cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔

የቤተክርስቲያንን ስርዓት ባማከለመልኩ የማንቂያው ደውል ቻናል ስርዐት ባለውመልኩ ጽሁፎችን እንለቅላችሀለን የዚህ ቻናል አላማው ሁሉንም ሰው የሚያስተምር ነው፡፡ ስናገኝ ደግሞ ስነጹፎችን ፣ ግጥሞችን ፣ ጭውውት ፣ እንዲሁም መዝሙሮችን እና ሌላም ሌላም ነገሮች እንለቅላችሇለን የቻናሉን ሊንክ ለጓደኞቻችሁ #ሼር በማድረግ አባላት እንጨምር #ሼር ለማንኛውም ነገር @Robellllll_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
491
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
🔴 የሀሙስ ውዳሴ ማርያም ንባብ በግዕዝ /ከነ ምልክቱ

የችሎት ውሎ…!! • መምህር ምህረተአብ አሰፋና • መምህርት ፌቨን ዘሪሁን ሕገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። "…ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ለአስር የተዳረጉት የእምነቱ ተከታይ ምእመናን እና መምህራን በሁለት ተከፍለው ልደታ ምድብ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ከ5 በላይ ከሆኑ ጠበቆቻቸው ጋር ቀርበው ነበር። 1. የመጀመሪው ተጠርጣሪዎች መዝገብ የተከፈተባቸው በእነ ፌቨን ሰም ነበር ይኸውም፦  1. ፌቨን ዘሪሁን  2. ብሩክታዊት ነብዩ  3. መሳይ ተፈራ  4. ተካልኝ ኢቲቻ 5. ወንደሰን ንጉሴ 6. ረ/ሳጅን ሰራዊት ጸጋ  7. ፋሲል አግደው 2. በሁለተኛው ተጠርጣሪዎች መዝገብ የተከፈተባቸው በእነ መምህር ምህረተኣብ አሰፋ ሲሆን እነሱም፦ 1. መምህር ምህረተአብ አሰፋ 2. አማኑኤል አያሌው 3. ኪሩቤል አሰፋ 4. ሰይፉ አለማየሁ 5. ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ ናቸው ፍ/ቤቱም በጠበቆቹ እና በፖሊስ የተደረገወን ክርክር ከሰማ በኋላ፦  1. ፌቨን ዘሪሁን  2. ብሩክታዊት ነብዩ 3. ፋሲል አግደው 4. መምህር ምህረተአብ አሰፋ 5. አማኑኤል አያሌው 6. ኪሩቤል አሰፋ … በእነዚህ ላይ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን ውስጥ ተጨማሪ ምርመራ 8 ቀን ፈቅዶ… 1. መሳይ ተፈራ  2. ተካልኝ ኢቲቻ  3. ወንደሰን ንጉሤ 4. ረ/ሳጅን ሠራዊት ጸጋ 5. ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ የተባሉትን ተከሳሾች ደግሞ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልግም በማለት እያንዳንዳቸው በ15 ሺ ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል። 6ኛ ተጠርጣሪ 4. ሰይፉ አለማየሁ በ30 ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፈቅዷል፡፡ "…በተለይ ጠበቆቹንም ዳኞቹንም ታዳሚዎችንም ፈገግ ካስባለውና ያስገረማቸው ደግሞ በእነ ምህረተአብ መዝገብ ከተዘረዘሩት ተከሳሾች በ4 ኛው ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው አቶ ሰይፉ አለማየሁ ማስረሻ የተባሉት እስረኛ የኮመርሽያል ተቋም ማናጀር ሲሆን በፖሊስ ተጠርጥሮ የተያዘው የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ እና አንዳንድ ነገሮች በፌስ ቡክ ላይ ሼር አድርገሃል ተብሎ መሆኑን ነው። "…በተራ ቁጥር 5 ላይ የተከሰሰችው ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ አዲስ የተባለችው የፖሊስ አባልም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው የፖሊስ ደንብ ለብሳ እኔም ለሃይማኖቴ በማለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ፎቶዋን ለጥፋለች ተብላ ነው። ምንጭ፦ መምህር ዘመድኩን በቀለ
إظهار الكل...
በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋይ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት "የተሾሙበትን" አስኬማና አልባሳትም አስረክበዋል። "እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ማኅበረ ቅዱሳን እንደዘገበው)
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
"እግዚአብሔር በመሰንቆ አመሰገኑት አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘመሩለት፡፡"መዝ 33÷2 ልዩ መንፈሳዊ የዜማ መሳሪያ ምርቃት መርሐ ግብር 🗓 እሑድ ጥቅምት 20/2015 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 10:00 ሰዓት 💒 በካቴድራሉ አዳራሽ በእለቱም 👉ትምህርተ ወንጌል 👉መነባነብ 👉የመሰንቆና የበገና ዝማሬ 👉መንፈሳዊ ጭውውት ይኖሩናል እንዳይቀሩ ተጋብዘዋል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 © ፈለገ ዮርዳኖስ ሚዲያ 👉የደ/መ/ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት Felege Yordanos Sunday School 👉የቴሌ ግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/debmewisundayschool 👉ፌስቡክ ገጻችንን ይቀላቀሉ https://www.facebook.com/የደመቅዱስ-ሚካኤል-ካቴድራል-ፈለገ-ዮርዳኖስ-ሰንበት-ትቤት-668409293227987/ 👉 የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ https://youtube.com/channel/UCI55ALZbi2nwFxBhtsY5RJQ
إظهار الكل...
መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው። መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው። መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴ ማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው። መስቀል ማኅተመ ሥላሴየሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው። መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው ስሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው። መስቀል ሰሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው። መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው። (ውዳሴ መስቀል በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
إظهار الكل...
ሥርዓተ ማህሌት ዘሐምሌ ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ << ፲፱ > በመጀመሪያ ሥርዓተ ነግስ፦ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። መልክአ ቂርቆስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ ዚቅ ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። ወረብ "ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። ዚቅ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። ወረብ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/ ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። ዚቅ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ ወረብ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ ዚቅ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡ ወረብ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/ ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/ መልክዐ ኢየሉጣ ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ መልክዐ ገብርኤል ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። ዚቅ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት። ወረብ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/ እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/ ምልጣን፦ ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ አመላለስ: ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/ ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/ ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ እስመ ለዓለም ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡ አመላለስ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/ ወረብ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር. ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን @metsor_tube @metsor_tube @metsor_tube @metsor_tube @metsor_tube @metsor_tube
إظهار الكل...
ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡ ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
إظهار الكل...
#በእንተ_ምጽዋት "ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈጣሪ ለመቅረብ እንደ ምጽዋት ክሂል የሚሰጥ የለም። ከሥራም ወገን ወድዶ ሰጥቶ እንደመቸገር በልቡና ኅድዓት (ፀጥታ ፣ ዕረፍት ፣ ሠላም) የሚያደርግ የለም። ሰጥተኽ መጽውተኽ አጥተኽ 'አላዋቂ' ቢሉኽ ይሻልኻል። ጨብጠኽ ይዘኽ አስተዳደር ዐዋቂ ከሚሉኽ።. . . ኅብስቱን ከውሃ ጣለው ብሎ ተናግሯልና። ከውሃ የጣሉት እንዳይመለስ ፣ 'ይ 'ሰጠኛል' ብለኽ አትስጥ ሲል ነው። አንድም ኀብስቱን ከእግዚአብሔር ፊት አኑረው ሲል ነው። በፍጻሜ ዘመንኽ ዋጋኽን ታገኛለኽ። ባለጸጋውን ለይተኽ ለድኻ አትስጥ። 'ይኽ ይገባዋል ይኽ አይገባውም' አትበል። አላ ኩሉ ሰብእ ይኩኑ ዕሩያነ በኅቤከ -በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለኽ መጽውት እንጂ! አስተካክለኽ በመስጠትኽ ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለኽ። ምንም የበቁ ባይኾኑ ነፍስ በመብል በመጠጥ ምክንያት ወደ ክቡር እግዚአብሔር ትሳባለችና! በምጽዋት ጊዜ 'ይኽ አይሁዲዊ ነው። ይኽ ከሀዲ ነው' አትበል። 'ይኽ ነፍሰ ገዳይ ነው' አትበል። ይልቁንስ ብታስታውለው ወንድምኽ ነው እንጂ። አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ።ከበጎው ነገር ወገን ለሰው ያደረግኽ እንደኾነ መክፈልን አትውደድ።. . . መጽውተኽ ብትቸገር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ቸርነት ከትካዝ ሥጋዊ ትድናለኽ! ከኹሉ በላይ ትኾናለኽ! ሰው ኹሉ ለገንዘቡ ሲገዛ እሱ ለእግዚአብሔር ይገዛልና። . . . 'በዝናም ያበቀለው በፀሓይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው' ብለኽ ምጽዋትኽን በትሕትና መጽውት። ጻድቃን በሚከብሩበት ጊዜ ይቅርታን ታገኛለኽ" (መጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ) ፣ አንቀጽ ፩ ፣ ምዕ.፲፪፣ ገጽ ፳፩ - ፳፫)
إظهار الكل...
"ነገ ለአንተ የተሸለ ነው" ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡ ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና። ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!! (ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.