ብዬ ጣልኳት አለቻቸው። ቀሳውስቱ ተናደዱ ወቀሷትም። አገልጋይዋ ከቦርሳው አውጥቶ ከመሬት ያነሳውን ደብዳቤ ለቄሶቹ አቀበላቸው። ቀኑ ጁመዓ ነው አምር ወደ መስጅድ ሊገባ ከበር ደርሷል። ሰባራዋን አጥንት አቀበሉት አነበባት። ፊቱ ተለዋወጠ። «ጁመዓ እንስገድና መስጅዱ ይፈርሳል። ቤትሽም ይገነባል። እስከምንሰግድ ከታገስሽን መልካም። ካልሆነ ሳንሰግድ እናፍርሰው።» የሚል ቃላትን ሰነዘረ። ጆሮዋን ጠረጠረች። ግርማ ሞገስ የተሞላበት የግብፁ መሪ የዕንባ ቋጠሮው ተፈቶ ማልቀስ ይዟል። ሴትዬዋም ጠየቀች እውነት በዚህ አጥንት ላይ ባለ መልዕክት ነው የተሸነፍከው? ይህ ነው ኢስላም?! ሁኔታው በጣም ገረሟታል "ቤቴን ለመስጅዱ ወቅፍ ሰጠሰቻለሁ" አለች። እስልምናን ተቀበለች። ቀሳውስቱ አቀርቅረው አለቀሱ ሸሃዳን ተቀበሉ። ዛሬ ዓለም በፍትህ እጦት ድርቅ ትታመሳለች። ሚስኪኖች ይሰቃያሉ። የደካሞች ቤት በጨካኞች ይፈርሳል። ላባቸውን እያፈሰሱ የሰሩት ቤት ለመናፈሻ እየተባለ በዶዘር ይመነገላል። ደካሞች ያለ መጠለያ ይቀራሉ። የግፍ መሪዎች ለሐብታም መዝናኛ ይገነቡበታል!! ፍትህን ከኢስላም ፈልጉ ሸር ሸር፡ ፡
إظهار الكل...
አላህ ሁለት ልቦችን ማገናኘት ከፈለገ የመሬት እና የሰማይ ያህል ርቀት ቢኖርም ያገናኛቸዋል
إظهار الكل...
እንደ እረኛው ሳይሆን እንደዛ ሲዲቁ..... •የጫሎች ወዳጅ የነአንዬ ስሙ አህመድ ነው የኔ ደስታዬ ማጣፈጫዬ የህይወት ቅመም አለይከ ሶላት ወሰላም• ﷺ ቅመም ስለውማ እህልና አገልግሉም እራሱ ቅመሙ ከሆነ በኋላ ነው.... አንድ እረኛ ነበር ለነቢ ሱለይማን ያልቀረበ ወርቃማ እድል ለርሱ የቀረበለት እድለኛ ረሱል በአባት አይናቸው እያዩት ••ከኔ ጋር በጀነት መኽተም ትሻለህ? ወይስ 80 ሴት በጎችን በዱንያ ትወስዳለህ?•• የእረኛው መልስ ውስጥ የአህመድ ጌታ ረቂቃ የቀደር ጥበብ ትገኛለች....°°አዋጅ የሙስጦፋ ፍቅር በጮሌነት ሓድራውም በመሽቀዳደም ሰርመድ አትገኝም°° እያለች የምትለፍፍ እረኛው ከበግ ለምድ የዘለለ ዐለም ያልነበረው ፡ ያንን የዐዘል ምንጭ ለትንፋሹም ያልተጎነጨ ነበርና °° አይ አይ 80 በጎች ይሻሉኛል°° ሲል ለወደደ ጣት የሚያስነክስ ምርጫውን ይፋ አወጣ ሐቢቡም እያዘኑ ሲያወጉት •• ካንተስ አሮጊቷ የሙሳ ጓድ ትሻላለች•• ብለው እድለቢስነቱን አረዱት.....ያቺ ጮሌ የሙሳ ሷሂባህ. .... አንድን የነቢ ሃሩን ወንድም ሓጃ ፈጽማ °°ልብሽ ምን ይልሻል ምን ላድርግልሽ?°° ቢሏት °°ወደ ኮረዳነቴ መልሰህ እጄን ይቅዛትና ጀነትን እንዝለቃት°°ያለችዋን አስተዋይ.....ተመጀንኩ በፍቅሩ ቀልብን እንጂ ጾታን ሸርጥ ባላደረገው። ••የሙሃባው ነገር ጠንቷል ለመዐበር ለሚደነጋገር ባህርም አያሻግር•• እዚህ ደግሞ የሸውቅ ነጋሪት በፈረጠሙ የናፍቆት አዱዳዎች ይጎሰማል.....አንጀቱ በጧሃ ነጅሙል ወሃጅ የተደቆሰው የአኢሸት አባት ኸበሩ እንዲህ ያለ ነው..... ከሺ ዐመታት ቀደም ብሎ ነው እርሱም ሳኒየስነይኑ የዋሻው ወዳጁም የዐለሙ ዘይኑ ውሃን ተጠምተው ባሉበት ሃለት አንዲት ኩባያ ወተት ያገኛሉ ሲዲቁ •• የወለደችኝ እናቴ ፊዳ ትሁንልዎ•• እያለ ጥማቸውን ከጥሙ አስቀድሞ እፊታቸው ሃድሮ ሲጎነጩ ይመለከት ያዘ ወተቱ የዛን አይናማ የጂብሪል ወዳጅ ጉሮሮ አርጥቦ ጥሙን ሲያረካለት ሲመለከት ፍቅርን በፈጠረው በአህመድ ጌታ እምላለሁ የርሱም ጥማት ተወገደ፡እንደ ፋርሱ እሳት ከሥሩ በረደ... الحبيب يشرب والمحب يرحى ይሂኔ ተፈቃሪው ይጎነጫል አፍቃሪም ይረካል ሲሉ የሱፊውን ቅኔ ይዘርፉና እዚያ ማዶ ደግሞ أحمق كصاحب نعجة ثمانين እንደ 80ዎቹ በጎች እረኛ ሞኝ አትሁን እያሉ ይተርታሉ! ጠየቅንህ ጌትዬ፡ እንደእረኛው ሳይሆን እንደዛ ሲዲቁ ጀነት ጀነት አሉኝ ጀነት ምናለበት የድሎቱ ሰበብ ጧሃ ከሌሉበት ሰላም ይድረሶት ሆዴﷺ ❤️ኢስነይን ሙባረክ ❤️
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.