cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዜና አበው ቅዱሳን

በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁ አስተያየት @ Kiduse Solomon2324 ብሎ በተጨማሪም ስልክ ቁጥር 0989740239 የአብሥራ ብሎ ማገኘት ይችላል ስንክሳር ምስባክ የቅዱሳን ታሪክ መተረክ ነገረ ሃይማኖት ድርሳናት ወረብ እና ዚቅ ብሒል አበው ዜና አበው ምክር አበው መንፈሳዊ ግጥሞች የጉባኤ ቤት ስብከቶች መዝሙሮች የቤተክርስቲያን ታሪክ የተለያዩ ነገሮች በዚህ ቻናል ማገኘት ይችላል

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
601
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
-130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

''እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው!'' ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
إظهار الكل...
إظهار الكل...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፯

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Photo unavailableShow in Telegram
“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”   — መዝሙር 47፥5 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!! መልካም በዓል
إظهار الكل...
#ዕርገት #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡ ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡     እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡ ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡ ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
❖ ቅዱስ ዳዊት ❖ ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ ወደ ላይ ዐረግኽ ምርኮን ማረክኽ ✥ ቅዱስ ያሬድ ✥ አማን በአማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ ✟ ዐርገ እግዚአብሔር ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሓን ✟ እንዲሉ ሊቃውንት በዓለ ዕርገቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገተ ልቡና ያድለን አምላከ ቅዱሳን
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የአምላካችን የክርስቶስ ዕርገት

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
     ✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁
“ዓቢይ ዜማ ተሰምዓ በሰማይ ዲበ መንበሩ እንዘ የዐርግ ወልድ ፤ ኵሎሙ መላእክት ትንሣኤሁ ዘመሩ መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል።” ቅዱስ ያሬድ
እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! ✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁 ዕርገት ከታች ወደ ላይ፥ከምድር ወደ ሰማይ መውጣት ማለት ነው።ቅዱስ ዳዊት፡-የጌታ ርደቱን (ከሰማይ ወደ ምድር መውረዱን) በመዝሙረ ትንቢት እንደ ተናገረ ሁሉ ነገረ ዕርገቱንም ተናግሯል።
"ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: " መዝ፡፵፮፥፭
“እግዚአብሔር በእልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤” በማለት የራቀውን አቅርቦ፥ የረቀቀውን አጉልቶ በመንፈስ ዘምሯል።መዝ. 46 ፥ 6 ይህ ትንቢት የሚፈጸምበት ሰዓት በደረሰ ጊዜም ጌታ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎ ወደ ቢታንያ ሄዷል። በአንብሮተ እድም ባርኳቸዋል (ሹሟቸዋል)። እየባረካቸውም ራቃቸው፥ወደ ሰማይም ዐረገ። ዕርገቱ በርህቀት እንጂ በርቀት አልነበረም ሉቃ፡፳፬፥፶። በእውነት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱ፣ በረከቱና ጠብቆቱ አይለየን የቅዱሳን ሐዋርያትም ምልጃ በረከታቸው ይድረሰን። አሜን🤲 ✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍁🍁🍁
إظهار الكل...
إظهار الكل...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፮

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።» ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
إظهار الكل...
ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ተስፋና ምልክት ናት ።ምክንያቱም እንደ ዘር ፍሬ ፣ ውስጥ እንዳለ እርሾ የመንግሥተ ሰማያት ሂደት የሚጀምረው ከቤተ ክርስቲያን ነውና ። ቅዱስ አግናጥዮስ
إظهار الكل...